16/08/2025
የሕይወት ዘመን መምህር; ምርጥ ሞደል ;የማይረሳ አባት: ቅን የዋህ መካሪ ወንድም ቤዛብህ ነብስህ በስላም ትረፍ::
📌 ላልተዘመረለት ጀግና የኢ/አ/ፌ ሀዉልት አቆመለት!!
| ተባባሪ ፕሮፌሰር በዛብህ ወልዴ ሃታኡ (ዶ/ር)፤ ከሐምሌ 23/1952 – ነሃሴ 19/2014 ዓ.ም
👉 ተባባሪ ፕሮፌሰር በዛብህ ወልዴ በቀድሞው ባሌ ክፍለ ሀገር ልዩ ስሙ ጊኒር በሚባል አካባቢ ሐምሌ 23/1952 ዓ.ም ተወለዱ፡፡
የእስፖርት ሳይንሱ አባት ዶ/ር በዛብህ ወልዴ ሰብእናው፥ ሙያው እና ሕይወቱ በአንድ ቃል ይገለጽ ቢባል ያ ቃል "ፈውስ" ነው።
እጁ የአካል ሰብራትን ሲጠግን ንግግሩ መንፈስን ከድቀት ይታደጋል።
ሁሉንም ሰው እንደየመልኩና እንደየ አመሉ በፍቅርና ከልብ በመነጨ ፈገግታ መቀበሉ፤ ለኹሉም የሚዳረስ የጊዜ በረከት የታደለ መሆኑ ወዳጆቹን ዘወትር እንዳስደነቀ ይኖራል።
ረጅም ቁመናው ብዙዎችን ለማስጠለል ለሚችለው ጠባዩ ጥሩ ምሳሌ ይሆናል።
ዕድልና አጋጣሚ አግኝተን ባወቅነው ፤በቀረብነው ፥ ባወጋነው ዘንድ የማይረሳ የሰው አብነት ነው።
ቸሩ እግዚአብሔር ነፍሱን ከደጋጎች ጎራ እንዲያሳርፍ እንጸልያለን።
በትምህርቱ ዘርፍ የነበራቸው አበርክቶ
***
➡️ ትምህርታቸውን በጅማ መምህራን ማሰልጠኛ ተቋም፣ በኮተቤ መምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጅ ፤በቡልጋሪያ አገር በሶፊያ ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፤በፖላንድ አገር በሚገኘው ዋርሶ የሰውነት ማጎልመሻ ማእከል ተከታትለው በከፍተኛ ማዕረግ ተመርቀዋል ።
➡️ በኮተቤ መምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጅና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመምህርነት፣ በምርምር ስራዎችና በማህበረሰብ አገልግሎት የላቀ አስተዋጽኦ አበርክተዋል፤
➡️ ከመጀመሪያ ደረጃ እስከ ሶስተኛ ዲግሪ መርሀ-ግብሮች በመምህርነት አገልግለዋል፤
➡️ በአገር ውስጥና ከአገር ውጪ በሚገኙ የተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በተጋበዥ መምህርነት፣ ተማሪዎችን በማማከርና የምርምር ስራዎችን በማቅረብ አገልግለዋል፤
በስፖርቱ ዘርፍ ነበራቸው አበርክቶ
***
በኢትዮጵያ ስፖርት ታሪክ ‹‹የአትሌቲክስ አባት›› ተብለው ከሚታወቁ የዘርፉ ምሁራንና ባለሙያዎች መካከል በግንባር ቀደምትነት የሚጠሩ አንጋፋና ባለውለታ ነበሩ፡፡
ከ20 አመት በላይ በአትሌቲክሱ ላይ እጅግ ደማቅ አሻራቸውን ያሳረፉ ሲሆን ከብዙው በጥቂቱ ለመጥቀስ:-
➡️ በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በዋና ፀኃፊነት፣
➡️ በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በዋና ፀኃፊነት፣ በሥራ አስፈጻሚ ኮ/አባልነት፣ በአቃቢ ነዋይነት አገልግለዋል።
➡️ በአትላንታና በሲድኒ ኦሎምፒክ በዝግጅትና በአመራር፤
➡️ በኤድመንተን ዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በአመራርነት፤
➡️ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በፕሬዚዳንትነት፣
➡️ በአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን
በፕሬዜዳንትነት እንዲሁም
➡️ በቴክኒክና በህክምና ኮሚቴ ሰብሳቢነት ፣በአቃቤ ነዋይነት እስከ ህልፈተ ህይወታቸው ድረስ ደከመኝ፣ ሰለቸኝ ሳይሉ አትሌቲክሱን ያገለገሉ የኢትዮጵያ ባለውለታ በመሆናቸው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሙሉ ወጪዉን በመሸፈን የመታሰቢያ ሐውልት በስማቸው አሰርቶላቸዋል።
ሐዉልቱም የፊታችን ጳጉሜ 2 በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ⛪ ቤተክርስቲያን ወዳጅ ዘመዶቹ ፣የሙያ አጋሮቹ እንዲሁም የቀድሞ ተማሪዎቹ በተገኙበት የሚመረቅ ይሆናል።
ተባባሪ ፕሮፌሰር በዛብህ ወልዴ ለኢትዮጵያ እስፖርት ላደረከዉ አስተዋፅኦ ሁሌም እናመሰግንሀለን ።🙏🙏🙏🙏🙏
ተባባሪ ፕሮፌሰር በዛብህ ወልዴ ሃታኡ ነሃሴ 19/2014 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡
በተስፋዬ አብዲሳ (ቻይና አብዲ)