
15/07/2024
በብዝሀነታችን ተደምረን በአብሮነታችን ደምቀን ፤ በህብረታችን ታሪካዊ አሻራ ማሳረፋችንን አጠናክረን እንቀጥላለን!
የኢትዮጵያውያን የከፍታ ሚስጢር ህብረታችን ነው።
አባት እናቶቻችን በህብረብሔራዊነት ደምቀው ዘመን ተሻጋሪ ታሪክ ሰርተዋል።
ኢትዮጵያ ታፍራና ተከብራ የኖረችው ዜጎቿ በውስጣቸው ያለውን ልዩነት ወደ ጎን በማለት ለአገር ክብር እና ለህዝብ ደህንነት ቅድሚያ በመስጠታቸው ነው።
በሁሉም ብሔር ብሔረሰብ ያሉን እንቁ ባህሎቻችን እና እሴቶቻችን ከትውልድ ትውልድ ሊሸጋገሩ የቻሉትም በየጊዜው የመጡ ወራሪ ሀይሎችን በጋራ መመከት በመቻላቸው ነው።
ኢትዮጵያውያን በተደመረ አቅም ለውጡን አምጥተዋል ፣ አፅንተዋል እንዲሁም አስቀጥለዋል።
ፓርቲያችን ህዝባችን ዕምቅ አቅሙን ተጠቅሞ ኑሮውን እንዲያሻሽል እና አገሩን እንዲያበለፅግ ከወሰዳቸው ቀዳሚ እርምጃዎች መካከል አገር በቀል የሆነውን የመደመር ፍልስፍና ተግባራዊ ማድረግ ነው፡፡
መደመር አቃፊ ነው። መደመር የሀሳብ ብዝሀነት እና ብዝሀ ማንነት የኢትዮጵያ ፀጋ መሆናቸውን በፅኑ ያምናል።
ፓርቲያች የተግባር ፓርቲ በመሆኑ አደርጋለሁ ባለበት ቅፅበት ዕቅዶቹን ይተገብራል። ለአብነትም አገራዊ ለውጡ ዕውን በሆነባት ዕለት ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ ለአገረ መንግስት ግንባታው ከሁሉም ተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር በትብብር በፉክክር እንደሚሰራ አመላክተው የነበረ ሲሆን ባለፉት የለውጥ ዓመታት የታየውም ይኸው ነው፡
ሁሉም ዜጋ ለአገሩ ታሪካዊ አሻራውን ማሳረፍ እንደሚገባው የማይዋዥቅ አቋም ያለው ፓርቲያችን ከሁሉም ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በትብብርና በፉክክር መስራት ኢትዮጵያን ወደ ልዕልና እንደሚወስዳት ይገነዘባል።
ከለውጡ በኋላም ኢትዮጵያውያን በመሰባሰባችን የማይታለፉ የሚመስሉ ፈተናዎችን ተሻግረናል ፤ ብሄራዊነትን አንግበን የአገራችንን ልዕልና አስጠብቀናል።
በጋራ በመቆማችን ተግዳሮቶች ሳይበግሩን አንፀባራቂ ድሎችን አስመዝግበናል።
እየተገባደደ ያለው ታላቁ የህዳሴ ግድባችን ክንዳች አስተባብረን ለጋራ ነገአችን በመነሳታችን የተገኘ ስኬት ነው።
በአረንጓዴ አሻራ እየተጎናፀፍን ያለው ስኬት ሌሎች አገራት ላይም መንፈሳዊ ቅናት ፈጥሯል።
የገጠሩም የከተማውም አርሶ አደሩም አርብቶ አደሩም በህብር ባይነሳ በስንዴ ምርታማነት ላይ ያስመዘገብነው ድል አይታሰብም።
በጋራ በመቆማችን ተደማጭነታችን ጨምሯል ፤ በዚህም ብሪክስን የመሳሰሉ ዓለም አቀፍ ተፅዕኖ ፈጣሪ ስብስቦች በራቸውን ከፍተውልናል።
የከተማችን ህዝብም አዲስ አበባን የሁላችንም ቤት በማለት ገፅታዋን ለመቀየር ቀን እና ሌት ከከተማ አስተዳደሩ ጎን ተሰልፎ በመትጋቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደ ስሟ ማበብ የጀመረች ከተማ ማየት ችሏል።
ታላቁ ትርክታችን የሆነውን ብሔራዊነትን አንግበን ፣በብዝሀነታችን ተደምረን በአብሮነታችን ደምቀን ፤ በህብረታችን ታሪካዊ አሻራ ማሳረፋችንን አጠናክረን እንቀጥላለን!
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት