Fikreselam General Hospital

Fikreselam General Hospital " Heartfelt Care and Serving Hands "

Dr. Sewit Getachew a well known infertility subspecialist is now available at Fikreselam General Hospital on Monday and ...
28/03/2026

Dr. Sewit Getachew a well known infertility subspecialist is now available at Fikreselam General Hospital on Monday and Thursday starting from 10:00 LT.

ዶ/ር ሰዊት ጌታቸው ከፍተኛ ልምድ ያላቸው የመካንነት ህክምና ሠብ ስፔሻሊስት ሲሆኑ በፍቅረሰላም አጠቃላይ ሆስፒታል ዘወትር ሠኞ እና ሀሙስ ከ10: ዐዐ ሰዓት ጀምሮ ይገኛሉ።

የማህበራዊ ሚዲያ ገፆቻችንን ፎሎ፣ ላይክ፣ ሼር በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ
— TikTok In Amharic:
https://www.tiktok.com/?
— Facebook:
https://web.facebook.com/profile.php?id=61555841617995
— Telegram:
https://t.me/fikreselamghospital

ፍቅረሰላም አጠቃላይ ሆስፒታል!
ለበለጠ መረጃ ፡
☎️ +251-939-595-960 ላይ ይደዉሉልን።
✨ወርቃማ ልቦች ፤ አገልጋይ እጆች✨

ፍቅረሰላም አጠቃላይ ሆስፒታል ከዚህ በታች በተጠቀሱት ክፍት የሥራ መደቦች ላይ ብቁ አመልካቾችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡
24/03/2026

ፍቅረሰላም አጠቃላይ ሆስፒታል ከዚህ በታች በተጠቀሱት ክፍት የሥራ መደቦች ላይ ብቁ አመልካቾችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡

20/03/2026
💊 የድህረ ወሲብ መከላከያ ኪኒን (Post Pill)"ለአደጋ ጊዜ እንጂ ለሁልጊዜ አይደለም!"የድህረ ወሲብ መከላከያ ኪኒን (Emergency Contraceptive Pill) ያልታሰበ ወይም ጥን...
16/03/2026

💊 የድህረ ወሲብ መከላከያ ኪኒን (Post Pill)

"ለአደጋ ጊዜ እንጂ ለሁልጊዜ አይደለም!"
የድህረ ወሲብ መከላከያ ኪኒን (Emergency Contraceptive Pill) ያልታሰበ ወይም ጥንቃቄ የጎደለው ግንኙነት ከተፈጸመ በኋላ እርግዝና እንዳይፈጠር ለመከላከል የሚያገለግል የሆርሞን መድኃኒት ነው።

🔍 መድኃኒቱ እንዴት ይረዳል?
• እንቁላል እንዳይለቀቅ ማድረግ (Delayed Ovulation)፦ ዋነኛው ስራው እንቁላል ከእንቁላል ማምረቻ (O***y) እንዳይወጣ በማዘግየት ከወንዱ ዘር (S***m) ጋር እንዳይገናኝ ማድረግ ነው።

• ማሳሰቢያ፦ እርግዝና ከተፈጠረ በኋላ መድኃኒቱን መውሰድ እርግዝናውን አያቋርጥም (አያስወርድም)።

⚠️ ማወቅ ያለብዎት 5 ወሳኝ ነጥቦች
1. የጊዜ ገደብ፦ ግንኙነት ከተፈጸመ በኋላ ቶሎ ሲወሰድ ውጤታማነቱ ይጨምራል። አብዛኞቹ ኪኒኖች እስከ 72 ሰዓት (3 ቀናት) ውስጥ መወሰድ አለባቸው

2. ውጤታማነት፦ መድኃኒቱ 100% እርግዝናን አይከላከልም።

3. የጎንዮሽ ጉዳቶች፦ የወር አበባ መዛባት (ቀድሞ መምጣት ወይም መዘግየት)፣ ማቅለሽለሽ፣ የጡት ህመም፣ ራስ ምታት እና ድካም ሊያስከትል ይችላል።

4. ከበሽታ አይከላከልም፦ይህ መድኃኒት እርግዝናን ለመከላከል እንጂ ከኤች.አይ.ቪ (HIV) ወይም ከሌሎች በግንኙነት ከሚተላለፉ በሽታዎች (STIs) አይከላከልም።

5. መደበኛ መከላከያ አይደለም፦ መድኃኒቱ ከፍተኛ የሆርሞን መጠን ስላለው እንደ መደበኛ የወሊድ መከላከያ (ለምሳሌ የዕለት ወይም የ3 ወር መርፌ) መጠቀም ለጤና ጎጂ ሊሆን ይችላል።

የማህበራዊ ሚዲያ ገፆቻችንን ፎሎ፣ ላይክ፣ ሼር በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ
— TikTok In Amharic:
https://www.tiktok.com/?
— Facebook:
https://web.facebook.com/profile.php?id=61555841617995
— Telegram:
https://t.me/fikreselamghospital

ፍቅረሰላም አጠቃላይ ሆስፒታል!
ለበለጠ መረጃ ፡
☎️ +251-939-595-960 ላይ ይደዉሉልን።
✨ወርቃማ ልቦች ፤ አገልጋይ እጆች✨

💎 የዓለም የኩላሊት ቀን ( March 12 ) ፦ "የኩላሊት ጤና ለሁሉም! "🔍 ኩላሊትን የሚጎዱ 5 ዋና ዋና ምክንያቶች- ያልተቆጣጠሩት የደም ግፊት፦ ለኩላሊት በሽታ ቀዳሚው መንስኤ ነው።- ...
12/03/2026

💎 የዓለም የኩላሊት ቀን ( March 12 ) ፦ "የኩላሊት ጤና ለሁሉም! "

🔍 ኩላሊትን የሚጎዱ 5 ዋና ዋና ምክንያቶች

- ያልተቆጣጠሩት የደም ግፊት፦ ለኩላሊት በሽታ ቀዳሚው መንስኤ ነው።
- የስኳር በሽታ፦ ከፍተኛ የደም ስኳር የኩላሊት ጥቃቅን የደም ስሮችን ይጎዳል።
- የመድኃኒት አጠቃቀም፦ የህመም ማስታገሻዎችን (ለምሳሌ፦ Diclofenac, Ibuprofen) ያለ ሐኪም ትዕዛዝ ለረጅም ጊዜ መውሰድ።
- ውፍረት እና የተሳሳተ አመጋገብ፦ ጨውና ስኳር የበዛባቸው ምግቦች።
- ሲጋራ ማጨስ፦ ወደ ኩላሊት የሚሄደውን የደም ዝውውር ይቀንሳል።

✅ ኩላሊትን ጤናማ ለማድረግ 8 ወርቃማ
ህጎች

1. ንቁ መሆን፦ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ የደም ግፊትን መቀነስ።
2. የደም ስኳርን መቆጣጠር፦ ስኳር ያለባቸው ሰዎች ዘወትር ምርመራ ማድረግ አለባቸው።
3. የደም ግፊትን መከታተል
4. ጤናማ አመጋገብ፦ የጨው መጠንን መቀነስ (በቀን ከ 5 ግራም ወይም ከ 1 የሻይ ማንኪያ በታች)።
5. በቂ ውሃ መጠጣት፦ በቀን ከ 1.5 እስከ 2 ሊትር ውሃ መጠጣት ኩላሊት ቆሻሻን እንድታስወግድ ይረዳታል።
6. አለማጨስ፦ ኩላሊት ላይ የሚደርሰውን ጫና ይቀንሳል።
7. የህመም ማስታገሻዎችን መቀነስ
8. የኩላሊት ምርመራ ማድረግ፦ በተለይ ስኳር ወይም ግፊት ካለብዎ በየዓመቱ ይመርመሩ።

የማህበራዊ ሚዲያ ገፆቻችንን ፎሎ፣ ላይክ፣ ሼር በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ
— TikTok In Amharic:
https://www.tiktok.com/?
— TikTok In Afaan Oromo:
https://www.tiktok.com/?
— Facebook:
https://web.facebook.com/profile.php?id=61555841617995
— Telegram:
https://t.me/fikreselamghospital

ፍቅረሰላም አጠቃላይ ሆስፒታል!
ለበለጠ መረጃ ፡
☎️ +251-939-595-960 ላይ ይደዉሉልን።
✨ወርቃማ ልቦች ፤ አገልጋይ እጆች✨

Dr. Biniyam G/Medhin a well known pediatric surgeon ,now available at Fikreselam General Hospital on Thursday from 6:00-...
12/03/2026

Dr. Biniyam G/Medhin a well known pediatric surgeon ,now available at Fikreselam General Hospital on Thursday from 6:00-8:00LT.

ዶ/ር ቢንያም ገ/መድህን ከፍተኛ ልምድ ያላቸው የህፃናት ቀዶ ሀክምና ስፔሻሊስት ሲሆኑ በፍቅረሰላም አጠቃላይ ሆስፒታል ዘወትር ሐሙስ ከ6:00 - 8:00 ሰዓት ይገኛሉ።

የማህበራዊ ሚዲያ ገፆቻችንን ፎሎ፣ ላይክ፣ ሼር በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ
— TikTok In Amharic:
https://www.tiktok.com/?
— TikTok In Afaan Oromo:
https://www.tiktok.com/?
— Facebook:
https://web.facebook.com/profile.php?id=61555841617995
— Telegram:
https://t.me/fikreselamghospital

ፍቅረሰላም አጠቃላይ ሆስፒታል!
ለበለጠ መረጃ ፡
☎️ +251-939-595-960 ላይ ይደዉሉልን።
✨ወርቃማ ልቦች ፤ አገልጋይ እጆች✨

⚠️ የኩክ ማጽጃ  ጉዳቶች1.  ኩክን ወደ ውስጥ መግፋት፦ ማጽጃውን በምንጠቀምበት ጊዜ ኩኩን ከማውጣት ይልቅ ይበልጥ ወደ ውስጥ በመግፋት የጆሮ ታምቡር (Eardrum) ላይ እንዲለጠፍ እና የ...
06/03/2026

⚠️ የኩክ ማጽጃ ጉዳቶች

1. ኩክን ወደ ውስጥ መግፋት፦ ማጽጃውን በምንጠቀምበት ጊዜ ኩኩን ከማውጣት ይልቅ ይበልጥ ወደ ውስጥ በመግፋት የጆሮ ታምቡር (Eardrum) ላይ እንዲለጠፍ እና የመስማት ችግር እንዲፈጥር እናደርጋለን።

2. የታምቡር መበሳት፦ ማጽጃውን በጣም ወደ ውስጥ ከገፋነው ቀጭኑን የጆሮ ታምቡር በመቅደድ ለዘላቂ የመስማት አለመቻል ችግር ሊዳርገን ይችላል።

3. ኢንፌክሽን፦ በጆሮ ቧንቧ ላይ ትናንሽ መቧጨሮችን በመፍጠር ባክቴሪያዎች በቀላሉ እንዲገቡና ኢንፌክሽን እንዲፈጠር ያደርጋል

4. መድረቅና ማሳከክ፦ ጠቃሚ የሆነውን ኩክ በሙሉ ስናስወግድ ጆሮአችን ይደርቃል፤ ይህም ከፍተኛ የማሳከክ ስሜት ይፈጥራል

✅ ጆሮን እንዴት ማጽዳት ይቻላል?

• ውጫዊውን ክፍል ብቻ፦ ገላዎን ከታጠቡ በኋላ በፎጣ ወይም ለስላሳ ጨርቅ የጆሮዎን ውጫዊ ክፍል (Pinna) ብቻ ይጥረጉ።

• ኩክ ከበዛባችሁ፦ ጆሮአችሁ እንደተደፈነ ከተሰማችሁ በቤት ውስጥ ጥቂት ጠብታ የወይራ ዘይት በመጠቀም ኩኩ እንዲለሰልስ ማድረግ እንዲሁም ወደ ሐኪም በመሄድ በባለሙያ ማፀዳት ይቻላል።

የማህበራዊ ሚዲያ ገፆቻችንን ፎሎ፣ ላይክ፣ ሼር በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ
• TikTok In Amharic:
https://www.tiktok.com/?is_from_webapp=1&sender_device=pc

• TikTok In Afaan Oromo:
https://www.tiktok.com/?_r=1&_t=ZS-94P9zfnlrzr

• Facebook:
https://web.facebook.com/profile.php?id=61555841617995

• Telegram:
https://t.me/fikreselamghospital

• Instagram:
https://www.instagram.com/fikreselam_general_hospital/

ፍቅረሰላም አጠቃላይ ሆስፒታል

📍አድራሻ - ሲኤምሲ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ከጋስት ሞል ጎን።
📍Location- https://maps.app.goo.gl/mc1ydidPRYfRJvjC6

ለበለጠ መረጃ ፡
☎️ +251-939-595-960 ላይ ይደዉሉልን።

✨ወርቃማ ልቦች ፤ አገልጋይ እጆች✨

ወገብዎን ለመጠበቅ የሚረዱ ወርቃማ ህጎች1. ዕቃ ሲያነሱ ጥንቃቄ ያድርጉ፦ ከባድ ዕቃከመሬት ሲያነሱ ከ ወገብዎ አያጎንበሱ፤ ይልቁንም ጉልበትዎን አጥፈው ቁጭ በማለት ዕቃውን ወደ ሰውነትዎ አስ...
03/03/2026

ወገብዎን ለመጠበቅ የሚረዱ ወርቃማ ህጎች

1. ዕቃ ሲያነሱ ጥንቃቄ ያድርጉ፦ ከባድ ዕቃ
ከመሬት ሲያነሱ ከ ወገብዎ አያጎንበሱ፤ ይልቁንም ጉልበትዎን አጥፈው ቁጭ በማለት ዕቃውን ወደ ሰውነትዎ አስጠግተው በግርዎ ጡንቻ ይነሱ።

2. ትክክለኛ አቀማመጥ፦ ወንበር ላይ ሲቀመጡ ጀርባዎ ቀጥ ማለቱንና እግርዎ መሬት መርገጡን ያረጋግጡ። አስፈላጊ ከሆነ ለወገብዎ ትራስ (Lumbar support) ይጠቀሙ።

3. እንቅስቃሴ ያድርጉ፦ የሆድና የጀርባ ጡንቻዎችን የሚያጠነክሩ እንቅስቃሴዎችን (Core exercises) መስራት ለአከርካሪ አጥንት ድጋፍ ይሆናል።

4. ጫማዎን ያስተውሉ፦ በጣም ረጅም ተረከዝ ያላቸው ጫማዎች የሰውነትን ሚዛን በማዛባት ለወገብ ህመም ይዳርጋሉ።

5. በቂ እረፍትና አተኛኘት፦ በጣም ለስላሳ በሆነ ፍራሽ ላይ አለመተኛት። በጎን ሲተኙ በጉልበቶችዎ መሃል ትራስ ማድረግ ወገብዎ እንዳይጣመም ይረዳል።

Dr. Gemechis Mamo, a well known Internal Medicine Specialist is now available at Fikreselam General Hospital from Monday...
27/02/2026

Dr. Gemechis Mamo, a well known Internal Medicine Specialist is now available at Fikreselam General Hospital from Monday to Saturday starting from 2:00LT - 6:00LT.

ዶ/ር ገመቺስ ማሞ ከፍተኛ ልምድ ያላቸው የውስጥ ደዌ ህክምና ስፔሻሊስት ሲሆኑ በፍቅረሰላም አጠቃላይ ሆስፒታል ዘወትር ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ከ2:00 -6:00 ሰዓት ይገኛሉ።

ፍቅረሰላም አጠቃላይ ሆስፒታል

📍አድራሻ - ሲኤምሲ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ከጋስት ሞል ጎን።
📍Location- https://maps.app.goo.gl/mc1ydidPRYfRJvjC6

ለበለጠ መረጃ ፡
☎️ +251-939-595-960 ላይ ይደዉሉልን።

✨ወርቃማ ልቦች ፤ አገልጋይ እጆች✨

ኩፍኝበፍጥነት የሚተላለፍ በቫይረስ የሚመጣ አየር ወለድ በሽታ ነው። ብዙ ጊዜ ከአምስት አመት እድሜ በታች ያሉትን ህፃናት የሚያጠቃ ቢሆንም በሁሉም የእድሜ ክልል ይከሰታል።ምልክቶቹ🔹ትኩሳት🔹እ...
24/02/2026

ኩፍኝ

በፍጥነት የሚተላለፍ በቫይረስ የሚመጣ አየር ወለድ በሽታ ነው። ብዙ ጊዜ ከአምስት አመት እድሜ በታች ያሉትን ህፃናት የሚያጠቃ ቢሆንም በሁሉም የእድሜ ክልል ይከሰታል።

ምልክቶቹ

🔹ትኩሳት
🔹እንደ ጉንፋን አይነት ስሜትና ደረቅ ሳል
🔷የምግብ ፍላጎት ማጣት
🔷ጠፍጠፍ ያሉ ቀይ ቀለም ያላቸው ከጭንቅላት ጀምሮ ወደ ሌላ የሰውነት ክፍል የሚስፋፋ የቆዳ ሽፍታ
🔹በአፍ ዉስጥ ያሉ ነጠብጣቦች
🔷 የአይን መቅላት እና ማንባት
🔷በአፍንጫ ፈሳሽ መብዛት

🔸መተላለፊያ መንገዶች

ኩፍኝ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፍ እና የመተንፈሻ አካላትን የሚያጠቃ ሲሆን የተበከለዉን አየር ሲስቡ ወይንም ቫይረሱ ያረፈባቸው እቃዎች በእጃቸው ከነካኩ እና ከዚያም ኣፍንጫ ፣ አፍ እና አይኖቻቸዉን ከነካኩ በቀላሉ ይተላለፋል።በሽታው በፍጥነት ሊተላለፍበት የሚችሉበት ቀናት ደግሞ የቆዳ ሽፍታ ከመታየቱ ከሶስት ቀን በፊትና ሽፍታ ከታየ ከአራት እስከ ስድስት ቀናት በሁኋላ ባለው ጊዜ ነው።

🔸ህክምና

ቫይታሚን ኤ መዉሰድ
በቂ እረፍት ማድረግ
ብዙ ፈሳሽ መጠጣት
ትኩሳት እና ህመምን ለመርዳት የህመም ማስታገሻ መዉሰድ

ድንገት ለቫይረሱ ተጋልጠዉ ከሆነ መከላል የቻላል?

አዎ የኩፍኝ ክትባቱን በ72 ሰዓታት ወስጥ ካገኙ የኩፍኝ በሽታን ሊያስቆም ወይም ከባድ እንዳይሆን ማድረግ ይችላል::

ፍቅረሰላም አጠቃላይ ሆስፒታል

📍አድራሻ - ሲኤምሲ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ከጋስት ሞል ጀርባ።
📍Location- https://maps.app.goo.gl/mc1ydidPRYfRJvjC6

ለበለጠ መረጃ ፡
☎️ +251-939-595-960 ላይ ይደዉሉልን።

✨ወርቃማ ልቦች ፤ አገልጋይ እጆች✨

Address

CMC
Addis Ababa

Telephone

+251939595960

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Fikreselam General Hospital posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category