PRO CARE Home Based Health Care Service Plc

PRO CARE Home Based Health Care Service Plc Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from PRO CARE Home Based Health Care Service Plc, Medical and health, Yeka, Addis Ababa.

PRO CARE is a home-based health care service provider that serves the medically challenged and aging population of Ethiopia using well trained and qualified professionals.

       #40+years_of_experience     ፕሮ ኬርበቤተሰብ ልክ!We treat you like family, because you are!ደሜን ለወገኔ❤"Give the Gift of Li...
14/06/2024

#40+years_of_experience

ፕሮ ኬር
በቤተሰብ ልክ!
We treat you like family, because you are!

ደሜን ለወገኔ❤
"Give the Gift of Life: Donate Blood 💉 "

☎️ +251 963054545
+251 911746398
✉️ info@procareet.com
🌐 www.procareet.com
📍 Wessen, Yeka, Addis Abeba, Ethiopia.

    #40+YearsOfExcellenceየአራስ ልጆች ገላ እጥበት Infant bathing 🧼 🧽 የባለሞያ (የነርስነት) አገልግሎት ውስጥ የህፃናትን እጥበት ለማከናወን ጥንቃቄ የተሞላበት ትኩ...
31/05/2024

 

#40+YearsOfExcellence
የአራስ ልጆች ገላ እጥበት
Infant bathing 🧼 🧽

የባለሞያ (የነርስነት) አገልግሎት ውስጥ የህፃናትን እጥበት ለማከናወን ጥንቃቄ የተሞላበት ትኩረትን ይሻል ፣እንዲሁም በየእለቱ የማይቋረጥ የሚከተሉትን ተግባራትን ያለማቋርጥ መተግበር አለባቸው።
በባለሞያ ነርስ የህፃናትን አስተጣጠብ ቅደም ተከተሎችን በተመለከተ ጥቂት ማሳያዎችን እናቀርባለን።
• የህፃኑን ማጠቢያ አከባቢ ማዘጋጀት 🛁🫧
የማጠቢያ ቦታው ቅዝቃዜ የሌለው ንፁህና ከንፋስ መከላከል የሚችል መሆኑን ማረጋገጥ
• አስፈላጊ የሆኑ ለህፃኑ እጥበት የምንጠቀምባቸውን ቁሳቁሶችን ማዘጋጀት 🧽🧼
ሳሙና 🧼፣ንፁህ ለብ ያለ ውሃ ፣ ማጠቢያ ፎጣና ⬜️ የማጠቢያ ሳህን
• የጥንቃቄ ቅደም ተከተሎችን መተግበር
- የማጠቢያው ውሃ ለብ ማለቱን ማረጋገጥ 370C በ ሴንቲ ግሬድ በዚህ አይነት ጥንቃቄ ውሃውን በክርናችን 💪🏽 የውሃውን ሙቀት መለካትና ማረጋገጥ።
- ህፃኑን በአንድ እጃችን ጣቶች አንገት እና ጭንቅላቱን በሚገባ በመያዝ በታችኛው የእጃችን ክፍል የጀርባውን ክፍል በመደገፍ እንዳይንሸራተትና እንዳያመልጠን በመቆጣጠር ወደ ውሃው ማስገባት።
- በመጀመሪያ ማጠቢያ ፎጣን በማራስ የህፃኑን ፊትና አንገት ከዚያም ጆሮውን አካባቢ ማጠብ። ይህ ሲሆን ወደ ህፃኑ ጆሮ፣ኣይን እና አፍ ውሃ እንዳይገባ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል።
- በመቀጠልም የህፃኑን ሌሎች አካላት ማጠብ በዚህን ወቅት መጠነኛ ሳሙና መጠቀም አስፈላጊ ነው፣ በዚህም ወቅት የህፃኑን በተፈጥሮ የተጣጠፉ ቦታዎች እንደ አንገቱ ስር ፣ እጆቹ እና እግሮቹ ላይ እንዲሁም ዳይፐር በሚያደርግባቸው ቦታዎች በጥንቃቄ ክትትል በማድረግ ተጠንቅቆ ማጠብ ያስፈልጋል።
- ከዚያም በተለመደው ጥንቃቄ በንፁህ ውሃ ህፃኑን ማልቅለቅ ።
- የውሃውን አወራረድ 💧 በጣም ረጋ ባለ አኳኋን መጨመር አስፈላጊ ነው።
- በመቀጠልም ህፃኑን በለስላሳ ፎጣ ⬜️ ሰውነቱን በማደራረቅና በመጠቅለል 🤱🤱 ማሞቅ ያስፈልጋል።
- በምናደራርቅበት ወቅት የቆዳ እጥፋቶቹ ውስጥ እርጥበት እንዳይኖር ለስላሳ ጨርቅ በመጠቀም በጥንቃቄ እና በሚገባ ማደራረቅ ያስፈልጋል።
- ለህፃናት ቆዳ ተብሎ የተዘጋጁ ቅባቶችን (baby oil) 🧴🧴 መጠቀም ከቆዳ ደርቀት ህፃኑን ለመጠበቅ አስፈላጊ ነው።
- በመጨረሻም ህፃኑን ምቹ የሆነ የህፃናት ልብስ በማልበስ የህፃኑን የሙቀት ምቾት ማረጋገጥ ተገቢ ነው።

ድርጅታች ፕሮ ኬር በሰለጠኑ ነርሶቹ በሳይንሳዊ እውቀት በመታገዝ ይህንን የጤና እንክብካቤ ቤትዎ ድረስ በመገኘት ይሰጣል። ለበለጠ መረጃ ከታች በተጠቀሱት ስልኮች ይደውሉ::

ፕሮ ኬር

በቤተሰብ ልክ!
We treat you like family, because you are!

☎️ +251 963054545
+251 911746398
✉️ info@procareet.com
🌐 www.procareet.com
📍 Wessen, Yeka, Addis Abeba, Ethiopia

    #40+YearsOfExcellence Patient feeding ታማሚን ምገባአስሩ ዋና ዋና  ለጤና ጠቃሚ የሆኑ ምግቦች1. ውሃ በየቀኑ ከ 8-10 ብርጭቆ /ኩባያ ውሃ ይጠጡ።2. አትክልት...
24/05/2024

 



#40+YearsOfExcellence 

Patient feeding
ታማሚን ምገባ

አስሩ ዋና ዋና  ለጤና ጠቃሚ የሆኑ ምግቦች

1. ውሃ በየቀኑ ከ 8-10 ብርጭቆ /ኩባያ ውሃ ይጠጡ።

2. አትክልት እና ፍራፍሬዎችን በምግብም ሆነ በፈሳሽ መልክ በሳምንት ከ 3-4 ጊዜ ይጠቀሙ

በተለይም አረንጓዴ ቀለም ያላቸውን አትክልት መመገብ ለጤና እጅግ ጠቃሚ ነው ።

3. ያልተፈተጉ የእህልና ጥራጥሬ ምግቦችን መመገብ ለጤና እጅግ ጠቃሚ ነው።

4. የጥራጥሬ ዝርያዎች እንደ ባቄላ፣ ቦሎቄ፣አጃ፣ገብስ፣ አተር እና ሽምብራ የመሳሰሉትን በሾርባና በሳላድ ምግብ አይነቶች ውስጥ በመጨመር በሳምንት ቢያንስ 1 ቀን ይጠቀሙ።

5. የአሳ ምግቦችን በሳምንት ከ 3-4 ጊዜ መመገብ ለጤና እጅግ ጠቃሚ ነው።

6. የአኩሪ አተር ወተትን መጠቀም የ ኮሌስትሮል መጠንን ስለሚቀንስ አዘውትረው ይጠቀሙ።

7. በየቀኑ ጥቂት የለውዝ ፍሬን በምግቦ ውስጥ በመጨመር መመገብ ለጤና እጅግ ጠቃሚ ነው።

8. እርጎን እና ወተትን አዘውትረው በመጠቀም የካልሺየም እጥረትን ይከላከሉ፣ በተለይም ከ 50 ዓመት በላይ ሲሆኑ ስለሚከሰት።

9. ዶሮ ፣ ወተት፣ ቶፉ እና እንቁላል ጥሩ የፕሮቲን ምንጮች ስለሆኑ  እነዚህን አዘውትሮ መመገብ ለጤና እጅግ ጠቃሚ ነው ።

10.  የአመጋገብ ስርዓትን በአግባቡ ማከናወን፣ ከመኝታ በፊት ብዙ መጠን ያላቸውን ምግቦች አለመመገብ፣ የረሃብ እና የጥጋብ ስሜትን ማዳመጥ፣ በተመሳሳይ ወይንም በተቀራራቢ ሰዓት መመገብ።

ድርጅታች ፕሮ ኬር በሰለጠኑ ነርሶቹ በሳይንሳዊ እውቀት በመታገዝ ይህንን የጤና እንክብካቤ ቤትዎ ድረስ በመገኘት ይሰጣል። ለበለጠ መረጃ ከታች በተጠቀሱት ስልኮች ይደውሉ::

 



#40+YearsOfExcellence

    #40+YearsOfExcellence Back care/ የጀርባ እንክብካቤየታማሚውን የጀርባ አካል የሰውነት ክብደት የሚያርፍባቸውን ነጥቦች ለይቶ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በመስጠት ማሻሸት እና...
10/05/2024

 



#40+YearsOfExcellence 

Back care/ የጀርባ እንክብካቤ

የታማሚውን የጀርባ አካል የሰውነት ክብደት የሚያርፍባቸውን ነጥቦች ለይቶ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በመስጠት ማሻሸት እና ማፅዳት ማለት ነው።

ይህም የደም ዝውውር በደንብ እንዲካሄድ ያደርጋል ንፅህናንም በመጠበቅ ካልተፈለገ የጀርባ የቆዳ መቁሰል እና ኢንፌክሽን እንዳይኖር ይከላከላል።

ባክ ኬር በትክክለኛ ባለሙያ በአስፈላጊው ጊዜ በመስጠት በስተመጨረሻ ከሚያጋጥም በአልጋ ላይ መኝታ የቆዳ ቁስለትን ለመከላከል መፍትሄ ነው።

 ፕሮ ኬር በሰለጠኑ ነርሶቹ በሳይንሳዊ እውቀት በመታገዝ ይህንን የጤና እንክብካቤ ቤትዎ ድረስ በመገኘት ይሰጣል። ለበለጠ መረጃ ከታች በተጠቀሱት ስልኮች ይደውሉ::

ፕሮ ኬር

በቤተሰብ ልክ!

We treat you like family, because you are!

☎️ +251 963054545

      +251 911746398

✉️ info@procareet.com

🌐 www.procareet.com

📍 Wessen, Yeka, Addis Abeba, Ethiopia

ፕሮ ኬር    ለመላው የፕሮ ኬር ቤተሰቦች እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላምና በጤና አደረሳችሁ!መልካም በዐል 🙏ፕሮ ኬር Procareበቤተሰብ ልክ!We treat you like family, b...
05/05/2024

ፕሮ ኬር
 



ለመላው የፕሮ ኬር ቤተሰቦች እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላምና በጤና አደረሳችሁ!

መልካም በዐል 🙏
ፕሮ ኬር Procare
በቤተሰብ ልክ!
We treat you like family, because you are!

☎️ +251 963054545

      +251 911746398

✉️ info@procareet.com

🌐 www.procareet.com

📍 Wessen, Yeka, Addis Abeba, Ethiopia

     Bed bath የአልጋ ላይ የሰውነት እጥበት የአልጋ ላይ የሰውነት እጥበት ማለት ታማሚው/ዋ በመኝታ (በአልጋ) ላይ እንዳሉ እጥበት ማድረግ ማለት ነው። ዋና ዋና ጥቅሞቹ የሚከተሉት ና...
26/04/2024

 



 

Bed bath 

የአልጋ ላይ የሰውነት እጥበት 

የአልጋ ላይ የሰውነት እጥበት ማለት ታማሚው/ዋ በመኝታ (በአልጋ) ላይ እንዳሉ እጥበት ማድረግ ማለት ነው። 

ዋና ዋና ጥቅሞቹ የሚከተሉት ናቸው፦

፨ የቆዳን ንፅህና ለመጠበቅ 

፨ መጥፎ ጠረንን ለመከላከል 

፨ የደም ዝውውርን ለማነቃቃት 

፨ የጤናማነት ስሜት እንዲበረታታ ለማድረግ 

፨ ምቾትን ለመጠበቅ 

አገልግሎቱ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች 

⨳  የአልጋ ቁራኛ ለሆኑ መንቀሳቀስ ለማይችሉ ሰዎች

⨳ ኮማ ውስጥ ለሆኑ ህሙማን 

⨳ የአጥንት አደጋ ለደረሰባቸው ህሙማን 

⨳ ለአእምሮ ህሙማን 

⨳ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ሰውነታቸው ለማይታዘዝላቸው ህሙማን (partial or general paralyzed ).

ድርጅታች ፕሮ ኬር በሰለጠኑ ነርሶቹ በሳይንሳዊ እውቀት በመታገዝ ይህንን የጤና እንክብካቤ ቤትዎ ድረስ በመገኘት ይሰጣል። ለበለጠ መረጃ ከታች በተጠቀሱት ስልኮች ይደውሉ::

ፕሮ ኬር

በቤተሰብ ልክ!

We treat you like family, because you are!

☎️ +251 963054545

      +251 911746398

✉️ info@procareet.com

🌐 www.procareet.com

📍 Wessen, Yeka, Addis Abeba, Ethiopia

     በአፍንጫ በኩል በሚገባ ቱቦ በሽተኛን መመገብNG tube feeding በአፍንጫ በኩል በሚገባ ቱቦ በሽተኛን መመገብማለት  በሠው የአፍንጫ ቀዳዳ ውስጥ ለህክምና አገልግሎት ሲባል እንዲ...
19/04/2024

 




በአፍንጫ በኩል በሚገባ ቱቦ በሽተኛን መመገብ
NG tube feeding
በአፍንጫ በኩል በሚገባ ቱቦ በሽተኛን መመገብ
ማለት በሠው የአፍንጫ ቀዳዳ ውስጥ ለህክምና አገልግሎት ሲባል እንዲገባ የሚደረግ እና እስከ ታካሚው ጨጓራ ድረስ ዘልቆ የሚቀመጥ ጠባብ እና ተጣጣፊ የሆነ ኘላስቲክ ቱቦ ነው።

የምንጠቀምባቸው ምክንያቶች
-የላመ አልሚ ምግብን በአፍ ለመመገብ ለማይችሉ ህሙማን በመመገብ
-በአፋቸው መድኃኒት ለመዋጥ የማይችሉ ታካሚዎች (ህሙማን)በፈሳሽ መልክ መድኃኒት እንዲወስዱ
-ጨጓራ ውስጥ ያለን ማንኛውንም ፈሳሽ ለማስወጣት እና ለምርመራ ለመጠቀም
-በጨጓራ ውስጥ ካለ ፈሳሽ በተነሳ ትንታ እንዳይከሰት ጨጓራን ከፈሳሽ ነፃ ለማድረግ
-በአጋጣሚ መርዛማነት ያላቸውን ፈሳሽ ነገሮች ከጠጣ ታማሚ ጨጓራ ውስጥ አጥቦ ለማውጣት

ኤንጂ ቲዪብን ለማስገባትም ሆነ ለማስወጣት በሰለጠኑ የጤና ባለሙያዎችን መጠቀም የግድ አስፈላጊ ነው።

ድርጅታችን ፕሮ ኬር አስተማማኝ እና የሰለጠኑ የጤና ባለሙያዎችን ይዞ ይጠብቃችኋል።

We treat you like family, because you are!

በቤተሰብ ልክ!

☎️ +251 963054545

      +251 911746398

✉️ info@procareet.com

🌐 www.procareet.com

📍 Wessen Addis Abeba, Ethiopia

     Urinary Catheterisationዩሪናሪ ካቴተራይዜሽን ማለት ሽንትን ተጣጣፊ በሆነ እና ካቴተር በሚባል ቀጭን ከሽንት ከረጢት እንዲወገድና እንዲጠራቀም የማድረግ ዘዴ ነው።ይህ ዘዴ...
12/04/2024

 





Urinary Catheterisation

ዩሪናሪ ካቴተራይዜሽን ማለት ሽንትን ተጣጣፊ በሆነ እና ካቴተር በሚባል ቀጭን ከሽንት ከረጢት እንዲወገድና እንዲጠራቀም የማድረግ ዘዴ ነው።

ይህ ዘዴ በዶክተሮች ወይም በነርሶች በሆስፒታል ወይም በቤት ውስጥ የሚከናወን ሲሆን ለሁለቱም ፆታዎች ያገለግላል።

ሽንትን በዚ መልኩ የመሽናቱ ዘዴ በሁለት መንገድ ይተገበራል። አንደኛው ለአጭር ጊዜ ሲሆን ይህም በጊዜያዊነት በደቂቃዎች ውስጥ የተጠራቀመውን ሽንት አሸንቶ የሚያበቃ ነው። ሁለተኛው ደግሞ ረዘም ላለ ጊዜ የማሸኛ ቱቦው እንዲቆም ተደርጎ ማጠራቀሚያ የኘላስቲክ ከረጢት ውስጥ እንዲጠራቀም ይደረጋል። ይህም በሆነ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ እንዲወጣ የሚጠበቅ ሲሆን እንደማስገባቱ ማውጣቱም በባለሙያ መከናወን አለበት።

ሁለት አይነት የካቴተር አይነቶች ሲኖሩ

1.አንደኛው በሽንት መሽኛ ትቦ(urethra) ውስጥ በማስገባት የምንጠቀምበት ነው በተለየ ጥንቃቄ ከጀርም የፀዳ አሰራር እንዲገባ ይደረጋል

2.ሁለተኛው ኮንዶም ካቴተር ይባላል ይህ በውጭኛው የወንድ ብልት በውስጡ በማስገባት ሽንቱ እየተጠራቀመ የሚወገድበት ሂደት ነዉ።

ይህን አይነቱ ካቴተር በ 24 ሰዐት ውስጥ ተፈቶ መቀየር አለበት።

ካቴተር የምንጠቀምባቸው ምክንያቶች

1.ህመምተኛው ወይም ህመምተኛዋ ሽንት የመቆጣጠር ችግር ሲኖርበት/ሲኖርባት

2.ሽንት ለመሽናት ባለመቻል ምክንያት ሽንት እንዲሸኑ የተለያዩ ዘዴዎችን ተጠቅመን አልሸና ካሉ ሽንት ለማሸናት

3.የተለያየ የሽንት ናሙና መሠብሠብ ዘዴ ሲታዘዝ

በቤተሰብ ልክ!
We treat you like family, because you are!

☎️ +251 963054545

      +251 911746398

✉️ info@procareet.com

🌐 www.procareet.com

📍 Wessen Addis Abeba, Ethiopia

     ! #የአረጋውያን ልዩ የጤና እንክብካቤ!!እድሜያቸው የገፋ አረጋውያንን በተለየ ሁኔታ መንከባከብን የሚመለከት የጤና የጤና እንክብካቤ አገልግሎት። (Geriatric Care)እድሜያቸው ...
05/04/2024




!
#የአረጋውያን ልዩ የጤና እንክብካቤ!!

እድሜያቸው የገፋ አረጋውያንን በተለየ ሁኔታ መንከባከብን የሚመለከት የጤና የጤና እንክብካቤ አገልግሎት። (Geriatric Care)
እድሜያቸው 65 አመትና እና ከዚያ በላይ የሁኑና የጤና እንክብካቤ የሚፈልጉትን ለሁለቱም የፆታ ክፍሎች የምንሠጠው እንክብካቤ ሲሆን የምንንከባከባቸው ግለሰቦች ለየት ያለ ባህሪና ፍላጎታቸው ላይ በማተኮር አካላዊ ስነ ልቦናዊ አዕምሮኣዊና ማህበራዊ ክፍተቶቻቸውን በመዳሰስ ለግለሰቦቹ እንደየፍላጎታቸው የምናቀርብላቸው እንክብካቤ አይነት ነው።

በዚህ የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ አረጋውያን የምናቀርብላቸው እንክብካቤ አላማው የጤናና የኑሮ ሁኔታቸውን በማገናዘብ ደረጃውን የጠበቀ እንክብካቤ በማድረግንና ደስተኛ ስሜት እንዲሰማቸው በማገዝ ሲሆን ማንኛውንም አይነት እንቅስቃሴ ቀስበቀስ ያለ ተጨማሪ ሰው ድጋፍ ራሳቸውን ችለው የሚተገብሩትን የኑሮ ሁነታ ለማመቻቸት እድል ለመፍጠር ነው።

ድርጅታችን ፕሮኬር ይህንን በብቃት ሊያከናውኑ የሚችሉ ባለሞያዎችን አዘጋጅቶ ይጠብቃችኋል።

😃








We treat you like family, because you are!
በቤተሰብ ልክ!

☎️ +251 963054545
+251 911746398
✉️ info@procareet.com
🌐 www.procareet.com
📍 Wessen Addis Abeba, Ethiopia

29/03/2024




!
!!

ቤድ ሶር የሚለው ቃል በአማርኛ አጭር የመፍቻ ትርጉም ባይኖረውም ለረጅም ጊዜ በአልጋ ላይ ታመው ከመቆየት የተነሳ ህሙማን ላይ ሊከሰት የሚችል የቆዳ ህመም ነው።

ተከታታይ እና ረዘም ላለ ጊዜ የሰውነት አካል ሳይገላበጡ ከሰነበቱ ወደ ቦታው የሚመላለሰውን የደም ዝውውር በማሣጠር የቆዳውን መልክ በመቀየር ቀጥሎም በመላጥና በመቁሰል ሀይለኛ ህመምን በማስከተል እየሰፋ የሚሄድ ትላልቅ ቁስል ይፈጥራል ።

ቁስለቱ እንዳይከሰት ቀድሞ መከላከል የሚቻል ሲሆን ከተከሰተ በኋላም በሰለጠኑ የጤና ባለሞያዎች በሚደረግ ያላሰለሰ ክትትልና ህክምና በማከም ወደ ቀድሞ ጤናማ ደረጃ መመለስ ይቻላል።

ሆኖም ግን በወቅቱ ክትትልና ህክምና በአግባቡ ካልተደረገ ቁስለቱ እየተስፋፋ ስለሚመጣ ለተለያዩ ኢንፌክሽኖች ከማጋለጡም በላይ ህልፈተ ህይወትን ሊያስከትል ይችላል!።

እኛም ለመፍትሔው ብቁ የጤና ባለሞያዎችን እናቀርባለን 😃








We treat you like family, because you are!
በቤተሰብ ልክ!

☎️ +251 963054545
+251 911746398
✉️ info@procareet.com
🌐 www.procareet.com
📍 Wessen Addis Abeba, Ethiopia

PRO CARE is a home-based health care service provider that serves the medically challenged and aging population of Ethiopia using well trained and qualified professionals.

Address

Yeka
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when PRO CARE Home Based Health Care Service Plc posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to PRO CARE Home Based Health Care Service Plc:

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram