Almu Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Almu, AIDS Resource Center, Addis Ababa.

26/11/2024
06/11/2024
27/09/2024

ፓርቲያችን ብልፅግና የሀገራችን ህልውና እንዲጠበቅና ሁለንተናዊ ብልፅግና እንዲረጋገጥ ይሰራል።

ሕዝብና ባለድርሻ አካላትን በቀጣይነት ማሳተፍና ማስተባበር እጅግ ጠቃሚ መሆኑን ያምናል።

ቀጣይነት ካለው የሕዝብና ባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ውጭ ልማትን ማፋጠን፣ የዴሞክራሲ ባህልን መገንባት፣ የሰላም እሴትን መገንባት፣ የህግ የበላይነትን ማስከበርና ፍትህን ማስፈን እንዲሁም ሀገራዊ መግባባትን ማጎልበት አይቻልም ብሎ ብልፅግና ያምናል።

በሁሉም የማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና የፖለቲካ መስኮች ሕዝብንና ባለድርሻ አካላትን በብቃት ለማስተባበርና ለማሳተፍ የሕዝብ ንቅናቄን እንደ ስልት መጠቀም አስፈላጊ ነው። የሕዝብ ንቅናቄ ለጋራ ዓላማ ሕዝብን በጋራ፣ በተደራጀና ስትራቴጂክ በሆነ አግባብ ከማንቀሳቀስና አቅምን ወደ ውጤት ከመቀየር ጋር ይያያዛል።

የሕዝብ ንቅናቄ ግለሰባዊ አስተሳሰብንና ተግባርን፣ የጋራ ማንነትንና የወል ተግባራትን በሞራል ለማነጽ ይጠቅማል። በተለይም የህዝብ ንቅናቄ ከልማት አኳያ ሀገራዊ ሀብትን ለአዎንታዊ ለውጥ ለመጠቀምና ዜጎች ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እድገት ለማስመዝገብ በሚደረገው ጥረት ቀጣይነት ባለው መልኩ በንቃት እንዲሳተፉ ለማስቻል ፋይዳው የላቀ ነው።

22/09/2024
18/09/2024

ጎሀችን በኮሪደር ልማታችን ብሎም በገዢ ትርክታችን ሲገለጥ!

በፓርቲያችን አርማ ላይ የብርሀን ፍንጣቂዎች ከውስጥ ወደ ውጭ ሲወጡ ያሳያል፡፡ በፓርቲ መተዳደሪያ ደንባችን በግልጽ ትርጉም ላይ እንደተቀመጠው ምልክቶቹ ውክልናቸው ለጎህ እንደሆነና ጎህ ጨለማን ሰንጥቆ የሚወጣ ብርሀን እንደመሆኑ፤ ብልጽግናም ኢትዮጵያን ወደ ከፍታና የብርሃን ዘመን ለማሸጋገር የሚታገል ፓርቲ መሆኑን የሚወክል የተስፋና የብልጽግና ዘመንን የሚያመላክት እንደሆነ ያትታል፡፡

የኮሪደር ልማታችንን ብቻ ወስደን ስንመለከት የብልጽግና ተምሳሌት ከሆነችው አዲስ አበባችን እምብርት ፒያሳ ተነስቶ ወደ ከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች እየተስፋፋና በየአካባቢው የነበረውን ገጽታ ውበት እያላበሰ ይገኛል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ይህ የዘመናዊ ከተሞች መገለጫ የሆነው ልማት ወደ ክልል ከተሞች የሰፋበት ሁኔታን ስንመለከት የብልጽግና አካሄድ ድንገቴ ሳይሆን ምን ያህል ከእያንዳንዱ እሳቤዎቹ ጋር የተሳሰረ እንደሆነ ለመረዳት አያዳግትም፡፡

በአጠቃላይ ፓርቲያችን ብልጽግና በግልፅ እንዳስቀመጠው ሀገራችን ኢትዮጵያ እስከ 2018 ወደ ሚጨበጥ ብርሀን የምትሸጋገርበት፤ በ2023 ደግሞ የአፍሪካ ተምሳሌት የምትሆን ሀገር የምንፈጥርበት፤ በ2040 በአለም አቀፍ ደረጃ ስመጥር የሆነች የብልጽግና ተምሳሌት ሀገር የመሆን ርዕያችን የሚገለጥበት ሂደትን ስናይ በአርማችን ላይ እንዳስቀመጥነው የብርሀን ፍንጣቂ ጎህ ከውስጥ ወደ ውጭ እየሰፋ፤ ከእያንዳንዱ ውጤት ትምህርት እየወሰደ እና ለቀጣይ ግብዓት እያደረገ የሚሄድ የልማት አቅጣጫ ያለን፤ የሀገራችንን ልማት አቅደን የምንፈጽም 7/24 ለልማት የምንተጋ ስብስቦች እንደሆን ስራችን ይመሰክራል አካሄዳችንም በትክክለኛው መንገድ ላይ እንደሆነ ውጤታችን በግልጽ ያሳያል፡፡

እንደ ኮሪደር ልማቱ ሁሉ ከውስጥ ጀምሮ እየሰፋ የሚሄደውን ጎህ በ2017 በጀት ዓመትም ደምቆ እንዲታይ እና የበለጠ እንዲገለጥ አብዝተን እንሰራለን!!

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት

18/09/2024

ኢትዮጵያዊ እሴቶችን ማጎልበት ለጋራ ተጠቃሚነት!

አብሮ መብላት፣ ተያይዞ ማደግ፣ ተጋምዶ መኖር፣ ሀዘንንም ደስታንም መካፈል የኢትዮጵያውያን ልዩ እሴቶቻችን ናቸው። የመተሳሰብ እሴታችን ድንበር ሳይገድበን ለአፍሪካውያን እህት ወንድሞቻችን እንድናስብና በምንችለው ሁሉ ከጎናቸው እንድንቆም አስችሎናል፡፡

አፍሪካውያን በቅኝ ግዛት በሚማቀቁበት ዘመን ኢትዮጵያውያን ሉዓላዊነታቸውን በመስዋዕትነታቸው አስጠብቀው የነፃነት ብርሀን ከመፈንጠቃቸው ባሻገር አለኝታነታቸውን በተለያየ አግባብ በመግለፅ የነፃነት ትግላቸውን እንዲያጠናክሩ የሞራል ስንቅም ሆነዋቸዋል፡፡

ታላቁን የዓባይ ወንዝ ጨምሮ የተፈጥሮ ሀብቶቿንም ቢሆን ብቻየን ልጠጣ፣ ብቻየን ልመገብ ሳትል ሁሉም የተፋሰሱ ሀገራት የተሻለ ተጠቃሚ የሚሆኑበትን የአሰራር ስርዓት ለመዘርጋት ብርቱ እንቅስቃሴ አድርጋለች፤ ማንንም በማይጎዳ አግባብ ተገንብቶ ወደ መጠናቀቁ የተቃረበውን ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እንደ ማሳያ መጥቀስ ይቻላል፡፡

የጋራ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለቀጠናዊ እና አህጉራዊ ትስስር የሚኖረውን ጉልህ ሚና በመረዳት የሚደረጉ ዲፕሎማሲያዊ እርምጃዎችም የትብብርና የፉክክር ሚዛንን የጠበቁ ናቸው፡፡
እኛ ኢትዮጵያውያን ለዘመናት በወንድማማችነት እና በእህትማማችነት ያስተሳሰሩን የማንነት መገለጫዎች፣ ዓለምን ያስደመሙ ድንቅ እሴቶች፣ ባህልና ወጎች ያሉን ህዝቦች ነን፡፡ ይህ ዓለም የሚመሰክረው ዘመናትን የተሻገረ የእኛ እውነት ነው፡፡

እነዚህን እሴቶች ይዘን ከሌሎች ሀገራት ጋር ሀገራዊ ክብርን ያስቀደመ፣ ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ፣ ለጎረቤት ሀገራት ቅድሚያን በመስጠት ቀጠናዊ ትብብርና የኢኮኖሚ ውህደት ላይ መሠረት ያደረገ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲን በመከተል ባለፉት የለውጡ አመታት የዛሬዋንና የነገዋን ኢትዮጵያ በፅኑ መሠረት ላይ ሊገነባ የሚችል የውጭ ግንኘነት ስራ እየተሰራን እንገኛለን፡፡

ብልፅግና ፓርቲ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ በፉክክር እና በትብብር መካከል ሚዛን በመጠበቅ፣ ተቃርኖዎችን በማስታረቅ የሚጓዝ መሆን እንዳለበት የሚያምን በመሆኑ ከዚሁ አንፃር ጠንካራ የውጭ ግንኙነትና የዲፕሎማሲ ስራዎች ተሰርተዋል፤ ፍሬም አፍርቷል፡፡ ለአብነትም የህዳሴ ግድባችን አሁን ያለበት ደረጃ ሊደርስ የቻለው የሁሉም ኢትዮጵያዊ የእውቀት የጉልበት እና የገንዘብ አሻራ እንደተጠበቀ ሆኖ በዲፕሎማሲ መስክ በፓርቲያችን እሳቤ ላይ በመሆን በተከናወነው ብርቱ ስራ ነው።

በፓርቲያችን ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዐብይ አህመድ እና በሌሎችም የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች እልህ አስጨራሽ ትግል እና የተግባቦት ብቃት የተገኘው፣ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ቅቡልነቷን በማጎልበት የግዙፉ የብሪክስ ስብስብ አባል መሆኗም ተጠቃሽ ነው፡፡

ኢትዮጵያ ዛሬ ላይ በፈጣን የለውጥ ጉዞ ላይ ናት ፤ በቅርቡ የተደረገው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያም ይህንን የተገኘውን ስኬት የሚያፀና፣ ሀገራችን የጀመረችውን ሁለንተናዊ የብልፅግና ጉዞ ፍጥነት የሚጨምር እና እውን የሚያረግ ሲሆን ፤ ከሀገራት ጋር የኢኮኖሚ ትስስርን በማሳደግ የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተጀማመሩ ተግባራትም ከራዕያችን ስኬታማነት ጋር የማይነጣጠሉ ናቸው።

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Almu posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram