Dr Mekdes Daba, Minister of Health, Ethiopia

Dr Mekdes Daba, Minister of Health, Ethiopia Minster of Health, Ethiopia

Happy
05/05/2025

Happy

04/05/2025

በልብ ሕክምና ዘርፍ ፈር ቀዳጅ የልብ ሐኪም የነበሩ እና ህዝባችንን ለረጅም አመታት በርህራሄ ባገለገሉት በዶ/ር ፍቅሩ ማሩ ከዚህ አለም መለየት የተሰማኝን ልባዊ ሀዘን እየገለፅኩ፥

ለመላ ቤተሰቦቻቸው፣ ለጓደኞቻቸው እና ለባልደረቦቻቸው ሁሉ ልባዊ መጽናናትን እመኛለሁ።

በአቡዳቢ ለተደረገልን መልካም አቀባበል ክቡር ፕሬዘዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን (His Highness Sheikh Mohamed bin Zayed Al Nahyan),ከልብ እያመሰገንኩ...
01/05/2025

በአቡዳቢ ለተደረገልን መልካም አቀባበል ክቡር ፕሬዘዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን (His Highness Sheikh Mohamed bin Zayed Al Nahyan),ከልብ እያመሰገንኩ፣ በከተማዋ በነበረን ቆይታ ከ"beginning fund" የማስጀመሪያ መርሐ-ግብር ጎን ለጎን ከተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች የጤና ሚኒስትር H.E. Abdul Rahman Bin Mohamed Al Owais እንዲሁም ከመሀመድ ቢን ዛይድ የሰብአዊነት ፋውንዴሽን ተወካዮች ጋር ተገናኝተን በኢትዮጵያ እና ከተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች መካከል ባለው የጤና ዘርፍ እንቅስቃሴ ልምድ ለመለዋወጥ፣ የወደፊት የትብብር መንገዶችን በመፈለግ እና ትብብሮችን በማስፋፋት ዙሪያ እና እንዲሁም በኢትዮጵያ ከመጀመሪያ ደረጃ ጤና አገልግሎት እስከ ከፍተኛ ደረጃ ሆስፒታሎች በባለሙያ ይዘት እና በጥራት የተሟላ የጤና መሰረተ ልማት ለማስፋፋት እያደረገን ባለው ጥረት ዙሪያ ተወያይተናል።

በተጨማሪም በአቡዳቢ የሚገኘውን የሼክ ሻክቡት እጅግ ዘመናዊ የሕክምና ማዕከልን (SSMC) ከማዕከሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ማርዋን አልካቢ እና ከአምባሳደር ዶ/ር ዑመር ሁሴን ጋር በመሆን የጎበኘን ሲሆን ፤ ይህ ጉብኝት በኢትዮጵያ የጤና መሠረተ ልማትንና የባለሙያዎችን ክህሎት ለማሳደግ ለሚደረጉ የወደፊት የትብብር ሥራዎች መሠረት የሚጥል ከመሆኑም አንፃር፣ በጤናው ዘርፍ ላቀድናቸው ግቦች መሳካት ከተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች ጋር በቅርብ ቅርበት የምንሰራ ይሆናል።

የእናቶችና ጨቅላ ህጻናት ጤና አገልግሎትን ለማሻሻል ከአፍሪካ ሀገራት መንግስታት ጋር በመቀናጀት እኤአ በ2030፣ 300,000 ጨቅላ ህጻናትን ከሞት ለመታደግና ለ34 ሚሊዮን እናቶችና ህጻናት...
01/05/2025

የእናቶችና ጨቅላ ህጻናት ጤና አገልግሎትን ለማሻሻል ከአፍሪካ ሀገራት መንግስታት ጋር በመቀናጀት እኤአ በ2030፣ 300,000 ጨቅላ ህጻናትን ከሞት ለመታደግና ለ34 ሚሊዮን እናቶችና ህጻናት ጥራት ያለው የህክምና አገልግሎት ለማቅረብ በማለም ታስቦ የተፀነሰዉ The beginning fund መርሀ ግብር በአቡ ዳቢ አል አይን ከተማ ካናድ ሆስፒታል ይፋ ተደርጓል።

በኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት በእናቶች፣ ጨቅላ ህፃናትና ህጻናት ጤና ላይ በተሰሩ ስራዎች እኤአ በ2000 ከ100,000 እናቶች 871 ይከሰት የነበረውን ሞት በቅርብ ወደ 267 መቀነስ መቻሉንና የጨቅላ ህፃናትን ሞትን በህይወት ከሚወለዱ 1000 ህፃናት ከነበረው 39 ሞት ወደ 26 እንዲሁም ከ5 ዓመት በታች ከ1000 ህፃናት 123 ይከሰት የነበረውን ሞት ወደ 47 መቀነስ የተቻለ ሲሆን በሁለተኛው የጤና ሴክተር ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የያዝናቸዉን ዕቅዶች ግብ ለመምታትና የጤና ባለሙያን ያማከለ የጤና አገልግሎት ለማስፋፋት የ “beginning fund” መርሀ ግብር ታላቅ እገዛ የሚኖረዉ ይሆናል።

የመሀመድ ቢን ዛይድ የሰብአዊነት ፋውንዴሽን፣ ኤልማ ፋውንዴሽን ፣ ሲፍ እና ጌትስ ፋውንዴሽንን ጨምሮ በተለያዩ ግብረሰናይ ድርጅቶች የተደገፈዉ “beginning fund” የእናቶችና የህፃናት ጤና ላይ ትኩረት በመስጠት የጤና ባለሙያን ያማከለ የጤና አገልግሎት ለማስፋፋት ታቅዶ የተፀነሰ መርሀግብር ንደመሆኑ አንፃር ድጋፉም በዋነኝነት የጤና ባለሙያዎችን አቅም ለማጠናከርና የጤና አገልግሎትን ለማዘመን የሚዉል ነዉ።

Thank you Mohamed bin Zayed Foundation for Humanity Gates Foundation

30/04/2025
26/04/2025
21/04/2025
ዛሬ የፋሲካን በዓል በቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በመገኘት ህሙማንን በመጎብኘት እና በስራ ላይ የነበሩ ባለሙያዎቻችንን በማበረታታት  በዓሉን በደመቀ ሁኔታ አሳልፈናል።እንዲሁም ወላጅ...
20/04/2025

ዛሬ የፋሲካን በዓል በቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በመገኘት ህሙማንን በመጎብኘት እና በስራ ላይ የነበሩ ባለሙያዎቻችንን በማበረታታት በዓሉን በደመቀ ሁኔታ አሳልፈናል።

እንዲሁም ወላጅ አልባ ህጻናትን እና አረጋዊያንን በመደገፍ ራሳቸዉን ከመቻል አልፈው ለሌሎች እንዲተርፉ በማድረግ አርዓያነት ያለው ስራ እያከነወነ በሚገኘው በሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ በመገኘት የማዕድ ማጋራት እና በአስኮ ለሚገኘው የህክምና ማዕከል የሚውል የአልትራሳውንድ ማሽን በድጋፍ አበርክተናል።

መልካም የትንሳኤ በዓል

በክርስትና  እምነት  የፍቅር፣ የደስታ፣  የተስፋ፣ የመታደስ በዓል ለሆነው የትንሳኤ በዓል በሰላምና በጤና እንኳን አደረሳችሁ፣ አደረሰን !!! በዓሉ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሰዉ ልጆች...
19/04/2025

በክርስትና እምነት የፍቅር፣ የደስታ፣ የተስፋ፣ የመታደስ በዓል ለሆነው የትንሳኤ በዓል በሰላምና በጤና እንኳን አደረሳችሁ፣ አደረሰን !!!

በዓሉ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሰዉ ልጆች ሲል የከፈለውን የፍቅር ዋጋ የምናስብበት እንደመሆኑ እኛም በመረዳዳት እሳቤ ተደጋግፈን፣ የተቸገሩ ወገኖቻችን ጠይቀንና ያለንን በፍቅር አካፍለን መንገዱን የምንከተልበት ያድርግልን።

በዓሉ የሠላም ፣ የፍቅር፣ የይቅርታ፣ የመቻቻል እና የአብሮነት እንዲሆንልን እመኛለሁ፡፡

መልካም የትንሳኤ በዓል!

19/04/2025

እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል አደረሳችሁ፤

ትንሣኤ የመሥዋዕትነት፣ የጽናት እና የተስፋ በዓል ነው።

የበደለው ዓለም ነው። የተሠዋው ግን ክርስቶስ ነው። ያጠፋው የሰው ልጅ ነው፣ የካሠው ግን ክርስቶስ ነው። ባለ ዕዳው ሰው ነው። ከፋዩ ግን ክርስቶስ ነው።

የክርስቶስ ሞት አንድም ለማዳን ነው፤ አንድም ለትምህርት ነው። ስለ ብዙዎች ሲባል መሥዋዕትነት ካልተከፈለ ብዙዎችን ማዳን አይቻልም። ሀገርን፣ ሕዝብን፣ ወገንን ማዳን ከተፈለገ መሥዋዕትነት መክፈል ይገባል። ቃል ክርስቶስ በቃሉ ብቻ አልተናገረም። በመስቀል ላይ ውሎ ፍቅሩን በተግባር ገለጠው እንጂ። ራሱ አስታራቂ፣ ራሱ ታራቂ፣ ራሱም መሥዋዕት ሆነ።

ዛሬ ኢትዮጵያን የሚወድ ሁሉ መሥዋዕት ለመሆን የተዘጋጀ መሆን አለበት። በሌሎች መሥዋዕትነት መጓዝ የኦሪት ሰዎችም አድርገውታል። ሺ በጎችንና ሺ ፍየሎችን ሠውተው ነበረ። አልሆነም እንጂ። ሀገርን ማዳን የሚቻለው ሌሎችን በመሠዋት አይደለም። ራስን በመሠዋት እንጂ። የራስን ጉልበት፣ ጊዜ እና ዕውቀት በመሠዋት እንጂ። የራስን ክብርና ኢጎ በመሠዋት እንጂ።

ሀገርን ለማዳን ወደ ትኅትና፣ ወደ ዕርቅ እና ወደ ምክክር መስቀል አውርዶ ራስን መሠዋት ያስፈልጋል። መስቀል መከራ ነው፤ ስድብ ነው፤ ግርፋት ነው፤ ውርደት ነው። ራሳችንን ለሰላምና ለዕርቅ መንገድ ስናዘጋጅ ከብዙዎች ዘንድ ስድብ፣ ርግማን፣ መከራ፣ ይጠብቀናል። የሚያዋጣን ግን ከሊቶስጥራ እስከ ቀራንዮ የኢትዮጵያን መስቀል መሸከም ነው። ለኢትዮጵያ ትንሣኤ ስንል መስቀሏን መሸከም።

ትንሣኤ ከጽናት በኋላ የሚገኝ ድል ነው። ከፊቱ የጅምላ ፍርድ አለው፤ ከፊቱ ውግዘት አለው፤ ከፊቱ ግርፋት አለው፤ ከፊቱ መራቆት አለው፤ ከፊቱ መከዳት አለው፤ ከፊቱ የፀሐይ መጨለም፣ የጨረቃ ደም መልበስ፣ የከዋክብትም መርገፍ አለው። በዚህ ሁሉ ግን በሸላቾቹ ፊት ዝም እንደሚል በግ ክርስቶስ በጽናት ቆመ። ስለ ዓላማ ሲባል መከራን ታገሠ። ስለ ሰው ልጅ ሲባል ሁሉን እየቻለ በጽናት ተጓዘ።

ሀገር ጽናት ትፈልጋለች። በመከራዎች እና በውግዘቶች ፊት በጽናት መቆም። በስድብና በንቀት ፊት በጽናት መቆም። እንደ ፀሐይ የሚታዩት ልሂቃን ሲጠፉ፣ እንደ ከዋክብት የሚታዩት ክቡራን ሲረግፉ በጽናት መቆም። አብረው የነበሩ ፈርተውና ተሽጠው ሲከዱ በጽናት መቆም - ሀገር ትፈልጋለች። በሚጸኑት ዘንድ የኢትዮጵያ ትንሣኤ እጅግ ቅርብ ብቻ አይደለም። የሚታይም ነው።

ትንሣኤ ተስፋ ነው። ፈተናው እንደሚያልፍ ተስፋ ይሰጣል። ዓርብን ላየ እሑድ የሚመጣ አይመስልም ነበር። የመቃብሩን ድንጋይ ላየ የሚነሣ አይመስልም ነበር። ማኅተሙን ላየ የሚፈታ አይመስልም ነበር። ጨለማውን ላየ ብርሃን ሩቅ ይመስል ነበር። ሁሉም ግን ተገለበጠ። ታሪክን የታሪኩ ጌታ ለወጠው።

ተስፋችን በደጅ ነው። ዓርብ ላይ እሑድን እናየዋለን። ከሞት ባሻገር ሕይወትን፣ ከመቃብር አልፈንም ትንሣኤን የምንመለከት ነን። የሚጨበጥ ሕልም የጠራ ምናብ አለን። ስለዚህም ወጀብና አውሎ ነፋስ አያስደንቀንም። ዛሬ ለነገ፣ ሞት ለትንሣኤ ቦታ እንደሚለቁ የምናውቅም፣ የምናምንም ነን።

ለኢትዮጵያ ትንሣኤ የሚተጉ ብዙዎች ናቸው። የሕማማቱ ጊዜ እያለፈ ነው። አሁን ዓርብ ወደ ማታ ላይ ነን። ከጸጥታው ቀን በኋላ የኢትዮጵያ ትንሣኤ ይመጣል። ከሄዱት ብዙዎች ይመለሳሉ። ከተሳሳቱት ብዙዎች ያስተውላሉ። ዓርብ ዕለት በከንቱ የጮኹት ብዙዎች ያፍራሉ። ፈራጆች ይፀፀታሉ። ተገዳዳሪዎች ይበታተናሉ። የመቃብር ጠባቂዎች ይደነግጣሉ። ኢትዮጵያ ግን አይቀሬ በሆነው ትንሣኤ ትነሣለች።

ትንሣኤው ከእሥራኤል ለዓለም እንደተገለጠው ሁሉ፣ ኢትዮጵያም ለዓለም ትገለጣለች።

የትንሣኤ በዓል የሚያስተምረንም ይሄንኑ ነው።

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ሚያዝያ 11 ቀን 2017 ዓ.ም

17/04/2025
የጤና ሚኒስቴር ሰራተኞች በመንግስት እና በጤና ሴክተር የ2017 የዘጠኝ ወራት አፈጻጸም ላይ ውይይት አካሄዱ_______ባለፋት ዘጠኝ ወራት እንደ ሀገር በተለያዩ ዘርፎች አበረታች ውጤቶች መመ...
16/04/2025

የጤና ሚኒስቴር ሰራተኞች በመንግስት እና በጤና ሴክተር የ2017 የዘጠኝ ወራት አፈጻጸም ላይ ውይይት አካሄዱ
_______

ባለፋት ዘጠኝ ወራት እንደ ሀገር በተለያዩ ዘርፎች አበረታች ውጤቶች መመዝገብ መቻሉን የገለፁት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ዶ/ር ተስፋዬ ቤልጅጌ የአፈጻጸም ዉጤትን መሰረት በማድረግ በሚቀጥሉት ሶስት ወራትም የላቀ ውጤት ማምጣት እንዲቻል ውይይት ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ መድረክ መሆኑን አስረድተዋል።

መድረኩ በሃገር አቀፍ ደረጃ የተከናወኑ ዋና ዋና ስራዎችን እና ውጤቶችን የምናይበት መሆኑን በመግለጽ እንደሀገር የተመዘገቡ እንዲሁም በጤና ሴክተር የተገኙ ዉጤቶችንና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን ያቀረቡት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችንም አብራርተዋል።

አሁናዊ የአለም፣ አህጉራዊ እና ሃገራዊ የኢኮኖሚ ገጽታዎችን፣ የመንግስት አገልግሎት እና የሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ፣ ዋና ዋና የመሰረተ ልማት እና ፕሮጀክቶች አፈጻጸም፣ የጸጥታ እና የዲፕሎማሲ ስራዎች እንዲሁም የማህበራዊ ዘርፍ ሪፖርት ገለጻ በመድረኩ የቀረቡ ሲሆን፤ የመድረኩ ተሳታፊዎች በቀረበው ሪፖርት ላይ ሀሳቦችን በማንሳት ተወያይተዋል።

ይህ የውይይት መድረክ ከመደበኛ የስራ አፈጻጸም ግምገማ በማድረግ ውጤታማነትን ለማጎልበት፣ ተግዳሮቶችን ለመፍታት እና የጤናውን ሴክተር አቅጣጫ ከሀገራዊ ልማት ግቦች ጋር ለማጣጣም ወሳኝ የግምገማ መድረክ መሆኑም በውይይቱ ላይ ተገልጿል።

በቀጣይ ወራትም ቀሪ ተግባራትን በትጋትና በላቀ ደረጃ መፈጸም፣ የሪፎርም ስራዎችን በፍጥነት መፈጸም፣ ተላላፊና ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች ላይ መከላከልና መቆጣጠር ላይ መረባረብ፣ የጤና አገልግሎት አሰጣጥን ማሻሻል፣ ሀብትን በውጤታማነት መጠቀም፣ የጤና መረጃዎችን በዲጂታል ስራዎች ማጠናከር፣ አዳዲስ ሀሳቦችን ማፍለቅና ጥቅም ላይ ማዋል እንዲሁም የጤና ባለሙያችና ሰራተኞችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የተጀመሩ ኢንሼቲቮችን በማፋጠን መተግበር ላይ በስፋት ሊሰራ እንደሚገባ ተገልጿል።

Website: moh.gov.et
Facebook: Ministry of Health,Ethiopia
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/
Tiktok: tiktok.com/
Telegram: https://t.me/M0H_EThiopia

Address

Ministry Of Health
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dr Mekdes Daba, Minister of Health, Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Dr Mekdes Daba, Minister of Health, Ethiopia:

Share