Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) I feel I am still a student, a beginner journalist with a great zeal to learn more.

I am climbing up the ladder and register remarkable achievement in my profession. This page is dedicated to serve you with reliable news and voice for voiceless.

የሰኔ ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ወደ 13.9 በመቶ ዝቅ አለ  | የሰኔ ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 13.9 በመቶ ሆኖ መመዝገቡን የኢትዮጵያ ስታቲክስ መረጃ ያመለክታል ። ይህ አሃዝ ከግን...
18/07/2025

የሰኔ ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ወደ 13.9 በመቶ ዝቅ አለ

| የሰኔ ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 13.9 በመቶ ሆኖ መመዝገቡን የኢትዮጵያ ስታቲክስ መረጃ ያመለክታል ።

ይህ አሃዝ ከግንቦት ወር 14.4 በመቶ የዋጋ ግሽበት ጋር ሲነፃፀር መጠነኛ ቅናሽ አሳይቷል።

በሰኔ ወር ከተመዘገበው የዋጋ ግሽበት ውስጥ የምግብ ነክ ዕቃዎች ድርሻ 11.7 በመቶ ሲሆን፣ ምግብ ነክ ያልሆኑ ዕቃዎች ደግሞ 17.3 በመቶ ደርሷል።

የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ጥሪ ማስታወቂያ  | የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ የሀገራችንን ክብር እና ገፅታ ከፍ በሚያደርግ መልኩ በተሳካ ሁኔታ ለማስተናገድ ከወዲሁ ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል...
18/07/2025

የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ጥሪ ማስታወቂያ

| የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ የሀገራችንን ክብር እና ገፅታ ከፍ በሚያደርግ መልኩ በተሳካ ሁኔታ ለማስተናገድ ከወዲሁ ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል፡፡

በመሆኑም በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሀገራችሁን ለማገልገል ለምትፈልጉ በጎ ፈቃደኞች ከእንግዶች አቀባበል እስከ አሸኛኘት ባለው መርሃ ግብር ላይ በጎ ፈቃደኛ የፕሮቶኮል ካዴቶችን አሰልጥኖ ዓመታዊ ስብሰባው እስኪጠናቀቅ ድረስ በተለያዩ የፕሮቶኮል ሥራዎች ላይ ለማሰማራት ይፈልጋል።

የምዝገባ ሊንክ፡ https://forms.gle/34PxUgPV2bgcZCbU9

የአውሮፓ ህብረት በሩሲያ ላይ አዲስ ማዕቀብ ጣለ  | የአውሮፓ ህብረት በሩሲያ የኢነርጂና የፋይናንሺያል ሴክተሮች ላይ አዲስ ማዕቀብ መጣሉን አሰታወቀ። ማዕቀቡ በ22 ባንኮች፣ ቀጥተኛ ኢንቨስ...
18/07/2025

የአውሮፓ ህብረት በሩሲያ ላይ አዲስ ማዕቀብ ጣለ

| የአውሮፓ ህብረት በሩሲያ የኢነርጂና የፋይናንሺያል ሴክተሮች ላይ አዲስ ማዕቀብ መጣሉን አሰታወቀ።

ማዕቀቡ በ22 ባንኮች፣ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ፈንድና አጋሮች ጋር የሚደረግ ማንኛውም ግብይት እንዲሁም በውኃ ውስጥ የሚገኙትን የኖርድ ዥረት ቧንቧዎችን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ መጠቀምን ይከለክላል ተብሏል።

ኅብረቱ ከታህሳስ 2022 ጀምሮ በ60 ዶላር በበርሜል የተቀመጠውን የሩስያ ድፍድፍ ዘይት ላይ ያለውን ዋጋ ወደ ተለዋዋጭ ዘዴ በመቀየር ከአማካይ የገበያ ዋጋ በ15 በመቶ ዝቅ እንዲል መወሰኑን ብሉምበርግ ዘግባ ያመለክታል።

በአማን ረሺድ

የክብር ግብዣ  | ለቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ በኋይት ሐውስ የተደረገላቸው የክብር የእራት ግብዣዕለተ ማክሰኞ የካቲት 7 ቀን 1959 ዓምState Dinner for His Imperial Maje...
18/07/2025

የክብር ግብዣ

| ለቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ በኋይት ሐውስ የተደረገላቸው የክብር የእራት ግብዣ

ዕለተ ማክሰኞ የካቲት 7 ቀን 1959 ዓም

State Dinner for His Imperial Majesty Haile Selassie I, Emperor of Ethiopia

Location: State Dining Room, White House, Washington, DC

ከምስሉ ላይ መመልከት እንደሚቻለው ጃንሆይ ወደ ግብዣው ቦታ የሄዱት ባዶ እጃቸው አልነበረም። የመጨረሺያውን ምስል ይመለከቷል።

Credit: LBJ Library photo by Mike Geissinger

" ሁሉንም ዋንጫዎች ማሸነፍ እንችላለን " ማዱኬ   | መድፈኞቹን የተቀላቀለው ኖኒ ማዱኬ በቀጣይ ከአርሰናል ጋር ሁሉንም ዋንጫዎች ለማሸነፍ እንደሚፋለም ከፊርማው በኋላ ተናግሯል። “ አላማች...
18/07/2025

" ሁሉንም ዋንጫዎች ማሸነፍ እንችላለን " ማዱኬ

| መድፈኞቹን የተቀላቀለው ኖኒ ማዱኬ በቀጣይ ከአርሰናል ጋር ሁሉንም ዋንጫዎች ለማሸነፍ እንደሚፋለም ከፊርማው በኋላ ተናግሯል።

“ አላማችን ሁሉንም ዋንጫዎች ማሸነፍ ነው “ ያለው ኖኒ ማዱኬ “ ይህን የማድረግ አቅም እንዳለን አምናለሁ “ ብሏል።

አክሎም “ አርሰናል አሁንም ግልጽ መለያ ያለው ምርጥ ቡድን ነው የእኔን አጨዋወት ወደ ቡድኑ እስከማመጣ ጓጉቻለሁ “ ሲል ተደምጧል።

" እዚህ በመሆኔ በጣም ደስተኛ ነኝ ፤ ቡድኑ ደረጃው ከፍ እንዲል መርዳት እፈልጋለሁ “ ኖኒ ማዱኬ

አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በበኩላቸው " ኖኒ ማዱኬ በሊጉ ካሉ ምርጥ ባለተሰጥኦዎች አንዱ ነው ብለዋል።

የብዙዎች መላ “የእናቶች ወግ ስለ ልጆች አስተዳደግ እና አመጋገብ” የፌስቡክ ግሩፕ  | የእናቶች ወግ ስለ ልጆች አስተዳደግ እና አመጋገብ ግሩፕ ከ700 ሺህ በላይ አባላት ያሉት የፌስቡክ ግ...
18/07/2025

የብዙዎች መላ “የእናቶች ወግ ስለ ልጆች አስተዳደግ እና አመጋገብ” የፌስቡክ ግሩፕ

| የእናቶች ወግ ስለ ልጆች አስተዳደግ እና አመጋገብ ግሩፕ ከ700 ሺህ በላይ አባላት ያሉት የፌስቡክ ግሩፕ ነው።

ግሩፑ የእናቶች ወግ ይባል እንጂ ብዙ አባቶች፣ ወጣቶች እና ያላገቡ የማኅበረሰቡ ክፍሎች ተሳታፊ እና አባላቱ ናቸው።

የግሩፑ አስተዳዳሪዎች (አድሚኖች) መካከል ዓለምፀሐይ ዘውድ አንዷ ስትሆን ከኢቢሲ ዶት ስትሪም ጋር ቆይታ አድርጋለች።

የግሩፑም ዓላማ መደጋገፍ እና መረዳዳት እንደሆነም ገልጻ፣ በግሩፑም ምክንያትም ብዙ እናቶች እንባቸው እንደታበሰ ትናገራለች።

ሌላኛዋ የግሩፑ አስተዳዳሪ (አድሚን) መቅደስ ማረ የቤተሰብ ጉዳዮችም በግሩፑ እንደሚመከር ገልጻለች። ወላጆች ስለልጆቻቸው የሚመካከሩበት እና ሐሳብ የሚያነሱበት መሆኑንም ነው ያነሳችው።

ማኅበራዊ ሚዲያ ለበጎ ከሚጠቀሙት መካከል የእናቶች ወግ ስለ ልጆች አስተዳደግ እና አመጋገብ ግሩፕ አንዱ እንደሆነም አንስታለች።

እፀሕይወት ዓለማየሁ ሌላዋ የግሩፑ አስተዳዳሪ (አድሚን) ስትሆን፤ ግሩፑ ለወላጆች ትልቅ እፎይታ የሰጠ እንደሆነ ገልጻለች።

ግሩፑ ትላልቅ ሥራዎች እየሠራ ያለ ግዙፍ ተቋም ነው ስትልም ለማሕበረሰቡ እያበረከተ ያለውን አስተዋጽኦ ገልጻለች።

ሰናይት አበራም የግሩፑ ሞደሬተር ስትሆን ግሩፑ ሴቶችን በተለያየ መልኩ የሚደግፍ መሆኑን ጠቁማ፤ በተለይም ሥራቸውን በማስተዋወቅ ረገድ እያደረገ ያለው አስተዋጽኦ ትልቅ እንደሆነ ተናግራለች።

ይህ ግሩፕ ብዙዎች ሀሳባቸውን እና የህይወት ልምዳቸውን የሚያካፍሉበት እንደሆነም ገልጻለች።

የግሩፑ አድሚኖች በኢቢሲ ቅጥር ግቢ በመገኘት ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን፤ ተቋሙ ከግቢው ጀምሮ እስከ ስቱዲዮው የሚደንቅ እንደሆነም አንስተዋል።

ኢቢሲ አንጋፋ ተቋም መሆኑንም በማንሳት፤ ስሙን የሚመጥኑ ሥራዎች እየሠራ እንደሆነ ገልጸዋል።

በሜሮን ንብረት

ሴት እንቁራሪቶች ከወንዶች ያልተፈለገ ጥያቄ ለማምለጥ የሞቱ መስለው እንደሚተኙ ጥናት አመላከተ  | በእንስሳት ዓለም ውስጥ የሚታዩት አስገራሚ የመዳኛ ስልቶችና ባህሪያት አሁንም ድረስ ተመራማ...
18/07/2025

ሴት እንቁራሪቶች ከወንዶች ያልተፈለገ ጥያቄ ለማምለጥ የሞቱ መስለው እንደሚተኙ ጥናት አመላከተ

| በእንስሳት ዓለም ውስጥ የሚታዩት አስገራሚ የመዳኛ ስልቶችና ባህሪያት አሁንም ድረስ ተመራማሪዎችን እያስደነቁ ይገኛሉ።

ከእነዚህም አንዱ ሴት እንቁራሪቶች ከወንድ እንቁራሪቶች የሚመጡ ያልተፈለጉ የጾታዊ ግንኙነት ጥያቄ ሙከራዎችን ለማስወገድ፣ የሞቱ መስለው እንደሚተኙ አዲስ ጥናት አመላከተ።

የእንስሳት ባህሪ ተመራማሪዎች ባደረጉት ምልከታ መሰረት፣ በተለይም የሴት እንቁራሪቶች ከወንዶች ከሚመጣ ከፍተኛ የግንኙነት ጥያቄ ሲያጋጥማቸው፣ የሞቱ በማስመሰል እንቅስቃሴ አልባ ሆነው ይተነፍሳሉ።

በዚህ ጊዜ እግራቸውን በመዘርጋት ወይም በመጠምዘዝ፣ ሞተው እንደሆነ ለመምሰል ይሞክራሉ። ይህ የመዳኛ ስልት የወንዱን ፍላጎት እንዲቀዘቅዝ በማድረግ ከሁኔታው እንዲያመልጡ ይረዳቸዋል ተብሏል።

ይህ ባህሪ በተለይ ወንዶቹ በርካታ ሴቶችን ለማባዛት በሚፈልጉበት ወቅት እና ሴቷ ገና ለመባዛት ዝግጁ ባልሆነችበት ጊዜ በብዛት እንደሚታይ ተመራማሪዎቹ ገልጸዋል።

እንደዚህ አይነት የማስመሰል ባህሪ ከዚህ ቀደም በሌሎች የእንስሳት ዝርያዎች ላይ ቢታይም፣ በእንቁራሪቶች ላይ ይህን ያህል ግልጽ ሆኖ መታየቱ እና ለዚህ ዓላማ ጥቅም ላይ መዋሉ አዲስና አስገራሚ ግኝት ነው ተብሏል፡፡

ይህ ጥናት የእንስሳትን የመኖርያ ስልቶች እና ልዩ ልዩ ባህሪያት ለመረዳት የሚያግዝ ሲሆን፣ ተፈጥሮ በራሷ ምን ያህል ብልህ እና ፈጣሪ እንደሆነች የሚያሳይ ነው ሲሉ መግለጻቸው ተዘገቧል፡፡

🇩🇪  ጀርመን እንገናኝ  I የኢትዮጵያውያን ስፖርት እና ባህል ፌዴሬሽን 20 አመቱን በጀርመን ፍራንክፈርት ሊያከብር ነው።የኢትዮጵያውያን ስፖርት እና ባህል ፌዴሬሽን ከመጪው ሐምሌ 22 እሰከ...
18/07/2025

🇩🇪 ጀርመን እንገናኝ

I የኢትዮጵያውያን ስፖርት እና ባህል ፌዴሬሽን 20 አመቱን በጀርመን ፍራንክፈርት ሊያከብር ነው።

የኢትዮጵያውያን ስፖርት እና ባህል ፌዴሬሽን ከመጪው ሐምሌ 22 እሰከ ሐምሌ 26፣ 2017 ዓ.ም 20ኛ አመት የምስረታ በአሉን በጀርመን ያከብራል።

የኢትዮጵያ ስፖርትና ባህል ፌደሬሽን በአውሮፓ (ESCFE) 20ኛ ዓመት ክብረ-በአሉን በጀርመን - ፍራንክፈርት ከተማ እንደሚያካሄድ ፌዴሬሽኑ በዛሬው እለት በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

ከሰላሳ በማያንሱ ክለቦች መካከል ከሚደረጉ የእግር ኳስ ውድድሮች ባሻገር የሃገር ባህልን የሚያንፀባርቁ የሙዚቃ ድግሶች እንደሚኖሩ ተገልጿል።

እንዲሁም 10 የሚያህሉ የሀገራችን ትላልቅ አርቲስቶች የሙዚቃ ዝግጅታቸውን ያቀርባሉ ተብሏል።

ከነዚህም አርቲስቶች ውስጥ ፀሀዬ ዩሀንስ ልጅ ሚካሄል ፣ ህብስት ጥሩነህ ፣ ብርሀኑ ትዘራና አዲስ ሙላት ይገኛሉ ተብሏል።

የኢትዮጵያ ስፖርት እና ባህል ፌዴሬሽን በ2025 ፍራንከፈርት ለሚካሄደው ፌስቲቫል ከኪንግሶሎ ፕሮሞሽን፣ ጋር በዚህ ዘርፍ በጋራ ለመስራት መስማማቱ ተገልጿል።

ፌደሬሽኑ የተመሰረተው እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1999 ሲሆን፣ ጠንሳሾቹ ከበሶስት ቡድኖች፣ ማለትም ከኢትዮ ፍራንክፈርት፣ ከኢትዮ ሆላንድ እና ከኢትዮ ፍራንስ የተውጣጡ የስፖርት አፍቃሪዎች ነበር።

ስብስቡ በየአመቱ እያደገ መጥቶ በ2005 በአውሮፓ በፌዴሬሽን ደረጃ ለመመዝገብ በቅቷል።

ፌደሬሽኑ በ20 አመታት ጉዞው ዛሬ ከ22 የአውሮፓ ከተሞች የተውጣጡ 40 የእግር ኳስ ቡድኖችን ያፈራ ሲሆን፣ 20 ቡድኖች በአንደኛ ዲቪዢዮን ሲጫወቱ 20ዎቹ ደግሞ በሁለተኛ ዲቪዚዮን የተሰለፉ ናቸው።

ክለቦቹ የተቋቋሙት በቤልጂየም፣ ኔዘርላንድ፣ ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ጣሊያን፣ ሰዊድን፣ ኖርዌይ፣ ስዊዘርላንድ፣ ኢንግላንድ፣ ፊንላንድ፣ አየርላንድ፣ ዴንማርክ፣ ሰፔይን፣ ኦስትሪያ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ነው።

አመታዊ ዝግጅቱ የእግር ኳስ ውድድርም ብቻ አይደለም፣ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን በሚኖሩበት የአውሮፓ አህጉር፣ ከህፃን እስከ አዛውንት በጉጉት የሚጠብቁት፣ ዘመድ አዝማድ፣ ጓደኛሞችን የሚያገናኙበት ማእከልም ነው።

የኢትዮጵያውያን ስፖርት እና ባህል ፌዴሬሽን በአውሮፓ (ESCFE) ኢትዮጵያውያንን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን በስፖርትና በባህል ቅርስ የሚያስተሳስር በአውሮፓ ብቸኛው ህጋዊ ተቋም ነው።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

ባለፉት 5 ዓመታት የኢትዮጵያ መንግሥት ወጪው ከገቢው በከፍተኛ ደረጃ እንደበለጠ ተገለጸ  | የኢትዮጵያ መንግሥት ባለፉት 5 ዓመታት ያወጣው ወጪ ከሚያገኘው ገቢ በከፍተኛ ደረጃ መብለጡን የኢ...
18/07/2025

ባለፉት 5 ዓመታት የኢትዮጵያ መንግሥት ወጪው ከገቢው በከፍተኛ ደረጃ እንደበለጠ ተገለጸ

| የኢትዮጵያ መንግሥት ባለፉት 5 ዓመታት ያወጣው ወጪ ከሚያገኘው ገቢ በከፍተኛ ደረጃ መብለጡን የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ባለሙያዎች ማህበር አስታውቋል።

የኢትየጵያ ኢኮኖሚክስ ባለሙያዎች ማህበር በዛሬው ዕለት 22ኛውን ዓለም አቀፍ ጉባዔ ያካሄደ ሲሆን፤ በመድረኩም ከወቅታዊ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ጥናታዊ ፅሁፎች ቀርበዋል።

በቀረበው ጥናትም የኢትዮጵያ መንግሥት ወጪው ከሚያገነው ከገቢ በከፍተኛ ደረጃ የበለጠ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በተቃራኒው መንግሥት ገቢው ከወጪው አንፃር አነስተኛ መሆኑን የገለጹት የማህበሩ ከፍተኛ ተመራማሪ ዶክተር አረጋ ሹመቴ፤ በጥናቱ 'የመንግሥት ወጪ አቅጣጫ ወዴት የሚያመዝን ነው?' የሚለውም መጠናቱን ገልጸዋል፡፡

"በከፍተኛ ሁኔታ የመንግሥት ካፓታል ወጪ መቀነሱም በጥናቱ ተረጋግጧል" ብለዋል፡፡

"ከ2016 ዓ.ም በፊት የመንግሥት ወጪ ትልቁን መደበኛ በጀት እየያዘ ኢንቨስትመንት እየቀነሰ መሄዱ ማሳያ ነው" ያሉት ዶክተር አረጋ "መንግሥት ትልቁ ኢንቨስተር ቢሆንም የሚጠበቀውን ያህል ግን ኢንቨሰት እያደረገ ለካፒታል በጀትም እየተያዘ አይደለም" ሲሉ ጠቁመዋል።

ሌላው ትኩረት የተደረገበት ጥናት የመንግሥት ዕዳ ላይ የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ ዕዳ ከፍተኛ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በመድረኩም "ማንኛውም ሀገር ዕዳ አለበት" የተባለ ሲሆን፤ ዕዳው ከሀገር ውስጥም ሆነ ከውጪ ሊሆን እንደሚችል ተናግረዋል።

ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ዕዳ ያለበት የውጭ ዕዳ በመሆኑና ዕዳውም የመጣው በመንግሥት በራሱ እና የመንግሥት ተቋማት እንደ ኤልፓ፣ ቴሌኮም እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመሳሰሰሉ ተቋማት ናቸው ብለዋል፡፡

በተመሳሳይ መልኩ ጥናቱ የኢትዮጵያ ዕዳ የመክፈል አቅሟም ለመመለከት የተሞከረ ሲሆን፤ ዕዳ የመክፈል አቅም የሚለካው ወደ ወጪ በሚላክ ምርት ጋር የተያያዘ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የኢትዮጰያ ዕዳ ከፍተኛው የውጭ ዕዳ በመሆኑ መለኪው ወደ ወጪ የሚላከው ምርቷ መሆኑ የተገለጸም ሲሆን፤ በዚህ አንፃር ሀገሪቱ ብዙ የውጭ ዕዳ አለባት ተብሏል፡፡ የሚካሄደዉ ጉባኤ እስከ ነገ የሚቀጥል መሆኑም ተገልጿል፡፡

ኪን ኢትዮጵያ የባህል ቡድን በቻይና የመጀመርያ ጉዞውን ሊያደርግ ነው   ኪን ኢትዮጵያ- "የኢትዮጵያ ማንሰራራት ብስራት” በሚል መሪ ሀሳብ በዓይነቱና በይዘቱ ለየት ያለ የጥበብ ጉዞ በቻይና ...
18/07/2025

ኪን ኢትዮጵያ የባህል ቡድን በቻይና የመጀመርያ ጉዞውን ሊያደርግ ነው

ኪን ኢትዮጵያ- "የኢትዮጵያ ማንሰራራት ብስራት” በሚል መሪ ሀሳብ በዓይነቱና በይዘቱ ለየት ያለ የጥበብ ጉዞ በቻይና ይጀምራል።

በቁጥር ከ70በላይ ሙያተኞች እና ከ50 በላይ የብሔር ብሔረሰቦች ሙዚቃና ባህል የሚቀርቡበት ነው ተብሏል።

ባጠቃላይ በዚህ ጉዞ ኢትዮጵያ ሙሉ በሙሉ ትተዋወቅበታለች ተብሏል።

የኢትዮጵያን ቱባ ባህልና ጥበብን ለዓለም ህዝብ ለማስተዋወቅ፤ የባህልና የጥበብ ዲፕሎማሲ በመስራት የሀገራችንን መልካም ገፅታ የመገንባት ዓላማ ያነገበ ኩነት እንደሆነም ነው የተገለጸው።

የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር እንዲሁም የመንግስት ኮሚኒኬሽን ሚኒስትር ከሻኩራ ፕሮዳክሽን ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነው ተብሏል።

በሙዚቃ ባለሙያ ካሙዙ ካሳ የቡድን መሪነት ወደ ቻይና በሚደረገው የጥበብ ጉዞ ኪነ-ጥበብን፣ ሥነ- ጥበብን እንደ ትልቅ መሣሪያ በመጠቀም ለሀገር ገጽታ ግንባታ የማይተካ ሚና ይኖረዋል ተብሏል።

በመግለጫው ላይ የተገኙት የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ የምትጓዙ የልኡካን ቡድን አባላት፤ መርሐ-ግብሩ የታለመለትን ዓላማ በማሳካት ግቡን እንዲመታ የበኩላችንሁን ታላቅ ሙያዊና ሀገራዊ ኃላፊነት እንድትወጡ አደራ እላችሁሀለሁ ብለዋል።

እንዲሁም ባገኛችሁት አጋጣሚ ሁሉ ያላችሁን አቅም አሟጣችሁ በመጠቀም የኢትዮጵያን መልካም ገጽታ ከፍ የማድረግ ታሪካዊ አደራ የተሸከማችሁ እያስገነዘብኩ ይሔንኑ ታላቅ ኃላፊነት በታማኝነት፣ በቁርጠኝነትና በፍጹም ትጋት እንዲትወጡት ከአደራ ጭምር መልዕክት ሳስተላልፍ በታላቅ መተማመንና በጠነከረ መንፈስ ነው ብለዋል።

አሁን ሀገራችን ኢትዮጲያ በፈጠራ ጥበብ በኩል አኩሪ ባህሏን ታሪኳንና የተፈጥሮ ፀጋዋን ለዓለም በተገቢው መንገድ በመግለፅ የዓለምን ትኩረት መሳብና ከውጤቱ ተጠቃሚ ለመሆን የምትችልበት ታላቅ ተግባር ተጀምሯል ብለዋል።

ሻኩራ ፕሮዳክሽን እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ስራ በመስራት “ኪን ኢትዮጵያ፡ የኢትዮጵያ ማንሰራራት ብስራት” የጥበብ ጉዞን ከፊታችን እሁድ ጀምሮ ጉዞዋቸውን ያደርጋሉ።

የሻኩራ ፕሮዳክሽን ሀላፊ አርቲስት ካሙዙ ካሳ በበኩሉ በዚህ የጥበብና የባህል ጉዞ የማናስተዋወቅው ነገር አይኖርም እድሉን ባግባብ ለመጠቀም ዝግጅታችን ጨርሰናል ብሏል።

ኢትዮጵያ አገራችን በቅርቡ በአባልነት በታቀፈችበት የብሪክስ አባል አገራት የሚደረገው ይህ ጉዞ ለውስጥ ሀገራዊ አንድነት፣ ለጠነከረ የሕዝብ ለሕዝብ ትስስርና አብሮነት፣ ለገጽታ ግንባታ፣ ለውስጣዊ ሰላምና ለሁለንተናዊ ብልጽግና ያለንን ባህላዊ ሀብት በተግቢው መልኩ መጠቀም ያስችላል ብለዋል።

ይህ ጉዞ ሀገራችን የላትን አኩሪ ባህሏን፣ ታሪኳንና የተፈጥሮ ፀጋዋን ለዓለም በማስተዋወቅም ከፍተኛ ጥቅምን ያስገኝላታል።

ከዚህ በተጨማሪ አርቲስት ካሙዙ ካሳ
ሶረን ትሬዲንግ እና ሎጀስቲክ በቻይና ላደረገው አስተዋጽኦ በልዩ ሁኔታ አመስግኗል።

የኢትዮጵያን ቱባ ባህልና ኪናዊ ፀጋ ለዓለም ህዝብ ለማስተዋወቅ ከ39 አመታት በኋላ የሚደረገው የዓለም አቀፍ ጉዞ (ኪን ኢትዮጵያ) ከዚህ ቀደም ከቀረቡ የባህል ሙዚቃዎች ሁሉ ለየት ባለመልኩ ሁሉም ብሔር ብሔረሰቦችን ያማከለ እና ትርዒቱ በሰርከስናና ባህላዊ ፍሽን ትርዒት ከዉብ የመድረክ ገፅታ ጋር የተላበሰ ነበር።

የኢትዮጵያ ማንሰራራት ብስራት) በቀጣይነትም ኢትዮጵያን ጨምሮ ብራዚልን፣ ሩሲያ፣ ህንድ፣ ቻይና፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ግብጽና ኢንዶኔዥያን በአባልነት ባቀፈው የብሪክስ አባል አገራት እና በሌሎች የአለማችን ሐገራት በተከታታይነት ይካሄዳል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ምሩቃን ቀን በደማቅ ሁኔታ ተከበረ📌 የቀድሞ የጎንደር ዩኒቨርስቲ ኘሬዝዳንቶች ወግ ተካሂዷል።  | የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ያስተማራቸውን ምሩ...
18/07/2025

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ምሩቃን ቀን በደማቅ ሁኔታ ተከበረ

📌 የቀድሞ የጎንደር ዩኒቨርስቲ ኘሬዝዳንቶች ወግ ተካሂዷል።

| የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ያስተማራቸውን ምሩቃን ያሰባሰበውን የቀድሞ ምሩቃን ቀን"ለሕይወት የተገናኙ፤ ለልህቀት የተዋሐዱ" በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ፕሮግራሞች በድምቀት አክብሯል።

ይህ መርሃ ግብር ምሩቃን ከተቋማቸው ጋር ያላቸውን ግንኙነት እንዲያጠናክሩ እና ለዩኒቨርሲቲው ያላቸውን ሃላፊነት እንዲወጡ ለማሰብ ታስቦ የተዘጋጀ ሲሆን በዕለቱ የዩኒቨርሲቲው ታሪክ፣ ስኬቶች እና የወደፊት ተስፋዎች የተንፀባረቁበት እና በቀድሞ ምሩቃን እና በተቋሙ መካከል ያለውን ትስስር ያጠናከረበት አጋጣሚ ሆኗል።

በተጨማሪም፣ የቀድሞ ምሩቃን ጎንደር ዩኒቨርስቲ በእውቀት፣ በቁሳቁስ፣ በገንዘብና በሃሳብ መደገፍ የሚችሉበትን መንገድ የሚዳስሱ የትምህርት መርሃ ግብሮች ቀርበው ገንቢ ውይይት ተደርጓል። ይህ ውይይት ምሩቃን ለዩኒቨርሲቲው እድገት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ የሚያስችሉ ተግባራዊ መፍትሄዎችን ለመለየት ወሳኝ ነበር።

የምሩቃን መመዝገቢያ ሥርዓት እና የማኅበር ምስረታ
የዩኒቨርሲቲው ምሩቃን ግንኙነታቸውን በተቋማዊ መንገድ እንዲመሩ የሚያስችል "የምሩቃን መመዝገቢያ ሥርዓት" ተዘርግቶ ምዝገባ መጀመሩ በዚሁ ዕለት የተገለጸ ሲሆን ይህ ሥርዓት ምሩቃን እርስ በርስ እና ከዩኒቨርሲቲው ጋር ያላቸውን ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ ሲሆን፣ ቀሪ ምሩቃንም በዚህ ሥርዓት ውስጥ እንዲመዘገቡ ጥሪ ቀርቧል።

በተጨማሪም፣ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ምሩቃን ማኅበር በይፋ የተመሰረተ ሲሆን፣ ማኅበሩን እንዲያስተባብሩ እና በፕሬዝዳንትነት እንዲመሩ ዶክተር ካሱ ከተማ ተሹመዋል። የማኅበሩ ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ደግሞ ዶክተር ተዋበች ቢሻው ተመርጠዋል። ከእነርሱ በተጨማሪ ዶክተር አስቻለው አባይነህ፣ ዶክተር ግርማ አባቢ፣ ዶክተር አንዳርጋቸው ሙሉ፣ ጋዜጠኛ ሊያ ሳሙኤል እና አቶ ስለሺ ግርማ የማኅበሩን ቦርድ አባላት ሆነው ተመርጠዋል። የማኅበሩ መቋቋም የምሩቃንን አንድነትና ትብብር በማጠናከር ለዩኒቨርሲቲው ቀጣይ እድገት አስተዋፅኦ እንደሚያደርግ ይጠበቃል።

ከሰዓት በኋላ በነበረው መርሃ ግብር ደግሞ "የመሪነት ትሩፋት የዓመታት ፤ ጥበብ በሚል መሪ ሃሳብ" የፕሬዚዳንቶች ወግ የተሰኘ ልዩ ፕሮግራም ተካሂዷል። በዚህ መድረክ ላይ ተቋሙን አሁን ላለበት ደረጃ ያደረሱ የቀድሞ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶች በአካል ተገኝተው የረዥም ጊዜ ልምዳቸውን አካፍለዋል። ፕሮፌሰር ያሬድ ወንድምኩን (ከአሜሪካ በዙም )፣ ፕሮፌሰር ይግዛው ከበደ፣ ፕሮፌሰር መንገሻ አድማሱ፣ ዶክተር ደሳለኝ መንገሻ እና የአሁኑ ፕሬዚዳንት ዶክተር አስራት አፀደወይን የተቋሙን ታሪክ፣ ተግዳሮቶች እና ስኬቶች በግል ተሞክሯቸው ላይ በመመስረት አቅርበዋል።

ይህ የዩኒቨርስቲው ኘሬዝዳንቶች ወግ በተለይ ለወጣቱ ትውልድ ትልቅ የስራ መነሳሳትን የሚሰጥ እና ከታላላቅ ምሁራን ልምድ የሚቀስምበት ዕድል ከመፍጠሩ ባሻገር ተቋሙን አሁን ላለበት ደረጃ ያደረሱ የቀድሞ መሪዎች እውቅና የሚሰጥበት እንደሆነ የጎንደር ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር አስራት አፀደወይን በመርሃግብሩ መክፈቻ ላይ ገልጸዋል።

አክሻባት፡ ትራባዞን ቱርክ 🇹🇷   በ ገብረማርያም ይርጋ    | በአለምአቀፍ የአዉሮፓ ባህል ፌስቲቫል ለመሳተፍ ወደ ቱርክ ከተጓዝን ሰንበተናል።  ኢትዮጵያንና ሰንደቋን ገጽታዎቿንና መንፈሷን...
18/07/2025

አክሻባት፡ ትራባዞን ቱርክ 🇹🇷
በ ገብረማርያም ይርጋ

| በአለምአቀፍ የአዉሮፓ ባህል ፌስቲቫል ለመሳተፍ ወደ ቱርክ ከተጓዝን ሰንበተናል። ኢትዮጵያንና ሰንደቋን ገጽታዎቿንና መንፈሷን፣ ህዝቦቿንና ታረኳንና ባህሏን ይዘን በድምቀት እየተሳተፈን እንገኛለን ።

ከሀምሌ 10 /2017 ዓ.ም ቱርክ ኢስታንቡል ደርሰን ዙሪያ ገባዉን ቃኝተን በሰሜናዊዋ ቱርክ በሚካሄደው አለምአቀፍ የአዉሮፓ ፌስቲቫል የኢትዮጵያን ባህል፣ ኪነ-ጥበብና እሴቶች የማስተዋወቅ ስራ ለመስራት ተሰይመናል።

አክሻባት፤ በቱርክ ሰሜናዊ ምስራቅ ጥቁር ባህር ጠረፍ ላይ በትራብዞን ግዛት የምትገኝ አውራጃ ከተማ ነች። ለብዙ ዘመናት በታሪክ፣ በህዝባዊ ወጎች እና ከተፈጥሮ ጋር ባለው ጥልቅ ትስስር በበለጸገ ባህላዊ ማንነቷ ትታወቃለች።

ይህ አኗኗሯና ሥነ-ሥርዓቶቿ የአክሻባትን ጥበባዊ አገላለጾች፣ የውበት እሴቶችን እና ባህላዊ ልምምዶቿን እና በባህሎቿ ውስጥ የተካተቱትን ሰፊ የሰው ልጅ ትዕምርቶችን የሚያንፀባርቁ ናቸዉ።

ቱርክ ትራባዞን አክሻባት የባህል ጥበብ እና ውበት መናገሻ አብሮነት ማሳያ ምሳያ ነች። የህዝቦቿ አኗኗር፣ በግሎባላይዜሽን ዓለም ውስጥ የባህሎቹ ከዘመናዊነት ጋር ሳይጣላ ሥር መስደድን፣ ማህበረሰብ ኪነጥበብን እንደ ቅንጦት ሳይሆን ትርጉም በመስጠት እና ቀጣይነት ያለዉ የታሪክ እጥፋት ወሳኝነት ተረድተዉ እየተጠቀሙበት እንደሆነ ያስተምራል።

አክሻባት ትራባዞን ህዝቡ በዋነኛነት ቱርክኛ ነው። ከፖንቲክ (ግሪክ)፣ ላዝ እና ካውካሰስ ባህሎች በታሪካዊ ፍልሰት እና ንግድ ስራ አማካኝነት ተጽእኖ አሳድረዉባታል።

ለአክሻባት ቱርክ በቃል የሚነገሩ ወጎች፣ የማህበረሰቡ እንግዳ ተቀባይነት ለአካባቢዉ መለያዎችና የኩራት የማህበራዊ መስተጋብር የማዕዘን ድንጋይ ናቸው።

አክሻባቶች ማህበረሰብን ያማከለ ውበት ጥበብ ለህዝብ እንጂ ለሊቃውንት አይተዉም ይላሉ።

ሙዚቃ፣ ውዝዋዜ እና ምግብ የማህበረሰብ ትስስርን የሚያጠናክሩ ለእኛ የተፈጠሩ ናቸው ይላሉ ። ከሥነ ሕንፃ እስከ ምግብ ስርዓታቸዉ ፣ የባህል ትስስር መፍጠሪያ መንገዳቸዉ ለተግባራዊነት እና ትክክለኛነት የሚሄዱበት ርቀት ያላቸዉን መሠጠት ያስተምራል።

ውበት የተፈጥሮ፣ ከልብ የመነጨ እንግዳዊ አክብሮት መገለጫ እና የሰለጠነ የእጅ ጥበብ ባለቤቶች አክሻባት፡ ትራባዞን ቱርክ።

Photo from :⁠-⁠)🌍

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን):

Share

GETU TEMESGEN - (ጌጡ ተመስገን)

ጌጡ ተመስገን ውልደቱና እድገቱ አዲስ አበባ ነው። በጋዜጠኝነት ሙያው፤ ለአገር እና ለሕዝብ በሠራቸው አይረሴ ሥራዎቹ በርካታ ሽልማቶችን አግኝቷል። የፈረንሳይ ቴሌቪዥን ባሰባሰበው የተመልካቾች ምዘና መሠረት ‹‹ባለንሥሩ ጋዜጠኛ ~ A Journalist with an eagle eye›› የሚል ስያሜ አግኝቷል።

Getu Temesgen was born and raised in Addis Ababa. As a result of his unforgettable journalistic works/TV productions, he has won various recognitions. He was named “The Journalist with an eagle eye” in an audience poll conducted by French TV.

ሦስት ሥራዎቹም በፈረንሳይኛ ቋንቋ ተተርጉሞ ቀርበውለታል። በአዘጋጁቹ ግብዣ አውሮፓ ፤ ጀርመን፣ ጣልያን፣ ፈረንሳይና ቤልጅየም ተጉዞ፤ ትምህርታዊ ጉብኝት በማድረግ አገር ቤት ተመልሷል።

His three TV productions were also presented for European audience in French language and as a result was invited by the producers to visit France, Germany, Italy and Belgium.”