MCM Eye Unit - Korean Hospital የኮርያ ሆስፒታል አይን ሕክምና ክፍል

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • MCM Eye Unit - Korean Hospital የኮርያ ሆስፒታል አይን ሕክምና ክፍል

MCM Eye Unit - Korean Hospital  የኮርያ ሆስፒታል አይን ሕክምና ክፍል MCM Eye Unit - Korean Hospital is a joint initiative of Ethiopian and American ophthalmologists and medical professors from sight for souls.

The goal of the partnership is to establish innovative eye care service delivery in Addis Ababa.

Uveitis Uveitis means inflammation inside the eye. It affects the part of the eye called the uvea which consists of the ...
17/09/2021

Uveitis
Uveitis means inflammation inside the eye. It affects the part of the eye called the uvea which consists of the iris, ciliary body and choroid.
Uveitis can cause serious problems and vision loss but with prompt treatment it can be controlled in most people. Some cases require specialist care as MCM eye unit offers.

Who gets it?
It is unknown why most people get uveitis. It can develop in people who are completely healthy.

However, there is a greater risk of uveitis in people with other inflammatory or autoimmune problems such as inflammatory bowel disease and inflammatory arthritis.
In some cases, uveitis is caused by an infection. Your ophthalmologist may
request investigations to check for an underlying cause.

Signs and symptoms
Symptoms depend on the type of uveitis present (whether it mainly affects the front or the back of the eye).
The most common symptoms are redness, light sensitivity, eye ache, and blur. It usually affects one eye, but in some people, both eyes will be involved

Treatment
There is no known cure for uveitis, but in most cases, it can be treated very effectively with a course of steroid eye drops over four to six weeks.
Severe cases involving the back of the eye usually require oral/injectable treatment as eye drops cannot pe*****te well. into the back of the eye.

17/09/2021
What is Glaucoma?Glaucoma is the second leading cause of blindness worldwide after cataracts but is the leading cause of...
09/03/2021

What is Glaucoma?

Glaucoma is the second leading cause of blindness worldwide after cataracts but is the leading cause of irreversible vision loss. It is an eye disease that affects more than 4% of the population in most African countries. There may be no symptoms of glaucoma as it is often a silent disease slowly developing over time.
Early detection, through regular and complete eye exams, is the key to protecting your vision from damage caused by glaucoma.

How does Glaucoma occur?
Glaucoma occurs when the intraocular pressure (IOP) within the eye is high enough to cause progressive damage to the optic nerve and nerve cells within the retina, resulting in vision loss.

22/11/2020

ከፀሃይ የሚመነጭ ከፍተኛ መጠን ያለው አልትራ ቫዮሌት ጨረር ለአይን ጠንቅ ነው። የአይናን ብሌን እንዲሁም ሌንስ ላይ ጉዳት ያስከትላል በተጨማሪም ለካንሰር መከሰት ምክንያት ይሆናል። አስተማማኝ የሆኑ አልትራ ቫዮሌት ጨረርን መከላከል የሚችሉ በሃኪም የሚታዘሁ መነፅሮችን መጠቀም አይንን ከጉዳት ተከላክለው ተፈጥሮን ያለስጋት ማጣጣም ያስችላል።

በኮርያ አጠቃላይ ሆስፒታል ውስጥ የሚገኘው የአይን ሕክምና ክፍላችን አስፈላጊውን የጥንቃቄ መመሪያ በመተግበር አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ ነው። በሕክምና ክፍላችን በመገኘት የአይን ምርመራዎን ያድርጉ።
ከሰአት በኋላ ቢመጡ ወረፋ ሳይጠብቁ በፍጥነት ይስተናገዳሉ።

Too much UV radiation from the sun is a real threat to vision. It can damage the eye's surface tissues, the cornea and the lens. Cataracts and eye cancers can eventually form from too much UV exposure. Luckily, wearing 100% UV or UV400 protection sunglasses is an effective way to protect your eyes while enjoying the outdoors.

Vision is for life. The MCM Eye unit at the Korean Hospital has taken all steps to provide a safe place for care. Don’t put it off. Come in for an eye exam today.

በኮሮና አይነት ወረርሽን ግዜ በርካቶች ከመደበኛ ህክምናቸው ይቀራሉ:: ጠንቃቃ መሆን  ሁሌም አስፈላጊ ነው:: በኮርያ አጠቃላይ ሆስፒታል ውስጥ የሚገኘው የአይን ሕክምና ክፍላችን አስፈላጊውን...
28/10/2020

በኮሮና አይነት ወረርሽን ግዜ በርካቶች ከመደበኛ ህክምናቸው ይቀራሉ:: ጠንቃቃ መሆን ሁሌም አስፈላጊ ነው:: በኮርያ አጠቃላይ ሆስፒታል ውስጥ የሚገኘው የአይን ሕክምና ክፍላችን አስፈላጊውን የጥንቃቄ መመሪያ በመተግበር አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ ነው። በሕክምና ክፍላችን በመገኘት የአይን ምርመራዎን ያድርጉ።
ከሰአት በኋላ ቢመጡ ወረፋ ሳይጠብቁ በፍጥነት ይስተናገዳሉ።

With the pandemic, many people put off routine exams and minor health care. Being careful is important, but so is eye care. Vision is for life. The MCM Eye unit at the Korean Hospital has taken all steps to provide a safe place for care. Don’t put it off. Come in for an eye exam today.

ዲጂታል እስክሪኖችና የአይናችን ጤና የፀሀይ ብርሃን ከሰባት ቀልማት (ቀይ፣ ብርቱካናማ፣ ቢጫ፣ አረንጓዴ፣ ሰማያዊ፣ ጥቁር ስማያዊና ሐምራዊ) የተፈጠረ ነዉ፡፡  ቀለማቱ ሲቀላቀሉ አሁን የምንመ...
22/06/2020

ዲጂታል እስክሪኖችና የአይናችን ጤና

የፀሀይ ብርሃን ከሰባት ቀልማት (ቀይ፣ ብርቱካናማ፣ ቢጫ፣ አረንጓዴ፣ ሰማያዊ፣ ጥቁር ስማያዊና ሐምራዊ) የተፈጠረ ነዉ፡፡ ቀለማቱ ሲቀላቀሉ አሁን የምንመለከተውን የብርሀን ቀለም ይሰጡናል፡፡እነዚህ ቀለማት እንደ አይነታቸው ሁሉ ጉልበታቸውና አይናችን ላይ የሚያሳድሩት ተፅእኖ ይለያያል። በአይን ከሚታዩ የብርሃን አይነቶች ጠንካራ ጉልበት ያለውና አይናችን ላይ ተፅእኖ የማደረስ አቅም ያለው ባለ ሰመያዊው ቀለም ነው። የሰማያዊ ብርሀን ዋናዉ ምንጭ የፀሀይ ብርሀን ሲሆን ሌሎች ዘመን አመጣሽ ቴክኖሎጂ የሆኑት ተንቀሳቃሽ ስልክ፣ ታብሌት ስልኮች፣ ኮምፒውተር ስክሪን፣ ቀጫጭን ኤልኢዲ ቴሌቪዥኖችና ከፍሎሮሰንት መብራቶችም ይኸው ብርሃን ይነሳል፡፡

በየለቱ ከምንጠቀማቸው የተለያዩ ስክሪኖች የሚነሳው ሰማያዊ ብርሀን መጠን ከፀሀይ ጋር ሲነፃፀር ትንሽ ቢሆንም ለዓይናችን ካለው ቅርበትና ስክሪኖች ላይ ከምናሳልፈዉ ረጅም ሰአት አንፃር ዓይናችን ላይ ከፍተኛ ጫና ይፈጥራል፡፡ በሰው ዓይን ሊታዩ የሚችሉት ጉዳት አምጭ የብርሃን ጨረሮች የዓይን ብሌንን እና ሌንስን አልፎ የውስጠኛው የብርሀን መቀበያ ክፍል ላይ ያርፋሉ፡፡ ይህ ደግሞ ለረጅም ገዜያት ሲደጋገም ዓይናችን ላይ ከእድሜ ጋር ያልተመጣጠነ የብርሀን መቀበያ ማርጀት ያመጣል፡፡ ሰማያዊ ብርሀን ዓይናችን ላይ ከሚያስከተለው ችግር በተጨማሪ በሰውነታችን ውስጥ የሆርሞን ለውጥ በማምጣት የተለመደውን የእንቅልፍ ሰዓትን ያዛባል ስለዚህም ከእንቅልፍ በፊት የኤሌክትሮኒክስ ሰክሪን ማየት አይመከርም፡፡

ዓይናችን ለረጅም ሰአት ለሰማያዊ ብርሀን ጨረሮች መጋለጥ የሚያመጣቸዉ ችግሮች፡-
• ከፍተኛ የሆነ የዓይን መድከምና ምቾት ማጣት
• ለማንበብ እና ለመስራት መሰልቸት
• የዓይን ድርቀት
• የዓይን መቅላትና ትኩረት ማድረግ አለመቻል
• የውስጠኛው ብርሃን መቀበያ ሕዋሶች ጉዳት

ይህንን ችግር ለመከላከል
• ስክሪኖች ላይ የምናሳልፈውን ሰዓት መቀነስ
• ሰማያዊ ብርሃን ወደ ዓይናችን እንዳይገባ ሙሉ በሙሉ የሚያስቀር የመነፅር ሌንሶችን መጠቀም
• የስክሪን ብርሃን መቀነሻ ልባሶችን መጠቀም
• ነፀብራቅን የሚቀንሱ መነፅሮችን መጠቀም ይመከራል

በኮርያ ሆስፒታል የአይን ህክምና ክፍላችን አስፈላጊውን ምርመራ በማድረግ የእይታና ብርሃን መከላከያ መነፅሮችን ማግኘት ይቻላል።

መልእክቱን ሼር በማድረግ ያጋሩ

የአይን ሞራ ግርዶሽ የሌንስ  ብርሃንን የማስተላለፍ አቅምን በመቀነስ እይታን ያዳክማል፤ የምሽት እይታ መቀነስና አንፀባረቂ ብርሃን መፍራትን ያስከትላል። መልካሙ ዜና ደግሞ እይታን በቀዶ ጥገ...
20/06/2020

የአይን ሞራ ግርዶሽ የሌንስ ብርሃንን የማስተላለፍ አቅምን በመቀነስ እይታን ያዳክማል፤ የምሽት እይታ መቀነስና አንፀባረቂ ብርሃን መፍራትን ያስከትላል። መልካሙ ዜና ደግሞ እይታን በቀዶ ጥገና ማስተካከልና መመለስ ይቻላል። ለበለጠ መረጃ የፌስቡክ ገፃችንን ያንብቡ ፡፡

Cataracts cloud the lens of the eye and cause vision to blur or dim. They can cause difficulty with night vision and sensitivity to light. The good news is that cataracts can be removed and vision restored. Learn more from our other cataract post.

ግላኮማ ወይም የአይን ግፊት ምንድነ ነው?ግላኮማ በዋነኝነት የዓይን ዉስጥ ፈሳሽ ግፊት ከተገቢዉ በላይ ጨምሮ የእይታ ማሰተላለፊያ ነርቭ ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ በጊዜ ሂደት መመለስ የማይ...
15/06/2020

ግላኮማ ወይም የአይን ግፊት ምንድነ ነው?

ግላኮማ በዋነኝነት የዓይን ዉስጥ ፈሳሽ ግፊት ከተገቢዉ በላይ ጨምሮ የእይታ ማሰተላለፊያ ነርቭ ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ በጊዜ ሂደት መመለስ የማይችል የእይታ አድማስ መቀነስና ሙሉ ለሙሉ የዓይን ብርሀንን የሚያሳጣ ህመም ነዉ፡፡ ግላኮማ ለከፋ አይነስውርነት የሚያጋልጥ የአይን ህመም ነው፡፡

ግላኮማን በሁለት ከፍለን ማየት እንችላለን ይህም ክፍት ማእዘን ግላኮማ (open angle glaucoma) እና ዝግ ማእዘን ግላኮማ (closed angle glaucoma) ፤ ብዙ ታማሚዎች ላይ በብዛት የሚከሰተው የክፍት ማእዘን ግላኮማ ለረጅም ጊዜ ምንም አይነት ምልክት አያሳይም ነገር ግን ምልክት መታየት ሲጀምር እይታ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶአል ማለት ነው።

ለክፍት ማእዘን ግላኮማ(open-angle glaucoma) አጋላጭ ሁኔታዎች ዉስጥ ዋናዋናዎቹ፡-
• እድሜ (ከ40 አመት በላይ)
• አይን ላይ የሚደርስ ምት
• በዘር በመተላለፍ
• ማዮፒያ (short-sightedness)
• ሌሎች የሰዉነት ህመሞች ለምሳሌ እንደ ደም ግፊት፣የስካር ህመምና የልብችግር
• ረጅም ጊዜ ኮርቲኮሰቴሮይድ መድሃኒቶችን መጠቀም
• ሲጋራማ ጨስና ከመጠን ያለፈ አልኮል መጠጣት

ለዝግ ማእዘን ግላኮማ(closed-angle glaucoma)ከሚያጋልጡ ነገሮች ዋናዋናዎቹ፡-
• እድሜ
• በተፈጥሮ ትንሽ መጠን ያለዉ የዓይን ኳስ
• ጻታ ( በሴቶች ላይ የበለጠ ይታያል)
• ከቤተሰብ ውስጥ ሲኖር
• ዓይን ላይ የደረሰ ምት ወይ ምአደጋ
• በዓይን ዉስጥ ያሉ ክፍሎች በተለያየ ምክንያት መቆጣት
• ህክምና ሳይደረግለት የቀረ የዓይን ሞራ

የዓይን ግፊት ልኬትና የእይታ አድማስ (visual filed) ልኬት ግላኮማን የከፋ ጉዳት ሳያደርስ ለማወቅ የሚያስችል የዓይን ህክምና ምርመራዎች ናቸው፡፡ የኦሲቲ (OCT) ምርመራ ደግሞ ነርቭ ላይ የደረሰውን ጉዳት መለካት ይቻላል። የእይታ ነርቭ ወደ ዓይናችን ኳስ ውስጥ ሚገባበትን የብርሀን መቀበያ ክፍል በዓይን መመርመሪያ መሳሪያ በመመልከት በግላኮማ ምክንያት የተከሰተ ለውጥ መኖር አለመኖሩን የዓይን ሀኪም ጋር ቀርቦ በመመርመር የከፋ ጉዳት ሳያደርስ ማወቅ ይቻላል፡፡

የግላኮማ እንደየደረሰበት ደረጃ የተለያየ ህክምና አማራጮች አሉ፡፡
• የመድሐኒት ህክምና
• የጨረር ህክምና
• የቀዶ ህክምና

በግላኮማ ምክንያት የሚከሰተ የእይታ መቀነስ ወይም ዓይነ ስውርነት ሊመለስ የማይችል ነው፡፡ በዋነኝነት የግላኮማ ህክምና የሚረዳው አንድ የግላኮማ ችግር የገጠመው ሰው ህመሙ ከታወቀ በኃላ እይታው ከዛ የባሰ እንዳይቀንስና ለዓይነ-ስዉርነት እንዳይዳረግ ነው፡፡ በተለይ ክፍት መአዘን ግላኮማ ምንም አይነት የህመም ምልክት ሳናስተውል ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳል፡፡ ለዚህም ነው ማንኛውም ሰው ቢያንስ በዓመት አንድ ጊዜ የዓይን ምርመራ ማድረግ አለበት ተብሎ የሚመከረው፡፡

የዓይን ሞራግርዶሽ ምንድን ነው?የአይን ሞራ ግርዶሽ የአይን እይታን የሚቀንስ ችግር ነው፡፡ የዓይናችን ብሌን በተለያዩ አሉታዊ በሆኑ የጊዜ ሂደት ለውጦች ምክንያት ብርሃን የማስተላለፍ አቅሙን...
10/06/2020

የዓይን ሞራግርዶሽ ምንድን ነው?

የአይን ሞራ ግርዶሽ የአይን እይታን የሚቀንስ ችግር ነው፡፡ የዓይናችን ብሌን በተለያዩ አሉታዊ በሆኑ የጊዜ ሂደት ለውጦች ምክንያት ብርሃን የማስተላለፍ አቅሙን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ሲያጣ ይከሰታል፡፡ በሀገራችን ለበርካታ ሰዎች እይታ ማጣት ምክንያት ሲሆን ማንኛውም ሰው ላይ የሚክሰት ችግር ቢሆንም አድሜያቸው የገፉ ሰዎች ላይ በብዛት ይክሰታል፡፡

ለዓይን ሞራ ግርዶሽ የሚያጋልጡ ነገሮች ፡-
☞እድሜ (50 አመት በላይ )
☞ለረጅም ጊዜ ለአልትራቫዩሌት/ጎጂ ጨረሮች መጋለጥ
☞ዓይን ላይ የሚደርስ አደጋ/ምት
☞በዘር በመተላለፍ
☞ስኳርና የረጅም ግዜ የኩላሊት እና መሰል ህመሞች
☞ሌሎች የዓይን ህመሞች
☞ማጨስ
☞የምግብ እጥረት
☞እስቴሮይድ መድኃኒቶችን ለረጅም ጊዜ መጠቀም

ምልክቶቹ ምን ምን ናቸው?
የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀስ በቀስ በጊዜ ሂደት እይታን እየቀነሰ በመጨረሻም ብርሀን ብቻ ለመለየት የሚያስችል እይታ አቅም ጋር ያደርሳል፡፡
በተጨማሪም፤
• ህመም የሌለው ቀስ በቀስ የቀን የአይታ መቀነስ
• አልፎ አልፎ ሁለት ምስል መታየት
• ደማቅ ወይም አንጸባራቂ ብርሀን መፍራት
• የአይን ብሌን መሀል ነጭ ምልክት መታየት

ሕከምናውስ ምንድነው?

በትክክለኛዉ ጊዜ ከታከመና የውስጠኛው የዓይን ክፍሎች ጤናማ ከሆኑ እይታን ሙሉ በሙሉ መመለስ ይቻላል፡፡ በዓይን ሞራ ግርዶሽ ምክንያት እይታ ሲቀንስ ያለዉ የህክምና አማራጭ የዓይን ቀዶ ህክምና ማድረግ ብቻ ነዉ፡፡
የተለያየ ዓይነት የቀዶ ህክምና አማራጮች ሲኖሩ እንዳለበት ደረጃና ሌሎች ተጓዳኝ ሁነታዎች ታይቶ በዓይን ሀኪሙና በታካሚዉ ምክክር ይወሰናል፡፡ ዋናዉ የቀዶ ህክምናዉ አላማ ብርሃን ማስተላለፍ ያቃተዉን የተፈጥሮ ሌንስ በማስወገዳ በምትኩ ሰዉ ሰራሽ ሌንስ ማስቀመጥ ነዉ፡፡ የዓይን ሞራ ግርዶሽን መታከም በሚገባዉ ጊዜ አለመታከም የዉስጠኛዉን የዓይን ክፍል እንዲቆጣ ከማድረግ በተጨማሪ ግላኮማን በማስከሰት ሊመለስ የማይችል የእይታ ማጣትን ያስከትላል፡፡

በ ኮሪያ ሆስፒታል አይን ሕክምና ክፍላችን ደረጃውን በጠበቀና ዘመናዊ መሳሪያ በመታገዝ በዘርፉ ከፍተኛ ልምድ ባላቸው ሐኪሞች የሞራ ምርመራና ቀዶ ጥገና እንሰጣለን።

Address

Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:00 - 16:30
Tuesday 08:00 - 16:30
Wednesday 08:00 - 16:30
Thursday 08:00 - 16:30
Friday 08:00 - 16:30
Saturday 08:00 - 11:00

Telephone

+251983360140

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when MCM Eye Unit - Korean Hospital የኮርያ ሆስፒታል አይን ሕክምና ክፍል posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram