
06/08/2025
የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ሰራተኞች በክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት በሰሊሆም የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል በመገኘት ነፃ የህክምና አገልግሎት ሰጡ።
የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ አዲስ አበባ ሃምሌ 30/2017 ዓ.ም
እንደሚታወቀው የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በተቋሙ ከሚሰጣቸው የጤና አገልግሎቶች መካከል በተጨማሪ ህክምና የሚሹ የማህበረሰብ ክፍሎችን እዛው ባሉበት ሄዶ የጤና የህክምና አገልግሎት እንደሚሰጥ ይታወቃል።
በተለይ የአዕምሮ ህሙማን ማዕከላት የአረጋውያንን ማቆያ ማዕከላት ወላጅ አልባ ህፃናት በጥቅሉ የተለያዩ መርጃ ማዕከላት ተቋሙ ለሚሰጣቸው የጤና አገልግሎቶች መዳረሻ ናቸው።
በመሆኑም በዛሬው እለት የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎትን አስመልክቶ በተቋሙ በCRC & MCC አስተባባሪነት 52 የሚደርሱ የጤና ባለሙያዎች በሰሊሆም የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል በመገኘት የተለያዩ የጤና ህክምና አገልግሎት ሰጥተዋል።
በዛሬው ዕለተ በሰሊሆም የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ለ352 ሰዎች የተደረገው የህክምና ድጋፍ ለታካሚዎቹ እጅግ እፎይታን የሰጠ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።
በተለይ በህክምና ሂደቱ ላይ የተሳተፉት ባለሙያዎች እንደገለፁት በዚህ ቦታ ተገኝቶ ይህንን ነፃ የህክምና አገልግሎት መስጠት ለነፍስ ደስታን ይሰጣል በማለት ተናግሯል። በተጨማሪም መሰል ኘሮግራሞች እንዲዘጋጅላቸውም የ CRC & MCC ክፍልን ጠይቀዋል ።
ተቋማችን የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ሰራተኞች ከዚህም በፊት በተለያዩ ግዚያት በሰሊሆም የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል በመገኘት ለወገኖቻችን የጤና አገልግሎት በመስጠት ለታማሚዎቹ እፎይታ መስጠታቸው ይታወሳል