16/11/2025
#ሰበር — የጂንካ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ከስራ ተባረሩ !
መርበርግ የተባለ አደገኛ ቫይረስ የ6 ሰዎችን ህይወት በቀጠፈ ማግስት የሆስፒታሉ ሜዲካል የዳይሬክሩ መባረር አነጋጋሪ ሆኗል።
ሜዲካል ዳይሬክተሩ የተባረሩትም አለማቀፉ ሚድያ በቫይረሱ የሞቱ ዜጎች መኖራቸውን በማረጋገጣቸው እንደሆነም የውስጥ ምንጮች ነግረውናል።
ከሰሞኑ ምንነቱ ባልታወቀ በሽታ የ 6 ሰዎች ህልፈትን ተከትሎ የማህበራዊ ሚድያዎች ትኩረት በጂንካ ሆስፒታል ላይ አነጣጥሯል።
ቫይራል ሄሞሬጅክ ፌቨር የተሰኘው አደገኛ የቫይረሶች ቡድን ተከተሰተ መባሉን ተከትሎ በተደረገ የሟቾች የደም ናሙና ምርመራ ውጤት ማርበርግ የተሰኘ አደገኛ ወረርሽኝ መከሰቱ ተሰምቷል።
የሟቾቹ የናሙና ምርመራ ውጤትን መነሻ በማድረግ በፌደራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴርና በኢትዮጽያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት በኩል የወረርሽኙን ክስተት ያረጋገጡ መግለጫዎችም በማህበራዊ ሚድያ ገጾቻቸው ያሰራጩ ሲሆን አለም ዓቀፉ የጤና ድርጅትም አፋጣኝ የገንዘብ፣ የሙያተኛና የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉም ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።
ይህንን ተከትሎ ከጀርመን ድምጽ ራድዮ ጣቢያ ዶቼቬሌ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ የሰጡት የጂንካ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ቢኒያም አስራት የወረርሽኙ ክስተት ሞት ማስከተሉን ያረጋገጡበትን ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ 4 ታካሚዎችና የህክምና እርዳታ ያደረጉላቸው 2 ሀኪሞች፤ 1 ዶክተርና 1 ነርስ ህይወት ማለፍን ያረጋገጡት ሜዲካል ዳይሬክተሩ የሟቾችን ቁጥር መግለጻቸው ተከትሎም ሜዲካል ዳይሬክተሩ ከስራቸው መባረራቸው ተሰምቷል።
የቀረበው ውንጀላም ለአለማቀፉ የሚድያ ተቋም DW የተከሰተውን ሃቅ ያረጋገጠ መረጃ ሰጥተሃል በሚል ውንጀላ መሆኑንም ከሆስፒታሉ የመረጃ ምንጮች ለማረጋገጥ ችለናል።
የፌደራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት በሰጡት በመግለጫ በሆስፒታሉ በቫይረሱ የተጠረጠሩ ሰዎችን እንጂ የሞቱ ሰዎች መኖራቸውን ያልገለጹ ቢሆንም ዳይሬክተሩ ይህንኑ ይፉ ማድረጋቸውን ተከተሎ ከስራ መታገዳቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ደርሷቸዋል።
የተከሰተው ቫይረስ እጅግ አደገኛና ገዳይ መሆኑ እየተገለጸ የሟቾችን ቁጥር መደበቅ ለምን እንደተፈለገ የታወቀ ነገር ባይኖርም ሃቁን ባለመደበቃቸው የተወነጀሉት ሜዲካል ዳይሬክተሩ ዶ/ር ቢኒያም አስራት አደገኛ ዛቻና የእስር ማስፈራሪያ እየደረሱባቸው መሆኑንም ለማረጋገጥ ችለናል።
ከስራ የተባረሩበት ደብዳቤ የደረሳቸው ሜዲካል ዳይሬክተሩን ለማነጋገር ተደጋጋሚ ጥረት ብናደርግም በዚህ ጉዳይ ምንም አስተያዬት ለማንም መስጠት እንደማይፈልጉ በመግለጽ ስልካቸውን ዘግተዋል።
ሆኖም ግን የእገዳ ደብዳቤው በክልሉ የጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ እንዳሻው ሽብሩ ጫና አድራጊነት የተጻፈባቸው መሆኑን ከሆስፒታሉ የውስጥ ምንጮች ለማረጋገጥ ችለናል።
በስራው ታታሪና ትጉህ የሆነው የጂንካው ተወላጅ ዶ/ር ቢኒያም ሆስፒታሉን ለማሻሻል እየተጋ ቢሆንም በተደጋጋሚ ጫና ውስጥ መቆየቱን ጠቁመው እውነተኛ መረጃ መስጠት ኃላፊነቱን በመወጣቱ ሊመሰገን ሲገባው ከስራ መታገዱ ተገቢ አይደለም ብለዋል።
በአለማቀፉ የጤና ተቋም ተረጋግጦ በመንግስት መግለጫ በተሰጠበት ጉዳይ መረጃ ምንም አይነት ክልከላ በሌለበት፤ ዶ/ሩ መባረር እውነታን ለመደበቅ የሚፈልግ አካል ሴራ ሊሆን ይችላል የሚሉት ምንጮቹ ሃቀኛ መረጃ እንዲሸፈን የተፈለገበት ምክንያት ግን ምን ሊሆን እንደሚችል አናቅም ብለዋል።
አስደንጋጭ እልቂት ያስከትላል የሚለው የቫይረሱ ስጋት ባጠላበት ጂንካ ሆስፒታል ከሟቾች ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸው በርካታ ዜጎች በተጠርጣሪነት ተለይተው በሚገኙበት በዚህ ወቅት
በከፍተኛ መደናገጥ ውስጥ የሚገኘው ነዋሪ ከመንግስት የሚሰጡ መመሪያዎችና የጥንቃቄ መልዕክት እየተጠባበቀ ቢሆንም የክልሉ ጤና ቢሮና የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት መገኛ በሆነው ጅንካ ክስተቱን በተመለከተ የክልሉ ልሳን የሆነው የደቡብ ሬድዮና ቴሌቭዥን ድርጅትም፤ የኢትዮጵያ ቴሌቭዥንንም ሆነ ሌሎች ሚድያዎች ዝምታን መምረጣቸው አነጋጋሪ ሆኗል።”
💥 ዶ/ር ቢኒያም አስራት በአስቸኳይ ወደ ስራው እንዲመለስ እንጠይቃለን! እውነት መናገር መረጃ ለሚዲያ መስጠት ወንጀል አይደለም። የሚመለከታቸው አለም አቀፍ ተቋማት ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጡ እንጠይቃለን። EHPM ለአለም አቀፍ ተቋማት እና ኤምባሲዎች በቀጣይ ቀናት ደብዳቤ የሚያስገባ ይሆናል።
በጂንካ ያላቹ ጤና ባለሞያዎች ስለ ዶ/ር ቢኒያም እና በMVD ምክንያት ስለሞቱት 6 ሰዎች የተብራራ መረጃ በ በአስቸኳይ ላኩልን!