
16/09/2025
✍️ የአይን ቆብ መርገብገብ (ማዮኪሚያ)
🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
🔹ማዮኪሚያ ይህ በጣም የተለመደው የዓይን መወዛወዝ አይነት ነው, ይህም በመለስተኛ እና አልፎ አልፎ በዐይን ሽፋን ጡንቻዎች መኮማተር ይታወቃል. ብዙውን ጊዜ ምንም ጉዳት የሌለው እና በራሱ መፍትሄ ያገኛል.
የዓይን መርገብገብ ያለፈቃድ ፣ ያልተለመደ የዐይን ቆብ መንቀጥቀጥ ማለት ነው። ይህ ያልተለመደ መንቀጥቀጥ በቀን ብዙ ጊዜ ሊከሰት ይችላል። የዓይን መንቀጥቀጥ ከባድ ከሆነ ፣ በእይታ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል።የአይን መንቀጥቀጥ የተለመደ እና አብዛኛውን ጊዜ ጉዳት የማያስከትል ነው፡፡ የአይን መንቀጥቀጥ አብዛኛውን ጊዜ ለደቂቃዎች ብቻ የሚቆይ ሲሆን አንዳንድ ጊዜ ደሞ ለቀናት ሊቆይ ይችላል አብዛኛውን ጊዜ የሚከሰተው አይን አካባቢ ያሉት ጡንቻዎች በሚደክሙበት ጊዜ ነው፡፡
🔵የአይን ቆብ መርገብገብ ምክንያቶች?
🔹 ጭንቀት
🔹 ድካም
🔹 የአይን ቆብ መዛል (ረጅም ሰአት ኮምፒዩተር ወይም ስልክ ላይ ማሳለፍ የአይን ቆብ እንዲዝል ያደርጋል)
🔹 የአይን መድረቅ
🔹 ጤናማ የአመጋገብ ስርአትን አለመከተል
🔹 ቡና እና ካፌንነት ያላቸውን መጠጦች እና ምግቦች አብዝቶ መጠቀም
🔹 አልኮል አብዝቶ መጠጣት
🔹 አለርጂ
🔹 የአይን ጡንቻዎች መዳከም
🔵የአይን ቆብ መርገብገብ እንዴት ማስቆም እችላለሁ?
🔹 ጭንቀት መቀነስ
🔹 እረፍት ማድረግ እና በቂ እንቅልፍ መተኛት
🔹 የአይን ቆብ መዛል ማስወገድ
🔹 ካፌንነት ያላቸውን ነገሮች መቀነስ
🔹 የአመጋገብ ስርአትን ማስተካከል
🔹 የአይን ድርቀትን መከላከል
🔹 አለርጂ ካለ እሱን ማከም
🔵ወደ ህክምና መሄድ ያለብኝ መቼ ነው?
🔹 የአይን ቆብ መርገብገብ ከሳምንት በላይ ከቆየ
🔹 በመርገብገቡ ምክንያት የአይናችን ቆብ ለመክፈት መቸገር ካለ
🔹 መርገብገቡ ከአይን አልፎ ወደ ፊት እና ሌሎች የሰውነት ክፍል ላይ ካለ
🔹 አብሮ የአይን መቅላት ወይም እብጠት/ፈሳሽ ካለ
🔹 የአይን ቆብ መዛል/በራሱ ሰአት መከደን ካለ
♦️ይህን እና ተያያዥ የሆኑ የአይን ጤና በተመለከተ የአይን ህክምና ክፍላችን በተሟላ የአይን ህክምና መሳሪያዎች በዶ/ር ቤዛዊት ታደገኝ የአይን ስፔሻሊስት ሀኪም እና የህፃናት አይን መንሸዋረር ህክምና ሰብስፔሻሊስት ሰኞ 8 ፡ 00፣እሮብ 8 ፡ 00 እና አርብ 9 ፡ 00 እናንተን ለማገልገል ዝግጁ ነው።
📍 Location: Girum hospital
አድራሻችን ከአዲስ ከተማ ክፍለከተማ ወደ ታይዋን ሰፈረ ሰላም መንገድ 100 ሜትር ዝቅ ብሎ
👉🏽 ለበለጠ መረጃ፡
☎️(011-2-757676/0913557076).
👉🏽ወይም በ 6️⃣7️⃣2️⃣2️⃣ ይደውሉልን::
⏰ Hours: As listed in the schedule (please note time slots).
👉🏽ለቀጠሮና ለበለጠ መረጃ፡
☎️(011-2-757676/0913557076).
👉🏽ወይም በ 6️⃣7️⃣2️⃣2️⃣ ይደውሉልን::
Thank you for trusting us with your healthcare needs! 💙