Abenet Medical Center

Abenet Medical Center 🏥 Abenet Internal Medicine 🏥

"One of the Best Private Healthcare Service Providers in Ethiopia"

05/01/2026
04/12/2025

ነርሲን ዲግሪ እንደሙያ (proffesional degree)አይደለም ብለዋል ፕሬዝዳንቱ ትራምፕ። ሙያ ካልሆነ ታድያ ምን ልንለው እንችላለን ?????
ማንም ሰው መማር ሳይኖርበት የነርስ ስራ ሊሰራ ይችላል ????
ምንም ሳይንስ ያላወቀ ምንም ትምህር የሌለው መድሀኒት ሊሰጠን ወይም መርፌ ሊወጋን ይችላል ማለት ነው? የነርስ ሙያ በመርፌ መስጠት ብቻም የተገደበ አይደለም እንደ ባህር የሰፋን ሙያ ለምን ግን???????????

02/12/2025

ለጤና ጥበቃችን እና ፐብሊክ health ኢንስቲትዩት በጋራ የሰራችሁን ስራ እጅግ በጣም አስገራሚ ነበረ።ኮርተንባችኋል እናመሰግናለን

  (Hemorrhagic Fever)  👇👇  (Hemorrhagic Fever) የሚባለው በሽታ በቫይረስ የሚመጣ ከባድ እና አንዳንዴም ለሞት ሊዳርግ የሚችል በሽታ ነው።እነዚህ በሽታዎች በሰውነት ...
16/11/2025

(Hemorrhagic Fever) 👇👇

(Hemorrhagic Fever) የሚባለው በሽታ በቫይረስ የሚመጣ ከባድ እና አንዳንዴም ለሞት ሊዳርግ የሚችል በሽታ ነው።

እነዚህ በሽታዎች በሰውነት ውስጥ የደም መርጋት ስርዓት ላይ ተፅዕኖ በማሳደር እና የደም ሥሮችን በመጉዳት ይታወቃሉ፤ በዚህም ምክንያት የውስጥ ደም መፍሰስ (hemorrhage) ያስከትላሉ።



በርካታ የተለያዩ የቫይረስ አይነቶች ሄሞራጂክ ፊቨር ሊያስከትሉ ይችላሉ። ከእነዚህም መካከል በዓለም ላይ በብዛት የሚታወቁት የሚከተሉትን ያካትታሉ፡-

☑️ ኤቦላ (Ebola)
☑️ ማርበርግ (Marburg)
☑️ ላሳ ፊቨር (Lassa Fever)
☑️ የክራይሚያ-ኮንጎ ሄሞራጂክ ፊቨር (Crimean-Congo Hemorrhagic Fever - CCHFV)
☑️ ዴንጊ ሄሞራጂክ ፊቨር (Dengue Hemorrhagic Fever)
☑️ ቢጫ ወባ (Yellow Fever)


=====

ምልክቶቹ በቫይረሱ አይነት ይለያያሉ፣ ግን በአጠቃላይ የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ፡-

👉ድንገተኛ ትኩሳት (Severe Fever)
👉ከፍተኛ የሰውነት እና የጡንቻ ህመም (Body Aches and Muscle Pain)
👉ድካም (Fatigue)
👉ራስ ምታት (Headache)
👉ማስታወክ እና ተቅማጥ (Vomiting and Diarrhea)
👉የሆድ ህመም (Abdominal Pain)
ከባድ በሆኑ ሁኔታዎች ደግሞ
👉የውስጥ_ደም_መፍሰስ: ከአፍንጫ፣ ከድድ፣ ከዓይን፣ ከቆዳ ስር የሚወጣ ደም፣ ወይም በሽንት/ሰገራ ውስጥ ደም መታየት።

?
=======
በሽታው የሚተላለፍበት መንገድ በቫይረሱ አይነት ይወሰናል፡-

1· ከተያዙ እንስሳት ጋር በመነካካት፡ በእንስሳት (ለምሳሌ አይጥ) ፣ ሽንት፣ ምራቅ ፣ ወይም ሌሎች ከሰውነት የሚለቀቁ ፈሳሾች በሚነካኩበት ጊዜ።
2· በነፍሳት ንክሻ፡
3· ከሰው ወደ ሰው፡
ከተያዘ ሰው የሚገኘው ደም፣ ምራቅ፣ የሰውነት ፈሳሾች ወይም ሌሎች ክምችቶች በቀጥታ በሚነካኩበት ጊዜ። ይህ ለበሽታው ከባዱ እና ዋነኛው ዓይነት የመተላለፊያ መንገድ ነው።

#ህክምናው
====
ለአብዛኛዎቹ የሄሞራጂክ ፊቨር በሽታዎች የተለየ እና ፈዋሽ የሆነ መድኃኒት የለም።

ህክምናው ብዙውን ጊዜ ደጋፊ እንክብካቤ (Supportive Care) መስጠት ላይ ያተኩራል፡-

1. የሰውነት ፈሳሾችን ማካካስ (Rehydration)
2. የኤሌክትሮላይት ሚዛን መዛባት ማስተካከል
3. የደም ግፊትን ማረጋጋት
4. የደም መርጋት ወይም ደም መፍሰስን መቆጣጠር
5. ለአንዳንድ ቫይረሶች (እንደ ኤቦላ እና ላሳ) ፀረ-ቫይረስ መድኃኒቶች አሉ።

‼️
====
አፋጣኝ አስፈላጊ የህክምና እርዳታ ማግኘት አስፈላጉ ቢሆንም፣በሺታውን ሙሉበሙሉ ማዳን የሚችል ህክምና የለም ‼️
መከላከል ብቸኛው ቁልፍ መንገድ ነው !

የሚከተሉትን ማድረግ ያስፈልግዎታል!!

👉 እጆችዎን በንፅህና ይታጠቡ፡ በሳሙና እና በንጹህ ውሃ ዘወትር ማጠብ አስፈላጊ ነው።
👉ከሌሎች ሰዎች (ክምችቶች) ራስዎን ይጠብቁ፡ ከሰዎች ደም፣ ምራቅ ወይም ሌሎች ከሰውነት የሚለቀቁ ፈሳሾች ንክኪዎች ራስዎን ይጠብቁ። ይህ ለቤተሰብ አባላት እና በተለይም ለህክምና ባለሙያዎች እጂግ አስፈላጊ ነው።
ብዙ የህክምና/ጤ ና ባለሙያዎች ህይወታቸውን የሚያጡበት ወረርሺኝ ነው።
👉 ከእንስሳት ይራቁ፣ አይጦችን እና ሌሎች እንስሳት ከቤትዎ አርቀው ያቆዩ። የሚታወቁ የእንስሳት ክምችቶች ባሉበት ስፍራ ጥንቃቄ አይለይዎት
👉ከነፍሳት ይጠበቁ ፣ አጎበር መጠቀም፡ ነፍሳት እና ወረርሽኙ ወደተከሰተበት ቦታ ፈጽሞ አይሂዱ ፣ አደገኛ ነው ፣ የመተላለፍ እድሉ አደገኛ ነው። ለህክምና ባለሙያዎች መከላከያ ይጠቀሙ እና ሙሉ አካላትዎን የሚደብቁ ልብሶች ይልበሱ። Mosquito net ይጠቀሙ።
👉ህክምና ሰራተኞች፡ ህክምና ሰራተኞች gloves ፣ mask እና ሌሎች የግል ጥበቃ መሳሪያዎችን (PPE) መጠቀም አለባቸው።

#በቅንነት #ሸር #አድርገው #ለሌሎችም #ያድርሱ፡፡

09/11/2025

የተፈጥሮ ፓርኮች ለጤናችን የሚሰጡን ጥቅሞች

31/10/2025

በቤታችን ከሚገኙ ኮስሞቲክሶች ውስጥ አደገኛ ኬሚካል እንዳለ ያውቃሉ?

Address

Lideta Condominiums, Near Tesfakokeb School
Addis Ababa

Telephone

+251922147942

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Abenet Medical Center posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Abenet Medical Center:

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram