St. Urael Internal Medicine Specialty Clinic ቅዱስ ዑራኤል የውስጥ ደዌ ልዩ ክሊኒክ

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • St. Urael Internal Medicine Specialty Clinic ቅዱስ ዑራኤል የውስጥ ደዌ ልዩ ክሊኒክ

St. Urael Internal Medicine Specialty Clinic ቅዱስ ዑራኤል የውስጥ ደዌ ልዩ ክሊኒክ Our team of skilled specialists is committed to providing exceptional healthcare services, ensuring patients receive the best possible medical attention.

St.Ureal Internal Medicine specialty clinic is a leading medical facility situated adjacent to the Rwanda Embassy, with a focus on offering unparalleled care in the fields of Internal Medicine and Diabetology. With years of experience and expertise in the medical field, we offer a wide range of services that cater to the needs of our patients. At St.Ureal Internal Medicine specialty clinic, we pri

oritize the health and wellbeing of our clients, making us the go-to clinic for all your internal medicine and diabetology needs.

ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ቶሎ ቶሎ ሽንት መሽናት፣ በሚሸኑበት ወቅት ህመም መኖር ወይም የማቃጠል ስሜት፣ ሽንት ለማምለጥ መሞከር፣ ማታ ማታ ከወትሮው በተለየ ለሽንት መነሳት፣የሽንት መልክ መቀየ...
27/03/2025

ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ቶሎ ቶሎ ሽንት መሽናት፣
በሚሸኑበት ወቅት ህመም መኖር ወይም የማቃጠል ስሜት፣ ሽንት ለማምለጥ መሞከር፣ ማታ ማታ ከወትሮው በተለየ ለሽንት መነሳት፣የሽንት መልክ መቀየር፣ የታችኛው ሆድ ላይ ህመም መኖር፣ ትኩሳት፣ ብርድ ብርድ ማለትና የመሳሰሉት የህመም ምልክቶች አለዎ? መሰል ስሜት ካለዎ የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ምልክት ስለሆነ የህክምና ባለሙያዎን ያማክሩ።

አድራሻችን፦ ቦሌ ሩዋንዳ ከሩዋንዳ ኤምባሲ ጎን ሲሆን በተጨማሪም እኛን ለማግኘት ከፈለጉ የሚከተሉትን ይጠቀሙ
❤️https://t.me/sturaelclinic
❤️https://www.instagram.com/sturaelclinic
❤️https://www.sainturaelclinic.com
❤️9424
❤️+251-940464646 /0940565656 /0913349301 +251-116662556
/0116663741
❤️Rwanda St Just Beside Rwanda Embassy Addis Ababa Ethiopia.
❤️sturaelclinic@gmail.coml" rel="ugc" target="_blank">https://sturaelclinic@gmail.coml

የድካም ስሜት፣ የሰዉነት ክብደት  መጨመር፣ ብርድ መቻል መቸገር/ከሰዎች በተለየ መብረድ፣ የጡንቻና የመገጣጠሚያ ላይ ህመም፣ የቆዳ ድርቀትና መጥቆር፣የፀጉር መቅጠን፣ መዉለድ መቸገር  አሊያም...
06/03/2025

የድካም ስሜት፣ የሰዉነት ክብደት መጨመር፣ ብርድ መቻል መቸገር/ከሰዎች በተለየ መብረድ፣ የጡንቻና የመገጣጠሚያ ላይ ህመም፣ የቆዳ ድርቀትና መጥቆር፣የፀጉር መቅጠን፣ መዉለድ መቸገር አሊያም ሴቶች ላይ የወር አበባ ዑደት መዛባት መከሰት ችግሮች መኖር ፣ የልብ ምት መቀነስ፣ መደበትና የመሳሰሉት የህመም ምልክቶች አለዎ? እንግያዉስ መሰል የህመም ምልክቶች የታይሮይድ ሆርሞን ማነስ የህመም ምልክት ሊሆን ስለሚችል የህክምና ባለሙያዎን ያማክሩ፡፡

አድራሻችን፦ ቦሌ ሩዋንዳ ከሩዋንዳ ኤምባሲ ጎን ሲሆን በተጨማሪም እኛን ለማግኘት ከፈለጉ የሚከተሉትን ይጠቀሙ
❤️https://t.me/sturaelclinic
❤️https://www.instagram.com/sturaelclinic
❤️https://www.sainturaelclinic.com
❤️9424
❤️+251-940464646 /0940565656 /0913349301 +251-116662556
/0116663741
❤️Rwanda St Just Beside Rwanda Embassy Addis Ababa Ethiopia.
❤️sturaelclinic@gmail.com" rel="ugc" target="_blank">https://sturaelclinic@gmail.com

❄️የሰዉነት የፈሳሽ መጠንበሰዉነታችን ዉስጥ ያለዉ የፈሳሽ መጠን ከ50 እስከ 75 በመቶ የሚደርስ ሲሆን ይህም በእድሜ፣ ፆታና የሰዉነት ስሪት ላይ ተመርኩዞ ሊለያይ ይችላል። በሰዉነታችን ዉስ...
06/03/2025

❄️የሰዉነት የፈሳሽ መጠን
በሰዉነታችን ዉስጥ ያለዉ የፈሳሽ መጠን ከ50 እስከ 75 በመቶ የሚደርስ ሲሆን ይህም በእድሜ፣ ፆታና የሰዉነት ስሪት ላይ ተመርኩዞ ሊለያይ ይችላል። በሰዉነታችን ዉስጥ ያለዉ ፈሳሽ መጠን በተለያዩ ምክንያቶች ቢለያይም አንድ በአማካይ 70 ኪግ የሚመዝን አዋቂ ሰዉ ሰዉነት ዉስጥ ያለዉ የፈሳሽ መጠን 60% ወይም 42 ሊትር ነዉ።

በሰዉነታችን ዉስጥ ያለዉን የሰዉነት ፈሳሽ ምጣኔ የሚወስኑት
1. እድሜ፦ ጨቅላ ህፃናት ያላቸዉ የሰዉነት ፈሳሽ መጠን እስከ 75 በመቶ የሚደርስ ሲሆን አዋቂዎች ደግም 50 በመቶ ይደርሳል።
2. ፆታ፦ ሴቶች ከወንዶች ይልቅ በሰዉነታቸዉ የበዛ ስብ ስላላቸዉ ከወንዶች አንፃር በሰዉነታቸዉ አነስተና የዉሃ ወይም ፈሳሽ ምጣኔ አላቸዉ።
3. የሰዉነት ስሪት፡- በስብ የተሞላ ህብረ ህዋስ በስጋ ከተሞላዉ ህብረህዋስ ያነሰ ዉሃ ይይዛል።
4. የሰዉነት ዉፍረት፦ በዕድሜ የገፉና ወፍራም ሰዎች አነስተኛ ፐርሰንቴጅ የሰዉነት ዉሃ መጠን አላቸዉ።
የሰዉነታችን 2/3ኛዉ ዉሃ በሴሎች ዉስጥ የሚገኝ ሲሆን ቀሪዉ ከሴሎች ዉጪ ይገኛል ( ይህም ኢንተርስቲሺያልና ኢንትራቫስኩላር በመባል ይከፈላል)። ከሰዉነታችን አካላት ውስጥ አንጎልና ኩላሊት ከፍተኛ ፐርሰንቴጅ ዉሃ ሲኖራቸዉ አጥንትና ጥርስ ደግሞ ዝቅተኛዉን ዉሃ ይይዛሉ።

ጤናማ የሰዉነት የፈስሽ ምጣኔ ለመጠበቅ አንድ ጤናማ የሆነ አዋቂ ሰዉ በቀን ቢያንስ 2 ሊትር ፈሳሽ መጠጣት አለበት።
የሰዉነት የፈሳሽ ምጣኔ እንዲጠበቅ የሚያደርገዉ የሰዉነታችን አካል ኩላሊታችን ናት። ኩላሊት ደምን በማጣራት ወደሰዉነታችን ተመልሶ የሚመጠጠዉን የዉሃ መጠን የምትቆጣጠር አካል ናት። በዚህም የተነሳ ፈሳሽ ሰዉነታችን ዉስጥ ሲበዛ በሽንት መልክ ከሰዉነታችንም እንዲወገድ በማድረግ የሰዉነት የፈሳሽ ምጣኔ እንዲጠበቅ ታደርጋለች።
መልሱን በፍጥነትና በተብራራ መልክ የመለሱት
1. ለገሰ ክብረት
2. ቼሪስ
3. ናቲ ናቸዉ።

አድራሻችን፦ ቦሌ ሩዋንዳ ከሩዋንዳ ኤምባሲ ጎን ሲሆን በተጨማሪም እኛን ለማግኘት ከፈለጉ የሚከተሉትን ይጠቀሙ
❤️https://t.me/sturaelclinic
❤️https://www.instagram.com/sturaelclinic
❤️https://www.sainturaelclinic.com
❤️9424
❤️+251-940464646 /0940565656 /0913349301 +251-116662556
/0116663741
❤️Rwanda St Just Beside Rwanda Embassy Addis Ababa Ethiopia.
❤️sturaelclinic@gmail.com" rel="ugc" target="_blank">https://sturaelclinic@gmail.com

❄️ምግብ ከበሉ በኃላ ገላን መታጠብ የጤና ችግር ያመጣል?🔑 እንደ አጠቃላይ ምክር ምግብ ከተመገቡ በኃላ ( በተለይ ብዙ ተመግበዉ) ቢያንስ ከ 30 ደቂቃ እስከ አንድ ሰዓት ድረስ ገላን ሳይታ...
14/02/2025

❄️ምግብ ከበሉ በኃላ ገላን መታጠብ የጤና ችግር ያመጣል?

🔑 እንደ አጠቃላይ ምክር ምግብ ከተመገቡ በኃላ ( በተለይ ብዙ ተመግበዉ) ቢያንስ ከ 30 ደቂቃ እስከ አንድ ሰዓት ድረስ ገላን ሳይታጠቡ መቆየት ይመከራል። ምግብ እንደተመገቡ ሻወር መዉሰድ የሆድ ቁርጠት፣ ምቾት ማጣት፣ የምግብ አልፈጭ ማለትና የሆድ መነፋት ስሜት ሞኖር እንዲኖር ያድረጋል።

🛀ለምን ሳይታጠቡ መቆየት ያስፈልጋል?

✔️ ጨጓራ ምግብ እንዲፈጭ ሰዉነት የደም ዝዉዉር ወደ ጨጓራ መላክ አለበት።
✔️ ምግብ ከበላን በኃላ ወዲያዉኑ ሻወር መዉሰድ የሰዉነት ሙቀትን ለማስተካከል ሲል ሰዉነታቸን የደም ዝዉዉርን ከጨጓራ ወደ ሌሎች የሰዉነት አካላት እንዲዛወር ያደርጋል።
ይህም የምግብ መፈጨት ሂደትን ያዉካል።
✔️ ሳይታጠቡ መቆየት ግን የምግብ የመፈጨት ሂደት ለማስጀመር ጊዜ/ ሰዓት ለመግዛት ያግዛል/ እንዲጀመር ያደርጋል።
✔️የምግብ መፈጨት ምቾት ማጣትን ለማስወገድ ምግብ ከተመገቡ በኃላ ቢያንስ ከ30 ደቂቃ እስከ አንድ ሰዓት መዘግየት ያስፈልጋል።
✔️ምግብ ከመመገብዎ አስቀድሞ ሻወር መዉሰድ ደግሞ የምግብ መፈጨትንንና የተፈጨዉ ምግብ ከአንጀት ወደስወነታችን መመጠጥን ያግዛል።

አድራሻችን፦ ቦሌ ሩዋንዳ ከሩዋንዳ ኤምባሲ ጎን ሲሆን በተጨማሪም እኛን ለማግኘት ከፈለጉ የሚከተሉትን ይጠቀሙ
❤️https://t.me/sturaelclinic
❤️https://www.instagram.com/sturaelclinic
❤️https://www.sainturaelclinic.com
❤️9424
❤️+251-940464646 /0940565656 /0913349301 +251-116662556
/0116663741
❤️Rwanda St Just Beside Rwanda Embassy Addis Ababa Ethiopia.
❤️sturaelclinic@gmail.com" rel="ugc" target="_blank">https://sturaelclinic@gmail.com

❄️የቫይታሚን ሲ የጤና ጥቅሞችቫይታሚን ሲ ለሰዉነት ማደግና መጎልበት አስፈላጊ የሆነ ቫይታሚን ሲሆን  ዉሃ ዉስጥ ከሚሟሙ ቫይታሚኖች ዉስጥ አንዱ ነዉ። ቫይታሚን ሲ ለሰዉነታችን ከሚሰጣቸዉ የ...
09/02/2025

❄️የቫይታሚን ሲ የጤና ጥቅሞች

ቫይታሚን ሲ ለሰዉነት ማደግና መጎልበት አስፈላጊ የሆነ ቫይታሚን ሲሆን ዉሃ ዉስጥ ከሚሟሙ ቫይታሚኖች ዉስጥ አንዱ ነዉ። ቫይታሚን ሲ ለሰዉነታችን ከሚሰጣቸዉ የጤና ጥቅሞች ዉስጥ
1. በሰዉነታችን ዉስጥ ለህብረ ህዋስ ማደግና መጠገን አስፈላጊ ነዉ
2. ለሰዉናትችን አስፈላጊ የሆነዉን ኮላጂን የሚባለዉን ፕሮቲን እንዲመረት ያደርጋል። ይህም ለቆዳ፣ ጅማት፣ ሊጋመንትና የደም ቧንቧዎችን ለመስራት ያገለግላል
3. ቁስል እንዲድን ያደርጋል
4. አጥንት፣ ጥርስና ካርቲሌጅን ለመጠገንና ለመጠበቅ ይረዳል።
5. የብረት ማዕድን ከአንጀታችን እንዲመጠጥ( ከአንጀት ወደ ደም ስር እንዲገባ) ያግዛል።
6. አንቲኦክሲዳንት ባህሪ አለዉ። አንቲኦክሲዳንት ምግብ ሲፈጭ( ሲሰባበር) የሚፈጠሩ ጎጂ ራዲካሎችን ለማስወገድ የሚረዱ ኒዩትረንቶች ናቸዉ።
ሰዉነታችን በራሱ ቫይታሚን ሲ በሰዉነታችን ዉስጥ ማምረት አይችልም። እንዲሁም ሰዉነታችን ቫይታሚን ሲን ማጠራቀም አይችልም። ሰዉነታችን ቫይታሚን ሲን የሚያገኘዉ ከምንመገበዉ ምግብ ነዉ።ስለህነም በቂ ቫይታሚን ሲ ያላቸዉ ምግቦችን መመገብ አስፈላጊ ነዉ።

አድራሻችን፦ ቦሌ ሩዋንዳ ከሩዋንዳ ኤምባሲ ጎን ሲሆን በተጨማሪም እኛን ለማግኘት ከፈለጉ የሚከተሉትን ይጠቀሙ
❤️https://t.me/sturaelclinic
❤️https://www.instagram.com/sturaelclinic
❤️https://www.sainturaelclinic.com
❤️9424
❤️+251-940464646 /0940565656 /0913349301 +251-116662556
/0116663741
❤️Rwanda St Just Beside Rwanda Embassy Addis Ababa Ethiopia.
❤️sturaelclinic@gmail.com" rel="ugc" target="_blank">https://sturaelclinic@gmail.com

በሰዉነታችን ዉስጥ ምን ያህል ሊትር ፈሳሽ አለ? የሰዉነታችንን የፈሳሽ መጠን የሚቆጣጠረዉ የሰዉነታችን አካልስ ማነዉ?አድራሻችን፦ ቦሌ ሩዋንዳ ከሩዋንዳ ኤምባሲ ጎን ሲሆን በተጨማሪም እኛን ለ...
03/02/2025

በሰዉነታችን ዉስጥ ምን ያህል ሊትር ፈሳሽ አለ?
የሰዉነታችንን የፈሳሽ መጠን የሚቆጣጠረዉ የሰዉነታችን አካልስ ማነዉ?

አድራሻችን፦ ቦሌ ሩዋንዳ ከሩዋንዳ ኤምባሲ ጎን ሲሆን በተጨማሪም እኛን ለማግኘት ከፈለጉ የሚከተሉትን ይጠቀሙ
❤️https://t.me/sturaelclinic
❤️https://www.instagram.com/sturaelclinic
❤️https://www.sainturaelclinic.com
❤️9424
❤️+251-940464646 /0940565656 /0913349301 +251-116662556
/0116663741
❤️Rwanda St Just Beside Rwanda Embassy Addis Ababa Ethiopia.
❤️sturaelclinic@gmail.com" rel="ugc" target="_blank">https://sturaelclinic@gmail.com

እንኳን ለብርሀነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሰዎት።በዓሉ የደስታ የሰላም እና የጤና እንዲሆንልዎ እንመኛለን።መልካም የጥምቀት በዓል።ቅዱስ ዑራኤል የውስጥ ደዌ ልዪ ክሊኒክለጤናዎ እንተጋለን።አድራሻች...
18/01/2025

እንኳን ለብርሀነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሰዎት።
በዓሉ የደስታ የሰላም እና የጤና እንዲሆንልዎ እንመኛለን።
መልካም የጥምቀት በዓል።
ቅዱስ ዑራኤል የውስጥ ደዌ ልዪ ክሊኒክ
ለጤናዎ እንተጋለን።

አድራሻችን፦ ቦሌ ሩዋንዳ ከሩዋንዳ ኤምባሲ ጎን ሲሆን በተጨማሪም እኛን ለማግኘት ከፈለጉ የሚከተሉትን ይጠቀሙ
❤️https://t.me/sturaelclinic
❤️https://www.instagram.com/sturaelclinic
❤️https://www.sainturaelclinic.com
❤️9424
❤️+251-940464646 /0940565656 /0913349301 +251-116662556
/0116663741
❤️Rwanda St Just Beside Rwanda Embassy Addis Ababa Ethiopia.
sturaelclinic@gmail.com" rel="ugc" target="_blank">https://sturaelclinic@gmail.com

❄️ከመጠን ያለፈ ላብ ( Hyperhidrosis)⭐ክፍል አንድከመጠን ያለፈ ላቦት አለ የሚባለዉ ሰዉነትዎ የሰዉነት ሙቀትን ለመቆጣጠር ከሚፈልገዉ በላይ ሲያልብዎ ነዉ። በእረፍት ላይ እያሉ፣ በ...
14/01/2025

❄️ከመጠን ያለፈ ላብ ( Hyperhidrosis)

⭐ክፍል አንድ

ከመጠን ያለፈ ላቦት አለ የሚባለዉ ሰዉነትዎ የሰዉነት ሙቀትን ለመቆጣጠር ከሚፈልገዉ በላይ ሲያልብዎ ነዉ። በእረፍት ላይ እያሉ፣ በቀዝቃዛ አየር ወቅት አልያም ያልበናል ብለዉ ባገመቱት ሰዓት ሊያልብዎ ይችላል።
ላብ ሽታ የሌለዉ ከላብ ዕጢ የሚመነጭ ፈሳሽ ነዉ። ላብ የሰዉነት ሙቀትን ለሚቆጣጠርና ከመጠን ያለፈ ሙቀትን ለመከላከል ይረዳል።

👇ከመጠን ያለፈ ለብ ምክልክቶች
❤️ የቆዳ እርጥብት
❤️ የልብስ መራስ
❤️ ከሰዉነትዎ አካል የላብ መንጠፍጠፍ
❤️ ማሳከክ፦ላብ ሰዉነትዎ እንዲቆጣ ካደረግዎ
❤️ የሰዉነት ጠረን መቀየር፦ በሰዉነትዎ ልይ ያሉ ባክቴሪያዎች ከላብ ጋር ሲደብለቁና ባክቴሪያዉ ላብ ላይ ሲያድግ
❤️ የእግር መዳፍ ቆዳ መሰነጣጠቅና መላላጥና የመሳሰሉት ናቸዉ።

👇ከመጠን ያለፈ ላብ ምልክቶች የሚታዩባቸዉ ቦታዎች
❤️ ብብት
❤️ የእግር ሶል
❤️ የእጅ መዳፍ
❤️ ጉንጭና ግንባር
❤️ ብልት አካባቢ
❤️ የታችናዉ ጀርባ አካባቢ ናቸዉ

አድራሻችን፦ ቦሌ ሩዋንዳ ከሩዋንዳ ኤምባሲ ጎን ሲሆን በተጨማሪም እኛን ለማግኘት ከፈለጉ የሚከተሉትን ይጠቀሙ
❤️https://t.me/sturaelclinic
❤️https://www.instagram.com/sturaelclinic
❤️https://www.sainturaelclinic.com
❤️9424
❤️+251-940464646 /0940565656 /0913349301 +251-116662556
/0116663741
❤️Rwanda St Just Beside Rwanda Embassy Addis Ababa Ethiopia.
❤️sturaelclinic@gmail.com" rel="ugc" target="_blank">https://sturaelclinic@gmail.com

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉእንኳን ለጌታችን ለመድሃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ ። በዓሉ የሰላምና የጤና እንዲሆንላችሁ ቅዱስ ዑራኤል የዉ...
06/01/2025

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ
እንኳን ለጌታችን ለመድሃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ ። በዓሉ የሰላምና የጤና እንዲሆንላችሁ ቅዱስ ዑራኤል የዉስጥ ደዌ ልዩ ክሊኒክ ከልብ ይመኛል።

ወቅታዊና ተከታታይ የጤና መረጃ ለማግኘት ገፃችንን ላይክ ያድርጉ።
አድራሻችን፦ ቦሌ ሩዋንዳ ከሩዋንዳ ኤምባሲ ጎን ሲሆን በተጨማሪም እኛን ለማግኘት ከፈለጉ የሚከተሉትን ይጠቀሙ
https://t.me/sturaelclinic
https://www.instagram.com/sturaelclinic
https://www.sturaelclinic.com/
https://www.facebook.com/sturaelclinic/
❤9424
❤+251-940464646 /0940565656 /0913349301 +251-116662556
/0116663741
❤Rwanda St Just Beside Rwanda Embassy Addis Ababa Ethiopia.
sturaelclinic@gmail.com" rel="ugc" target="_blank">https://sturaelclinic@gmail.com See less

❄️ የአፍዎን ጤንነት እንዴት መጠበቅ ይችላሉ?የአፍዎ ጤንነት ሁኔታ ስለ አጠቃላይ የሰዉነትዎ ጤና ሁኔታ ፍንጭ ሊሰጥ እንደሚችል ያዉቃሉ? አፍዎ ዉስጥ የተከሰተ የጤና ችግር ሌላዉን የሰዉነት ...
04/01/2025

❄️ የአፍዎን ጤንነት እንዴት መጠበቅ ይችላሉ?

የአፍዎ ጤንነት ሁኔታ ስለ አጠቃላይ የሰዉነትዎ ጤና ሁኔታ ፍንጭ ሊሰጥ እንደሚችል ያዉቃሉ? አፍዎ ዉስጥ የተከሰተ የጤና ችግር ሌላዉን የሰዉነት ክፍል ሊጎዳ እንደሚችል ያዉቃሉ?
የአፍዎን ጤንነት በየቀኑ መጠበቅ ያስፈልጋል።
ስለሆነም
⭐ ጥርስዎን በቀን ሁለቴ መቦረሽ ያስፈልጋል፦ሲቦርሹ ፍሎራይድ የጥርስ ሳሙና ይጠቀሙ
⭐ ጤናማ አመጋገብ ይከተሉ፤ እንዲሁም ስኳርነት ያላቸዉን ምግቦች ይቀንሱ።
⭐ የጥርስ ቡርሽዎን በየሶስት ወሩ ይቀያይሩ። ብሩሹ ከተበላሸ ወይም ከላሸቀ ቀደም ብለዉም ቢሆን ይቀይሩ።
⭐ ሲጋራ ከማጨስ ይቆጠቡ
⭐ የጥርስ ሀኪም ጋ በመሄድ ቢያን በአመት አንዴ ክትትል ያድርጉ። ድድዎትንም መታየት ሊያስፈልግ ይችላል።
⭐ ምግብ ከተመገቡ በኃላ በጥርስዎ መካከል የሚቀርን የምግብ ትራፊዎች ያፅዱ።

አድራሻችን፦ ቦሌ ሩዋንዳ ከሩዋንዳ ኤምባሲ ጎን ሲሆን በተጨማሪም እኛን ለማግኘት ከፈለጉ የሚከተሉትን ይጠቀሙ
❤️https://t.me/sturaelclinic
❤️https://www.instagram.com/sturaelclinic
❤️https://www.sainturaelclinic.com
❤️9424
❤️+251-940464646 /0940565656 /0913349301 +251-116662556
/0116663741
❤️Rwanda St Just Beside Rwanda Embassy Addis Ababa Ethiopia.
❤️sturaelclinic@gmail.com" rel="ugc" target="_blank">https://sturaelclinic@gmail.com

💥ላለፈው ሳምንት ጥያቄ መልስየጉበት መቆጣት (ሄፓታይቲስ )ሄፓታይቲስ ለጉበት መቆጣት የሚሰጥ ጠቅለል ያለ ስያሜ ሲሆን በጉበት ቫይረሶች፣ኬሚካሎች፣ መድሃኒቶች፣አልኮሆል መጠጦችና የሰዉነታችን ...
31/12/2024

💥ላለፈው ሳምንት ጥያቄ መልስ

የጉበት መቆጣት (ሄፓታይቲስ )
ሄፓታይቲስ ለጉበት መቆጣት የሚሰጥ ጠቅለል ያለ ስያሜ ሲሆን በጉበት ቫይረሶች፣ኬሚካሎች፣ መድሃኒቶች፣አልኮሆል መጠጦችና የሰዉነታችን በሽታ መከላከል አቅም ከመጠን በላይ ወይም ያልተገባ ምላሽ ሲሰጥ የሚከሰት የጤና ችግር ነዉ።
የጉበት ኢንፌክሽን አንዲከሰት የሚያደርጉ ዋነኞቹ የጉበት ቫይረሶች ሄፓታይቲስ ኤ፣ ሄፓታይቲስ ቢ፣ ሄፓታይቲስ ሲ፣ ሄፓታይቲስ ዲና ሄፓታይቲስ ኢ የሚባሉት ናቸዉ። ከነዚህም ዉስጥ ሄፓታይቲስ ቢና ሄፓታይቲስ ሲ ስር የሰደደ የጉበት ችግር እኒከሰት ያደርጋሉ።
የጉበት ቫይረስ ኢንፌክሽኖችን መከላከል ይቻላል። ይህም
1. ስለታማ ነገሮችን በጋራ ባለመጠቀም
2. ደምን ጨምሮ ማንኛዉንም የሰዉነት ፈሳሽንና የተበከሉ እቃዎችን ከነኩ በኃላ እጅን በዉና ሳሙና መታጠብ
3. ጥንቃቄ የጎደለዉ የግብራስጋ ግንኙነት ከማድራግ መቆጠብ
4. መርፌ በጋራ አለመጠቀም
5. ክትባት መዉሰድ፦ በተለይ የጉበት ቫይረስ ኤና ቢ ክትባት ስላላቸዉ ክትባቱን መዉሰድ ያስፈልጋል።
6. የምግብና ዉሃ ንፅህናን መጠበቅ

መልሱን በትክክልና በተሟላ መልኩ ያብራራዉና የመለሰዉ ለገሰ ክብረት ሲሆን ከተወሰኑ ግድለቶች ዉጪ ናቲም መልሶታል። ስለተሳትፎያችሁ እናመሰግናለን።

አድራሻችን፦ ቦሌ ሩዋንዳ ከሩዋንዳ ኤምባሲ ጎን ሲሆን በተጨማሪም እኛን ለማግኘት ከፈለጉ የሚከተሉትን ይጠቀሙ
❤️https://t.me/sturaelclinic
❤️https://www.instagram.com/sturaelclinic
❤️https://www.sainturaelclinic.com
❤️9424
❤️+251-940464646 /0940565656 /0913349301 +251-116662556
/0116663741
❤️Rwanda St Just Beside Rwanda Embassy Addis Ababa Ethiopia.
❤️sturaelclinic@gmail.com" rel="ugc" target="_blank">https://sturaelclinic@gmail.com

❄️የታይሮይድ ሆርሞን ከመጠን በላይ መጨመርየልብ ምት መፍጠን፣ ለመቀነስ ሳያስቡ የሰዉነት የክብደት መቀነስ ( የሰዉነት መክሳት)፣ መነጫነጭ፣ የሙድ መቀያየር፣ የእንቅልፍ ችግር ( እንቅልፍ ...
25/12/2024

❄️የታይሮይድ ሆርሞን ከመጠን በላይ መጨመር

የልብ ምት መፍጠን፣ ለመቀነስ ሳያስቡ የሰዉነት የክብደት መቀነስ ( የሰዉነት መክሳት)፣ መነጫነጭ፣ የሙድ መቀያየር፣ የእንቅልፍ ችግር ( እንቅልፍ መተኛት መቸገር)፣ ሴቶች ላይ የወር አበባ ዑደት መዛባት ችግር ( የፍሰት መጠን መቀነስ አሊያም ለወራት እየጠፋ ምመጣት)፣ የእጅ መንቀጥቀጥ፣ የጡንቻ መስነፍ፣ የሰዉነት ማላብ፣ ከሰዎች በተለየ ሙቀት ያለመቻል፣ የምግብ ፍላጎት መጨመር፣ ሰገራ ቶሎ ቶሎ መምጣት፣ የፀጉር መርገፍ፣ የጥፍር መቀየር፣ ነገሮች ላይ ትኩረት ማድረግ መቸገር፣ በፊትለፊት በኩል አንጋትዎ ላይ እብጠት ማየትና የመሳሰሉት የህመም ምልክቶች አለዎ?
እንግዲያዉስ መሰል ምልክቶች ከታየብዎ የታይሮይድ ሆርሞን ከመጠን በላይ መጨመር ( ታይሮቶክሲኮሲስ) የህመም ምልክት ሊሆን ስለሚችል የህክምና ባለሙያዎ ጋ በመሄድ ምርመራ ያድርጉ።

አድራሻችን፦ ቦሌ ሩዋንዳ ከሩዋንዳ ኤምባሲ ጎን ሲሆን በተጨማሪም እኛን ለማግኘት ከፈለጉ የሚከተሉትን ይጠቀሙ
❤️https://t.me/sturaelclinic
❤️https://www.instagram.com/sturaelclinic
❤️https://www.sainturaelclinic.com
❤️9424
❤️+251-940464646 /0940565656 /0913349301 +251-116662556
/0116663741
❤️Rwanda St Just Beside Rwanda Embassy Addis Ababa Ethiopia.
❤️sturaelclinic@gmail.com" rel="ugc" target="_blank">https://sturaelclinic@gmail.com

Address

On The Road To Bole Michael , Just Beside Rwanda Embassy (ወደ ቦሌ ሚካኤል በሚወሰደው መንገድ ሩዋንዳ ኢምባሲ አጠገብ)
Addis Ababa
RWANDASTREET

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when St. Urael Internal Medicine Specialty Clinic ቅዱስ ዑራኤል የውስጥ ደዌ ልዩ ክሊኒክ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to St. Urael Internal Medicine Specialty Clinic ቅዱስ ዑራኤል የውስጥ ደዌ ልዩ ክሊኒክ:

Share

Category

ቅዱስ ዑራኤል የዉስጥ ደዌ ልዩ ክሊኒክ

12 Years ago St. Urael Medical Service plc Opened its door in the heart of Addis Ababa - Urael srea on St. Urael Building with the aim of providing quality service to the public. Currently, St. Urael Medical Service plc is owned by three doctors who have vast experience in the field of medicine and public health management.

🎯Mission

🏹 To provide efficient and effective medical service by working together with and utilizing qualified, honest and motivated staff and state-of-art technology.

🏹 To work towards a sustainable and continued positive relationship with government health authorities that allows the formation of private-public partnership.