Ethiopian Pharmaceuticals Supply Service - EPSS

Ethiopian Pharmaceuticals Supply Service - EPSS Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ethiopian Pharmaceuticals Supply Service - EPSS, Addis Ababa.

Ethiopian Pharmaceutical Supply service , EPSS
, procure ,manage and distribute RDF & Heath Programme Products for governmental health facilities to supply quality assured essential pharmaceutical with affordable prices & a sustainable manner in Eth

"የሀዘን መግለጫ" ⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳የቅርንጫፋችን የስራ ባልደረባ የነበሩት ወ/ሮ የኔነሽ አያሌው ከየካቲት 20 ቀን 2005 ዓ.ም  እስከ ህይወታቸው ህልፈት ድረስ በመድኃኒት...
29/07/2025

"የሀዘን መግለጫ"
⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳

የቅርንጫፋችን የስራ ባልደረባ የነበሩት ወ/ሮ የኔነሽ አያሌው ከየካቲት 20 ቀን 2005 ዓ.ም እስከ ህይወታቸው ህልፈት ድረስ በመድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት አዳማ ቅርንጫፍ የፋይናንስ ባለሙያ በመሆን ሲያገለግሉ ቆይተዋል።

ወ/ሮ የኔነሽ አያሌው ባለትዳር እና የሁለት ሴትና የአንድ ወንድ ልጅ እናትም ነበሩ፤

ይሁን እንጂ ወ/ሮ የኔነሽ አያሌው ባጋጠማቸው ድንገተኛ ህመም ምክንያት በተወለዱ በ44 አመታቸው ሐምሌ 21 ቀን 2017 ዓ.ም ከዚህ አለም ድካም አርፈዋል።

ለቤተሰቦቻቸው፤ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እንዲሁም ለስራ ባልደረቦቻቸው ሁሉ መፅናናቱን እንመኛለን።

ማስታወቂያ                           የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት በፀደቀው አዲሱ አዋጅ 1354/ 2017 መሰረት የህክምና ግብዓቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ :ጥራቱን በጠበ...
29/07/2025

ማስታወቂያ




የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት በፀደቀው አዲሱ አዋጅ 1354/ 2017 መሰረት የህክምና ግብዓቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ :ጥራቱን በጠበቀ እና ቀጣይነት ባለው መልኩ አቅርቦቱን ለማሣደግ ይረዳው ዘንድ ከአገልግሎቱ የግዥ መዘርዝር ወጭ የሆኑ የህክምና ግብዓቶች (Non- PPL items) በባለ ብዙ አማራጭ የአቅርቦት ስርዓት (multi-Vender sourcing System) ወደ ትግብራ ለማስገባት እየተሰራ ይገኛል፡፡

ስለሆነም ይህንን ስርዓት ለመተግበር የህክምና ግብዓት አስመጪዎችን (Importers) ለማሳተፍ እና ግንዛቤ ለመፍጠር የጤና ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ጋር በመተባበር ሐሙስ 24/11/2017 ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ የዌብነር ውይይት ተዘጋጅቷል፡፡

አስመጭዎች ከታች በተቀመጠው ሊንክ ቀድሞ በመመዝገብ የውይይቱ ተሣታፊ እንድትሆኑ በአክብሮት ተጋብዘዋል፡፡ በእለቱ በኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የፌስቡክና የዮቲዮብ ቻናል የቀጥታ ስርጭት የሚደረግ በመሆኑ ጭምር እየገለጽን በፕሮግራሙ ላይ እንዲሳተፉ፣ አስትያየት እና ጥያቄ እንድትጠይቁ የመድኃኒት አቅርቦት ሰንሰለቱ ዋነኛ አጋር እንዲትሆኑ እጥሪአችንን እናቀርባለን፡፡

https://zoom.us/webinar/register/WN_PcZgYKbtQyCmqcotiuwACA

> ለበለጠ መረጃ፡- በ0943516129 አቶ መስፍን በርሄ ን ያነጋግሩ

ማገልገል ክብር ነው

የመሰረታዊ የህክምና ግብአቶች አቅርቦት
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት

የስራ አፈፃፀም መመዘኛ ስርዓት (PMS) በተሻለ መልኩ በተቋሙ የዉስጥ አቅም በማበልፀግ ወደ ስራ ለመግባት ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁ ተገለፀ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ከዚህ ቀደም አገልግሎቱ የኢትዮጵያ ...
28/07/2025

የስራ አፈፃፀም መመዘኛ ስርዓት (PMS) በተሻለ መልኩ በተቋሙ የዉስጥ አቅም በማበልፀግ ወደ ስራ ለመግባት ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁ ተገለፀ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ከዚህ ቀደም አገልግሎቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሲስተምን ሲጠቀም የቆየ ሲሆን ፤ ለአጠቃቀም አስቸጋሪ በመሆኑ ምክንያት በዉስጥ አቅም ሲስተሙን በማበልፀግ ለቡድን መሪዎች ከሐምሌ 18-21 ቀን 2017 ዓ.ም ከአሜሪካ ኢንተርናሽናል ሄልዝ አልያንስ (AIHA) ጋር በመተባበር የአሰልጣኞች ስልጠና በአዳማ ከተማ መሰጠቱን የአገልግሎቱ የሰዉ ሀብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የትምህርት እና ስልጠና ቡድን መሪ አቶ አድነዉ ወልደ ትንሳይ ገልፀዉ ተቋማዊ ራዕይ እንዲሳካ የሰዉ ሀይል ግንባታ ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

ባለሞያዎች ከተቋሙ ራዕይ፣ ተልዕኮና ስትራቴጂክ እቅድ ጋር የተናበበ ግብ እንዲኖራቸዉ ፤ የተሻለ አፈፃፀም እንዲመዘገብ ፤ ልዩ ክህሎትና የፈጠራ ስራዎች ጎልተዉ እንዲወጡ ፤ መልካም የመረጃ ተግባቦት እንዲኖርና ዉጤት ተኮር መመዘኛና እዉቅና አሰጣጥ እንዲፈጠር የሚያስችል ስርዓት እየተዘረጋ መሆኑን አቶ ፅጋቡ ገብሩ የእቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ቡድን መሪ አስረድተዋል።

በተያያዘም ቁልፍ የአፈፃፀም አመላካቾችን የማጥራትና የማደራጀት ስራ መከናወኑን ፤ የስልጠና መመሪያዎች መዘጋጀታቸዉን የእቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ቡድን መሪዉ አስታዉሰዋል።

ተቋሙ ዘመኑን የዋጀ የERP አሰራር ተግባራዊ ማድረጉን ተከትሎ ግልፀኝነትና ተጠያቂነትን ለማስፈን ፤ ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ በባለቤትነት ለማስተዳደር በትጋት እየተሰራ ሲሆን የሰራተኞች የስራ አፈፃፀም መመዘኛ ስርዓትን (PMS) በተሻሻለ መልኩ በማበልፀግ የዘመነና የተሳለጠ የመረጃ ፍሰት እንዲመጣ እየተሰራ መሆኑን የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት የሲስተም ማበልፀግ ቡድን ተጠሪ አቶ ሳሙኤል ጌታዬ ገልፀዋል።

የስልጠናዉ ተሳታፊ የሆኑት አቶ አበበ በየነ የመድኃኒትና የህክምና ግብዓቶች ጥራት ቁጥጥርና ክትትል ቡድን መሪ ሲሆኑ ሲስተሙ በተፈለገዉ ልክና መጠን ለማስተዳደርና ለመቆጣጠር ተሻሽሎ መቅረቡ ፤ ተቋሙ በራሱ ሰርቨር በመጠቀሙ የመረጃዎች ደህንነትን ለመጠበቅ አመቺ እንደሆነና አገልግሎቱ ከሚጠቀማቸዉ የተለያዩ ስርዓቶች ጋራ በቀላሉ ለማቀናጀት የሚያስችል ሲስተም መሆኑ መልካም እንደሆነ አንስተዋል።

ሌሎች በዋና መስሪያ ቤት ያሉ የአሰልጣኝ ሰልጣኝ (TOT) ቡድን መሪዎችም ለተቋማዊ ስኬት የበኩላቸዉን ሀላፊነት እንደሚወጡ ተናግረዉ KPI የማጥራት ስራ ወሳኝ እንደሆነ ገልፀዋል።

የPMS ስልጠና ከዚህ ቀደም ለቅርንጫፍ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ባለሞያዎች ፤ የእቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ እንዲሁም የሰዉ ሀብት አስተዳደር ተወካይ ሰራተኞች የተሰጠ ሲሆን በቀጣይ ደግሞ ለዳይሬክተሮች የሚሰጥ ይሆናል።

#ማገልገል ክብር ነዉ
አማኑኤል ወርቃየሁ

የሴቶች ፣ ወጣቶች ና ህፃናት ዳይሬክቶሬት  ባሳዩት የሥራ አፈፃፀም  እዉቅና አገኙ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የሴቶች ፣ ወጣቶች ና ህፃናት ዳይሬክቶሬት በ15ኛው...
27/07/2025

የሴቶች ፣ ወጣቶች ና ህፃናት ዳይሬክቶሬት ባሳዩት የሥራ አፈፃፀም እዉቅና አገኙ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የሴቶች ፣ ወጣቶች ና ህፃናት ዳይሬክቶሬት በ15ኛው የጤና ዘርፍ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ የመዋቅሮች አመታዊ እቅድ አፈጻጸም ውይይት ለተከታታይ ሶስት ቀናት በአማራ ክልል በባህር ዳር ከተማ በተካሄደዉ መድረክ አገልግሎቱ በ2017 ዓ.ም በጀት አመት ከፍተኛ አፈጻፀም በማስመዝገብ የእዉቅና ሰርተፍኬት ተሸላሚ ሆኗል፡፡

በተለይም አገልግሎቱ ማህበራዊ ሀላፊነትን ከመወጣት አንፃር ሰፊ ስራዎችን በማከናወኑ ፤ የህጻናት ማቆያ መስራቱ ፤ ሰራተኞች በስራ ቦታ ፆታዊ ትንኮሳ ሲደርስባቸዉ የሚያመለኩቱበት ሶፍትዌር በመስራቱ፣ የቁጥጥርና የተጠያቂነት ስርዓት ማሳደግ ፣ ለቅርንጫፎች ድጋፍዊ ጉብኝት ማድረግ ፣ የተለያዩ መተዳደሪያ ደንቦችና አሰራሮች በመስራት የስራ ሂደቱን ስራዎች ደረጃውን ያሟላ እንዲሆን ማድረግ የተሠሩ ስራዎች ነበሩ።

የሴቶች ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ፣ የአገልግሎቱ የማህበራዊ ድጋፍ ተሳትፎ ማሳደግ ፣ ሴት አመራሮችን ማብቃት የህፃናት የቀን መዋያ የወለጆች ዕርካታ ዳሰሳ ጥናት ተደርጋል ፣ የስራ ሂደት አገልግሎትን በተመለከተ በዋናው መ/ቤት የሰራተኞችን እርካታ ዳሰሳ ጥናት ተደርጋል ፣ የመድኃኒት ግዥ መዘርዝር ሶስተኛ ህትመት(PPL 3rd edition) ከስርዓተ- ፆታ አንፃር ትንተና ተሰርቷል።

በመድኃኒትና ህክምና መገልገያዎቸ የእናቶች ህፃናትና አካል ጉዳተኞች ፍትሃዊ ተጠቃሚ መሆናቸውን ከሚመለከታቸው ክፍሎች መረጃ በማሰባሰብ ትንተና መሰራቱ በአጠቃላይ በጤናው ሴክተር ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳች አካቶ ትግበራ አፈጻጸም መሻሻል ላሳዩት ቁርጠኝነት እንዲሁም የጤና ፍትሀዊነት እንዲረጋገጥ በማድረግ ሂደት በበጀት የጤናው ዘርፍ አፈጻጸም የተሻለ ስራ በመስራቱ ለእዉቅና ሰርተፍኬቱ ፣ ለላፕቶፕ ስጦታ እና የዋንጫ እንዳበቃቸዉ የአገልግሎቱ ሴቶች ፣ ህፃናት እና ወጣቶች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ አለምፀሀይ ዳታ ገልፀዋል፡፡

25/07/2025
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ሰራተኞች  በሀገራዊ  #የልማት ዕቅድ አፈጻጸሞች  እና በ2018 በጀት አመት የእቅድ አቅጣጫዎች   ላይ ውይይት  አካሄዱ፡፡=================...
24/07/2025

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ሰራተኞች በሀገራዊ #የልማት ዕቅድ አፈጻጸሞች እና በ2018 በጀት አመት የእቅድ አቅጣጫዎች ላይ ውይይት አካሄዱ፡፡
==========================================

የጤና ሚኒስትር ድኤታ ወ/ሮ ፍሬህይወት አበበ ፣ የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ ፣ የማኔጅመንት አባላት እና መላው የዋናው መስሪያ ቤት ሠራተኞች በ2017 በጀት አመት #እቅድ ክንውኖች #አፈጻጸም እና በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ሀገራዊ የልማት ዕቅድ አቅጣጫዎች ላይ ሀምሌ 17/2017 ዓ.ም ውይይት አካሂደዋል ።

በውይይቱ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የጤና ሚኒስትር ድኤታ ወ/ሮ ፍሬህይወት አበበ እንደገለፁት ውይይቱ እንደ ሀገር በተለይም በጤናው ዘርፍ በበጀት ዓመቱ ለማከናወን የታቀዱ ሥራዎችን እና ዕቅዱን ለማሳካት ከሰራተኛው የሚጠበቀውን ሚና ለማሳወቅ ያለመ መሆኑን ገልፀዋል ።

አለም አቀፍ የኢኮኖሚ አዝማሚያዎችን ተከትሎ የሀገራት እድገት መኖሩ በተለይም የሀገራችን #በማክሮ ኢኮኖሚው፤ማህበራዊ ልማት የታዩት ለውጦች #የሀገር በቀል ኢኮኖሚው ውጤት በእለቱ ቀርቦል፡፡የህዳሴ ግድባችንን ጨምሮ የትልልቅ ፕሮጀክቶች አፈጻጸም እያደገ መምጣቱ የመንግስትን ቁርጠኝነት ማሳያ መሆኑ በእለቱ ተገጸዋል፡፡

ሀገራዊ የመንግስት የልማት እቅድና አፈፃፀም ከተነሱ ሀሳቦች አለም አቀፍ የኢኮኖሚ እንደ ሀገር ያለው ተፅዕኖ ፣ የሀገርን ኢኮኖሚ ማሳደግ ፣ አዳዲስና ነባር ኢንዱስትሪዎችን ማስፋፋት ፣ የውጪ ሀገር የስራ እድል ተጠቃሚነትን ማሳደግ ፣ ሎጀስቲክስና ንግድ ማሳለጥ ፣ ጥራት ያለው የማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ ማጠናከር ይገባል፡፡

በተለይም #የጤናው ዘርፍ የሀገር ውስጥ ፋርማስቲካልና የህክምና መሳሪያ አምራቾችን አቅም ማሳደግ ፣ እንደ ተቋም በቀጣይ አመት በዋነኝነት ማሳካት የሚገባን ውል የተገባለት #የመድኃኒት ፍላጎት እና አቅርቦት ስርዓት ለማሳካት መስራት መሆኑን የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር በዝርዝር አቅርበዉ ፤ የጤናውን ዘርፍ አቅም ለማሳደግ ብሎም የህክምና ግብዓት አቅርቦትን ለማሻሻል ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖራቸው ተናግረዋል ።

ወርቅ እና #ቡናን ጨምሮ ወደ ውጭ የሚላኩ #የኤክስፖርት ምርቶች ላይ ከፍተኛ ቁጥጥር በማድረግ አዳድስ የንግድ መዳረሻዎችን ማስፍፍት እና የሀገር ውስጥ ምርታማነትን ማሳደግ እንዲሁም በኢንዱስትሪው፤በግብርና ፤በማኑፋክቸሪንግ፤በኮንስትራክሽን እና በአገልግሎት ዘርፎች የሚሰሩ በርካት ተግባር መኖራቸውን በውይይቱ ላይ ቀርቧል፡፡

ተቋሙ እንደ ሀገር የተያዙ ዕቅዶችን በማሳካት በኩል ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው በመረዳት ሁሉም የሥራ መሪና ሠራተኛ የተሰጠውን ኃላፊነት በአግባቡ መወጣት እንደሚኖርበት ዋና ዳይሬክተሩ አሳስበዋል ።

በመንግስት እና በህዝብ ትብብር የተሰሩ መልካም ስራዎች በመኖራቸው እውቅና የሚሰጣቸው ናቸው ያሉት ተወያዮቹ አሁንም የሰላም ፤የኑሮ ውድነት፤ #የመኖሪያ ቤት እጥረት፡የመብራት መቆራረጥ የበለጠ ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራባቸው ይገባል ብለዋል፡፡በውይይቱ ከተሳታፊዎች የተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ከመድረኩ ተሰጥቶባቸዋል ።

# ማገልገል ክብር ነዉ!
ማኅሌት አበራ

23/07/2025

#የመንግስት ግዥ አና ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር በወ/ሮ መሰረት መስቀሌ የተመራ ልዑካን ቡድን አባላት በአገልግሎቱ ያደረጉት ምልከታ

22/07/2025

#የመሰረት ድንጋይ የሆነ ፤ #የጨዋታ ህግ ቀያሪ /Game Changer / #ለመድኃኒት አቅርቦት ሰንሰለቱ መሰረታዊ ችግርን የሚፈታው፤ #አኩል ተጠያቂነት የሚያሰፍነው #ውል የተገባለት የመደኃኒት ፍላጎት እና አቅርቦት #ስርዓት/ comitted Demand/

የጤና ሚንስቴር እና ተጠሪ ቋማት የማኔጅመንት አባላት ” #በመትከል ማንሰራራት ” በሚል መሪ ቃል 7ኛውን ዙር የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ አከናወኑ ፨፨፨፨፨፨፨የጤና ሚኒስቴር ሚንስትር ዶ/...
21/07/2025

የጤና ሚንስቴር እና ተጠሪ ቋማት የማኔጅመንት አባላት ” #በመትከል ማንሰራራት ” በሚል መሪ ቃል 7ኛውን ዙር የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ አከናወኑ
፨፨፨፨፨፨፨

የጤና ሚኒስቴር ሚንስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ፣ ሚኒስትር ድኤታዎች ፣ የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ ፣ የጤናው ዘርፍ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና የአገልግሎቱ የማኔጅመንት አባላት ሐምሌ 14 ቀን 2017 ዓ.ም በቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ቅጥረ ጊቢ እና እንጦጦ ፓርክ በመገኘት #ችግኝ ተክለዋል፡፡

የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ እንዳሉት በሃገር አቀፍ ደረጃ ላለፉት 6 ዓመታት ሲካሄድ በነበረው የአረንጓዴ አሻራ ዘመቻ የአገልግሉቱ አመራሮችና መላው ሰራተኞች ንቁ ተሳታፊ እንደነበሩ አስታዉሰው ዘንድሮም የችግኝ ተከላና እንክብካቤው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል፡፡

በተጨማሪም ጤና ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማቱ አምራችና ጤነኛ ማህበረሰብን ለመፍጠር ሰፊ ስራዎች እየተሰሩ ሲሆን በጎነት ለጤናችን በሚል የጤና ሚኒስቴር ዋና መልእክት እስከ 300ሺ ችግኞችን ለመትከል በርብርብ ላይ እንደሆኑ ዶ/ር ተገኔ ረጋሳ በጤና ሚኒስቴር የኮሙኒኬሽንና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ተናግረዋል፡፡

በዘንድሮዉም አመት #የአረንጓዴ አሻራ ሀገራዊ ዘመቻ ለምግብነት ፣ ለመድኃኒትነት እና ሀገር በቀል የሆኑ ችግኞች እየተተከሉ ነው፡፡

#ማገልገል ክብር ነዉ
ዘጋቢ አማኑኤል ወርቃየሁ

በመድሃኒት እና ህክምና መሳሪያ አቅርቦት መሻሻል ላይ  የተመዘገቡ  ውጤቶችን  ለማስቀጠል  በየደረጃው ያለ አመራር ቁርጠኝነት ወሳኝ መሆኑን  እንዲሁም ውል የተገባለትን የአቅርቦት ስርአት መ...
20/07/2025

በመድሃኒት እና ህክምና መሳሪያ አቅርቦት መሻሻል ላይ የተመዘገቡ ውጤቶችን ለማስቀጠል በየደረጃው ያለ አመራር ቁርጠኝነት ወሳኝ መሆኑን እንዲሁም ውል የተገባለትን የአቅርቦት ስርአት መተግበር እንደሚገባ ተገለፀ፡፡
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ የመድኃኒት እና ህክምና መሳሪያዎች ዳይሬክቶሬት የ2017 በጀት ዓመት ተግባራት አፈፃፀም ግምገማ አካይዷል ፡፡

የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ በአፈጻጸም መድረኩ ላይ እንዳሉት በበጀት ዓመቱ የመድሃኒት እና የህክምና መሳሪያዎች አቅርቦት ችግር ለመፍታት በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ገልጸዋል ፡፡

የመድሃኒት አቅርቦት ችግርን ለመፍታት ህብረተሰቡን ፣ባለሀብቱን አጋር አካላትን በማስተባበር በርካታ የማህበረሰብ መድሀኒት ቤቶች መገንባት መቻሉን የገለጹ ሲሆን በጤና የህክም መሳሪያዎች እና ቁናቁሳ ማሟላት ስራመሰራቱንም አስታውቀዋል ፡፡

የህክምና ግብዓት አቅርቦትን ለማሻሻል ከኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ እና ከሌሎች አካላት ጋር ያለው ቅንጅት ጥሩ መሆኑን ገልጸዋል ፡፡

የዘርፉን የግብዓት ችግር በዘላቂነት ለመፍታት በበጀት አመቱ የመድሃኒት እና የህክምና መሳሪያዎች አቅርቦት ለውጥ እንዲመጣ ያስቻሉ የማህበረሰብ መድሃኒት ቤት ማስፋፋት እና የውስጥ አቅምን በመጠቀም በቀጣይም በሁሉም አካባቢ ማስፋት ይገባል ብለዋል ፡፡

ለዚህም በየደረጃው ያለ አመራር በቁርጠኝነት መስራት አለበት ብለዋል ፡፡

ከኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ ጋር አስገዳጅ የመድሃኒት ግዢ ውል ስርዓት እንደሚጀመር ገልጸው በየደረጃው ያለው አመራር ለመድሀኒት ግዢ የሚውል በጀት ማስያዝ የአመራር ቁርጠኝነትን እንደሚፈልግ አሳስበዋል ፡፡

የቢሮ ምክትል ኃላፊ እና የህክምና አገልግሎቶች ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሀብቴ ገብረ ሚካኤል በበኩላቸው የዘርፉን ችግሮች ለመፍታት በተሰራው ስራ ከፍተኛ ለውጥ ቢመጣም የህክምና ግብዓቶች አያያዝ እና አጠቃቀም ላይ መሰረታዊ ለውጥ መምጣት እንደሚገባ ገልጸዋል ፡፡

የዘርፉን ችግሮች ለመፍታት የተቀመጡ የመድሃኒት አስተዳደር ስርዓቶችን መተግበር እንዲሁም ተጠያቂነትን ማረጋገጥ የቀጣይ ትኩረት መሆናቸውን አቶ ሀብቴ አስታውቀዋል፡፡

ምንጭ፣ የክልልሉ ጤና ቢሮ

Address

Addis Ababa

Telephone

+251112763276

Website

https://t.me/epsaethiopia2012

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Pharmaceuticals Supply Service - EPSS posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Ethiopian Pharmaceuticals Supply Service - EPSS:

Share