
11/07/2023
ከሰሞኑ ቁርአን በተቃጠለባት ስዊድን ውስጥ የኩዌት መንግስት በስዊዲሽ ቋንቋ የተተረጎመ 100ሺ ቁርአን አሳትሞ እንደሚያከፋፍል ገልጿል..
ሀሩን ሚዲያ፥ ሐምሌ 4/2015..
ከሰሞኑ ቁርአን በተቃጠለባት ስዊድን ውስጥ የኩዌት መንግስት በስዊዲሽ ቋንቋ የተተረጎመ 100ሺ ቁርአን አሳትሞ እንደሚያከፋፍል ገልጿል። በቅርቡ የዒድ አል አድሀ በዓልን ተከትሎ በሀገሪቱ ውስጥ አንድ ጽንፈኛ ግለሰብ ቁርአንን በማቃጠሉ ሳቢያ ከፍተኛ ቁጣን መቀስቀሱ ይታወሳል። ይህ ቁጣ ከሀገሪቱ አልፎ በመላው ሙስሊሙ አለም ውግዘትን ያስከተለ ሲሆን የስዊድን መንግስትም ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ኪሳራ እንደገጠመው ተገልጿል። ይህንን ተከትሎም ቁርአንን ማቃጠልን በህግ የሚከለክል ድንጋጌ ለማርቀቅ እንቅስቃሴ እንደጀመረ መግለጹ ይታወሳል።..
© ሀሩን ሚዲያ
___________
በቴሌግራም፥ https://t.me/harunmedia
በዩቲዩብ ፥ http://bit.ly/3MXs17j