ADONA Mindful Counseling

ADONA Mindful Counseling Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ADONA Mindful Counseling, Psychotherapist, Addis Ababa.

21/06/2022

ስለ አገልግሎታችሁ እናመሰግናለን
Thank you for your contribution

በአለርት ማዕከል የሴቶች ህፃናት እና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት የሚመራው የማዕከላችን የሴቶች መረብ ኳስ ቡድን ለፐብሊክ ሰራተኞች በተዘጋጀው የቮሊቮል ውድድር ላይ ተሳታፊ በመሆን እንዲሁም ...
19/06/2022

በአለርት ማዕከል የሴቶች ህፃናት እና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት የሚመራው የማዕከላችን የሴቶች መረብ ኳስ ቡድን ለፐብሊክ ሰራተኞች በተዘጋጀው የቮሊቮል ውድድር ላይ ተሳታፊ በመሆን እንዲሁም በማሸነፍ የዋንጫ እና የሜዳልያ ሽልማት ተቀብሏል። የሴቶች መረብ ኳስ ተጫዋቾቻችንን ላስመዘገቡት ውጤት ምስጋናችንን ልናቀርብ እንወዳለን!!!

በዛሬው ዕለት የአለርት አህሪ የወንዶች የእግር ኳስ ቡድን ከውዳሴ ዳያግኖስቲክ ሴንተር የወንዶች የእግር ኳስ ቡድን ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ጀሞ በሚገኘው የቦስኮ ሜዳ ያደረገ ሲሆን በጨዋታው ሁ...
07/05/2022

በዛሬው ዕለት የአለርት አህሪ የወንዶች የእግር ኳስ ቡድን ከውዳሴ ዳያግኖስቲክ ሴንተር የወንዶች የእግር ኳስ ቡድን ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ጀሞ በሚገኘው የቦስኮ ሜዳ ያደረገ ሲሆን በጨዋታው ሁለቱም ቡድኖች ያሉባቸውን ክፍተቶች የለዩበት በቀጣይም እንዴት ማስተካከል እንደሚችሉ የተማሩበት እንዲሁም እንደጤና ተቋም በጋራ የሚሰሩባቸው መንገዶች ላይ ውይይት ያደረጉበት ጊዜ ሆኗል!!!

የአለርት ማዕከል የወጣት ሰራተኞች ፎረም በዛሬው ዕለት የእስልምና እምነት ተከታይ ለሆኑና 120 ለሚሆኑ በማዕከላችን በሁሉም የህክምና ክፍሎች ተኝተው ህክምናቸውን ለሚከታተሉ እንዲሁም የህክም...
21/04/2022

የአለርት ማዕከል የወጣት ሰራተኞች ፎረም በዛሬው ዕለት የእስልምና እምነት ተከታይ ለሆኑና 120 ለሚሆኑ በማዕከላችን በሁሉም የህክምና ክፍሎች ተኝተው ህክምናቸውን ለሚከታተሉ እንዲሁም የህክምናውን አገልግሎት ለሚሰጡ የህክምና ባለሙያዎች ታላቁን የረመዳን ፆም ምክንያት በማድረግ እንኳን አደረሳችሁ በማለት የቴምር ስጦታ አበርክተዋል።

ስፓርት ለሁሉ በሚያዘጋጀው አመታዊ ውድድር ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት የአለርት/አህሪ የሴቶች የመረብ ኳስ ቡድን በትላንትናው እለት የኦቢኤን የሴቶች የመረብ ኳስ ቡድንን 2ለ1 በሆነ ውጤት ያሸ...
17/04/2022

ስፓርት ለሁሉ በሚያዘጋጀው አመታዊ ውድድር ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት የአለርት/አህሪ የሴቶች የመረብ ኳስ ቡድን በትላንትናው እለት የኦቢኤን የሴቶች የመረብ ኳስ ቡድንን 2ለ1 በሆነ ውጤት ያሸነፈ ሲሆን የወንዶች የመረብ ኳስ ቡድናችን ግን በኦቢኤን አቻው 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።

በአለርት ማዕከል የወጣቶች ጉዳይ ቡድን የሚመራው የማዕከላችን የወጣቶች ፎረም መጋቢት 16/2014 ዓ.ም ባስተባበሩት እና በሰሊሆም የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል በተከናወነው ነፃ የህክምና ...
31/03/2022

በአለርት ማዕከል የወጣቶች ጉዳይ ቡድን የሚመራው የማዕከላችን የወጣቶች ፎረም መጋቢት 16/2014 ዓ.ም ባስተባበሩት እና በሰሊሆም የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል በተከናወነው ነፃ የህክምና አገልግሎት ካምፔይን ላይ በመገኘት የህክምና አገልግሎቱን ለሰጡ የጤና ባለሙያዎችና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች በዛሬው እለት የእውቅና እና የምስጋና ፕሮግራም ተከናውኗል። በዕለቱም በቀጣይ ስራዎች ዙርያ ውይይት ተደርጓል።

በአለርት ማዕከል የሴቶች ህፃናት እና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት የሚመራው የማዕከላችን የወጣቶች ማህበር በሆስፒታላችን በተለያዩ ክፍሎች ማለትም የቆዳ የውስጥ ደዌ የአጥንት የህፃናት የፊዚዮ ...
25/03/2022

በአለርት ማዕከል የሴቶች ህፃናት እና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት የሚመራው የማዕከላችን የወጣቶች ማህበር በሆስፒታላችን በተለያዩ ክፍሎች ማለትም የቆዳ የውስጥ ደዌ የአጥንት የህፃናት የፊዚዮ ቴራፒ እና የሳይካትሪ ህክምና ስፔሻሊቲ ሀኪሞችን ነርሶችን እና ላብራቶሪ ቴክኒሻኖችን በማስተባበር በአይነቱ ልዩ የሆነ የህክምና አገልግሎት እንጦጦ ለሚገኘው ሰሊሆም የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ለሚገኙ 120 አዋቂዎችና ህፃናት በዛሬው እለት ሰጥተዋል። ይህ የወጣቶች ማህበር ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ የተለያዩ በጎ ተግባራትን በተለያዩ ድርጅቶች ሲያከናውን የቆየ ሲሆን በዛሬውም ዕለት ከማህበሩ አካውንት ገንዘብ ወጪ በማድረግ ለታካሚዎቹ የሚሆን የ100 ኪሎ ጤፍ እና 9 እሽግ (275) የተለያየ ቁጥርና ሳይዝ ያላቸውን የአዋቂና የህፃናት ዳይፐሮችን እንዲሁም ከበጎ ፈቃደኛ ሰራተኞች የተሰበሰቡ 75 መፅሀፍትን ለሰሊሆም የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማህበር ድጋፍ አድርጓል።
በፕሮግራሙ ላይ ለተሳተፋችሁ ሀኪሞች ነርሶች ላብራቶሪ ቴክኒሻኖች ስፒች ቴራፒስቶች የሳይካትሪ ባለሙያዎች እና ፕሮግራሙን ስታስተባብሩ ለዋላችሁ የተከበራችሁ የማህበሩ አመራሮች ከልብ የመነጨ ምስጋናችንን በአክብሮት ልንገልፅ እንወዳለን!!!

ታላቁ የ5 ኪ.ሜ የሴቶች እሩጫ ሁለተኛ ዙር የግሩፕ ፎቶዎች
19/03/2022

ታላቁ የ5 ኪ.ሜ የሴቶች እሩጫ ሁለተኛ ዙር የግሩፕ ፎቶዎች

የአለርት ማዕከል የሴቶች ህፃናት እና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ከAHF ኢትዮጵያ ጋር በጋራ በመሆን በሆስፒታላችን ሰራተኛ ለሆኑ ሴት ሰራተኞች በአህሪ የምርምር  ማዕከል ለሚሰሩ ለተመረጡ ሴ...
13/03/2022

የአለርት ማዕከል የሴቶች ህፃናት እና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ከAHF ኢትዮጵያ ጋር በጋራ በመሆን በሆስፒታላችን ሰራተኛ ለሆኑ ሴት ሰራተኞች በአህሪ የምርምር ማዕከል ለሚሰሩ ለተመረጡ ሴት ሰራተኞች ለጤና ሚኒስቴር የተመረጡ ሴት ሰራተኞች እና በAHF ኢትዮጵያ ለሚሰሩና ለተመረጡ ሴት ሰራተኞች በድምሩ ለ100 ሴቶች በአመታዊው የ5 ኪ.ሜ ታላቁ የሴቶች ሩጫ ላይ ሙሉ ወጪያቸውን በመሸፈን እንዲሮጡ ተደርጓል። በሩጫው ላይ ተሳታፊ ለሆናቹ ሰራተኞቻችን እና ለAHF ኢትዮጵያ የከበረ ምስጋናችንን ልናቀርብ እንወዳለን!!!

ስፖርት ለሁሉ በሚያዘጋጀው ስፓርታዊ ውድድር ላይ እየተሳተፈ የሚገኘው የአለርት/አህሪ የወንዶች የእግር ኳስ ቡድን በዛሬው እለት 4ኛ ጨዋታውን አድርጓል። የዛሬውን ጨዋታ ከዘውዲቱ ሆስፒታል ጋ...
12/03/2022

ስፖርት ለሁሉ በሚያዘጋጀው ስፓርታዊ ውድድር ላይ እየተሳተፈ የሚገኘው የአለርት/አህሪ የወንዶች የእግር ኳስ ቡድን በዛሬው እለት 4ኛ ጨዋታውን አድርጓል። የዛሬውን ጨዋታ ከዘውዲቱ ሆስፒታል ጋር ያደረገው ቡድናችን ከሙሉ የጨዋታ የበላይነት እና ስነምግባር ጋር 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል!!!

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ADONA Mindful Counseling posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram