Awal 0913808195

27/02/2025
07/02/2025

ሰሚ ካለ‼️

ከ3 ወራት በላይ አልፈዋል፣ አሁንም 159 ሙስሊም ሴት ተማሪዎች በአክሱም ትግራይ፣ በሒጃባቸው ምክንያት ከትምህርት ገበታ ውጪ ተደርገዋል፤ የመማር መብት ተነፍገዋል። ምንም እንኳን የትምህርት ሚኒስቴር መመሪያ ሒጃብ ለብሶ መማርን ቢፈቅድም የአክሱም ሙስሊም ሴቶች ሒጃብ ለብሰው መማር ተከልከለዋል። በአገሪቱ ካሉ ትምህርት ቤቶች በተለየ አክሱም ሒጃብ ከልክላለች።

ይህ ሲሆን Ministry of Education Ethiopia እና እና የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር Ministry of Women and Social Affairs ዝምታ መርጠዋል። Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council (የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትም) ደብዳቤ ከመፃፍ የዘለለ የሰራው ስራ አናውቅም።

የነዚህ ልጆች ከትምህርት ገበታ ውጪ መደረግ ከባድ የመብት ጥሰት ነው፤ ብዙ እንድምታዎች አሉት። ከምንም በላይ ተማሪዎቹ እንደ ዜጋ የመብት ጥሰት ሲፈፀምባቸው የሚደርስላቸው አካል በማጣታቸው በአገር፣ በሕግ እና በወገን የነበራቸውን እምነት እንዲሸረሸር አድርጎታል። እነዚህ ልጆች በክልል እና በወረዳ አስተዳደሮች የመብት ጥሰት መብት ሲፈፀምባቸው የትምህርት ሚኒስቴር፣ የሴቶች እና ማሕበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር እንዲሁም በፌደራሉ መጅሊስ የነበራቸውን ወይም ሊኖረቸው ይችል የነበረው እምነት እንዲያጡ ተደረገዋል። አንገታቸውን እንዲደፉ ተደርገዋል። የመማር መብታቸው ተነፍጎ ሊደርስላቸው የሚችል አካል እንደሌለ አይተዋል። ያሳዝናል።
159 ሙስሊም ሴት ተማሪዎች እምነታቸውን ያዘዛቸው ሒጃብ በመልበሳቸው ከትምህርት ገበታ ውጪ ሲደረጉ ምንም አለማድርጋችን ያበሳጫል። እነዚህ ልጆች ሒጃብ በመልበሳቸው ሲባረሩ ምንም ያላደረገ ወይም ያለለ ኢማም/ዳዒ እንዴት ብሎ ነው አፉን ሞልቶ ስለ ሒጃብ ኢስላማዊ ግዴታነት ዳዕዋ የሚያደርገው? 159 ሴቶች ከትምህርት ገበታ ውጪ ሲደረጉ ምንም ያላደረገ የሴቶች ሚኒስቴር በምን ሞራል ነው አንዲትም ሴት ከትምህርት መቅረት የለባትም የሚለው? 159 ሴቶች ከትምህርት ገበታ ውጪ ሲደረጉ ምንም ያላደረገ ትምህርት ሚኒስቴር በምን ሞራል ነው ሴቶችን የማከለ እና አካታች የትምህርት ስርዓት ነው የምከተለው ማለት የሚችለው?

Hagos

of education Ethiopiacation Ethiopiaducation Ethiopia

Address

Addis Ababa

Telephone

+251913808195

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Awal posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category