
23/06/2025
===በጣም ያሳዝናል‼️====
🗯በቃላት ደረጃ እንኳ መልስ ከሰጡን ብዬ ሙሉ ቪዲዮውን ተመለከትኩት። ቅስም በሚሰብር ሁኔታ ባለሙያዎች የጠየቁትን ጥያቄ ትተው ስለ ሌላ ጉዳይ ሲያወሩ፣ ጊዜው አለቀ። ክፍል ሁለት ቢኖረው ብዬ ተመኘው።
⚓️አንዳንድ ቦታ ላይ የሚያሳዝኑ ንግግሮች ሁላ ነበሩ። ከነዚህም ውስጥ፦
📌1ኛ፦ "እኔ እና እናንተ ለቀጣይ 15 - 20 ዓመታት ቀበቷችንን ጠበቅ አድርገን ለጊዜውም ቢሆን እንቸገር፣ እኛ ባያልፍልን እንኳ ልጆቻችን ያልፍላቸዋል" ሲሉ ይደመጣሉ።
💥እኛ የጤና ባለሙያዎች ራበኝ፣ ታረዝኩ፣ ልጆቼን ማስተዳደር፣ ማስተማር አልቻልኩም ያልነው እንደት ብለን ቀበቷችንን እናጥብቅ? ረሀብ 20 ዓመት ይጠብቀናል? ልጆቻችን ምን በልተው አድገው ፣ እንዴት ተምረው ነው ወደፊት ጥሩ ኑሮ የሚኖሩት?
💥እርስዎንና እኛን እኩል ቀበቷችንን ጠበቅ እናድርግ ሲሉ እርሱዎ ተርበዋል? ታርዘዋል? ልጅ ለማሳደግ ተቸግረዋል? የዕውነት በጣም ያሳዝናል።
📌ሌላኛው ደግሞ " የትኛውም የአፍሪካ ሀገር የኢትዮጵያ መንግሰትን ያህል ለጤና ሴክተር የበጀት ድጋፍ አያደርግም" የሚለው ነው።
💥እንግዲህ ሚጢጢዬዋ ሩዋንዳ አንድ ሆስፒታል ለማደስ ፤ ለመስራት ሳይሆን ለማደስ፤ 250 ሚሊዮን ዶላር ትመድባለች።
በ 2024/25 እንኳ 462 ቢሊየን ዶላር ለጤና ዘርፍ መድባለች -just ለ 14.5 ሚሊየን ህዝብ ( 2025 Data)።
🗯ይህ ማለት ሩዋንዳ ለአንድ ሆስፒታል ማደሻ ብላ የምትበጅተው ገንዘብ Almost ለእኛ ለጤናው ዘርፍ ከሚማደበው በጀት ጋር እኩል ነው -- 130 ሚሊዮን ህዝብ ይዘን።
🗯 ራበኝ ብዬ ስጠይቅ፣ ጋዎን የለበስክ ፖለቲከኛ ነህ የሚል ማሸማቀቂያ ከተሰጠኝ፤ ብዙ ተስፋ ያደረኩበት የጠቅላይ ሚንስትሩ ስብሰባ በዚህ መልኩ ከተደመደመ ከዚህ በኋላ ተስፋዬ ማነው⁉️
Henok Abraham