ዲቦራ ክሊኒክ፤Dibora Clinic

ዲቦራ  ክሊኒክ፤Dibora Clinic በዚህ ፔጅ ሰለማነኛውም የጤና ችግርና ምክንያቶችና መፍትሄቸ?

28/01/2026
የሰው የደም አይነት
16/01/2026

የሰው የደም አይነት

24/08/2025

👉ስለ ሾተላይ (Rh-isoimmunization) ማወቅ ያለብን ነጥቦች⚠️
በዶ/ር ዳዊት መስፍን ፤ የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት

💥 ሾተላይ የሚባለው በሽታ ከሁለተኛ ጀምሮ የሚወለዱ ህፃናትን የሚያጠቃ በሽታ ሲሆን ይህም በእናትና በፅንሱ መሀከል የደም አይነት አለመጣጣም(Rh incompatability) ምክንያት የሚከሰት ነው።

💥 ሾተላይ የሚከሰተዉ የሴቲቱ የደም አይነት Rh negative ፣ የባል የደም አይነት Rh positive እና የፅንሱ ደግሞ Rh positive ከሆነ ሲሆን በተጨማሪም በተለያዩ ምክንያቶች Rh positive ደም ወደ ሴቲቱ ደም ከገባ ወይም ከወሰደች ነው።

🌟 ነጥብ

💥 ሚስት Rh negative መሆን ይኖርባታል እና ፅንሱ Rh positive መሆን ይኖርበታል
💥 ባል Rh negative ከሆነ ሾተላይ አይከሰትም

🌟 ሾተላይ ለምን ይከሰታል?

👉 የሰው ልጅ ከወላጆቹ ዘረመል ተነስቶ ከ4 የደም አይነቶች ውስጥ አንዱን ሊይዝ ይችላል። እነኝህም
1. “A”
2. “B”
3. “AB”
4. “O” ተብለው ይጠራሉ።

👉 በሰውነት ውስጥ የሚገኙ ቀይ የደም ህዋሶች(RBCs) የላይኛው ሽፋናቸው ላይ Rh የተባለ ፕሮቲን (protein) ካላቸው ሴቲቱ Rh positive ናት ማለት ሲሆን እነኚህ ፕሮቲኖች ከሌሉ ደግሞ Rh negative ናት ማለት ነው።

ለምሳሌ:- ሴቲቱ የደም አይነቷ B ቢሆንና ቀይ የደም ሴሎቿ ላይ Rh ፕሮቲን ካለ B Positive ናት ማለት ነው፤ እነኚህ Rh ፕሮቲኖች ከሌሉ ደግሞ B Negative ናት ይባላል።

👉 አንዲት ሴት ሾተላይ የሚባለው ችግር ሊከሰትባት የሚችለው እሷ Rh negative ሆና በተለያዩ አጋጣሚዎች Rh positive የሆነ ደም ወደሰውነቷ ሲገባ ሰውነቷ እነኚህን Rh positive የደም አይነቶች የሚያጠፉ(የሚገሉ) ንጥረ ነገሮች (Antibodies) ሲያመነጭ (ሲያመርት) ነው። እነኚህም እስከ እድሜልክ በሰውነቷ ይቆያሉ።

👉 እነኚህ የተመረቱት ተከላካይ ንጥረ ነገሮች(Antibodies) የመጀመሪያው ልጅ ላይ ምንም ተፅዓኖ ሳይኖራቸው ልጁ በሰላም ሊወለድ ይችላል ነገር ግን የሁለተኛው ፅንስ የደም አይነቱ Rh positive ከሆነ ወደ ፅንሱ በማለፍ የፅንሱን Rh positive የቀይ የደም ህዋሶች ያጠቃሉ ማለት ነው፤ ይህም ፅንሱን ለተለያየ አደጋዎች ሊያጋልጠው ይችላል።

👉 ይህም ችግር ፅንሱ ላይ የተለያዩ ጉዳቶችን ሊያመጣ ይችላል ፤ እነኚህም

☘️ በፅንሱ የተለያዩ የአካል ክፍሎች ውሀ መቋጠር - Fetal hydrops
☘️ በተደጋጋሚ የፅንስ መውረድ - Miscarriage
☘️ የፅንሱ የደም ማነስ - Fetal anemia
☘️ ፅንሱ በማህፀን ውስጥ እንዳለ ጊዜው ሳይደርስ ህይወቱ ማለፍ
☘️ ህፃኑ ከተወለደ በውሃላ ቆዳው ቢጫ መሆን እና የጨረር ህክምና ማስፈለግ(phototherapy)
☘️ በከፍተኛ ደም ማነስ ምክንያት ደም ለመውሰድ መጋለጥ

🌟 ሾተላይ እንዴት ይታከማል?

👉 Rh negative የሆነችው እናት ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩት ነገሮች ከገጠሟት
☘️ ባለቤቷ Rh positive ከሆነ
☘️ ውርጃ ካጋጠማት
☘️ ከማህፀን ውጭ እርግዝና ካጋጠማት
☘️ ከእንግዴ ልጅ ላይ የሚነሳ እጢ(Gestation trophoblastic disease) ካጋጠማት
☘️ በእርግዝና ወቅት አደጋ ከደረሰባት፤
☘️ በክትትል ወቅት ከእንግዴ ልጅ ወይም ከሽርት ዉሃ በመሳሪያ ናሙና ከተወሰደ

👉👉 Anti D የተባለ ኢሚውኖግሎቡሊን (immunoglobulin) መድሀኒት በመውሰድ ሾተላይን መከላከል ይቻላል።

💥☘️ በእርግዝና ጊዜ Anti D የተባለውን መ

09/08/2024

የካንሰር ታካሚን ልንረዳባቸው የምንችልባቸው ቀላል መንገዶች!!!

10ቱ ታካሚዎችን መርጃ ልዕልናዎች‼️🙏

እንደ ማህበረሰብ የመረዳዳት እና የመተጋገዝ ባህል ቢኖረንም በካንሰር የተያዙትን ጓደኞቻችንን፣ ዘመዶቻችንን፣ ጎረቤቶቻችንን እንዲሁም በግል የማናቃቸውን ግለሰቦች ለመርዳት ያለን ቁርጠኝነት ግን እምብዛም ነው። ይህንን በድፍረት እንድከትብ ያስገደደኝ በሀገራችን ያለውን ጥቂት ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ዋቢ በማድረግ ነው። መንግስታዊ ያልሆኑ በካንሰር ዙሪያ የሚሰሩ ድርጅቶች ቢቆጠሩ በሽታው ካደረሰው ማህበራዊ ቀውስ አንፃር ምንም ነው ሊባል ይቻላል። አለም አቀፍ ጥናቶች እንደተነበዩት በኢትዮጵያ በየአመቱ ቢያንስ 77,000 ሰው በካንሰር እንደሚያዝ ሲሆን ወደ 50,000 ገደማው ደግሞ በየአመቱ በዚህ በሽታ ይሞታል። ለዛሬ ታድያ አንድ ሰው እንደ ግለሰብ እነዚህን የካንሰር ታካሚዎች በቀላሉ ሊረዳባቸው የሚችልባቸውን መንገዶች እንዲህ ሰድሬያቸዋለው።

1) የካንሰር ታካሚዎችን በሚታከሙባቸው ሆስፒታሎች(በተፈቀደ ሰዓት) ወይም በማረፊያ ቦታዎች ለመጎብኘት/ለመጠየቅ መሞከር!!!

የካንሰር ታካሚ የሆኑ ግለሰቦች በህብረተሰቡ በሚደርስባቸው ጫና እራሳቸውን በቀላሉ ከማህበረሰባዊው መስተጋብሮች የሚያገሉ ስለሆነ ለብቸኝነት የመጋለጥ ዕድላቸው የሰፋ ነው። እንደ ሀገራችን ባሉ በኢኮኖሚው ዝቅ ባሉ ሀገራቶች ደግሞ ቤተሰብን የማስተዳደር ጫና ስለሚኖር ታካሚዎች ብቻቸውን የመታከም ዕድላቸው ከፍተኛ ነው። ስለሆነም ይህን በመረዳት የታካሚዎችን የግለኝተኝነት መብት(Privacy) በማክበር የጥየቃ ፕሮግራም ማዘጋጀት ይቻላል።

2) የካንሰር ታካሚዎችን የሀይማኖት መብት ባከበረ መልኩ የፀሎት እና የስነ ልቦና ማበረታቻ መድረኮችን ማዘጋጀት፤ ይህም ለእነሱ የምንሰጠው ግዜ በውስጣቸው ያለውን የስነ ልቦና ጫና እንዲቀንስ ያደርገዋል።

3) ቁምነገር እና ዋዝን ያዘለ አጭር የሞባይል መልዕክት ለመላክ መሞከር፤ ቀልዶችን በወረቀት ፅፎ መስጠት ወይም ከቻልን በአካል ተገኝተን እያዋዛን መንገር እንዲሁም የፖስት ካርድ ስጦታን መስጠት ቢቻል መልካም ነው።

4) በራስ ተነሳሽነት የታካሚውን ስራ ሊያቀሉ የሚችሉ ነገሮችን ነቅሶ አውጥቶ እነዛን ጉዳዮች መፈፀም። በተለይ የታካሚውን ልጆች መንከባከብ፣ ምግብ አብስሎ መመገብ፣ ፀጉር መስራት እና ንፅህናን መጠበቅ እና የመሳሰሉት

5) ታካሚዎቹን ባገኘናቸው አጋጣሚ ለማቀፍ መሞከር፦ ዕቅፋት በራሱ የሚሰጠው ጥሩ መልዕክት አለ! ብዙ ሰው የማያቀው ነገር ቢኖር የካንሰር ህክምናን ውድነት እና በቀላሉ መገኘት አለመቻሉን ነው። ስለሆነ ከተቻለ ከሞራል ድጋፉ በተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ ሊደረግባቸው የሚችልባቸውን መንገዶች ማፈላለግ እንደ ትልቅ መፍትሄ ተቀምጧል።

6) ደም መለገስ፦ የካንሰር በሽታን ወይም ህክምናውን ተከትሎ የሚመጣን የደም ማነስ ለማዳን ደምን መለገስ ፍቱን አማራጭ ነው። በተለይ በደም ካንሰር ለሚሰቃዩ ጨቅላ ህፃናት በህይወት የመኖር ተስፋቸውን ያለመልማል‼️

7) ሂውመን ሄር ወይም ዊግ መለገስ፦ የካንሰር ህክምናን ተከትሎ የሚመጣ ጊዜያዊ የፀጉር መመለጥ ስለሚኖር ብዙ ታካሚዎች ለስነ-አዕምሮ እንዲሁም ለስነ-ልቦና ጫና ስለሚዳረጉ በተቻለ አቅም የፀጉር ዊጎችን ወይም ተፈጥሯዊ ፀጉሮችን መለገስ ይቻላል።

8) የጡት ማስያዣን መለገስ፦ በጡት ካንሰር ለተያዙ ዕንስቶች እንደ ዋንኛ ህክምና የሚቆጠረው ጡትን ሙሉ በሙሉ የሚያስወግደው ቀዶ ጥገና እራሱን የቻሉ አሉታዊ ተፅንኦዎች ይኖሩታል። ስለዚህ እንስቷን ሊያግዝ የሚችል በበሽታው ያልተጠቃውን ሌላኛው ጡት ቀዶ ጥገና ከተሰራው የጡት ደረት ጋር የሚያይዝ ጡት ማስያዣ(

26/05/2022

ቋቁቻ (Pityriasis versicolor) ምንድነው?

ቋቁቻ የተለመደና በፈንገስ አማካኝነት የሚመጣ የቆዳ ህመም ነው

👉 ምልክቶቹ
ቋቁቻ በአብዛኛው ጀርባ ፣አንገት፣ደረትና የላይኛው የእጃችን ክፍል አካባቢ ይወጣል

ጠቆር ያሉ (hyperpigmented) ፣ ነጣ ያሉ (hypopigmented) አንዳንዴም ቀላ ያሉ ክብ ወይም እንቁላል ቅርጽ(oval) ሽፍታዎች ሲኖሩት እነዚህ ሽፍታዎች ላይም ትንንሽ ቅርፊቶች ይታያሉ

ሽፍታዎቹን በጣታችን ስንለጥጠው ወይም ፋቅ ፋቅ ስናረገው ቅርፊቶቹ በደንብ ይጎላሉ

የተለመደ ባይሆንም አንዳንዴ የማሳከክ ስሜት ሊኖር ይችላል

👉 ምን አይነት ሰዎች ላይ ይከሰታል
በአብዛኛው በወጣትነት እና በጎልማሳነት የእድሜ ክልል ውስጥ ይከሰታል

👉 ለቋቁቻ የሚያጋልጡን ሁኔታዎች
- በተፈጥሮ ተጋላጭነት (genetic predisposition) ይህም በቤተሰብ አባላት ውስጥ እንዲከሰት ሊያደርግ ይችላል
- ሞቃታማ አካባቢ መኖር
- የበሽታ የመከላከል አቅም መዳከም
- እርግዝና
- ቆዳችን ወዛም ከሆነ
- Oily የሆኑ ቅባቶችን መጠቀም
- ከመጠን ያለፈ ላብ

👉 ቋቁቻ እንዴት ይታከማል?
ሽፍታው በቆዳ ሐኪም ታይቶ ከተረጋገጠ በኋላ ሐኪሙ በሚያዘው መሰረት በሚቀባ፣ በሻምፖ ወይም በሚዋጥ መድሀኒት ህክምናው ይሰጣል

ከህክምናው በኋላ ሽፍታው ላይ የነበሩት ቅርፊቶች ይጠፋሉ ይህም የህመሙን መዳን ያመለክታል

ነገር ግን ሽፍታው ወጥቶበት የነበረው ቦታ ወደ መደበኛው የቆዳችን ቀለም ለመመለስ ሳምንታትን/ወራትን ሊወስድ ይችላል

👉 ቋቁቻ ከሰው ወደሰው ይተላለፋል?
ቋቁቻ ከሰው ወደሰው አይተላለፍም

ለቋቁቻ መንስኤ የሆኑት የፈንገስ አይነቶች(በጥቅሉ Malassezia ተብለው ይጠራሉ) ከቆዳችን ጋር ተስማምተው የሚኖሩ (normal flora) ሲሆኑ ለህመሙ የሚያጋልጡን ሁኔታዎች ሲፈጠሩ ወደ በሽታ አምጪነት የሚቀየሩ ናቸው፤ለዚህም ነው ህመሙ ደጋግሞ የሚከሰትብን

👉እንዴት እንከላከለው?

ቋቁቻ ደጋግሞ የሚከሰትብን ከሆነ እና በተለይም በሞቃታማ አካባቢ የምንኖር ከሆነ ከቆዳ ሐኪም ጋር በመመካከር ህክምናውን በሳምንት ወይም በሁለት ሳምንት ወይም በወር አንድ ጊዜ ለተወሰኑ ወራቶች በመውሰድ ቋቁቻ የሚመላላስበትን የጊዜ ፍጥነት መቀነስ ይቻላል

በተጨማሪም፡-

Oily የሆኑ ቅባቶችን አለመጠቀም

ከጥጥ የተሰሩ ልብሶችን መልበስ(በተለይ ከውስጥ የምንለብሳቸው)

ሰውነታችን ላይ የሚጣበቁ ልብሶችን አለማዘውተር

✔️ በመጨረሻም
ከቆዳ ሐኪም ውጪ የተሰሩ ቪድዮችን አይተን ወይም የቆዳ ሐኪም ሳናማክር መድሀኒቶችን ገዝተን ባለመጠቀም ቆዳችንን ከተጨማሪ ጉዳት እንከላከል‼️

ዶ/ር ዮሐንስ ታደሰ ፤ የቆዳና አባላዘር ህክምና ስፔሻሊስት
በሆሳዕና ከተማና አካባቢው የቆዳ ህክምናና ምክር ሲፈልጉ - 0929296463

07/05/2022

ብጉር | Acne vulgaris

◈ ብጉር በአብዛኞቻችን ዘንድ የሚታወቅ፤ ወዝ አመንጪ እጢዎች ተከማችተው በሚገኙባቸው የአካል ክፍሎች ላይ (ፊት ፣ ደረት ፣ የላይኛው የጀርባ ክፍል) የሚወጣ የቆዳ ህመም አይነት ነው።

◈ ብጉር ከጨቅላ ህጻናት ጀምሮ የሚከሰት ቢሆንም በአብዛኛው ከ12-25 የእድሜ ክልል ውስጥ በሚገኙ ወጣቶች ላይ ይታያል።

◈ ብጉር አብዛኛውን ጊዜ ወንዶች ላይ የሚከሰት ሲሆን ከወጣትነት የእድሜ ክልል በኋላ (30 እና 40ዎቹ) የሚከሰተው የብጉር አይነት ግን በብዛት ሴቶች ላይ ይታያል።

➡ ለብጉር መከሰት አራት መሰረታዊ ሁኔታዎች ምክንያት ናቸው

1- Follicular hyperkeratinization; ይህም የሞቱ ህዋሳት ተጠራቅመው የወዝ መተላለፊያ ቱቦ እንዲዘጋ ያደርጋል

2-የወዝ በብዛት መመረት (increased sebum production)

3-Propionibacterium acne የሚባለው የባክቴሪያ አይነት

4-ብግነት (Inflammation)

➡ ብጉርን እና ብጉር መሰል ሽፍታዎችን (Acneiform eruption) የሚያባብሱ ነገሮች

👉ጭንቀት (stress)
👉ከመጠን ያለፈ ውፍረት
👉በወር አበባ አካባቢ
👉የሚዋጡም ሆነ የሚቀቡ መድሀኒቶች (steroids, phenytoin...)
👉በስራ ሁኔታ የሚያጋጥሙ ኬሚካሎች

👉በቆዳችን ላይ በሚከሰተ መፈጋፈግ (friction) ወይም ጫና (pressure) ፤ ለምሳሌ በህመም ሆነ በሌላ ምክንያት ለረጅም ግዜ በጀርባው የሚተኛ ሰው ጀርባው ላይ ብጉር ሊወጣ ይችላል ወይም የጡት ማስያዣ ገመድ የሚያርፍባቸው ቦታዎች ላይ ሊወጣ ይችላል
👉 ለረዥም ሰአት የፊት ማስክ ማድረግ
👉በውስጣቸው comedogenic ingredients የያዙ የፊትና የጸጉር ቅባቶች

➡ ብጉር እንዴት ይታከማል?

✔️ ብጉር በአብዛኛው ከእድሜ ጋር ተያይዞ የሚመጣ የቆዳ ህመም በመሆኑ በራሱ የሚጠፋውም ከእድሜ ጋር ተያይዞ ነው ፤ ስለዚህም ምልክቶቹን መቆጣጠር እንጅ በህክምና ማዳን (በአንድ ህክምና እስከ መጨረሻው እንዳይመጣ ማድረግ) አይቻልም።

በዚህም ምክንያት የብጉር ህክምና ወራትን የሚፈጅ በመሆኑ ታካሚዎች ከቆዳ ሐኪማቸው ጋር እየተመካከሩ ህክምናውን መከታተል ይኖርባቸዋል።

✔️ እዚህ ጋር ብጉር በራሱ ጊዜውን ጠብቆ የሚጠፋ ከሆን መታከም ለምን ያስፈልጋል የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል ፤ብጉር ከሚያሳድረው የስነ-ልቦና ጫና በተጨማሪ ሳይታከም በቆየ ቁጥር ፊታችን ላይ ጠባሳ የመፍጠር እድሉ የሰፋ ስለሆነ በጊዜ መታከሙ ይመከራል።

✔️ የብጉር ህክምና እንደ ጥንካሬው መጠን በሚቀባ ፣ በሚቀባና በሚዋጥ ወይም በሚዋጥ መድሀኒት ሊታከም ይችላል

✔️ ከዋናው ህክምና በተጨማሪ በውስጣቸው Salicylic acid, Benzyle peroxide የያዙ መታጠቢያ ሳሙናዎች መጠቀም ያስፈልጋል

➡ ከህክምናው በተጨማሪ ማድረግ የሚጠበቅብን

👉እንቅስቃሴ ማድረግ (ጭንቀት ለመቀነስ ይረዳል)
👉ብጉሮቹን ለማፍረጥ አለመሞከር (ጠባሳ እንዲፈጠር ስለሚያደርግ)
👉ለቆዳ ጤና መጠበቂያም ሆነ ለውበት የምንጠቀማቸው ምርቶች Oil-free & non-comedogenic መሆናቸውን ማረጋገጥ
👉ፀሐይ መከላከያ (sun-screen) መጠቀም (መጠቀም ያለብን የፀሐይ መከላከያ እንደ ቆዳችን አይነት ስለሚለያይ የቆዳ ሐኪም ያማክሩ)
👉ቆዳችን ላይ ጫና (pressure) የሚፈጥሩ ነገሮችን (helmets, ስልክ, የቦርሳ/የጡት ማስያዣ ገመድ, የፊት ማስክ) መቀነስ
👉ሰውነታችንን ካላበን መታጠብ

✔️ በመጨረሻም ከቆዳ ሐኪም ውጪ የተሰሩ ቪድዮችን አይተን ወይም የቆዳ ሐኪ

02/05/2022

🤰የማስታወስ ችሎታችንን ከፍ ሊያደርጉልን የሚችሉ የምግብ አይነቶች

አሳ፦ አሳ በውስጥ ለአእምሮ ጤና ጠቃሚ የሆነውን ኦሜጋ 3 /omega 3/ በመያዙ ለአእምሮ ጤና ጠቃሚ ነው።

እንዲሁም በአሳ ውስጥ የሚገኘው ኦሜጋ 3 የአእምሯችንን ሴሎች ከጉዳት ይከላከላል።
ስለዚህም አሳን አዘውትረን በመመገብ የአእምሯችንን ጤንነት በመጠበቅ የማስታወስ ችሎታችን ከፍ እንዲል ያደርጋል።
ለውዝ፦ ለውዝ ለአእምሯችን ጤንነት ጠቃሚ በሆኑ ኝጥረ ነገሮች የበለጸገ በመሆኑ የማስታወስ ችሎታችንን ከፍ ሊያደረጉልን ይችላሉ ከሚባሉ የምግብ አይነቶች ይመደባል።
በተጨማሪም ለውዝ በውስጡ ለአእምሮ ነርቭ ጤንነት ጠቃሚ የሚባሉትን እንደ ቪታሚን ሲ እና ቪታሚን B6 አይነት ንጥረ ነገሮች የበለጸገ በመሆኑም የማሳታወስ ችሎታችንን ከፍ ያደርጋል ተብሏል።
አቮካዶ፦ በአቮካዶ ውስጥ የሚገኙት የፋቲ አሲድ ቅባቶች አእምሯችን ንቁ እና ጤነኛ እንሆን በማድረግ ከፍ ያለ የማስታወስ ችሎታ እንዲኖረን ይረዳሉ።
ቀይ ሽንኩርት፦ ሻል ያለ የማስታወስ ችሎታ እንዲኖረን ከፈለግን በምጋባችን ውስጥ በርከት ያለ ሽንኩትር ጨምሮ መመገብ ይመከራል ምክንያቱ ደግሞ ሽንኩርት በውስጥ በያዘው አንቲኦክሲዳንት ንጥረነገር አእምሯችንን ከጉዳት ስለሚከላከል ነው።
አፕል፦ አፕል ወይም ፖም በውስጡ ኩዌርስቲን የተባለ አንቲ ኦክሲዳንት ንጥረ ነገር የበለጸገ በመሆኑ አእምሮን ከጉዳት በመከላከል የማስታወስ ችሎታችን እንዲጨምር ያደርጋል።
ቀይ ስር፦ ቀይ ስር በአይረን የበለጸገ በመሆኑ ደማችን በቂ ሄሞግሎቢን እንዲያገኝ በማድረግ አእምሯችን በቂ ኦክሲጅን አግኝቶ ጤነኛ እንዲሆን በማደረግ ለማስታወስ ችሎታችን መጨመር አይነተኛ ሚና አለው።
ማር፦ ማር በተፈጠሮ ሀይል ሰጪ ምግብ በመሆኑ አዘውትረን የምንወስድ ከሆነ የአእምሯችንን የማሳታወስ አቅም ከፍ እንዲል ያግዛል።
ውሃ፦ ውሃን አዘውትሮ መጠጣት ለአእምሯችን ጤንነት እና የማስታወስ ችሎታን ከፍ በማድረግ ረገድ ያለው ሚና ከፍተኛ በመሆኑን ውሃን አዘውተረን መጣጣት ይመከራል።

29/04/2022

መጥፎ የአፍ ጠረን መከላከያ ዘዴዎች፡፡
~©~©~~~
መጥፎ የአፍ ጠረን መከላከያዎችን እና መወሰድ ስላለባቸው መፍትሄዎች ፦
1. የአፍን ፣ የድድ፣ የምላስን እና የጥርስን ንጽህና መጠበቅ ፤ በንጽህና መያዝ፡፡ ጥርስን ቢያንስ በቀን ሁለት ጊዜ ከምግብ በኋላ በቡርሽ
ማጽዳት/ መፋቅ ያስፈልጋል፡፡
2. የተቦረቦረ የጥርስ አካል ካለ የተቦረቦረውን ጥርስ አካል ማሥሞላት ። ምክንያቱም የተቦረቦረ ጥርስ በውሥጡ ጥቃቅን ተህዋሲያኖችን (ባክቴሪያዎችን) በውሥጡ ደብቆ ያሥቀምጣል። እነዚህ ተዋህሲያኖች በአፍ ውሥጥ የሚቀሩትን የምግብን ትርፍራፊዎች በመመገብ የምግቡን ይዘት ወደ ተለያዪ ተረፈ ምርት (ingredient) ይቀዪሩታል። ከሚመረቱት ነገሮች መካከል አንዱ የሰልፈር ይዘት ጋዝ አንዱ ነው። ይህ ጋዝ ከምንተነፍሰው አይር ጋር በመቀላቀል እና በመውጣት መጥፎ የአፍ ጠረን ያሥከትላል። በመሆኑም የተቦረቦረ ጥርስ አካል ካለ ወደ ሀኪም ሂዶ መታከም ፥ ማስሞላት ያሥፈልጋል፡፡
3. በቡርሽ የማይፀዳ የቆሸሸ ጥርስ አካል ካለ ወደ ሀኪም ቤት ሄዶ በማሽን ማሳጠብ፡፡
4. የቆሰለ የድድ ፥ የከንፈር ፣ የምላስ አካል ካለ (Necrotizing ulcerative tissue ) ወደ ሀኪም ቤት ሄዶ መታከም፡፡
5. የአትክልት ፣ የፍራፍሬ ፣ የአዝርዕትና የጥራጥሬ ምግቦችን መመገብ ማዘውተር፡፡
6. በአፍ ውስጥ የአክታ (የምራቅ) መድረቅ ካለ በቂ ፈሳሽ መጠጦችን በመውሰድ ችግሩን መቅረፍ፡፡
7. የጉሮሮ ፣ የላንቃ ፣ የላይኛው የሳንባ ክፍል ብግነት/inflammation/ ፣ ቁስለት (ulcerative) ካለ ወደ ሀኪም ቤት ሄዶ በመታከም ማዳን፡፡
8. የቫይታሚን "ቢ" ፥ "ሲ" ይዘት ያላቸውን ምግቦችን መመገብ፡፡
9. የጉሮሮን አካባቢ የምራቅ መወፈር እና በጉሮሮ አካባቢ የመጠራቀም ሁኔታ ካለ በንጹህ ውሃ በማፍለቅለቅ መጉጠመጥ/Gargling of pharynex with water/። ችግሩ የማይቃለል ከሆነ ወደ ሀኪም ቤት ሄዶ ከሀኪም ጋር በማማከር የጉሮሮን አካባቢ በመድሃኒት በማፍለቅለቅ መጉመጥመጥ ይቻላል፡፡
10. ገና በመብቀል ላይ ያለን ጥርስ፤ ጥርሱ በሚበቅልቀት ጊዜ ብዙ ጊዜ በአካባቢው ወይም በዙሪያው ያለው ድድ የመቁሰል ሁኔታ ሥለሚኖረው፣ የጥርሱን ንጽህና መንከባከብ፤ ህመም ካለው ወደ ሀኪም ቤት ሄዶ መታከም ፣
11. የድድ መድማት ችግር ካለ ወደ ሀኪም ቤት ሄዶ መታከም፡፡
12. አንዳንድ ሰዎች ወትት እንዲሁም የወተት ይዘት ያላቸውን ምግቦች በሚመገቡበት ወቅት የማይሥማማቸው ከሆነ (Lactos intolerance or milk intolerance) ካለ ወደ ሀኪም ቤት ሄድ መታከም።
በአጠቃላይ መጥፎ አፍ ጠረንን ችግር ለማስወገድ ወደ ሀኪም ጋ ሄዶ ሀኪም በማማከር ችግሩን መቅረፍ ይቻላል፡፡
በዶ/ር አዱኛዉ

Address

ALEM BANK
Addis Ababa

Telephone

+251901057578

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ዲቦራ ክሊኒክ፤Dibora Clinic posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram