ዶ/ር ብሩክ ስፖርት ህክምናና ቴራፒ 40 ምንጭ Dr. Biruk Sports Medicine & Therapy 40 Minch

  • Home
  • Ethiopia
  • Arba Minch'
  • ዶ/ር ብሩክ ስፖርት ህክምናና ቴራፒ 40 ምንጭ Dr. Biruk Sports Medicine & Therapy 40 Minch

ዶ/ር ብሩክ ስፖርት ህክምናና ቴራፒ 40 ምንጭ Dr. Biruk Sports Medicine & Therapy 40 Minch Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ዶ/ር ብሩክ ስፖርት ህክምናና ቴራፒ 40 ምንጭ Dr. Biruk Sports Medicine & Therapy 40 Minch, Physical therapist, Arba Minch'.

16/09/2023
12/09/2023

🌻🌻🌻እንኳን ለአዲሱ 🌻🌻🌻አመት በሰላም 🌻🌻🌻አደረሳችሁ🎄🌼🌼🌼🌼🌻🌻🌻🌻 2016🌻🌻🌼🌼🌼 🌼የሰላም🌾🌾 የጤና የደስታ የስኬት ዘመን ይሁን ልዎት መልካም 🌻🌻አዲሰ ዓመት🎄🎄💚💛❤️💚💛❤️

Dr. Biruk Sport Medicine and Therapy Center
17/08/2023

Dr. Biruk Sport Medicine and Therapy Center

★★★★★ · Fysioterapiklinik

የሎሚ ልጣጭ የማንጥልባቸው 9 ምክንያቶች በርግጥ የሎሚ ልጣጭ መራራ ነው። ከመራራንቱ ጀርባ ግን የጤና ጠቀሜታው ላቅ ያለነው ። እናም እርግጠኞች ነን እነዚህን የጤና ምክሮች ካነበቡ በኃላ ሎ...
21/07/2023

የሎሚ ልጣጭ የማንጥልባቸው 9 ምክንያቶች
በርግጥ የሎሚ ልጣጭ መራራ ነው። ከመራራንቱ ጀርባ ግን የጤና ጠቀሜታው ላቅ ያለነው ። እናም እርግጠኞች ነን እነዚህን የጤና ምክሮች ካነበቡ በኃላ ሎሚን ከነልጣጩ ቅርጥፍጥፍ አድርገው እንደሚበሉት።

1. ከፍተኛ የምግብ ንጥረ ነገርን ይዟል፦ ካሎሪን፣ፋይበር፣ ፕሮቲን፣ቅባት፣ ቫይታሚን ሲ ከብዙዎቹ ጥቂቶቹ ናቸው።

2. የአፍ ጤናን ይጠብቃል፦ የጥርስና የድድ ኢንፌክሽን ዋና መንስሔ የሆነውን Streptococcus mutans የተስኘውን ባክቴሪያ ይዋጋል።

3. ከፍተኛ ጸር- ወክሳጅ (Antioxidant) በመሆኑ ሴሎቻችንን የሚጎዱ መርዛማ ነገሮችን ከሰውነታችን ያስወግዳል።

4. የጸረ- ተዋህሲያንና የጸረ- ፈንገስ ንጥረ ንገሮችን በውስጡ ይዟል።

5. የተፈጥሮ የበሽታ የመከላከል አቅማችንን ያሳድጋል።

6. የልብን ጤና ይጠብቃል።

7. ጸረ-ካንሰር ንጥረ ነገሮች በውስጡ በመያዙ በርካታ ካንሰር አምጪ ምክንያቶችን ይፋለማል።

8. የአሞት ጠጠር ህመምን ያክማል።

9. ለቆዳ ውበት ወሳኝ ነው። ልጣጩ ደርቆና ተፍጭቶ ከሩዝ ዱቂትና ከቀዝቃዛ ወተት ጋር ተቀላቅሎ ቆዳዎን ቢቀቡት በአጭር ጊዜ ውስጥ ቆዳዎ ውብ ይሆናል።

21/07/2023

ኩላሊቶን የሚጎዱ 18 ነገሮች

1. ቀይ ስጋ
2. የአልኮል መጠጥ
3. የገበታ ጨው
4. ካፊን- በሻይ፣በቡና፣በኮካኮላና በቸኮሌት ውስጥ የሚገኝ
5. ሰው ሰራሽ ማጣፈጫዎች
6. የወተት ተዋፆዎች
7. ካርቦኔትድ መጠጦች /ጋዝ ያላቸው መጠጦች
8. ሲጋራ ማጨስ
9. በዘረ-መል የተዘጋጁ ምግቦች
10. ብዙ ፈሳሽ መወሰድ
11. ከፍተኛ ፖታስየም ያላቸውን አትክልት አዘውትሮ መመገብ/ስኳር ድንች፣ነጭ ቦለቄ ናቡናማ እንጉዳይ የመሳሰሉት
12. ከመጠን በላይ የህመም ማሳታገሻ እንክብሎችን መውሰድ
13. የሰርዲን አሳ
14. እስፒናች
15. የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አለመስራት
16. የኩላሊት ኢንፌክሽን ሲያጋጥም ተከታትሎ ብቂ ሕክምና አለማድረግ
17. ብቂ እንቅልፍ አለማግኘት
18. ሽንት መቋጠር

የጀርባ ሕመም (Back pain)ዕድሜያቸው ከ30-40 ዓመት የሆኑ ሰዎች የሐኪም ፊት እንዲያዩ ከሚያስገድዳቸው ወይም ስራ ከሚቀሩባቸው ምክንያቶች አንዱ የጀርባ ሕመም ነው፡፡ በዚህ ዕድሜ የጀ...
21/07/2023

የጀርባ ሕመም (Back pain)

ዕድሜያቸው ከ30-40 ዓመት የሆኑ ሰዎች የሐኪም ፊት እንዲያዩ ከሚያስገድዳቸው ወይም ስራ ከሚቀሩባቸው ምክንያቶች አንዱ የጀርባ ሕመም ነው፡፡ በዚህ ዕድሜ የጀርባ ሕመም የተለመደ አለም አቀፍ የጤና ችግር ከመሆኑም በተጨማሪ ለአካል ጉዳት ከሚዳርጉ ምክንያቶች መካከል አንዱም ነው፡፡ ሌላው አስደንጋጭ መረጃ ብዙ ሰዎች በዕድሜ ዘመናቸው ቢያንስ አንዴ በጀርባ ሕመም መጠቃታቸው ነው፡፡ ይሁንና እንደመታደል ሆኖ የጀርባ ሕመምን ለመከላከለም ሆነ ሕመሙ ሲያጋጥም በፍጥነት ከሕመሙ ለመውጣት የሚያስችሉ የቤት ውስጥ ሕክምናዎችን ጨምሮ የአኗኗር ዘይቤን ማስተካከል በሳምንት ውስጥ ፈውስን የሚያስገኝ ቢሆንም ሕመሙ በወራት የዘለቀ እንደሆነ ግን ችግሩ ከበድ ያለና የተለያዩ የጤና ችግሮች ውጤትም ሊሆን ይችላል፡፡

በተደጋጋሚ ለጀርባ ሕመም የሚያጋልጡ ምክንያቶች
1. የጡንቻ ወይም የሊጋሜንቶች ውጥረት
2. ድንገተኛ የጡንቻ መኮማተር
3. የጡንቻ መሳሳብ ወይም ውጥረት
4. የዲስክ መጎዳት
5. አደጋዎች (ስብራት ወይም መውደቅ)
6. እርግዝና
7. በዕድሜ መግፋት
8. ከፍተኛ የሰውነት ክብደት
9. የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አለማድረግ
10. ሲጋራ ማጨስ
11. ካንሰርና የአንጓ ብግነት
12. የኩላሊት ጠጠር ወይም ኢንፌክሽን
13. ድባቴና ጭንቀት እንዲሁም የህብለ ሰረሰር በቀላሉ መሳሳብና ቀዳዳ መፍጠር ናቸው፡፡

የጀርባ ሕመም አባባሽ ምክንያቶች
1. ያለ አግባቡ ዕቃዎችን ማነሳት (ተጠማዞ፣ተንጠራርቶ እና ወገባችንን እና እግራችንን ወጥሮ ማንሳት)
2. ከባድ ነገሮችን ያለ አግባቡ ማንሳት
3. ድንገተኛና የማይመች እንቅስቃሴ ማድረግ
4. ረጅም ጊዜ መቆም ወይም መቀመጥ
5. ረጅም ሰዓት ያለ እረፍት መንዳት
6. ወገባችንን ከመቀመጫ መደገፊያ ጋር ለጥፎ ከመቀመጥ ይልቅ ጎብጦ መቀመጥ ናቸው፡፡

የጀርባ ሕመም መኖሩን የሚጠቁሙ ምልክቶች
1 .የጡንቻ ሕመም
2. ጀርባችንን የመውጋት ስሜት
3. ሕመሙ ወደ እግራችን የዘለቀ እንደሆነ
4. በሚያጎነብሱበት፣ዕቃ በሚያነሱበት፣በሚቆሙበትና በሚራመዱበት ጊዜ ሕመም መሰማት
5. ጋደም በምንልበት ጊዜ የሕመም ሁኔታ መሻሻል ናቸው፡፡

ኮረሪማና የጤና በረከቱ  ውልደቱ ሕንድ ነው፡፡ ሳይንሳዊ ስያሜው Elettaria ይባላል፡፡ በእንግሊዘኛ Cardamon ወይም Cardamom በመባል ይጠራል ኮረሪማ፡፡ በዓለም ላይ እጅግ ውድ ...
13/07/2023

ኮረሪማና የጤና በረከቱ

ውልደቱ ሕንድ ነው፡፡ ሳይንሳዊ ስያሜው Elettaria ይባላል፡፡ በእንግሊዘኛ Cardamon ወይም Cardamom በመባል ይጠራል ኮረሪማ፡፡ በዓለም ላይ እጅግ ውድ ከሚባሉ እና መልካም ማዕዛ ወይም ጣዕም ካላቸው ቅመሞች አንዱ ነው፡፡ ለብዙ መቶ ዓመታት በባህላዊ ሕክምና ውስጥ ትልቅ ድርሻ ነበረው፡፡ በአገራችንም ከቂቤ ማንጠሪያነት አንስቶ ኮረሪማ ለብዙ ምግቦች ማጣፈጫነት እንጠቀመዋለን፡፡ ይህ ቅመም ከምግብ ማጣፈጫነት በዘለለ በሳይንስ የተረጋገጡ ከፍተኛ የሆኑ የጤና ጥቅሞች እንዳሉት ይነገራል፡፡

1. ካንሰርን ለመካለከል ይረዳል፡- ይህ ትንግርታዊ ቅመም በውስጡ በያዘው አንቲ -ኦክሲደንት ወይም ፀረ-ወክሳጅ ኬሚካላዊ ንጥረነገር የተነሳ የካንሰር መነሾ ሕዋሳትን በመዋጋት ይገታል፡፡

2. የደም ግፊትን ይቀንሳል፡- በልባችንና በሌሎች የሰውነታችን አካላት ዙሪያ ያሉ ውሃዎችን በሽንት መልክ በማስወገድ የደም ግፊት መጠንን በእጅጉ ይቀንሳል፡፡

3. የሰውነት መመረዝን ይከላከላል፡- ሰውነታችን የሚመረዘው ለበአድ ነገሮች ሲጋለጥ ነው ኮረሪማ ደግሞ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ኢንፍላሜሽን ወይም መመረዝ ወይም ብግነትን በመከላከል ሰውነታችን ለዘላቂ በሽታዎች እንዳይጋለጥ ይከላከላል፡፡

4. የጥርስ የጤና እክሎችን ያስወግዳል፡-የጥርስ ኢንፌክሽኖችን ጨምሮ በአፍ ውስጥ የሚፈጠርን መጥፎ የአፍ ጠረን በያዘው ንጥረ ነገር ጋሻነት ያባርራል፡፡ ባይገርማችሁ ብዙዎቹ ማስቲካዎች ሲመረቱ ለጣዕማቸው ኮረሪማን በግብዓትነት ሳይቀር ይጠቀሙታል፡፡

5. ትንፈሳንናየኦክስጂን አጠቃቀምን ያሳድጋል፡- በኮረሪማ ውስጥ ያለው ንጥረ ነገር ወደ ሳንባችን የሚገባው አየር እንዲጨምርና አተነፋፈሳችን እንዲሻሻል ያደርጋል፡፡

6. ኮረሪማ የጉበትን ጤንነት ለመከላከል፣ የጭንቀት ባህሪያትን ለመቀነስ፣ ክብደት ለመቀነስ፣ ለማቅለሽለሽና ለትውኪያ መፍትሔ ይሰጣል፡፡

7. ፀጉርን የመጠገን ሕክምና ይሰጣል፡- ኮረሪማ አብዝቶ በዕለት ገበታ ውስጥ መመገብ የፀጉር መርገፍና መንጣት ችግርን ከማስወገድ ባሻገር ለፀጉራችን መብዛትና ርዘመት ከፍተኛ አስተዋፆ ያደርጋል፡፡

8. ባክቴሪያ ያወድማል፡-ጥናቶች እንዳረጋገጡት ኮረሪማ 14 የሚደርሱ የተለያዩ ባክቴሪያዎችን ያወድማል፡፡ ኮረሪማ አዘውትረው የሚመገቡ ሰዎች የተፈጥሮ በሽታ የመከላከል አቅማቸው ከመጨመሩ ባሻገር ሰውነታቸው ባክቴሪያ እንዲከላከል ረድቷቸዋል፡፡

9. ከቆዳ አለርጂ ይጠብቃል፡- ኮረሪማ ፀረ ባክቴሪያ ንጥረነገር በውስጡ ስለያዘ ለቆዳ አለርጂ፣ ለቆዳ መሸብሸብና በቆዳ ላይ ለሚወጡ ጥቋቁር ነጠብጣቦች መፍትሔ የሚሰጥ ሲሆን በተለይ በሞቃታማ አካባቢዎች ስትሮክ የተሰኘውም በአንጎል ደም ቧንቧ ጥበት የሚከሰትን የደም ግፊት ይከላከላል፡፡

ማሳሰቢያ፡-

ኮረሪማን በአነስተኛ መጠን መጠቀም ተገቢ ሲሆን ብዛት ያለው መጠን በምግብ ውስጥ ጨምሮ መጠቀም ግን የጨጓራ መቆጣትና የጨጓራ ቁስለት ሊያስከትል ይችላል፡፡ ስለሆነም ጥንቃቄ ያሻል፡፡

የዘቢብ የጤና በርካታ በረከቶች እንሆየደረቁ ፍራፍሬዎች ጥቅሞች አባቶቻችን ከጥንት ዘመን ጀምሮ በስፋት ይጠቀሙባቸው ነበር ፡፡ ከነዚህ መካከል ዘቢብ ከፍተኛ መጠን ያለው ንጥረ ነገር እና ቫይ...
08/07/2023

የዘቢብ የጤና በርካታ በረከቶች እንሆ

የደረቁ ፍራፍሬዎች ጥቅሞች አባቶቻችን ከጥንት ዘመን ጀምሮ በስፋት ይጠቀሙባቸው ነበር ፡፡ ከነዚህ መካከል ዘቢብ ከፍተኛ መጠን ያለው ንጥረ ነገር እና ቫይታሚኖችእንዳሉት ይታመናል።
ዘቢብ በእራሳቸው አነስተኛ ቁጥር ያላቸውን ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችን ከሆኑት ውስጥ-በፖታስየም ፣ በማግኒዥየም እና በብረት የበልጻገ ነው ። እንዲሁም የደረቁ ወይኖች የፀረ-ሙቀት አማቂ ናቸው ፡፡ ተስማሚ ባህሪዎች ቢኖሩም ዘቢብ “ለማድረቅ” ሂደት ትኩረት መስጠቱ አስፈላጊ ነው ፡፡ ለምሳሌ ፣ ነጭ ዘቢብ ወርቃማ ቀለሙን የሚይዘው እንደ ሰልፈር ዳይኦክሳይድ ባሉ ተጠባባቂዎች ብቻ ነው ፡፡
ጥቂት ዘቢብ ወደ 120 kcal ያህል ይይዛል ነገር ግን ለረጅም ጊዜ አይጠግብም ነገር ግን ለአጭር ጊዜ ኃይል ይሰጣል ፡፡

እንደ ፈጣን የኃይል ምንጭ ዘቢብ ከፈተና ፣ ከውድድር ፣ ከአካል ብቃት እንቅስቃሴ ወይም ከረጅም የእግር ጉዞ በፊት መመገብ ምቹ ሁኔታን ያመጣል። በመሆኑም ዘቢብ መመገብ የሚከትሉትን የጤና ጠቀሜታዎች ይሰጣል
1. የደም ግፊትን ይቀንሳል
2. ካንሰርን ይከላካላል
3. የደም ስኳር መጠንን ይቆጣጠራል
4. ልቆዳ ጤንነት
5. ነርቫችንን ያነቃቃል
6. ሃይል ያላብሰናል
7. የደረት ህመምን ይቀንሳል
8. የጥርስ መበስበስን ይቀንሳል
9. የማስታወስ ችሎታችን ያዳብራል
10. ከስውነታችን ውስጥ መርዛማና ዩሪያ እንዲወገድ ይረዳል
ይሞክሩት!

ጤና አዳም (Arugula)ውልደቱ አውሮፓ ባልካን አካባቢ ነው፡፡ ሳይንሳዊ ስያሜው አሩጉላ (Arugula) ይሰኛል፡፡ፀረ- ባክቴሪያ፣ፀረ-ፈንገስ፣ፀረ- መርዝማ እና ፀረ- ውክሳጅ ተግባራትን ያ...
06/07/2023

ጤና አዳም (Arugula)
ውልደቱ አውሮፓ ባልካን አካባቢ ነው፡፡ ሳይንሳዊ ስያሜው አሩጉላ (Arugula) ይሰኛል፡፡ፀረ- ባክቴሪያ፣ፀረ-ፈንገስ፣ፀረ- መርዝማ እና ፀረ- ውክሳጅ ተግባራትን ያከናውናል፡፡ በአውሮፓ የባህል ሕክምና ውስጥ ገናና ስም አለው፡፡ ዛሬም ቢሆን በአውሮፓ ባህላዊ ሕክምና ውስጥ በስፋት ጥቅም ላይ ይውላል፡፡ በአገራችንም ቢሆን ለሰው ልጅ ጤና የሚሰጠውን ፈውስ በመመልከት ጤና- አዳም የሚል ስያሜን አትርፎለታል፡፡ በሻይ፣ በቡና፣ በወተት፣ ተወቅጦ በውሃ ተብጥብጦ ይጠጣል፡፡ጤና አዳም ለውጥ ማጣፈጫ በመሆን በሽሮና በበርበሬ ውስጥ ሳይቀር በመግባት ይታወቃል፡፡ምግብ ጣዕሙን ጠብቆ እንዲቆይም የማድረግ ብቃት አለው፡፡ ለአብነት አይብን ማንሳት እንችላለን፡፡ ዛሬ ስለዚህ ታአምረኛ ተክል ሳይንስ ያረጋገጣቸውን የጤና በረከቶች እናጋራችሁአለን፡፡
1. የተመገባችሁት ምግብ አልስማማ ካላችሁ፣ በጋዝ(አየር) ምክንያት ሆዳችሁን የሚነፋ፣ቁርጠት ካጋጠማችሁ ምናልባትም ትውከትና ተቅማት በምግብ መመረዝ ምክንያት ካጋጠማችሁ ጤና አዳም እርጥቡን በውሃ ጨምቃችሁ ጠጡ፡፡ ከቻላችሁ የተወሰነ ቅንጣቢ አኝካችሁ በውሃ አወራርዱት ውጤቱን በፍጥነት ታዩታላችሁ፡፡ ምክንያቱም ጤና አዳም ባክቴሪያዎችን በመግደል አኩሪ ገድል አለውና፡፡
2. የቆዳና የእግር ፈንገስ ያስቸግራችኋል፡፡ ዘመናዊ መድኃኒት በመፈለግ ጊዜና ገንዘብዎን አያባክኑ፡፡በቀላሉ ጤና አዳሙን ይውቀጡና እግሮን ቀብተው ያሳድሩት መፍትሔውን ያገኙታል፡፡
3. የጡንቻና የአጥንት መገጣጠሚያ ሕመም ካለብዎት በየዕለቱ ለተወሰኑ ወራት ጠዋት ጠዋት ጤና አዳም ጨምቀው በውሃ ይጠጡ ለችግሮ መፍትሔ በቅፅበት ያገኛሉ፡፡
4. ሴቶች በተለይ ከወር አበባ መምጣት ጋር በተያያዘ ለሚከሰት የጠለመደ የሆድ ቁርጠት ለብ ያለ ውሃ ከጤና አዳም ጭማቂ ጋር ብትጠጡ ቁርጠት ደና ሰንብት ይሉታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ አእምሮችሁንና በአጠቃላይ የነርቭ ስርዓታችሁን ዘና የማድረግ ብቃት አለው፡፡
5. ጤና አዳም ጎጂ ነፍሳትን የማባረርና የመግደል ልዩ ብቃት አለው፡፡ ስለሆነም ቢንቢን፣በረሮ፣የወባ ትንኝና፣ዝምብ የመሳሰሉትን ከቤትዎ የማባረር ችሎታ ስላለው ጤና አዳሙን ወቅጦ በውሃ በጥብጦ በመርጨት በሽታ አምጪ ነፍሳትን በቀላሉ መከላከል ይችላሉ፡፡
6. ጤና አዳም በውስጡ በያዘው ፀረ- መርዛማ ንጥረነገርና ፀረ-ባክቴሪያ በፊቶ ቆዳ ላይ የሚገኙ የሞቱ ሕዋሳትን በማስወገድ የፊት መጨማደድና የለጊዜ ማርጀትን ይከላከላል፡፡ ወቅጠው ፊትዎን ማታ ተቀብተው ጠዋት ለብ ባለ ውሃ ቢታጠቡት ልዩነቱን ያገኙታል፡፡
7. ከፍተኛ የቫይታሚን ሲ ንጥነገር የየያዘ በመሆኑ የተፈጥሮ የበሸታ አቅማችንን በማጎልበት በበሽታ በቀላሉ እንዳንጠቃ ይረዳናል፡፡ ስለሆነም ጠዋት በባዶ ሆድዎ በውሃ ውስጥ የተወሰነ ጭማቂ ጤና አዳም የመጠጣት ልምድ ያዳብሩ፡፡
8. ጤና አዳምን በሻይ ፣በቡና፣በውሃ ወይም እንዲሁ አኝከው የሚወጡ ሴቶች የወር አበባ ሑደታቸው ጤናማ ይሆናል፡፡ የተዛባም ከሆነ እንዲስተካከል ያደርጋል፡፡
9. በእንቅልፍ እጦት ለምትቸገሩ መልካም ዜና አለው ጤና አዳም፤ ብቻ እንናተ አዝውትራችሁ ተመገቡት ሰላማዊ እንቅልፍ እሱ ይቸራችኋል፡፡
10. ለደም ግፊት ጤና አዳም ወሳኝ መድኃኒት ነው፡፡ የደም ፍሰትን ያሻሽላል፣ደም ቧንቧ ጥበት ያሰፋል፡፡ በአጠቃላይ የልብ ጤናን ይጠብቃል፡፡
11. ጤና አዳም በአስም፣በሽንት ፊኛ ኢንፊክሽን ለሚሰቃዩ ሰዎችም ትልቅ መፍትሔ እንደሆነ በሳይንስ ተረጋግጧል፡፡

ጦስኝ (Thyme) የደም ግፊት ጠላትከአራት መቶ በላይ ዝርያ ያለው ጦስኝ በጥንት ግብፃዊያን ሰዎች ከሞቱ በኃላ በድናቸው ሳይበሰብስ ረጅም ዓመታት ለማቆየት ይጠቀሙበት የነበረ የቅመም ዘር ነ...
01/07/2023

ጦስኝ (Thyme) የደም ግፊት ጠላት

ከአራት መቶ በላይ ዝርያ ያለው ጦስኝ በጥንት ግብፃዊያን ሰዎች ከሞቱ በኃላ በድናቸው ሳይበሰብስ ረጅም ዓመታት ለማቆየት ይጠቀሙበት የነበረ የቅመም ዘር ነው፡፡ ግሪኮችም ቢሆኑ በጥሩ ማዕዛው ተማርከው እንደ እጣን በማጨስ ይጠቀሙበት ነበር፡፡ ያአሁኑ ዘመናዊ የሕክምና ዓለምም ባያዘው 18 አይነት ንጥረ ነገር የተነሳ ጦስኝን ለተለያዩ መድኃኒት መስሪያነት በመጠቀም ላይ ይገኛል፡፡

ቅባት፣ፕሮቲን፣ካርቦ አይድሬት፣ቫይታሚን ኤ፣ዲ፣ ቢ6 እነ ሲ እንዲሁም ማግኒዚየም፣ ብረት ፣ ፋይበር እና ካልሲየም ይዟል፡፡ ቀጥለን በሳይንስ የተረጋገጡ የጦስኝ ጠቀሜታዎችን እንመልከት፡፡

1. ከፍተኛ የደም ግፊትን በእጅጉ ይቀንሳል፡- የተለያዩ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት ጦስኝ ስብ የጋገሩ የደም ቧንቧዎች በማስፋት ደም ያለምን መጨናነቅ በትቧዎቹ ውስጥ በቀላሉ እንዲዘዋወር በማድረግ ከፍተኛ የደም ግፊት መቀነሱ ተረጋግጧል፡፡ ባይገርማችሁ ዘመናዊ የደም ግፊት መቀነሻ መድኃኒቶች በአብዛኛው የሚሰሩት ጦስኝን በመጠቀም ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የደም ቅባት መጠን ወይም ኮሌስትሮልንም መቀነሱ ተረጋግጧል፡፡

2. ሳልን ያስቆማል፡- ጦስኝን ቀቀል ውሃውን መጠጣት ሳልን ጨምሮ አጣዳፊ ብሮንካይተስ የተሰኘውን የመተንፈሻ አካል ሕመም ያስቆማል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በሳል ሳቢያ የሚቆስልን ጉሮሮ ፈውስ ይሰጣል፡፡

3. የተፈጥሮ የበሽታ የመከላከል አቅማችንን ያጎለብታል፡- ጦስኝ በሽታ ተከላካይ የሆኑትን ጠቃሚ ቫይታሚኖች እንደ ቫይታሚን ሲ፣ኤ እና ዲ የመሳሰሉትን በመያዙ በማንኛውም ጊዜ ቅጠሉን ቀቅለን እንደ ሻይ ብንጠጣ በቀላሉ ጉንፋን ጨምሮ ሌሎች የመተንፈሻ አካላት በሽታዎችን መከላከል ይቻላል፡፡

4. ፀረ-ሻጋታ ነው፡- በቀላሉ ሊሻጋቱ የሚችሉ እንጀራን ጨምሮ ማናቸውም ነገሮች ላይ የጦስኝ ቅጠል ብናደርግበት ከመሻገት ይድናል፡፡

5. ጦስኝ ጸረ- ነፍሳት ነው፡- በቤት ውስጥና ከቤት ውጭ ነፍሳትና ተባዮች ካስቸገራችሁ የጦስኝ ቅጠል ቀቅላችሁ የሚያስቸግራችሁ ቦታ እርጩት፡፡ ውጤቱን በፍጥነት ያዩታል፡፡

6. ከመልካም ማዕዛው በተጨማሪ ፀረ- ፈንገስና ፀረ-ሕዋሳት ይዘት ስላለው በጥርስ ሳሙናና በገላ ሽቶዎች ውስጥ ሳይቀር በቅመምነቱ በዘመናዊ መልኩ ይገባል፡፡

7. ስሜታችንን (mood) ከፍ ለማድረግ ይረዳል፡፡ ጦስኝ በውስጡ የያዘው Carvacrol የተሰኘው ንጥረ ነገር የአእምሮችን ሕዋሳትን በማነቃቃት ጥሩ ስሜት እንዲሰማን ያደርጋል፡፡

8. ጥሩ የምግብ ምንጭ ነው፡- በፈረንሳይና በጣሊያን አገራት እና በአብዛኛው ሜዲትራኒያን አካባቢ ጦስኝ የተለያዩ ሶሶዎችን ወይም ስጎዎችን ለመስራት ያገለግላል፡፡

9. ለቡግር ማጥፊያነት ያገለግላል፡- ፀረ-ባክቴሪያ ንጥረነገር ስላለው ከብዙዎቹ ያለሐኪም ትዕዛዝ ከሚሸቱ ዘመናዊ የቡግር ማጥፊያ መድኃኒት የተሻለ ነው፡፡ እርጥቡን ጦስኝ ወቅጦ በብጉሩ ላይ ለተወሰነ ሰዓታት በማስቀመጥ መታጠብ ውጤታማ ያደርጋል፡፡

ቀይስርን የመመገብ የጤና ጥቅሞች Health Benefits of Beetroot *ለጉበት ጤናማነትቀይስር ውስጥ የሚገኝ ቤታይን የተባለ ንጥረነገር የጉበትን አገልግሎት የማነቃቃት አቅም አለው።*...
23/06/2023

ቀይስርን የመመገብ የጤና ጥቅሞች
Health Benefits of Beetroot

*ለጉበት ጤናማነት

ቀይስር ውስጥ የሚገኝ ቤታይን የተባለ ንጥረነገር የጉበትን አገልግሎት የማነቃቃት አቅም አለው።

*ከሳንባ ጋር ተያያዥ ችግሮችን ይከላከላል

ቀይስር ቫይታሚን ሲ በውስጡ ስለያዘ የአስም ምልክቶች እንዳይነሱ ይረዳል፣ በሽታ የመከላከል አቅማችን እንዲዳብርም ያግዛል። ቤታ ካሮቲን የሚባለው ንጥረ ነገር በሳንባ ካንሰር የመጠቃት እድልን ይቀንሳል።

*ካታራክትን ይከላከላል

ቤታ ካሮቲን የሚባል ንጥረ ነገርን የያዘው ቀይስር ከእድሜ ጋር ሊመጣ የሚችልን የአይን ሞራ እንዳይከሰት ይከላከላል።

*የሃይል መጠንን ይጨምራል

ቀይስር በካርቦሀይድሬት የበለፀገ ስለሆነ ሀይል ሰጭ ከሚባሉት ምግቦች እንዲመደብ ያደርገዋል።

*ካንሰርን ይከላከላል

አንዳንድ ጥናቶች ቀይስር ከቆዳ፣ ከሳንባ እና ከአንጅት ካንሰር የመከላከል አቅም እንዳለው ያሳያሉ።

የነጭ ሽንኩርት መድኃኒትነት ምን ያህል ያውቃሉ።1. ነጭ ሽንኩርት ስራን በትክክል ለማከናወን፣ የሰውነት ሕዋሳትን ጤናማ ለማድረግ ፣ድካምን ለማስወገድ፣ዕድሜን ለመጨመር፣በአይጥና በልዩ ልዩ ተ...
18/06/2023

የነጭ ሽንኩርት መድኃኒትነት ምን ያህል ያውቃሉ።

1. ነጭ ሽንኩርት ስራን በትክክል ለማከናወን፣ የሰውነት ሕዋሳትን ጤናማ ለማድረግ ፣ድካምን ለማስወገድ፣ዕድሜን ለመጨመር፣በአይጥና በልዩ ልዩ ተባዮች የሚመጡትን ተስቦ በሸታዎችን ለመከላከል ነጭ ሽንኩርት መብላት በጣም ጠቃሚ ነው፡፡

2. ማንኛውም ሰው መጥፎ ሽታ ባለበት አካባቢ ለፅዳት ከመሰማራቱ በፊት ነጭ ሽንኩርት ከትፎ ቢበላ ከማንኛውም በሽታ ከሚያመጡ ተዋህሲያን ለመዳን ይቻላል፡፡

3. በቂ ሕክምና በሌለበት አካባቢ በቁስል ለሚሰቃይ ሕሙማን በነጭ ሽንኩርት ጭማቂ አጥቦ በቁስሉ ዙሪያ በመደምደም በፋሻ ወይም በንፁህ ጨርቅ በማሰር ሕመምተኛውን ለመፈወስ ይችላል፡፡

4. ነጭ ሽንኩርት ቀቅሎ እንፋሎቱን የካንሰርንና የቲቢ በሽታዎችን ለመከላከልና በሳንባ አካባቢ ብርድና ጉንፋን ለማዳን ፍቱን መድኃኒቱ ነው፡፡

5. ብርድ ብርድ በሚያሰኝ ሕመምና በተለይም በጥርስ ሕመም ለሚሰቃዩት ሕሙማን ሁለት ራስ ነጭ ሽንኩርት የውስጠኛውን ሽፋናቸውን በመላጥ በሁለቱም ጉንጫቸው በተለይም በተነቃነቀው ጥርስ በኩል ነክሰው ረዘም ላሉት ሰዓት ቢጠቀሙበት መልሶ መልሶ ይጠነክራል፡፡

6. ለአስም፣ ለጉሮሮ ክርካሪ ወይም ኮርታ ለተባለው በሽታ እንዲሁም ጉሮሮ ለማፅዳት የነጭ ሽንኩርት ጭማቂ በስኳር ወይም በማር መጠጣት የተፈተነ መድኃኒት ነው፡፡

7. ነጭ ሽንኩርት የራስ ምታትና የደም ብዛት ያለባቸው ሰዎች ከ3 እስከ 5 ቀናት በማከታተል ሦስት ሦስት ፍንካች በቀን ሦስት ጊዜ ቢበሉ ከድካምና ከደም ብዛት ሊፈወሱ ይችላሉ፡፡

8. በደም መርጋት ምክንያት ለሚሰቃዩ ፣የልብ በሽታን፣ የፊንጢጣ ኪንታሮትና የእግር ደም ሥር እብጠት varicose የተባሉትን በሽታዎች ለመከላከልና ለመዳን ነጭ ሽንኩርት በመብላት መፈወስ ይችላል፡፡

9. ነጭ ሽንኩርት የቆላ ቁስል፣ችፌን፣የጨጓራ በሽታን ወረርሽኝን ኮሌራን ሳይቲካን የቁርጥማትን ሕመምን እንደሚያድን የተረጋገጠ ነው፡፡

አላስፈላጊ ስብ እንዲኖረን ምክኒያት የሚሆኑ 9 ልምዶች1- ልንተኛ ስንል መመገብ(ከምናዳብራቸው አላስፈላጊ ልምዶች መኀከል አንዱ እና ዋነኛው ልንተኛ አከባቢ የመቀማመስ ባህላችን ነው፡፡ ሰውነ...
14/06/2023

አላስፈላጊ ስብ እንዲኖረን ምክኒያት የሚሆኑ 9 ልምዶች

1- ልንተኛ ስንል መመገብ
(ከምናዳብራቸው አላስፈላጊ ልምዶች መኀከል አንዱ እና ዋነኛው ልንተኛ አከባቢ የመቀማመስ ባህላችን ነው፡፡ ሰውነት በዛ ሰዓት በተገቢው መልኩ የሰጠነውን ነገር መፍጨት ስልማይችል በእንቅልፋችን እና በ መጨረሻው ምግባችን መሀል የሚኖረውን ልዩነትማስፋት ይኖርብናል፡፡)

2- ያልተመጠነ እንቅልፍ
(ለሰውነታችን ቋሚ የሆነ የእንቅልፍ ሰዓት ካላበጀንለት ሰውነታችን ለ ሆረሞን መዛባት ይጋለጣል ፡፡ይህ ደግሞ የፍላጎት መዘበራረቅን ስለሚያስከትል የእንቅልፍ እጥረትን እንደምግብ እጥረት እንዲረዳው በማድረግ የምግብ አወሳሰዳችን እንዲጨምር ያደርጋል፡፡)

3- ከልብ ሳይሆኑ መመገብ
(በ ቲቪ፣ በ ሞባይልም ሆነ በተለያዩ ነገሮች ውስጥ ተውጠን የምንመገብ ሲሆን ከ ሌላው ጊዜ በ 50% የበለጠ ካሎሪ እንደምንወስድ የአሜሪካን ጆረናል ኦፍ ኒውትሪሽን ያደረገው ጥናት ያመለክታል፡፡ )

4- ጭንቀት እና ውጥረት
(አሜሪካን ውስጥ የተደረገው ጥናት እንደሚያሳየው እንደዚህ ያለ የስሜት መረበሽ ከፍተኛ የሆነ የስሜት ረሀብን ስለሚያስከትል አብኛው ሰው በመመገብ ከዚህ ስሜት ለመሸሽ ይሞክራል ይህ ደግሞ ለአላስፈላጊ ውፍረት ያጋልጣል፡፡)

5- በፍጥነት መመገብ
(በችኮላ መመገብ እየተመገብን ያለነውን ምግብ በተገቢው መንገድ ማላመጥ እንዳንችል ያደርጋል ይህ ደግሞ ያለመጥገብ ስሜትን ስለሚፈጥር ብዙ እንድንመገብ ምክኒያት ይሆናል፡፡ ሳይንስ እንደሚያመለክትው የሰው ልጅ በተረጋጋ መልኩ ከተመገበ እስከ 20 ደቂቃ ሊፈጅበት ይችላል ይህ ደግሞ በተገቢው መንገድ እንድናላምጥ እና እየበላን እንደሆነ እንዲሰማን ስለሚያረግ ቶሎ የመጥገብን ስሜት ይፈጥራል፡፡ )

6- እንቅስቃሴ አለማረግ(እረፍት ማብዛት)
(የአካል እንቅስቃሴ ለጤና ከፍተኛ ጥቅም እንዳለው ሁሉ አላስፈላጊ ስቦችንም ያጠፋል፡፡ ሰዎች አንድ ቦታ ላይ ሲቆዩ ያለምክኒያት የመመገብ በሀሪያቸው ይዳብራል፡፡ )

7- ቁርስን መዝለል
(የጤና ባለሞያዎች የቁርስ ሰዓት ለሰው ልጅ ወሳኙ የምግብ ሰዓት እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ የቀኑ የሜታቦሊዝም ስርዓታችንን ለሰውነታችን የሚወስንለት ከመሆኑም ባሻገር በቀን ውስጥ የምንመገበውን ካሎሪም በተገቢው መንገድ መሰባባር እንዲችል ይረዳዋል፡፡)

8- የበዛ ጨው መጠቀም
(ከመጠን ያለፈ የጨው አጠቃቀም አላስፈላጊ የፈሳሽ ክምችት እንዲኖረን በማድረግ ለ ደም ግፊት የሚያጋልጠን ከመሆኑም በላይ ለአላስፈላጊ ውፍረትም ይዳርገናል፡ )

9- በቂ ፈሳሽ አለመውሰድ
(የሰው ልጅ በ አማካኝ በ ቀን 2 ሊትር ውሃ መውሰድ የሚኖርበት እደሆነ የጤና ባለሞያዎች ይናገራሉ፡፡ ፈሳሽ አላስፈላጊ ቆሻሻዎችን ከሰውነታችን ውስጥ እንድናስወግድ ከማድረጉም በላይ የሰውነታችንን ስብ የመቀነስም አቅም አለው፡፡

28/05/2023

ፈጣን ትኩረት የሚያስፈልጋቸው 10 የህመም ምልክቶች

ለሕይወት አስጊ የሆኑ ሁኔታዎችን የሚያመለክት ህመም ብዙውን ጊዜ ኃይለኛ እና በድንገት የሚጀምር ሲሆን ከሌሎች ብዙ ምልክቶች እና መገለጫዎች ጋር የተያያዘ ነው።

👉 ፈጣን ትኩረት የሚያስፈልጋቸው የሕመም ምልክቶች የሚከተሉት ናቸው:-

✳️ በፍጥነት የሚጀምር የራስ ምታት

የራስ ምታት ህመምዎ በድንገት የሚከሰት ከሆነና ሊቋቋሙት በማይችሉት ሁኔታ ከባድ ከሆነ፤ የደም ቧንቧ ግድግዳ ላይ እብጠት ሲፈጠር የሚከሰተው የአንጎል አኑሪዝም (Brain Aneurism) ሊኖርብዎት ይችላል።

በተገቢው ሁኔት ህክምና ካልተደረገልዎት የደም ቧንቧዎቹ ሊፈነዱ ይችላሉ፤ ይህም ገዳይ ለሆኑት ስትሮክ ወይም ከፍተኛ የአንጎል ደም መፍሰስ ያጋልጣል።

✳️ ቀዝቃዛ ነገር ሲጠጡ የጥርስ ሕመም

የኢናሜል (የጥርስዎ ውጫዊ ሽፋን) (Enamel) ከተጎዳ ወይም ከበሰበሰ፤ በጥርስዎ ውስጥ ያሉትን ነርቮች ሊያጋልጣቸው ይችላል።

ይህም የበሰበሰው የጥርስዎ ክፍል ከማንኛውም ቀዝቃዛ ወይም ሙቅ ነገሮች ጋር ሲገናኝ ሊቋቋሙት የማይችሉት ህመም እንዲሰማዎት ያደርጋል።

ከህመሙ በተጨማሪ የተጋለጠው ነርቭ ወደተለያዩ የሰውነት ክፍሎችዎ ሊሰራጭ ለሚችል የባክቴሪያ ኢንፌክሽን አደጋ ያጋልጥዎታል። ከፍተኛ የጥርስ ህመም ከጀመርዎ ወደ ጥርስ ሀኪምዎ ይሂዱ።

✳️ በእጁ፣ በእጅ አንጓ እና በክንድ ላይ ያለ ህመም

ህመም ወይም የመደንዘዝ ስሜት በጣቶችዎ ላይ (በተለይም በአውራ ጣት፣ በአመልካች ጣት እና በመሃል ጣት)፣ በመዳፍ እና በእጅ አንጓ እንዲሁም ወደ ክንድዎ ከተስፋፋ ወይም ከተዛመተ የካርፓል ተነል ሲንድሮም (Carpal Tunnel Syndrome) ሊኖርብዎ ይችላል።

በጊዜ ካልታከሙ የእጅዎ ጡንቻዎች ሊዝሉ እና እጅዎ ሥራውን በአግባቡ ላይወጣ ወይም ሙሉ ለመሉ ተግባሩን ሊያጣ ይችላል። ለተለያዩ የህክምና አማራጮች በተቻለ ፍጥነት ሐኪምዎን ያማክሩ።

✳️ በደረትዎ አካባቢ የሚዛመት (የሚሠራጭ) ህመም

የደረት ህመም አይነተኛ የልብ ህመም ምልክት ነው፤ የሚከሰተውም ወደ ልብዎ በሚሄደው የኦክስጂን እጥረት ምክንያት ነው።

ህመሙ ወደ መንጋጋዎ፣ ትከሻዎ ወይም አንገትዎ ሊሄድ ይችላል።

✳️ በጀርባዎ መሃል አካባቢ የሚረብሽ ህመም

ህመሙ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየባሰ ከሄደ እና ከትኩሳት እና ከማቅለሽለሽ ጋር አብሮ ከሆነ፤ የኩላሊት ኢንፌክሽን ሊኖርብዎት ይችላል።

በተቻለ ፍጥነት ዶክተርዎን ያማክሩ። ኢንፌክሽኑ በኩላሊቶች ላይ ዘላቂ ጉዳት፣ የደም መመረዝ ችግር ወይም ሙሉ ለሙሉ የኩላሊት ሥራ ማቆም ሊያስከትል ይችላል።

✳️ ከታችኛው የጀርባ ክፍል የሚጀምርና እግርዎን የሚጎዳ ህመም

ይህ ዓይነቱ ህመም በሲያቲክ ነርቭ (Sciatic Nerve) ላይ በደረሰ ጉዳት ወይም ጫና ምክንያት የሚመጣው የሲያቲክ በሽታ (sciatica) ምልክት ነው። በሽታውን እንዴት መንከባከብ እንዳለብዎት እና የሚያደርጉትን የሕክምና አማራጮችን ከጤና ባለሙያ ጋር ይማከሩ።

በተጨማሪም የእግር መስነፍ (Weakness)፣ የሽንት ፊኛ ስሜት ማጣት (የሽንት መምጣት ስሜትን አለማወቅና አለመረዳት) ወይም አዲስ የተከሰተ ሽንትን የመቆጣጠር ችግር ካለብዎ፤ ቋሚ ፓራሊሲስ (የሰውነት መስነፍ) የሚያመጣውና አልፎ አልፎ የሚከሰተው ካውዳ ኢኩኒያ ሲንድረም (Cauda Equina Syndrome) አለብዎት ማለት ነው።

✳️ በታችኛው የቀኝ ሆድዎ አካባቢ ያለ ህመም

ትኩሳት፣ ማቅለሽለሽ እና/ወይም ማስመለስ እያጋጠመዎት ከሆነ፤ ትርፍ አንጀት (Appendicitis) ሊኖርብዎት ይችላል። የትርፍ አንጀት መፈንዳት ለሕይወት አስጊ የሆነ ኢንፌክሽንን ያስከትላል።

✳️ የሆድ ወይም የዳሌ ህመም

በወር አበባ ጊዜ የሚከሰት የሆድ ቁርጠት ለብዙ ሴቶች የተለመደ ነው።

ከጊዜ ወደ ጊዜ እየባሰ ከሄዱ ወይም ካልጠፋ (ካልቆመ) በማህፀን ውስጥ ያድጋል ተብሎ የሚታሰበው ቲሹ ከማህፀን ውጭ ማደግ የሚጀምርበት ሁኔታ ኢንዶሜትሪዩሲስ (Endometriosis) ችግር ሊኖርብዎ ይችላል።

ምርመራ ለማድረግ የማህፀንና ጽንስ ባለሙያ ጋር ይሂዱ። ይህን ምርመራ አለማድረግ የመካንነት አደጋን ይጨምራል።

✳️ በእግር ላይ የመጨምደድ ወይም የሚያሰቃይ ህመም

ህመም ያለበት የእግር ክፍል ከቀላ፣ ከሞቀ እና እብጠት ካለው ዲፕ ቬይን ትሮምቦሲስ በመባል የሚታወቅ የደም መርጋት ሊኖርብዎት ይችላል።

የአልትራሳውንድ ምርመራ ለማድረግ ዶክተርዎን ይጎብኙ። ህመም የሚሰማብዎትን ቦታ በፍጽም አይሹት፤ ምክንያቱም ይህን ማድረግ የረጋው ደም ወደ ልብዎ ወይም ወደ ሳንባዎ እንዲሄድ ሊያደርግ ይችላል።

✳️ በእግርዎ ላይ የመደንዘዝ እና በመርፌ የመወጋት ስሜት

እግሮችዎ የሚደነዝዙ፣ የሚያቃጥልዎት ወይም የሚንቀጠቀጡ ከሆነ በስኳር ህመም ምክንያት የነርቭ መጎዳት ሊኖርብዎ ይችላል።

መልካም ጤንነት!!

Address

Arba Minch'

Telephone

+251938975708

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ዶ/ር ብሩክ ስፖርት ህክምናና ቴራፒ 40 ምንጭ Dr. Biruk Sports Medicine & Therapy 40 Minch posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to ዶ/ር ብሩክ ስፖርት ህክምናና ቴራፒ 40 ምንጭ Dr. Biruk Sports Medicine & Therapy 40 Minch:

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram