የአርባ ምንጭ ከተማ ጤና ጽ/ቤት/Arbaminch Town Health Office

የአርባ ምንጭ ከተማ ጤና ጽ/ቤት/Arbaminch Town Health Office Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from የአርባ ምንጭ ከተማ ጤና ጽ/ቤት/Arbaminch Town Health Office, Medical and health, Arba Minch'.

31/10/2023
የአርባምንጭ ከተማ ጤና ጽ/ቤት እና ድልፋና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2015 በጀት ዓመት የላቀ አፈፃፀም በማስመዝገብ የዋንጫና የሴርትፊኬት ተሸላሚ ሆኑ፤አርባ ምንጭ ሐምሌ 22/2015 ዓ...
29/07/2023

የአርባምንጭ ከተማ ጤና ጽ/ቤት እና ድልፋና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2015 በጀት ዓመት የላቀ አፈፃፀም በማስመዝገብ የዋንጫና የሴርትፊኬት ተሸላሚ ሆኑ፤

አርባ ምንጭ ሐምሌ 22/2015 ዓ.ም (የአርባምንጭ ከተማ ጤና ጽ/ቤት)

የጋሞ ዞን ጤና መምሪያ የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም እና የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ በዛሬው ዕለት የተገመገመ ሲሆን የአርባምንጭ ከተማ ጤና ጽ/ቤት በጤናው ዘርፍ የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አፈፃፀም የላቀ ውጤት በማምጣት የዋንጫ እንዲሁም ድልፋና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በዞኑ ውስጥ ካሉ ሆስፒታሎች የተሻለ አፈጻጸም በማስመዝገብ በ2ኛነት የሰርትፊኬት ተሻላሚ መሆን ችለዋል።

ዜና ዕረፍት!!በአርባ ምንጭ ከተማ የድልፋና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ጤና ባለሙያ (ጤና መኮንን)በሆኑት በአቶ ገናናው ፍሰሐ ህልፈተ ህይወት የተሠማንን ጥልቅ ሀዘን በመግለጽ ለመላው ቤቴሰቦ...
17/07/2023

ዜና ዕረፍት!!
በአርባ ምንጭ ከተማ የድልፋና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ጤና ባለሙያ (ጤና መኮንን)በሆኑት በአቶ ገናናው ፍሰሐ ህልፈተ ህይወት የተሠማንን ጥልቅ ሀዘን በመግለጽ ለመላው ቤቴሰቦቻቸውና ወዳጅ ዘመዶቻቸው በሙሉ መጽናናቱን እንመኛለን !!

በአርባ ምንጭ ከተማ ጤና ጽ/ቤት በዛሬው ዕለት በቀን 8/10/2015 ዓ.ም በሥነ-ተዋልዶ ጤና እና የአፍላ ወጣቶትና ወጣቶች ጤና ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ የንቅናቄ መድረክ ከባለድርሻ አካላት...
15/06/2023

በአርባ ምንጭ ከተማ ጤና ጽ/ቤት በዛሬው ዕለት በቀን 8/10/2015 ዓ.ም በሥነ-ተዋልዶ ጤና እና የአፍላ ወጣቶትና ወጣቶች ጤና ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ የንቅናቄ መድረክ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተደርጓል።

10/06/2023
08/06/2023
07/05/2023
የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት (HPV ክትባት) ዕድሜያቸው 14 ዓመት ለሞላቸው ሴት ልጃገረዶች ከሚያዚያ 24/2015 ጀምሮ እስከ ሚያዚያ 27/2015 በትምህርት ቤቶች እየተሰጠ ነው...
02/05/2023

የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት (HPV ክትባት) ዕድሜያቸው 14 ዓመት ለሞላቸው ሴት ልጃገረዶች ከሚያዚያ 24/2015 ጀምሮ እስከ ሚያዚያ 27/2015 በትምህርት ቤቶች እየተሰጠ ነው፡፡

ኮሌራ ምንድን ነው? እንዴትስ መከላከልና ማከም ይቻላል?   ስለ ኮሌራ በአጭሩ !!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!ኮሌራ በባክቴሪያ አማካኝነት የሚከሰትና በአብዛኛው በተበከለ ውኃ አማካኝነት...
19/04/2023

ኮሌራ ምንድን ነው? እንዴትስ መከላከልና ማከም ይቻላል?

ስለ ኮሌራ በአጭሩ !!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

ኮሌራ በባክቴሪያ አማካኝነት የሚከሰትና በአብዛኛው በተበከለ ውኃ አማካኝነት የሚተላለፍ ህመም ነው፡፡ ኮሌራ ሲከሰትም አጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት በማስከተል በሰውነት ውስጥ የሚገኝን ፈሳሽ አሟጦ በማስወጣት አቅምን በማዳከም አፋጣኝ ሕክምና ካልተደረገ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ጤነኛ ሰውም ቢሆን ለሞት የሚዳርግ በሽታ ነው፡፡

በአጠቃላይ ኮሌራ በአደጉት ሀገራት ዘመናዊ ፍሳሽ እና የውኃ የማጣራት የኮሌራ ህመም ስርጭቱ እንዲቀንስ እና ለመቆጣጠር አስችሏል፡፡ ይሁን እንጂ በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት ግን በድህነት፣ ንጽሕና ጉድለት፣ ጦርነት፣ ስደት እና ተፈጥሮአዊ አደጋዎች ምክንያት ኮሌራ በተደጋጋሚ በአፍሪካ፣ ደቡብምስራቅ እስያ እና ሄይቲ ሲከሰቱ ይታያል፡፡

ለኮሌራ በሽታ አጋላጭ ሁኔታዎች

የተበከለ ውኃ መጠጣት፧
የተበከለ ምግብ መመገብ፧
የግል እና አካባቢ ንጽሕና ጉድለት፧
ሜዳ ላይ መጸዳዳት፧
የመጸዳጃ ቤቶችን በአግባቡ አለመጠቀም

የበሽታው ምልክቶች!

ተቅማጥ (Diarrhea)፡- በድንገት የሚከሰት ብዛት ያለው አጣዳፊ ውኃ መሰል ተቅማጥ (የሩዝ ውኃ የሚመስል) ትውከት (Nausea and vomiting)፡- ማቅለሽለሽ ኮሌራ በሚከሰትበት በመጀመሪያዎቹ ጊዘያት በስፋት ሲታይ በተደጋጋሚ ማስመለስ ደግሞ ለሰዓታት ሊቀጥል ይችላል። ኮሌራ የትኩሳት ወይም የቁርጥማት ህመም ላይኖረው ይችላል።

የፈሳሽ ማጣት (Dehydration)፡- ይሁን እንጂ በፍጥነት ህክምና ካላገኘን በሰውነታችን ውስጥ ያለውን ፈሳሽ ተሟጥጦስለሚያልቅ የአቅም ማነስ፣ የቆዳ መሸብሸብ፣ የዐይን መሰርጎድ የአፍ መድረቅ ብሎም ሞት ያስከትላል፡፡

ይህ የፈሳሽ ማጣት ደግሞ በሰውነታችን ውስጥ የሚገኙ ጠቃሚ ማእድናትን ከፈሳሽ ጋር አብሮ ስለሚወጡ ለከፋ ጉዳት ይዳርጋሉ ለምሳሌ ለጠዩንቻ ህመም፣ ደም ግፊት ማነስ፣ በሰውነት ውስጥ ያለው ኦክሲጅን መጠን መቀነስ እና ራስን መሳት ብሎም በአፋጣኝ ካልታከም ለሞት ሊዳርግ ይችላል፡፡

የመከላከያ መንገዶች
1. ንጹህ ውሃ መጠጣት እና መጠቀምዎን
2. እጅዎን በወሣኝ የእጅ መታጠቢያ ጊዚያት በሳሙና እና በንፁህ ውሃ ይታጠቡ
3. መጸዳጃ ቤቶችን ይጠቀሙ
4. ምግብን በመቀቀል፣ በማብስል አንዲሁም ንጽህናውን በመጠበቅ ይጠቀሙ
5. የአከባቢ ንጽህናን በአግባቡ ይጠብቁ

የአርባምንጭ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የ2015 በጀት ዓመት የ9 ወራት የዋና ዋና ተግባራት ዕቅድ አፈፃፀም ግምግማ ተደርጓል።
18/04/2023

የአርባምንጭ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የ2015 በጀት ዓመት የ9 ወራት የዋና ዋና ተግባራት ዕቅድ አፈፃፀም ግምግማ ተደርጓል።

በአርባ ምንጭ ከተማ ጤና ጽ/ቤት  በባለሙያነትና በአመራርነት እንዲሁም በመሰራችነት ለረጅም ዓመታት ባገለገሉት በሥራ ባልደረባችን በአቶ መዓዛ ሙአ ድንገተኛ ኅልፈት የተሰማንን ጥልቅ ሐዘን እ...
12/04/2023

በአርባ ምንጭ ከተማ ጤና ጽ/ቤት በባለሙያነትና በአመራርነት እንዲሁም በመሰራችነት ለረጅም ዓመታት ባገለገሉት በሥራ ባልደረባችን በአቶ መዓዛ ሙአ ድንገተኛ ኅልፈት የተሰማንን ጥልቅ ሐዘን እየገለጽን ለሟች ቤተሰቦች፣ ለሥራ ባልደረቦችና ጓደኞች መጽናናትን እንመኛለን!!!

ለኤች አይ ቪ ይበልጥ ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ ያተኮረ  የምክር፣ምርመራ ፣ህክምና እንዲሁም የመከላከልና ቁጥጥር ተግባራት ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀ ተጠናክሮ መሰራት እንዳለበት...
08/04/2023

ለኤች አይ ቪ ይበልጥ ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ ያተኮረ የምክር፣ምርመራ ፣ህክምና እንዲሁም የመከላከልና ቁጥጥር ተግባራት ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀ ተጠናክሮ መሰራት እንዳለበት ተገለፀ።አርባምንጭ ፣መጋቢት 30/2015 ዓ/ም (አ/ምንጭ ከተማ ጤና ጽ/ቤት) የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት የዘርፈብዙ ምላሽ ኤች አይቪ/ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ዳይሬክቶሬት ከግሎባል ፈንድ ጋር በመቀናጀት የሥራ ሂደቱን የ2015 በጀት ዓመት የ9 ወራት ዕቅድ አፈፃፀምና የቀሪ ወራት የትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋራ ውይይት አድርጓል። በውይይቱ ከአርባምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል፣ከአርባምንጭ ድል ፋና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል፣ከሼቻና ከወዜ ጤና ጣቢያዎች የተጋበዙ የዘርፉ ባለሙያዎችና እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል። በከተማው የኤች አይ ቪ ሥርጭት ከፍተኛ በመሆኑ መዘናጋት ሳይኖር ለኤች አይ ቪ ይበልጥ ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ ያተኮረ የምክር፣ምርመራ ፣ህክምና እንዲሁም የመከላከልና ቁጥጥር ተግባራት ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀ ተጠናክሮ መሰራት እንዳለበት ተነስቷል።

የዝናብ ወቅትን ተከትሎ በወረርሽን መልክ ሊከሰቱ ይችላሉ ተብሎ  የሚያሰጉ በሽታዎች ቅድመ መከላከል ላይ ትኩረት ማድረግ እንድምያስፈልግ ተገለፀ።አርባምንጭ ፣መጋቢት 23/2015 ዓም (አ/ምን...
01/04/2023

የዝናብ ወቅትን ተከትሎ በወረርሽን መልክ ሊከሰቱ ይችላሉ ተብሎ የሚያሰጉ በሽታዎች ቅድመ መከላከል ላይ ትኩረት ማድረግ እንድምያስፈልግ ተገለፀ።አርባምንጭ ፣መጋቢት 23/2015 ዓም (አ/ምንጭ ከተማ ጤና ጽ/ቤት) የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት ጤናና ጤና ነክ ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ ዳይሬክቶሬት በሥሩ ለሚተዳደሩ ከሦስቱም ጤና ተቋማት (ከድልፋና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል፣ከሼቻ ጤና ጣቢያ እና ከወዜ ጤና ጣቢያ) ለተወጣጡ 30 የጤና ባለሙያዎች ቀጣይ ክረምት ጊዜያትን ተከትሎ ሊከሰቱ ይችላሉ ተብሎ የሚያሰጉ በሽታዎችን (ኮሌራ/አተት፣ወባ....እንዲሁም ሌሎች በቅኝትና አሰሳ ሥር ያሉ ኩፉኝ፣ፖልዮ ወዘተ በሽታዎች ቀድሞ ለማወቅ፣ ለመከላከልና ለመቆጣጠር ይቻል ዘንድ ቅድመ ዝግጅት ስልጠናና ውይይት መድረክ እያካሄደ ይገኛል።

29/03/2023
11/03/2023

Address

Arba Minch'

Telephone

+251912943809

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የአርባ ምንጭ ከተማ ጤና ጽ/ቤት/Arbaminch Town Health Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram