12/08/2023
ከማህፅን ውጭ እርግዝና
(ECTOPIC PREGNANCY)
ከማህፅን ውጭ እርግዝና የሚከሰተው የዳበረው እንቁላል ከዋናው የማህፀን ክፍል ውጭ ሲያድግ ነው። ብዙውን ጊዜ የሚከሰተው በማህፀን ቱቦ ውስጥ ነው። አንዳንድ ጊዜ በሌሎች የሰውነት ክፍሎች ማለትም ኦቫሪ (ovary)፣ የሆድ ዐቃ (abdominal cavity) ወይም የማህፀን ጫፍ (cervix) ላይ ይከሰታል።
🏩🏨ምልክቶች
መጀመሪያ ላይ ምንም ምልክቶች ላይታዩ ይችላሉ። ይሁን እንጂ አንዳንድ ከማህፀን ውጭ እርግዝና ያለባቸው ሴቶች የተለመዱ የእርግዝና ምልክቶች አሏቸው - የወር አበባ መቋረጥ ፤ የጡት ህመም እና ማቅለሽለሽ።
ሶስት ክላሲክ ምልክቶች የምንላቸው ፥ የሆድ ህመም፣ ደም መፍሰስ (vaginal bleeding) እና የወር አበባ መቆረጥን (amenorrhea) ያጠቃልላል።
🌡🧪🩸ስለ ከማህፀን ውጭ እርግዝና ቅድመ ማስጠንቀቂያ
ብዙውን ጊዜ ቀለል ያለ ደም መፍሰስ (light vaginal bleeding) አና ማህፀነ አካባቢ ህመም (pelvic pain) ናቸው።
🩺🩹🖍 አደገኛ ምልክቶች
በሆድ ውስጥ ከባድ የደም መፍሰስ።
ራስን መስት, የደም ግፊት መውረድ እና የልብ ምት መጨመር።
🖋🦠🏨ከማህፀን ውጭ እርግዝና እንዲከሰት የሚያደርጉ ምክንያቶች
- ከዚህ ቀደም ከማህፀን ውጭ እርግዝና
ተከስቶ ከነበረ
- ኢንፌክሽን (በግንኙነት የሚተላለፉ)
- የማህፀን ቱቦ ቀዶ ጥገና
- ሲጋራ ማጨስ
👨⚕🩸💉 ምርመራ
- የእርግዝና ምርመራ
- አልትራሳውንድ እና
- ሌሎች የደም ምርመራዎች።
🔬የማህፀን ውጭ እርግዝና ሕክምና
ከማህፀን ውጭ እርግዝናው ከባድ ደም መፍሰስ ካስከተለ, ድንገተኛ ቀዶ ጥገና ያስፈልጎታል።
🧬💊🩺 እንዴት መከላከል ይቻላል?
- በግብረ ሦጋ ግንኙነት የሚተላለፉ
ኢንፌክችኖችን መከላከል (የጾታ
አጋሮችን ቁጥር በመገደብ አና ኮንደም
በመጠቀም)
- አለማጨስ
ለተጨማሪ መረጃና ህክምና አብርሃም መካከለኛ ክሊኒክ ጎራ ይበሉ።
ስፔሻሊስት ሐኪም ያማክሩ።
አድራሻችን፤
አርባምንጭ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጀርባ
ስልክ ቁጥር፡-
0913106911/ 0911052389