Shangul Hospital ሻንጉል ሆስፒታል

Shangul Hospital ሻንጉል ሆስፒታል This pages meant to give you medical information, news and advice ይህ ገፅ ሀኪሞች እና ታካሚዎች እንዲግባቡ ለታካሚ ቀለል ባለ መልኩ መረጃ ለመስጠት ነው።

በሻንጉል ሆ/ል በቀዶ ህክምና የተወገደ 8.9 ኪሎግራም የሚመዝን የማህፀን እጢ (Ovarian tumor).************ዶ/ር ምንግዜም አዲስ (የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት) አሶሳ
25/10/2025

በሻንጉል ሆ/ል በቀዶ ህክምና የተወገደ 8.9 ኪሎግራም የሚመዝን የማህፀን እጢ (Ovarian tumor).
************
ዶ/ር ምንግዜም አዲስ (የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት)
አሶሳ

አስደሳች ዜና********በቅርቡ በሸንጉል ሆ/ል አለም የደረሰበትን የመጨረሻውን ዘመናዊ 128 slice CT scan እያስመጣ መሆኑን ስናሳውቅ በደስታ ነው።ይህ ዘመን አመጣሽ 128 Slice...
30/09/2025

አስደሳች ዜና
********
በቅርቡ በሸንጉል ሆ/ል አለም የደረሰበትን የመጨረሻውን ዘመናዊ 128 slice CT scan እያስመጣ መሆኑን ስናሳውቅ በደስታ ነው።
ይህ ዘመን አመጣሽ 128 Slice CT scan; ዝቅተኛ ካንሰር አምጪ ጨረር (Radiation) እና ከፍተኛ የምስል ጥራት (image quality) ያለዉ በመሆኑ የሚተማመኑ ዘመናዊ የሕክምና መሳሪያን በሽንጉል ሆ/ል በቅርብ ይጠብቁ!
********
ሸንጉል ሆ/ል
አሶሳ፤

Hospitaalli Shengul erga hundeeffamee kaasee hawaasa keenya bal'aa ta'eef tajaajila kennaa tureera. Haa ta'u malee namoo...
26/08/2025

Hospitaalli Shengul erga hundeeffamee kaasee hawaasa keenya bal'aa ta'eef tajaajila kennaa tureera. Haa ta'u malee namoonni tokko tokko kaffaltii hojii garmalee kaffalla jedhu, kunis sirrii akka hin taane isin beeksisuuf maxxanfama:
1: Tajajila Da'umsa: Birrii kuma 8
2: Yaalii baqaqsanii deessissuu (C/S): Birrii kuma 15
3: Baqaqsanii yaalu Appendicitis/Tirf anjetil/kulkula appeendiksi: Birrii kuma 15
4: Baqaqsanii hodhuu cirracha Hadhooftuu : Birrii kuma 25
5: Taayirooyidii (quufa mormaa) balleessuu: Birrii kuma 25
6: Baqaqsanii hodhuu Hernia (BUA): Birrii kuma 20
7: Baqaqsanii hodhuu ujummoo fincaanii (BPH): Birrii kuma 25
8: Baqaqsanii hodhuu ciccituu qaama saalaa,kormommuu (kintaarotii), fistulas: 15,000.
9: Ujummoolee Vaarikoosii: .
ML (Birr 15,000)
Stripping (Birr 20,000)
10: Baqaqsanii Hodhuu Fiibrooyidii Gadameessaa: Birrii kuma 20
11: Baqaqsanii Hodhuu Gadameessaa: Birrii kuma 25
12: Caba Daa’immanii fi Ga’eessotaa Wal’aansa Konsarvaatiivii: 6,000
13: Baqaqsanii Hodhuu Caccaba mudhii : 35,000 (Dulloonni: 40,000) .
14: Baqaqsanii hodhuu Harka Caccabsuu: Birrii kuma 30
15: Baqaqsanii Hodhuu Qaama Cabaa Birrii kuma 30

Siree: Birrii 800/Guyyaa
Tajaajila Anesthesia: Guutuu (2000 - 4000 Birrii) Walakkaa (2000 Birr)

Odeeffannoo dabalataaf qaamaan nu qunnamaa Dhuftanii nu haasofsiisuu dandeessu.

**************
Shengul Hospital

ሸንጉል ሆ/ል ከተመሠረተ ጀምሮ ሰፊ ለማህበረሰባችን ክፍል አገልግሎት እየሰጠ መሆኑ ይታወቃል። ሆኖም አንዳንድ ሰዎች የሚናገሩት የተጋነነ ኦፕሬሽን ክፍያ እንደምናስከፍል አግባብነት እንደሌለዉ...
26/08/2025

ሸንጉል ሆ/ል ከተመሠረተ ጀምሮ ሰፊ ለማህበረሰባችን ክፍል አገልግሎት እየሰጠ መሆኑ ይታወቃል። ሆኖም አንዳንድ ሰዎች የሚናገሩት የተጋነነ ኦፕሬሽን ክፍያ እንደምናስከፍል አግባብነት እንደሌለዉ ለማሳወቅ ሲባል የተለጠፈ
1: በምጥ ማዋለድ: 8,000 ብር
2: በኦፕሬሽን (C/S) ማዋለድ: 15,000 ብር
3: የትርፍ አንጀት ሰርጀሪ: 15,000 ብር
4: የሐሞት ጠጠር ሰርጀሪ: 25,000ብር
5: የእንቅርት ሰርጀሪ (thyroidectomy): 25,000 ብር
6: የሄርኒያ (ቡአ) ሰርጀሪ: 20,000 ብር
7: የሽንት ቱቦ መዘጋት (BPH) ሰርጀሪ: 25,000 ብር
8: ለኪንታሮት፣ ፊንጢጣ መሰንጠቅ ፊስቱላ ሰርጀሪ: 15,000.
9: የእግር ደም ስር መወጣጠር (Varicose vein):
ML (15,000 ብር)
Stripping (20,000 ብር)
10: ከማህፀን እጢዎች ኦፕሬሽን ሰርጀሪ: 20,000 ብር
11: የማህፀን መንሸራተት ሰርጀሪ: 25,000 ብር
12: የህፃናት እና የአዋቂዎች አጥንት ስብራት በጀሶ(Conservative) ህክምና: 6,000
13: የታፋ አጥንት ስብራት ኦፕሬሽን:35,000 (የቆየ: 40,000)
14: የእጅ አጥንት ስብራት ኦፕሬሸን: 30,000 ብር
15: የቁርጭምጭሚት አጥንት ስብራት ኦፕሬሽን: 30,000 ብር

የአልጋ: 800 ብር/በቀን
የአንስቴዥያ (ማደንዘዣ) አገልግሎት: ሙሉ (2000 - 4000ብር) ግማሽ (2000 ብር)

ለበለጠ መረጃ ሆ/ል በአካል ቀርበው ማነጋገር ይቻላል።

**********
ሸንጉል ሆ/ል

ደም ልገሳ በሸንጉል ሆ/ል ሰራተኞች እና ታካሚዎች ተከናውኗል:: Robera Teshome
09/08/2025

ደም ልገሳ በሸንጉል ሆ/ል ሰራተኞች እና ታካሚዎች ተከናውኗል::
Robera Teshome

09/08/2025
ዛሬ እሁድ ሐምሌ 27/ በሸንጉል ሆ/ል በቀዶ ህክምና ክፍል፣ በአጥንት ክፍል እና በማዋለጃ ክፍል ስምንት (08) ሰርጀሪ የተሰራ ሲሆን ከ35 አመት ታካሚ  የወጣ 459 የሐሞት ጠጠሮች ከሌሎ...
03/08/2025

ዛሬ እሁድ ሐምሌ 27/ በሸንጉል ሆ/ል በቀዶ ህክምና ክፍል፣ በአጥንት ክፍል እና በማዋለጃ ክፍል ስምንት (08) ሰርጀሪ የተሰራ ሲሆን
ከ35 አመት ታካሚ የወጣ 459 የሐሞት ጠጠሮች ከሌሎቹ ልዩ ነበር።
በዶ/ር ሮቤራ ተሾመ (ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት) የተመራ ቡድን እናመሰግናለን።

  📢🚑The Good News is coming soon!Robera Teshome Mohamed Musa Merghani Awod Yibeltal Alem Mengizem Addis Aragaw Kibret Ar...
01/08/2025

📢🚑
The Good News is coming soon!
Robera Teshome Mohamed Musa Merghani Awod Yibeltal Alem Mengizem Addis Aragaw Kibret Arage Birhane M***i Abu Fahmi
Elias Molla Sibhat Getachew

 #እንቅርት (Goiter)====ታይሮይድ የተባለው አንገታችን መሀል አካባቢ በተፈጥሮ የሚገኘው ጠቃሚ እጢ (Gland) ሲተልቅ እንቅርት (Goiter) ይባላል። ታይሮይድ የተባለው እጢ ከማንቁ...
21/07/2025

#እንቅርት (Goiter)
====
ታይሮይድ የተባለው አንገታችን መሀል አካባቢ በተፈጥሮ የሚገኘው ጠቃሚ እጢ (Gland) ሲተልቅ እንቅርት (Goiter) ይባላል። ታይሮይድ የተባለው እጢ ከማንቁር (Adam's Apple) ትንሽ ዝቅ ብሎ የሚገኝ ሲሆን በኖርማል ሰው በእይታ አይታወቅም።

የታይሮይድ እጢ ታይሮክሲን የተባሉ ሆርሞኖችን ያመነጫል። እነዚህ ሆርሞኖች በሰውነታችን በርካታ ስራዎችን ይሰራሉ። ከእነዚህም ስራዎቹ መካከል የሙቀት ሁኔታ፣ ሙድ፣ ስሜታዊነት፣ የልብ ምትና የምግብ መፍጨት ስርአት ይገኙበታል።

☑️ #የእንቅርት #አይነቶች #ምን #ምን #ናቸው?

1. #ቀላል (Simple Goiter):-

ይህ ካንሰር ያልሆነና ሆሮሞን በከፍተኛ ሁኔታ የማያመነጭ ነው።

2. #ኢንደሚክ (Endemic Goiter):-

ይህ የአዮዲን እጥረትን ተከትሎ የሚመጣ ሲሆን በሀገራችን በከፍተኛ ሁኔታ ይገኛል። አዮዲን ታይሮይድ ሆርሞን ለመስራት አስፈላጊ ነው። የአዮዲን እጥረት ሲኖር የዚህ ዓይነት እንቅርት ይከሰታል። አዮዲን ያለው ጨው በመጠቀም መከላከል ይቻላል።

3. #ሆርሞን #የሚያመነጭ (Toxic Goiter):-

ይህ የሚከሰተው እባጩ ከፍተኛ ሆርሞን በማመንጨት በልብና በሌሎች የሰውነት ክፍሎች ጉዳት ሲያደርስ ነው።

4. #ካንሰር:-

አንዳንድ እንቅርት ከጅምሩ ካንሰር ሲሆን ሌላው ደሞ በጊዜ ሂደት ወደ ካንሰርነት የተቀየረ እንቅርት ነው። በፍጥነት ማደግና የድምፅ መጎርነን የዚህ ዓይነት እንቅርት ምልክት ነው።

☑️ #አጋላጭ #ነገሮች #ምንድን #ናቸው?
======
🔹 እንደ ሊቲየም (ለአእምሮ የሚታዘዝ) ያሉ መድሀኒቶች
🔹 የአንገት ጨረር ህክምና (በተለይ በልጅነት የሚሰጥ)
🔹 የሴት ፆታ
🔹 እድሜ አርባ አመት አካባቢ መሆን
🔹 የታይሮይድ እጢ ብግነት
🔹 አውቶ ኢሚውን ዲዚዝ (ሰውነት ራሱን ሲያጠቃ) ዋናዎቹ ናቸው።

☑️ #ምልክቶች
======
1. አንገት ላይ እባጭ (እንቅርት)
2. ጉሮሮ የማነቅ ስሜት
3. የድምፅ መጎርነን
4. ለመተንፈስ መቸገር
5. ሳል
6. ለመዋጥ መቸገር
7. የልብ ምት መጨመር
8. ማላብ:- ምንም ሳይሰሩና ሙቀትም ሳይጨምር
9. የእጅ መንቀጥቀጥ
10. መጨነቅ
እነዚህ ምልክቶች በከፊል ወይም ሁሉም ሊኖሩ ይችላሉ።

☑️ #ምርመራው
=======
1. የሐኪም የሰውነት ምርመራ (Physical Exam)
2. የሆርሞን ምርመራ
3. አልትራሳውንድ
4. የናሙና ጥናት (ፓቶሎጂ)
5. የአንገት ሲቲ ስካን
6. ሌሎች መሰረታዊ የላቦራቶሪ ምርመራዎች

☑️ #ህክምናው
=======
1. #ክትትል ብቻ:- ከምርመራ በኋላ የሚወሰን ሲሆን ለትንሽና ለማያመነጭ እንቅርት።
2. #መድሀኒት:- በተለይ ከፍተኛ ሆርሞን የሚያመነጭ ከሆነ ግድ መወሰድ አለበት። ይህ ሰይደረግ ኦፕሬሽን ማድረግ አደገኛ ስለሆነ አይቻልም።
3. #ኦፕሬሽን:- ሆርሞን በመድሃኒት ከተስተካከለ በኋላ የሚደረግ ሲሆን እጢው በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ይወጣል።

🙏🙏🙏

ጤና ነክ እና ሌሎችም አስተማሪ የሆኑ መረጃዎችን ለማግኘት እና ለማማከር በሚከተሉት አድራሻዎች ያገኙናል፡
ፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100076171566897
ቴሌግራም https://t.me/ba051219

በሸንጉል ሆ/ል የተሰሩ Major ሰርጀሪዎች ************     ሸንጉል ሆ/ል ስለመረጡ እናመሰግናለን!
19/07/2025

በሸንጉል ሆ/ል የተሰሩ Major ሰርጀሪዎች
************
ሸንጉል ሆ/ል ስለመረጡ እናመሰግናለን!

የድንገተኛ ልብ ሕመምን ለመከላከል✔ በፋይበር የበለፀጉ ምግቦችን መመገብእንደ ስንዴ፣ሲሪያል፣ ፍራፍሬ፣አትክልት እና አጃን መመገብ ከኮሌስትሮል ወደ ሰውነታችን እንዳይወስድ ማድረግ አቅም አለው...
18/07/2025

የድንገተኛ ልብ ሕመምን ለመከላከል

✔ በፋይበር የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ

እንደ ስንዴ፣ሲሪያል፣ ፍራፍሬ፣አትክልት እና አጃን መመገብ ከኮሌስትሮል ወደ ሰውነታችን እንዳይወስድ ማድረግ አቅም አለው

✔ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ

እንቅስቃሴን ማድረግ ለድንገተኛ የልብ ሕመም ተጋላጭነትን ይቀንሳል በቀን ቢያንስ ለ30 ደቂቃ እንቅስቃሴ ያድርጉ

✔ለሰውንት ተስማሚ የሆኑ የስብ ዓይነቶችን ምግቦች መመገብ

ይህም ማለት ከስጋ እና ጮማ ከበዛባቸው ምግቦች ይልቅ እንደ አሳ፣ኦቾሎኒ፣እና አቮካዶ የመሳሰሉትን መመገብ

✔ ሲጋራ ማጤስን ማቆም

ሲጋራን በመደበኛ ሁኔታ የሚያጨሱ ከሆነ እራስዎን ለድንገተኛ የልብ ሕመም በከፍተኛ ሁኔታ ይዳርጋል

✔ የሚወስዱትን የጨው መጠን መቀነስ

ጨውን መመገብ የሚያዘወትሩ ከሆነ የደም ግፊትዎን እንዲጨምር ያደርጋሉ፡፡ስለዚህ የሚመገቡትን የጨው መጠን ይቆጣጠሩ፣

✔ ጭንቀትን መቀነስ

ከፍተኛ የሆነ ጭንቀት ካለብዎ ራስዎን ለአደጋ እየጣሉ ስለሆነ ለመቀነስ ይሞክሩ

✔ የስኳር መጠንዎን መቆጣጠር

የስኳር ሕመም ለልብ ሕመም በከፍተኛ ሁኔታ የሚያጋልጥ ስለሆነ በሚገባ ይቆጣጠሩ

✔ የደም ግፊት መጠንዎን በሚገባ መቆጣጠር

የደም ግፊት ለልብ ሕመም ተጋላጭነትን ስለሚጨምር በሚገባ መቆጣጠር ይኖርብዎታል፡፡ መድኃኒት የሚወስዱም ከሆነ በሐኪምዎ ትዕዛዝ መሠረት ይተግበሩ

✔ የአልኮል መጠጥ አለማዘውተር

አልኮልን በአብዛኛው የሚጠጡ ከሆነ እራስዎን ለደም ግፊት መጨመር ያጋልጣሉ ይህም በተዘዋዋሪ ለልብ ሕመም ይዳርግዎታል

እባክዎን ለወዳጅዎ ያካፍሉ!

ጤና ይስጥልኝ

Address

Asosa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Shangul Hospital ሻንጉል ሆስፒታል posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Shangul Hospital ሻንጉል ሆስፒታል:

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram

Category