09/11/2025
የተቀናጀ የብልህ ጅምር የጤና አገልግሎት በክልሉ ተግባራዊ ማድረግ ያለዕድሜ በመዉለድ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች ለመከላከል የጎላ ድርሻ እንዳለዉ ተገለፀ።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ ከኢትዮጵያ የቤተሰብ መምሪያ ጋር በመተባበር የተቀናጀ የብልህ ጅምር የጤና አገልግሎት ዙሪያ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል ።
ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ጤና የእ/ወ/ህፃናትና ሥርዓተ ምግብ ዳይሬክቶሬት የእናቶች ወጣቶችና አፍላ ወጣቶች ኬዝ ቲም አስተባባሪ አቶ አለፎም ረዳ በስልጠና ማስጀመሪያ መድረክ ላይ እንዳሉት የዚህ ፕሮግራም በክልሉ ተግባራዊ መደረጉ የወጣቶችና አፍላ ወጣቶችን ጤና ከማሻሻሉ በተጨማሪ የክልሉን የቤተሰብ ዕቅድ ሽፋን ከፍ የሚያደረግ በመሆኑ ነው ።
ይህ ፕሮገራም በተለይ ዕድሜያቸው ከ15-24 ያሉ አድስ ተጋቢዎች የቤተሰብ ዕቅድ እየተጠቀሙ እርግዝናን ለማዘግየት እንዲችሉ ያግዛል ያሉት አቶ አለፎም ያለዕድሜ ከመዉድ ጋር ተያይዞ የሚከሰቱ የጤና ችግሮችን ለመቅረፍ እና ወጣቶች እና አፍላ ወጣቶች በኢኮኖሚ ራሳቸውን እስክያበቁ እርግዝናን ለማዘግየት የጎላ ድርሻ እንደአለዉ ተናግረዋል ።
በክልሉ ጤና ቢሮ የቤተሰብ ዕቅድ ባለሙያ ሲስተር መለሀሰን አጠይብ ይህ ፕሮግራም የአሶሳ ከተማን አስተዳደር ጨምሮ በክልሉ በተመረጡ 12 ወረዳዎች በሚገኙ የጤና ተቋማት ላይ ተግባራዊ እየተደረገ ስለሆነ ወጣቶች እና አፍላ ወጣቶች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ በየጤና ተቋማት የሚገኙ የጤና አመራሮችና የጤና ባለሙያዎች ለፕሮግራሙ ዉጤታማነት በትኩረት መሰራት እንደአለባቸዉ ገልፀው በቢሮ በኩልም አስፈላጊዉ እገዛ ይደረጋል ብለዋል።
ብልህ ጅምር ተግባራዊ ማድረግ ያለዕድሜ በእናቶች ላይ የሚደርሰዉን የጤና ችገሮች ከመቅረፉ በተጨማሪ ለህፃናት ጤና አስተዋጽኦ እንደአለዉ የገለፁት ደግሞ በክልሉ ጤና ቢሮ የወጣቶች እና አፍላ ወጣቶች ባለሙያ ሲስተር ፀጋነሽ በየነ ናቸው ።
የክልሉ ወጣቶች የጤና ካዉንስል ፕረዚዳንት ወ/ሮ ሀቢባ ያህያ በበኩላቸው ይህ ፕሮግራም የወጣቶች እና አፍላ ወጣቶች የቤተሰብ ዕቅድ አጠቃቀም ለማሻሻል የጎላ ድርሻ ስለአለው ለተግባራዊነቱ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን እገዛ ማድረግ እንደአለባዉ አሳስበዋል ።
በስልጠና መድረኩ ላይ ከአሶሳ ዞን ከተወጣጡ የጤና ጣቢያ ሀላፊዎች፣የጤና ኤክሰቴንሽን የትስስር ባለሙያዎች ፣የጤና ጣቢያ የወጣቶች ጤና ተጠሪና ከክልሉ ጤና ቢሮ የሚመለከታቸው አካላት ተሳትፈዋል ።
ጥቅም 30/2018 ዓ.ም