01/10/2022
Bronchitis /ብሮንካይትስ
ብሮንካይትስ የምንለው ህመም የሳንባችን ቱቦዎች በቫይረስ በባክቴርያ ወይንም በሌሎች ኬሚካሎች ምክንያት ሊከሰት ይችላል።
ብሮንካይትስ ህመም በሁለት ዓይነት ሊከፈል ይችላል።
1, (Acute Bronchitis) ለአጭር ጊዜ የሚቆይ በአብዛኛው በኢንፌክሽን ምክንያት የሚከሰት ሲሆን ለሳምንታት የሚቆይ ሲሆን አንዳንዴም ለወራት ሊዘልቅ የሚችልበት ሁኔታም ሊኖር ይችላል። ይህም የሚሆነው የሳንባችን ቱቦዎች ሙሉ ለሙሉ ለመዳን ረጅም ጊዜን ሊወስዱ ስለሚችሉ ነው። በአብዛኛው ጉንፋንን ተከትሎ የሚመጣም ነው።
2, (Chronic Bronchitis) ለረጅም ጊዜ የሚቆይ በአብዛኛው በአካባቢያዊ ምክንያቶች የሚከሰት ነው።
ሲጋራን ማጤስ ብሮንካይትስን በማስከተልና በማባባስ ቀዳሚውን ቦታ ይይዛል።ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ብሮንካይት ስ በአመት ሁለት ጊዜና ከዚያ በላይ እጅግ ሊባባስ የሚችል ሲሆን ይህም በቅዝቃዜ ወራቶች የሚከሰት ነው። ነገር ግን በጭራሽ የማይለቅ ሳል የአስም ውይንም የኒሞኒያ ምልክት ሉሆን ይችላል።
የብሮንካይትስ ምልክቶች ምንድን ናቸው?
*የማያቋርጥ ሳል አልፎ አልፎ አክታ የቀላቀለ
*ሲርሲርታ
*ብርድ ብርድ ማለት
*የደረት መጨምደድ
*ጉሮሮ የመከርከር ስሜት
*የሰውነት ህመም
*ትንፋሽ ማጠር
*ራስ ምታት ናቸው።
ሃኪምዎን ማማከር የሚገባው መቼ ነው?
በአብዛኛው ብሮንከይትስ በቤት ውስጥ ህክምናዎች የሚድን ሲሆን
* ሳሉ ከሶስት ሳምንት በላይ ከቆየ
*የማይበርድ ትኩሳት ከሶስት ቀናት በላይ ካለን
*ደም የቀላቀለ አክታ ከኖረን
*ፈጣን አተነፋፈስ ወይንም የደረት ውጋት ካለን
*ከፍተኛ ድካም ወይንም ግራ መጋባት ካለን
*በተደጋጋሚ ብሮንካይትስ የሚያጠቃን ከሆነ ወደ ሀኪም በመሄድ ህክምና ማድረግ ተገቢ ነው።
ብሮንካይትስ ህመም እንዴት ይታከማል?
ብሮንካይትስ የተጠቃ አንድ ሰው በቂ እረፍትን መውሰድ ፣ብዙ ፈሳሽ መጠጣት፣ የውሃ እንፋሎትን መታጠን እንዲሁም ሳል እንዲቀንስለት የሳል ማስታገሻ መድሃንቶችንና የራስ ምታት መድሀኒቶችን በመጠቀም ከህመሙ ሊያገግም ይችላል።
ይህ አይነት ህክምና ለአጭር ጊዜ ለሚቆየው ብሮንካይት ስ (Acute Bronchitis) የሚረዳ ሲሆን ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ብሮንከይትስ (Chronic Bronchitis) ሙሉ ለሙሉ የሚያድነው ህክምና የሌለው ሲሆን ህመሙን ለማስታገስ ግን የሚሰጡ ህክምናዎች አሉ።
እነኚም፥
*የሳል ማስታገሻ መድሀኒቶች
*ብሮንኮዳየሌተርስ ፥ የሳንባችንን ቱቦዋች እንዲከፈቱ የሚረዱ መድሀኒቶች
*ሙኮላይቲክስ ፥ አክታን በቀላሉ እንዲወገድ የሚያቀጥኑ መድሀኒቶች
*ኣንቲባዮቲክስ ፥ በባክቴሪያ ምክንያት የሚከሰቱ ኢንፌክሽኖችን ለማከም የሚረዱ መድሀኒቶች እንደአስፋላጊነቱ በሃኪም ሊታዘዝሎት ይችላል።
ህክምናውንም በአግባቡ እና በታዘዘልዎ መሰረት መጠቀም አስፈላጊ ነው።
ለተጨማሪ ጤና መረጃ የቴሌግራም ቻላናች ይቀላቀሉ የፈለጉትን ይጠይቁን በፍጥነት መልስ እንሰጦታታለን ሁሌም መልካም እንመኝሎታለን
https://t.me/+UbojqWNhpSZ01_-m