
28/07/2025
የ 2017 አመታዊ የ ስራ ሪፖርት ግምገማ እና የ 2018 አመታዊ የስራ ዕቅድ ዝግጅት፨፨፨
በዛሬው ዕለት የ አዋሽ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ የ18 ዲፓርትመንት ሀላፊዎችም ከጠዋቱ 2 ሰዐት በተገኙበት አመታዊ የስራ ሪፖርት ግምገማ እና ለ 2018 የስራ ዕቅዶችን የተቋሙ ሀላፊ አቶ አሊ አደም ባሉበት አስጀምረዋል ፣አክለውም የተቋሙ ሀላፊ የሪፖርት ግምገማው ለ 7 ቀናት የሚካሄድ ሲሆን በየ ዲፓርትመንቱ ያሉ ችግሮች ከስራው ጋር በተያያዘ ቀርቦ ለማህበረሰቡ የተሻለና ጥራት ያለው አገለግሎት ለመስጠትና ለ 2018 የተሻለ የስራ አፈፃፀሞችን ይበልጥ ለማድረግ እንሚረዳና ተቋሙም አስፈላጊውን ግምገማ አድርጎ ከጨረሰ በኋላ ክፍተት የታየባቸውን ዲፓርትመንቶች አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትልም ለማድረግም ዝግጁ እንደሆነ ገልፀዋል ፨፨፨