12/12/2025
Asaakî Macsenta 4tô Adda Ogaysime Pooliyoh Dalkak Aftabi Gaadih Qimbisiyyi Taddiira Haawash Qaafiyat Fanteenal Qaduuk Qimbissiisen.
አራተኛ ዙር የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ዛሬ የተጀመረ ሲሆን በዕለቱም የከተማው ጤና ፅ/ቤት ኃላፊ ሲ/ር ማሊካ ኢብራሂም ተገኝተው ዘመቻውን ያስጀመሩ ሲሆን ማንኛውም ዕድሜው ከ 5ዓመት በታች ያለ ህፃን መከተብ ስላለበት የከተማው ህብረተሰብ የተለመደ ትብብራቸውን እንዲያደርጉ ጠይቀዋል
የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ
****
ፖሊዮ (የልጅነት ልምሻ) ዘላቂ የአካል ጉዳትንና ሞትን የሚያመጣ አደገኛ በሽታ ነው። ለፖሊዮ በሽታ ምንም ዓይነት መድኃኒት ያልተገኘለት ሲሆን ዋና መከላከያ መንገዱም ክትባት ብቻ ነው።
ዘመቻው ከታህሳስ 3 እስከ 6 ቀን 2018 ዓ/ም ባሉት 4 ቀናት በሁሉም በከተማችን ባሉ ቀበሌዎች የሚሰጥ ይሆናል::