ዶ/ር ይስሃቅ ዘሪሁን /Dr.Yisihak Zerihun- Orthopaedic surgery /የአጥንት ህክምና

  • Home
  • Ethiopia
  • Awassa
  • ዶ/ር ይስሃቅ ዘሪሁን /Dr.Yisihak Zerihun- Orthopaedic surgery /የአጥንት ህክምና

ዶ/ር ይስሃቅ ዘሪሁን /Dr.Yisihak Zerihun- Orthopaedic surgery /የአጥንት ህክምና Help our people understand orthopaedic condition and modern way of orthopaedic treatment

Parosteal osteosarcoma--limb salvage hemicortical resection and cement reconstruction-በ 20 አመት ወጣት ላይ ከጉልበት ጀርባ የተከሰትን የ...
20/07/2025

Parosteal osteosarcoma--limb salvage hemicortical resection and cement reconstruction-በ 20 አመት ወጣት ላይ ከጉልበት ጀርባ የተከሰትን የአጥንት ካንሰር እግር ሳይቆረጥ ካንሰሩን ለይቶ የማስወገደ ሰርጀሪ አከናውነናል።ከመሰራቱ በፊት እና ከተሰራ በኃላ ያለውን የ ራጅ ፎቶ ከታች ያሰቀመጥኩላቹ ሲሆን ማንኛውም የህመም ስሜት የቀላቀለ እብጠት በአካላችን ላይ ስናስተዉል ሳንዘገይ ወደ ህክምና ተቋም በመሄድ ምርመራ ማድረግ ይመከራል።

22/06/2025

የአጥንት ስብራት እና ዘላቂ ጉዳቶቹ
===================
ℹ️ የአጥንት ስብራትን በወቅቱ አለማከም ለከባድ እና ዘላቂ የጤና እክሎች ሊዳርግ ይችላል።
ያልታከመ ስብራት የሚያስከትላቸው ዋና ዋና አደጋዎች የሚከተሉት ናቸው፤
ℹ️ የተሳሳተ የአጥንት መዳን (Malunion): አጥንቱ በተዛባ ሁኔታ ከዳነ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ህመም፣ የአካል ቅርጽ መዛባት እና የእንቅስቃሴ ገደብ ያስከትላል።
ℹ️ አለመፈወስ (Nonunion): አጥንቱ ጨርሶ ላይጠገን ይችላል፤ ይህም የማያቋርጥ ህመም እና የአካል አለመረጋጋት ይፈጥራል።
ℹ️ ከባድ ኢንፌክሽን (Osteomyelitis): በተለይ የተከፈተ ስብራት ለአደገኛ የአጥንት ኢንፌክሽን ሊያጋልጥ ይችላል።
ℹ️ ሌሎች ዘላቂ ጉዳቶች: ሥር የሰደደ ህመም፣ የመገጣጠሚያ መገተር፣ ሽባነት፣ የውስጥ ደም መፍሰስ እና በልጆች ላይ የእድገት መዛባት ሊከሰቱ ይችላሉ።
ስለዚህ፣ የአጥንት ስብራት ምልክቶች (ከባድ ህመም፣ እብጠት፣ ቅርጽ መለወጥ) ካዩ ወዲያውኑ የህክምና እርዳታ ያግኙ። ትክክለኛ እና ፈጣን ህክምና ከዘላቂ ጉዳት ይጠብቀዎታል።

🛑በባህላዊ ህክምና ምክንያት የሚመጣ አካለ ጎደሎነት ይቁም❗️

04/05/2025
26/04/2025
23/11/2024
30/09/2024

በአካላችን ላይ በሚገኝ ማንኛዉም መገጣጠሚያ ላይ የሚከሰትን የመድረቅ ችግር በማደንዘዣ ያለምንም ህመም እንዲንቀሳቀስ ማድረግ እንደሚቻል ያውቃሉ? ከታች የምትመለከቱት ቪዲዮም በሆስፒታላችን የአንድን ወጣት የደረቀ የ ጉልበት መገጣጠሚያ ያለምንም ህመም በማደንዘዣ እንዲንቀሳቀስ ስናደርግለት ያሳያል።

10/09/2024

መልካም አዲስ አመት
BAGA BIRRAAN ISINIIF BARI' E
HAPPY NEW YEAR

At AO- ADFA - pre basic - management of fracture course for Orthopeadic residents from Ethiopia ,somaliland and Madagasc...
04/09/2024

At AO- ADFA - pre basic - management of fracture course for Orthopeadic residents from Ethiopia ,somaliland and Madagascar .Haile is there as he is the Ambassador for the Australian doctors for Africa( ADFA) . Thank you Ao and ADFA for your support to improve the Ethiopian Orthopeadics.
, , ,

የ BOSAD Ethiopia ን ገፅ በመወዳጀት ቤተሰብ ይሁኑ
26/08/2024

የ BOSAD Ethiopia ን ገፅ በመወዳጀት ቤተሰብ ይሁኑ

የ BOSAD Ethiopiaን ገፅ በመወዳጀት ጠቃሚ መረጃዎችን ይከታተሉ።
21/08/2024

የ BOSAD Ethiopiaን ገፅ በመወዳጀት ጠቃሚ መረጃዎችን ይከታተሉ።

🧒🏽 ዛሬ የምናስተዋዉቃችሁ ህጻን ፍቅር ትባላለች (ለዚህ ጽሁፍ ሲባል ስሟ ተቀይሯል)።
ፍቅር የስምንት አመት ታዳጊ ስትሆን በትምህርትዋ የሁለተኛ ክፍል ጎበዝ እና ተጨዋች ተማሪ ነበረች፡፡ ለቤተሰቦችዋ የመጀመሪያ ልጅ የሆነችው ፍቅር ከእለታት በአንድ ቀን ከትምህርት ክፍለ ጊዜ በኋላ እንደተለመደው ከጓደኞችዋ ጋር በትምህርት ቤታቸው ግቢ ውስጥ እየተጫወቱ በመውደቋ ምክንያት የቀኝ ክርኗ ላይ ቀለል ያለ ጉዳት ያጋጥማታል። በወቅቱ የነበሩት የትምህርት ቤት መምህራኖች የበኩላቸዉን በመረባረብ የመጀመሪያ የህክምና እርዳታ ከሰጧት በኋላ ቀጣይ ህክምና እንድታገኝ ለወላጆችዋ በማሳወቅ ወደ ቤትዋ ይልኳታል።
🧒🏽ፍቅር ቤቷ ከደረሰች በኋላ ወላጆቿ የህክምና አማራጭ ያደረጉት በሰፈራቸው የሚገኘውን ባህላዊ ህክምና በመሆኑ፣ ግዜ ሳያባክኑ ወዲያዉኑ ይዘዋት ይሄዳሉ። እርሱም ታዲያ ፍቅር የቀኝ የክርን አጥንት ስብራት ሊኖራት እንደሚችል በመግለጽ የህጻኗን እጅ አሽቶ በቀርከሃ አጥብቆ በማሰር፣ በሶስት ቀን ልዩነት እየመጣች እንደገና መታሸት እና መታሰር እንዳለባት በመንገር ወደ ቤት ይሸኛቸዋል፡፡ ቤተሰቡቿም እንደተባሉት አደረጉ። ከአስር ቀን በኋላ ሳቂታዋ ፍቅር ስቃዩ እየባሰባት መጣ፡፡ ዛሬ ከሌላው ቀን በተለየ ሁኔታ ትንሿ ፍቅር እጅጉን ደክማለች፡፡ የሁኔታዉን መባባስ ያዩት ቤተሰቦችዋ ሌላ አማራጭ ስላልነበራቸው ወደ ህክምና ተቋም እያለቀሱ ይዘዋት መጡ። የሆነዉ ነገር ሁሉ ለሁላችንም እጀጉን አሳዛኝ እና ልብን የሚሰብር ነበር፡፡ ፍቅር ሙሉ ሰውነትዋ አብጦ፣ የሰውነቷም የሙቀት መጠን እጅግ በጣም ጨምሮ፣ ሲቃ በተናነቀው ድምጽ እያቃሰተች ትተነፍሳለች፡፡ አጥንቷ ወደ ውጪ ወጥቶ እና ኢንፌክሽኑ ተሰራጭቶ ከሞት አፋፍ ላይ ደርሳ ስለነበር አፋጣኝ የህይወት አድን ርብርብ በማድረግ የበሰበሰውን የቀኝ እጅ ከክርኗ በላይ በቀዶ ጥገና በማስወገድ ህይወቷን ማትረፍ ተችሏል፡፡ፍቅር በአሁኑ ሰአት እነዛ የጭንቅ ጊዜያት አልፈው አዲስ ቀን ለማየት የበቃች ብትሆንም የወደፊት እጣ ፈንተዋ ግን ያሳስባታል፡፡
🧒🏽 ፍቅር የመዉደቅ አደጋ እንደደረሰባት ወዲያዉኑ ወደ ጤና ተቋም እድሉን አግኝታ ብትሄድ ኖሮ፣ በቀላሉ ቆዳዋ ሳይከፈት ለእንደዚህ አይነት ስብራት ለማከም በተሰሩ ለሶስት ሳምንት ብቻ የሚቆዩ ሁለት ቀጫጭን ሽቦዉች በማስገባት እና በጀሶ በመደገፍ ወዲያዉኑ ወደ ትምህርት ገበታዋ በሙሉ ጤንነት ትመለስ ነበር። እንደዚህ አይነቱ በቀላሉ መታከም እና መስተካከል የሚችል ቀላል የአካል ጉዳት የህጻናትን አካል በማሳጣት ለቋሚ አካለ ጎደሎነት እንዲዳርግ መፍቀድ ተገቢ ስለማይሆን ሁላችንም የበኩላችንን እንወጣ።
🧒🏽 ፍቅር የኔም፣ ያንተም፣ ያንችም፣ የሁላችንም ልጅ ናት።
👉እንደ ፍቅር አይነት ያሉ ህጻናት ትክክለኛዉን ህክምና እንዲያገኙ በማድረግ ከቋሚ የአካል ጉዳት በጋር እንከላከል።

የማህበራዊ ድረገጾቻችንን ለመቀላቀል
📱ቴሌግራም (https://t.me/BOSADEthiopiaGroup)
📱ፌስቡክ (https://www.facebook.com/profile.php?id=61560501783370&mibextid=LQQJ4d)
📱ኢንስታግራም (https://www.instagram.com/bosadethiopia?igsh=ZXJzZ3hvNGhoemE4&utm_source=qr)
📱ቲክቶክ (https://www.tiktok.com/=8o6caTHTg7Z&_r=1)

የሞባይል አፕሊኬሽኑን ለማውረድ
📲 https://apps.apple.com/us/app/bosad/id6478068016
📲 https://play.google.com/store/apps/details?id=com.bosad.booklet

🛑No more disability accepted from traditional bone setting!
🛑በባህላዊ ህክምና ምክንያት የሚመጣ አካለ ጎደሎነት ይቁም!

16/08/2024

👉🏽ባለፉት ክፍሎች ላይ የመውደቅ አደጋ ለደረሰበት/ባት ልጅ ምን አይነት የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ እና ምንምን አይነት ጥንቃቄዎችን ማድረግ አለብን የሚለውን አይተናል።

🛑አሁን ደግሞ ማድረግ ከሌለብን ነገሮች መካከል አንዱ የሆነውን እንንገራችሁ።

📌 የተጐዳውን ህፃን ከወደቀበት ስፍራ ስናነሳ እና የተጎዳውን ቦታ እንዲሁም ሌላ ተጨማሪ ጉዳት መኖሩን ለማረጋገጥ ሰውነቱን በምናንቀሳቅስበት ጊዜ ከፍተኛ የሆነ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል።

📌በምናንቀሳቅስበትም ወቅት ልጁን/ልጅቷን በተስተካከለ መሬት ላይ መሆኑን/መሆኗን ማረጋገጥ፣ ካለን ደግሞ በአከርካሪ መደገፊያ ቦርድ (spine board) ላይ በማስተኛት እና የትኛዉ የሰዉነት ክፍል እንደተጎዳ/ች እና ከፍተኛ ህመም እንደሚሰማው/ ሚሰማት መጠየቅ አለብን፡፡
ልጁ/ልጅቷ ያልተናገረውን/ችውን የተደበቀ ጉዳት ለመለየት ከራስ ቅል እስከ እግር ጥፍር ድረስ ምርመራ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

☑️እንደዚህ ማድረግ ከቻልን የመውደቅ አደጋ ይደረሰበትን/ባትን ልጅ ከተጨማሪ የአከርካሪ እንዲሁም የ ህብረ-ሰረሰር ጉዳት መታደግ እንችላለን።
በአቅራቢያችሁ ስለመጀመሪያ የህክምና እርዳታ የሰለጠኑ ባለሞያዎች ካገኛችሁ እነሱ በሚሰጧችሁ መመሪያ ብቻ አንቀሳቅሷቸው።

የማህበራዊ ድረገጾቻችንን ለመቀላቀል
📱ቴሌግራም (https://t.me/BOSADEthiopiaGroup)
📱ፌስቡክ (https://www.facebook.com/profile.php?id=61560501783370&mibextid=LQQJ4d)
📱ኢንስታግራም (https://www.instagram.com/bosadethiopia?igsh=ZXJzZ3hvNGhoemE4&utm_source=qr)
📱ቲክቶክ (https://www.tiktok.com/=8o6caTHTg7Z&_r=1)

የሞባይል አፕሊኬሽኑን ለማውረድ
📲 https://apps.apple.com/us/app/bosad/id6478068016
📲 https://play.google.com/store/apps/details?id=com.bosad.booklet

🛑No more disability accepted from traditional bone setting!
🛑በባህላዊ ህክምና ምክንያት የሚመጣ አካለ ጎደሎነት ይቁም!

Address

Awassa

Telephone

+251924739592

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ዶ/ር ይስሃቅ ዘሪሁን /Dr.Yisihak Zerihun- Orthopaedic surgery /የአጥንት ህክምና posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to ዶ/ር ይስሃቅ ዘሪሁን /Dr.Yisihak Zerihun- Orthopaedic surgery /የአጥንት ህክምና:

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram