
18/09/2025
የአለም የህሙማን ደህንነት ቀን /World Patient Safety Day/ በሀዋሳ አላሙራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ተከበረ።
********************************************
ዛሬ በቀን 8/01/18 ዓም በአላሙራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የአለም የህሙማን ቀን ስለ ህሙማን ደህንነት ግንዛቤ ማስጨበጫ በመስጠት፣ የፅዳት ዘመቻ በማድረግ እንዲሁም የጤና ትምህርት በመስጠት ተከብሯል።
“ደህንነቱን የጠበቀ ክብካቤ ለሁሉም ጨቅላ ህፃናትና ህፃናት” በሚል መሪ ቃል በተካሄደው ክብረ በአል ላይ የሆስፒታል ማናጅመንት የስራ ክፍል አስተባባሪዎች እና ስታፍ ተሳታፊ ሆነዋል።
ልንከላከላቸው የምንችላቸውን የህክምና ሞቶችን እንዲሁም ጉዳቶችን ማስቀረት ዋነኛ ትኩረታችን ሊሆን እንደሚገባ ያሳሰቡት የአላሙራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ አቶ ዮሴፍ ዮዌ፣ ህሙማንን ከፍ ሲል ደህንነታቸውን ጠብቆ ማከም፣ ዝቅ ሲልም አለመጉዳት መርሀችን ሊሆን ይገባል ብለዋል።
የበአሉ ተሳታፊዎችም በቀረበው የግንዛቤ ማስጨበጫ ላይ የተለያዩ ሀሳቦችን አንስተው ሰፊ ውይይት የተካሄደ ሲሆን፣ የህሙማንን ደህንነት ጠብቆ አገልግሎት ለመስጠት የገቡትንም ቃል-ኪዳን አድሰዋል።