23/01/2026
የጉበት ላይ ስብ (ከአልኮል መጠጥ ውጪ)
🩺 የጉበት ላይ ስብ ምንድነው ?
👉 የጉበት ህዋሳት በስብ ክምችት ሲሸፈኑና አንዳንድ ጊዜም በውስጣቸው ሲሰገሰግ የጉበት ላይ(Steatohepatitis) ስብ እንላለን።
🩺 መንስሄዎቹ ምንድናቸው ?
👉 በአጠቃላይ ጤናማ ያልሆነ የአኗኗር ዘይቤን ተከትሎ የሚመጣ ሲሆን ፡
- የሰውነት የኢንሱሊን መጠን መብዛትና
- ከመጠን ያለፈ ውፍረት ዋነኛ መንስሄዎች ናቸው።
🩺 በምንና እንዴት ይታወቃል ?
👉 የጉበት ላይ ስብ ዋነኛው ማረጋገጫ ምርመራ ከጉበት ላይ ተወስዶ በሚመረመር ናሙና ቢሆንም በአልትራሳውን መሳሪያ በተለይ ከፍ ያለው ደረጃ ላይ በቀላሉ ማወቅ ይቻላል ።
🩺 የህመም ደረጃዎቹ ምንድናቸው ?
👉 የጉበት ላይ ስብ ደረጃዎች በአጠቃላይ በአልትራሳውን እይታ በሦስትይመደባል ፡
1. ዝቅተኛ
2. መካከለኛ እና
3. ከፍተኛ ደረጃ በመባል
🩺 ምልክቶቹ ምንድናቸው ?
👉 ከፍተኛ ደረጃ ካልደረሰ በስተቀር የጉበት ላይ ስብ የተለየ ምልክት የለውም
👉 አልፎ አልፎ በቀኝ የላይኛው የሆድ ክፍል የህመም ስሜት ሊኖር ይችላል
🩺 በጊዜ ካልታከመ ምን ሊያስከትል ይችላል ?
👉 የጉበት ላይ ስብ በጊዜ ካልታከመ የጉበት ቁስለት ፤ ካንሰር ብሎም የማይመለስ የጉበት መድከም ሊያስከትል ይችላል ።
🩺 እንዴት መከላከል ይቻላል ?
👉 የአኗኗር ዘይቤን ማስተካከል ፡
- ክብደትን መቀነስ
- ጤናማ አመጋገብ
- የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ዋነኞቹ ናቸው ።
🩺 እንዴት ይታከማል ?
👉 የጤና ባለሙያው የጉበት ላይ ስብ መኖሩን ካረጋገጠ በኋላ ፡
- ቫይታሚን ኢ
- ፓዮግሊታዞን
- የኮለስትሮል መድዓኒትና
- እንደአስፈላጊነቱ ሜትፎርሚን በመባል የሚታወቀውን የስኳር ህመም መድዓኒት ሊታዘዝ ይችላል ።
‼️ ያስታውሱ ፡
👉 የጉበት ላይ ስብ "ድምጽ አልባ ገዳይ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች" ከሚባሉት ውስጥ ዋነኛው ሲሆን መከላከሉና በጊዜ መታከሙ እነዚህን ጉዳቶች ለማስቀረት ይረዳል።
#የጉበትስብ
🙏
Dr Elias G
አድራሻ ፡ ሎጊታ አሮጌው ስታድየም ጎን ከማውንቶሊቭ ት /ት ፊት ለፊት