Ethiopian Pharmaceutical Supply Agency Gondar Branch

Ethiopian Pharmaceutical Supply Agency Gondar Branch I supply !!

እንቁጣጣሽ!!!🌼!!!
11/09/2023

እንቁጣጣሽ!!!🌼!!!

ጎንደር ቅርንጫፍ መስሪያቤት የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር አከናወነ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨የኢትጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ጎንደር ቅርንጫፍ መስሪያ ቤት  ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ  ከጎንደር...
22/07/2023

ጎንደር ቅርንጫፍ መስሪያቤት የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር አከናወነ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

የኢትጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ጎንደር ቅርንጫፍ መስሪያ ቤት ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ ከጎንደር ከተማ አስተዳደር በተረከበው ቦታ ላይ በየአመቱ ችግኝ በመትከል ፣ በመንከባከብ እና ጥበቃ በማድረግ የአረንጓዴ አሻራውን ሲያሳርፍ መቆየቱ የሚታወቅ ሲሆን፡፡

በዚህም ኢትዬጵያን አረንጓዴ ለማልበስ በዛሬዉ እለት የጎንደር ቅርንጫፍ ሰራተኞች ከ 500 በላይ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር ተከናውኗል ።

#ማገልገል ክብር ነዉ

30/03/2023
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ጎንደር ቅርንጫፍ የጎንደር ከተማ በሚያዘጋጀው የጤና እግር ኳስ ውድድር የማራኪ ክፍለ ከተማን 11ለ 3 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸነፈ።
31/01/2023

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ጎንደር ቅርንጫፍ የጎንደር ከተማ በሚያዘጋጀው የጤና እግር ኳስ ውድድር የማራኪ ክፍለ ከተማን 11ለ 3 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸነፈ።

ቅርንጫፉ መስሪያ ቤቱ የሁለተኛ ሩብ አመት የቆጠራውን እያካሄደ ይገኛል።የመጋዝን አያያዝ እና አስተዳደርን በማዘመን አመታዊ ቆጠራ ወደ ሩብ አመት ቆጠራ እንዲሁም ቆጠራው የሚወስደውን ግዜ በአ...
14/01/2023

ቅርንጫፉ መስሪያ ቤቱ የሁለተኛ ሩብ አመት የቆጠራውን እያካሄደ ይገኛል።
የመጋዝን አያያዝ እና አስተዳደርን በማዘመን አመታዊ ቆጠራ ወደ ሩብ አመት ቆጠራ እንዲሁም ቆጠራው የሚወስደውን ግዜ በአማካኝ ከ15 ቀን ወደ አንድ ቀን ማውረድ የቻለው የመአኤ ጎንደር ቅርንጫፍ በታታሪ ሰራተኞቹ በመታገዝ የ2015 ዓ/ም የሁለተኛ ሩብ አመት የቆጠራውን በብቃት እና በጥራት ከአንድ ቀን በታች ለመጨረስ አልም ቆጠራውን እያካሄደ ይገኛል።

ሁለቱ አጋር ተቋማት በደም ልገሳ እየተሳተፉ ይገኛል...የመድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ጎንደር ቅርንጫፍ እና የጠዳ ሳይንስ ኮሌጅ በጋራ የስምምነት ሰነድ በመፈራረም ስራ ከጀመሩበት ግዜ ጀምሮ በጋ...
12/01/2023

ሁለቱ አጋር ተቋማት በደም ልገሳ እየተሳተፉ ይገኛል...
የመድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ጎንደር ቅርንጫፍ እና የጠዳ ሳይንስ ኮሌጅ በጋራ የስምምነት ሰነድ በመፈራረም ስራ ከጀመሩበት ግዜ ጀምሮ በጋራ በርካታ ተግባራትን እየፈፀሙ ያሉ ተቋማት ሲሆኑ የዚህ ተግባር አንዳ አካል የሆነው የደም ልገሳ መርሀግብር በየሶስት ወሩ በሁለቱ ተቋማት ሰራተኞች ደሜን ለወገኔ በሚል መሪ ቃል ለአምስተኛ ግዜ ደም እየለገሱ ይገኛል።
Teda Health Science College

06/01/2023

እንኳን ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሰን፤ አደረሳችሁ!

በዓሉ የሠላም፣ የፍቅር እና የደስታ እንዲሆን እንመኛለን!

ማገልገል ክብር ነው!!!!!

ከመአኤ ጎንደር ቅርንጫፍ!!

27/12/2022

መልካም አፈፃፀም ላሳዩ የስራ ክፍሎች አውቅና በአግሎቱ ተሰጣቸው።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

ለቅርንጫፍ መስሪያ ቤቶች ፣ ዳይሬክቶሬቶች ፣ ቡድን መሪዎች እንዲሁም ሴት አመራሮች እውቅና የተሰጠ ሲሆን ሀገር በጦርነት በነበረችበት ወቅት የህክምና ግብአት ላቀረቡ ቅርንጫፎችም ልዩ ሽልማት ተሰጥቷል፡፡

በቅርንጫፍ አምሰት ጥሩ አፈጻጸም ያላቸው ቅርንጫፎች አዲስ አበባ ቁጥር 1፣ ጎንደር ፣ ሃዋሳ ፣ አዳማ እና ባህር ዳር ።

እንደ ሃገር ጦርነት እና በግጭት በነበረበት ወቅት የህክምና ግብአትን ለህብረተሰቡ በማቅረብ ከመንግስት አካላት ጋር በመቀናጀት ያደረሱ እንደ ደሴ ፣ ነቀምት ፣ ጎንደር ፣ ነጌሌ ቦረና ፣ ሰመራ ፣ ባህር ዳር እና አሶሳ ቅርንጫፎች ልዩ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡

የመድኃኒትና የህክምና መገልገያዎች ኮንትራት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ፤ የመጋዘን አያያዝና ክምችት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት እና የመድኃኒትና የህክምና መገልገያዎች ጥራትና ቁጥጥር ዳይሬክቶሬቶች ባስመዘገቡት ውጤት እዉቅና አግኝተዋል፡፡

ጥሩ አፈፃፀም ላመጡ ሴት ሃላፊዎችም አገልግሎቱ እዉቅና የሰጠ ሲሆን የድሬደዋ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ አስናቀች ለችሳ እና የመጋዘን አያያዝና ክምችት አስተዳደር ዳይሬክተር ወ/ሮ ገዳምነሽ አስፈራው እውቅና ተሰጥቷል ፡፡

ሽልማቱ የበለጠ ለመስራት የሚያነሳሳቸው መሆኑን እና ውጤት ያመጣን መሸለም ባህል መሆን ይገባዋል ሲሉ እውቅናውን የተቀበሉ የሥራ አመራሮች ተናግረዋል።

#ማገልገል ክብር ነው።

አማኑኤል ወርቃየሁ

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ጎንደር ቅርንጫፍ በ2013 ዓ/ም በአጠቃላይ ከቅርንጫፍ መስሪያ ቤቶቾ አንደኛ በመሆን ተሸላሚ የነበር መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን በ2014 ዓ/ም በተደረገው ...
26/12/2022

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ጎንደር ቅርንጫፍ በ2013 ዓ/ም በአጠቃላይ ከቅርንጫፍ መስሪያ ቤቶቾ አንደኛ በመሆን ተሸላሚ የነበር መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን በ2014 ዓ/ም በተደረገው ግምገማ ቅርንጫፉ በወቅታዊ ሁኔታ ላይ የነበር ቢሆንም በአሰራር እና በአሰመዘገበው ውጤት የላቀ አፈፃፀም በማስመዘገብ ተሸላሚነቱን ማስጠበቅ ችሏል።
በተጨማሪም ቅርንጫፍ መስሪያ ቤቱ አገረ በገጠማት ፈተና በህክምናው ዘረፍ የግብአት አቅርቦት ላደረገው ከፍተኛ አስተዋጸኦ የዋንጫ እና የምስጋና ሰርተፍኬት ተሸላሚ መሆን ችሏል።

25/11/2022
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ጎንደር ቅርንጫፍ የ2015 በጀት አመት አንደኛ ሩብ አመት የስራ አፈፃፀም ግምገማ በቆላድባ ከተማ በማካሄድ ላይ ይገኛል።አገር በገጠማት ፈተና የግብአት...
22/10/2022

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ጎንደር ቅርንጫፍ የ2015 በጀት አመት አንደኛ ሩብ አመት የስራ አፈፃፀም ግምገማ በቆላድባ ከተማ በማካሄድ ላይ ይገኛል።
አገር በገጠማት ፈተና የግብአት አቅርቦቱ ላይ የአንበሳውን ድርሻ የሚወስደው ቅርንጫፉ በአጠቃላይ ከ 288 ሚሊዮን በላይ ግብአት አሰራጭቷል።
ተቋሙ ደራሽ ስራዎች ቢበዙበትም በመደበኛ ስራ ተጽዕኖ ሳያድርበት እየሰራ እንደሚገኝ እና ከአለፈው በጀት አመት አፈፃፀም እንዲሁም ከእቅድ አንፃር አመርቂ ውጤት እያስመዘገበ እንደሚገኝ የአፈፃፀም ሪፖርት ያቀረብት ተወካይ የእቅድ ክትትል ባለሞያ አቶ ደረጀ ሙሌ ገልፀዋል።

ጎንደር ቅርንጫፉ የ2015 የመጀመሪያው ሩብ አመት አጣቃላይ ቆጠራ በአንድ ቀን አጠናቆ ወደ ስራ ተመለሰ ::አገር በገጠማት ፈተና ግብአት በማድረስ እንዲሁም ዕለታዊ ስራዎቹ ፉታ ቢያሳጡትም ከ...
15/10/2022

ጎንደር ቅርንጫፉ የ2015 የመጀመሪያው ሩብ አመት አጣቃላይ ቆጠራ በአንድ ቀን አጠናቆ ወደ ስራ ተመለሰ ::
አገር በገጠማት ፈተና ግብአት በማድረስ እንዲሁም ዕለታዊ ስራዎቹ ፉታ ቢያሳጡትም ከመርህ ዝንፍ የማይለው በቁርጠኝነት ስራዎችን ለመከወን ፈተና የማይበግረው የቅርንጫፉ ስራተኛ በ2014 የጀመረውን በየሩብ አመቱ ቆጠራ ማካሄድ በ2015 በጀት አመትም የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ጎንደር ቅርንጫፍ ዛሬ 05/02/2014 በአንድ ቀን ቆጠራውን አጠናቆ ወደ መደበኛ ስራው ተመልሷል።

09/09/2022
ጎንደር ቅርንጫፉ ድጋሚ ተመሰከረለት …………..                                                                                           ...
08/09/2022

ጎንደር ቅርንጫፉ ድጋሚ ተመሰከረለት ………….. የመድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ጎንደር ቅርንጫፍ ጷጉሜ 3/2013 ዓ/ም የአለም አቀፍ የጥራት አስተዳደር በመተግበር የ Iso 9001:2015 ስረተፍኬት ባለቤት መሆኑ ይታወቃል፡፡ በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት ገምግሞ የጥራት እዉቅናዉን የሰጠዉ የኢትዮጲያ ተስማሚነት ጥራት ኤጀንሲ በየአመቱ የጥራት አስተዳደር ተግበራዉ ቀጣይነት ፣ መሻሻሎችን እና ሰነዶችን መሰረት ኦዲቲ (Surveillance Audit) የሚያደርጉ በመሆኑ በቅርንጫፉ በአካል በመገኝት ኦዲቱን (Surveillance Audit) አከናዉኗል፡፡ የኦዲቱ ዉጤት የተሰጠዉን ሰርተፍኬት የሚያስቀጥል ፣ የሚያሳግድ ወይም የሚያሰነጥቅ ሊሆን እንደሚችል ያሳዎቁት ኦዲተሮቹ የኦዲቱ ግብም የጥራት አስተዳደር ቀጣይነቱን ፣ የተደረጉ መሻሻሎችን እና ሰነዶችን በተቀመጠዉ እና አለም አቀፍ ስታንዳርድ መሰረት የተከተለ ሲሆን በኦዲቱ መሰረትም ቅርንጫፉ አለማቀፍ የጥራት መመዘኛወችን ያሟላ መሆኑ የተረጋገጠ በመሆኑ ቅርንጫፉ የጥራት አስተዳደር ያሰቀጠለ መሆኑ ተመስክሮለታል፡፡

የመድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ጎንደር ቅርንጫፍ በሐምሌ ወር 2011 ዓ/ም የአረንጓዴ አሻራ ለማሰቀመጥ ከጎንደር ከተማ አስተዳደር የችግኝ ቦታ በመረከብ በወቅቱ የነበረዉን የኤጀንሲዉ አመታዊ የስ...
26/08/2022

የመድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ጎንደር ቅርንጫፍ በሐምሌ ወር 2011 ዓ/ም የአረንጓዴ አሻራ ለማሰቀመጥ ከጎንደር ከተማ አስተዳደር የችግኝ ቦታ በመረከብ በወቅቱ የነበረዉን የኤጀንሲዉ አመታዊ የስራ አፈፃፀም ግምገማ ተከትሎ በግዜዉ በነበሩ የኤጀንሲዉ ዋና ዳይሬክተር ፣ ም/ዋና ዳይሬክተሮች እንዲሁም የጤና ሚኒሰተር አመራሮች በተገኙበት የችግን በተከለለዉ ቦታ ላይ ችግኞች የተተከሉ ሲሆን ለችግኙ በየግዜዉ አስፈላጊዎን እንክብካቤ ሲያደርግ የቆየዉ ቅርንጫፉ በዚህ አመትም አረንጓዴ አሻራችን እናስቀጥላለን መትከል ብቻ ሳይሆን ተንከባክበን እናጸድቃለን በሚል መሪ ቃል መላ የመ/ቤቱ ሰራተኞች በነቂስ በመዉጣት ችግኞችን የመንከባከብ እንዲሁም ባለ ክፍት ቦታ ከከተማዉ ግብራና ጽ/ቤት ያገኛቸዉን 500 (አምስት መቶ) አዲስ ችግኞችን በተለያየ ቦታ መትከል ተችሏል፡፡ Gondar city communication Teda Health Science College

Address

Ethiopia, Amhara, Gondar
Azezo (4)

Telephone

+251918725144

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Pharmaceutical Supply Agency Gondar Branch posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Ethiopian Pharmaceutical Supply Agency Gondar Branch:

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram