Mekaneselam General Hospital

Mekaneselam General Hospital This page is used for sharing new things/over all services related to the hospital and gain best con

የትምህርት ዕድልከዲፕሎማ ወደ ዲግሪ
13/12/2022

የትምህርት ዕድል

ከዲፕሎማ ወደ ዲግሪ

07/09/2022
የመካነ  ሰላም ጠቅላላ ሆስፒታል ከፍለው መታከም ለማይችሉ ዜጎች የክረምት በጎ ፍቃድ የነፃ ምርመራና ህክምና አገልግሎት እየሰጠ ነው።==========================መካነ ሰላም፣ ነ...
22/08/2022

የመካነ ሰላም ጠቅላላ ሆስፒታል ከፍለው መታከም ለማይችሉ ዜጎች የክረምት በጎ ፍቃድ የነፃ ምርመራና ህክምና አገልግሎት እየሰጠ ነው።
==========================
መካነ ሰላም፣ ነሀሴ 16/2014ዓ.ም (መካነ ሰላም ኮሙኒኬሽ) የመካነ ሰላም ጠቅላላ ሆስፒታል በክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት "በጎነት ለጤናችን" በሚል መሪ ቃል ከፍሎ የመታከም አቅም ለሌላቸው ዜጎች ከዛሬ ጀምሮ ለ6 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ የነፃ ምርመራና ህክምና አገልግሎት በበጎ ፍቃደኛ የህክምና ባለሙያዎች መስጠት ጀምሯል።

የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሀሰን አሊ እንደገለፁት የክረምት በጎ ፍቃድ የነፃ ምርመራና ህክምና አገልግሎቱ አላማ በተለያዩ በሽታዎች እየተሰቃዩ ከፍሎ የመታከም አቅም ለሌላቸው የህብረተሰብ ክፍሎችን ከስቃያቸው ለመታደግ፣ ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ለማህበረሰቡ የተጠናከረ ትምህረት ለመስጠትና ማህበረሰቡ ወደ ጤና ተቋም መጥቶ የመታከም ልምዱ እንድዳብር ለማድረግና ያለመ ነው ብለዋል።

በዚህ መሰረት በበጎ ፍቃድ አገልግሎቱ በቢሊ የመጀመሪያ ጤና ክብካቤ አሃድ ለ61 ነፍሰ ጡር እናቶች የአልትራሳውንድ ምርመራና የህክምና አገልግሎት ተሰጥቷል ያሉት ስራስኪያጁ የደም ግፊት፣ የስኳር፣ የአይን እንድሁም የኤች አይቪ ምርመራና የህክምና አገልግሎትን ጨምሮ በዛሬው ዕለት 220 ለሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች በበጎ ፍቃደኛ ባለሙያዎች የነፃ ምርመራና ህክምና እንደተሠጠ ገልጸዋል።

ከዚህ ጎን ለጎን ባለሙያዎቹ ተገቢውን አገልግሎት እንድሰጡ በህክም ባለሙያዎች የክሊኒካል ኦድት ስራ ሲሰራ መዋሉን ገልፀው ወደፊትም የማህበረሰባችንን የጤና ችግሮችን ለመፍታት ጥራት ያለውና ፍትሀዊ የሆነ የህክምና አገልግሎት ለመስጠት በትኩረት እንሰራለን ብለዋል።

የመካነ ሰላም ጠቅላላ ሆስፒት የነርሶች ዳይሬክተር እና የቢኤስሲ ነርሲንግ ባለሙያ የሆኑት አማረ ጋሻው በበኩላቸው የሆስፒታሉ ባሙያወች አለ ምንም አስገዳጅነት በራሳቸው ተነሳሽነት በበጎ ፍቃድ አገልግሎት ከፍሎ የመታከም አቅም ለሌላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች የምርመራና የህክምና አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን ተናግረዋል።

የምርመራና የህክምና አገልግሎቱ ሲደረግላቸው ያነጋገርናቸው የህብረተሰብ ክፍሎችም በበኩላቸው የመካነ ሰላም ጠቅላላ ሆስፒታ በነፃ በሰጣቸው የህክምና አገልግሎት መደሰታቸውን ገልፀዋል።

በመካነ ሰላም ጠቅላላ ሆስፒታል የክረምት በጎ ፍቃድ የምርመራና የህክምና አገልግሎቱ እስከ ነሀሴ 21/2014 ዓ.ም ድረስ ለስድስት ተከታታይ ቀናት ይሰጣል።

21/08/2022
የቅጥር ማስታወቂያየመካነ ሠላም ጠቅላላ ሆስፒታል ፋርማሲ ፕሮፌሽናል/Pharmacy Professional/በቅጥር አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡1. የሚቀጠርበት መ/ቤት ስም መካነ ሰላም ጠቅላላ ...
02/08/2022

የቅጥር ማስታወቂያ
የመካነ ሠላም ጠቅላላ ሆስፒታል ፋርማሲ ፕሮፌሽናል/Pharmacy Professional/በቅጥር አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
1. የሚቀጠርበት መ/ቤት ስም መካነ ሰላም ጠቅላላ ሆስፒታል
2. ክፍት የስራ መደቡ
a. መጠሪያ ፋርማሲ ፕሮፌሽናል/Pharmacy Professional
b. ደረጃ XII
c. ደመወዝ 7071
d. ብዛት 01/አንድ/
e. የስምሪት ሁኔታ በቋሚነት
ከታች በቀረበዉ ማስታወቂያ መሰረት መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች በአካል መካነ ሰላም ጠቅላላ ሆስፒታል የሰዉ ሀብት ቡድን ቢሮ ቁጥር 40 በአካል በመምጣት ወይም በEmail አድራሻችን mekaneselamhospitalhr2012@gmail.com መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን በEmail የምትመዘገቡ አመልካቾች የፈተና ቀን ኦርጅናል መረጃ ይዛችሁ መቅረብ ይኖርባችኋል፡፡

የቅጥር ማስታወቂያየመካነ ሠላም ጠቅላላ ሆስፒታል የህጻናት ህክምና ነርስ ፕሮፌሽናል/Pediatric Nurse Professional/በዉጭ ዝዉዉር አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡1. የሚቀጠርበት ...
25/07/2022

የቅጥር ማስታወቂያ
የመካነ ሠላም ጠቅላላ ሆስፒታል የህጻናት ህክምና ነርስ ፕሮፌሽናል/Pediatric Nurse Professional/በዉጭ ዝዉዉር አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
1. የሚቀጠርበት መ/ቤት ስም መካነ ሰላም ጠቅላላ ሆስፒታል
2. ክፍት የስራ መደቡ
a. መጠሪያ የህጻናት ህክምና ነርስ ፕሮፌሽናል/Pediatric Nurse Professional/
b. ደረጃ በያዙት
c. ደመወዝ በያዙት
d. ብዛት 01/አንድ/
e. የስምሪት ሁኔታ በቋሚነት
ከታች በቀረበዉ ማስታወቂያ መሰረት መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች በአካል መካነ ሰላም ጠቅላላ ሆስፒታል የሰዉ ሀብት ቡድን ቢሮ ቁጥር 40 በአካል በመምጣት ወይም በEmail አድራሻችን mekaneselamhospitalhr2012@gmail.com መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን በEmail የምትመዘገቡ አመልካቾች የፈተና ቀን ኦርጅናል መረጃ ይዛችሁ መቅረብ ይኖርባችኋል፡፡

የቅጥር ማስታወቂያ  የመካነ ሠላም ጠቅላላ ሆስፒታል የአካባቢ ጤና አጠባበቅ ባለሙያ/environmental health ባለሙያ በቅጥር አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡1. የሚቀጠርበት መ/ቤት ስም...
21/07/2022

የቅጥር ማስታወቂያ
የመካነ ሠላም ጠቅላላ ሆስፒታል የአካባቢ ጤና አጠባበቅ ባለሙያ/environmental health ባለሙያ በቅጥር አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
1. የሚቀጠርበት መ/ቤት ስም መካነ ሰላም ጠቅላላ ሆስፒታል
2. ክፍት የስራ መደቡ
2.1. መጠሪያ የአካባቢ ጤና አጠባበቅ ባለሙያ/environmental health
2.2. ደረጃ XI
2.3. ደመወዝ 6193/ስድስት ሽህ አንድ መቶ ዘጠና ሶስት/ብር
2.4. ብዛት 1/አንድ/
3. የስምሪት ሁኔታ በቋሚነት
ከታች በቀረበዉ ማስታወቂያ መሰረት መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች በአካል መካነ ሰላም ጠቅላላ ሆስፒታል የሰዉ ሀብት ቡድን ቢሮ ቁጥር 40 በአካል በመምጣት ወይም በEmail አድራሻችን mekaneselamhospitalhr2012@gmail.com መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን በEmail የምትመዘገቡ አመልካቾች የፈተና ቀን ኦርጅናል መረጃ ይዛችሁ መቅረብ ይኖርባችኋል፡፡

21/05/2022

Address

Borena
Bahir Dar
0983962578

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mekaneselam General Hospital posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Mekaneselam General Hospital:

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram

Category