Medan Clinic / መዳን ክሊኒክ

Medan Clinic / መዳን ክሊኒክ A Healthcare You Rely On!

03/09/2024

በዓለማችን ከሚኖሩ ስምንት ሰዎች አንዱ የአእምሮ ህመምተኛ (with Mental disorder) እንደሆነ ያውቃሉ? (WHO 2024 data)
እንግዲያውስ ልንገርዎ 75% የመታከም ሀሳብም የለው።

09/08/2024

Medan@Home መዳን@ቤትዎ
Virtual Home care የቨርችዋል የቤት ለቤት ህክምና
ይደዉሉ ይመዝገቡ ይታከሙ!

ጤና ሁሉም ነገር ነው! ህይወታችን ጤናችን ነው። ቀኖቻችን የአካላዊ፣ አእምሮአዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ጤናችን ሁኔታ ናቸው። /our days are our physical, mental, econ...
04/08/2024

ጤና ሁሉም ነገር ነው!
ህይወታችን ጤናችን ነው። ቀኖቻችን የአካላዊ፣ አእምሮአዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ጤናችን ሁኔታ ናቸው። /our days are our physical, mental, economical and social health conditions./
በምንም ጉዳይ: በማንኛውም ጊዜ: በየትም ስፍራ ስለእርስዎና ልጆችዎ ሁኔታ በሙሉ ልብ የሚያማክሩት :- ብቃቱ የተረጋገጠ፣ ኃላፊነት የሚሰማው፣ የረጅም አመታት ልምድና የጥሩ ሀኪሞች ግንኙነት / network/ ያለው በመልካም ሥነ ምግባርና በጥብቅ የሙያ ፕሮቶኮል የተመሠገነ፣ በጥራቱ ደንበኞች ዋስ የሚጠ'ሩለት ታማኝ የቤተሰብዎ የጤና አጋር ማን ነው?!
☎️+251984142737
Telegram: https://t.me/+KE9pazFgbCg1ZjJk

ይደዉሉ: ይመዝገቡ :መዳን የቤተሰብ ሀኪምዎን 24/7 በነፃ ያማክሩ!

የህፃናትና ታዳጊዎች ህክምና: የማህፀንና ፅንስ: የውስጥ ደዌና የቀዶ ጥገና፤ የነርቭና የመገጣጠሚያ ፤የቆዳና የፀጉር ፤ የጥርስና አፍ ውስጥ፣ የውፍረት የሱስና የድብርት ህክምና!
በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ የት መሄድ እንዳለብዎት ሳያማክሩን አይወስኑ።
https://t.me/+KE9pazFgbCg1ZjJk

02/08/2024

የዓለም 'የእናት ጡት ማጥባት' ሳምንት ነው ። በወንዛችን ልጇን ስታጠባ መታየትን የምታፍር እናት ትልቅ ችግር አይመስለኝም። የኢንተርኔት ትውልድ ባህሪ በፍጥነት ስለሚያጋራ ለወጣት እናቶች በሙሉ ጡት ማጥባት የሚያኮራ እና cool ነገር መሆኑን የማታውቁ (ግራ ያጋቧችሁ) ካላችሁ ደውሉልን።
ይልቅ ብዙ ጊዜ የሚያጋጥመው ችግር በተለይ primiparous/ ገና የመጀመሪያቸውን የወለዱ እህቶቻችን ''ጡቴ ወተት የለውም'' በማለት ከመቅጽበት ወደ Formula ወተት መሮጥ ነው። ይኸም በእውነቱ የድህረ-ወሊድ ክትትል የምናደርግላቸው ባለሙያዎች ክፍተት ተደርጎ ሊወሰድ የሚገባው ነው።
ጡት ማጥባት ትዕግስት፣ ስልጠናና ልምምድ የሚፈልግ፤ ለህፃናት አካላዊና አእምሮአዊ ጤና እንዲሁም ለእናትና ልጅ ሥነልቦና እስከአሁን ምትክ ያልተገኘለት እጅግ ውድ በረከት መሆኑ ተረጋግጧል። ይህን የተረዳች እናት ስለ ጡት ወተት አመራረት፣ ስለ ጡት ጫፍ ና የህፃኑ ከንፈርና አገጭ አቀማመጥ / Attachment/፣ ስለ ጡት አቀያየርና ስለ ማጥቢያ ጊዜያት ተገቢውን ስልጠና ብንሰጣት እንደዚሁም ከወሊድ ጋር ተያይዘው ለሚከሰቱ የድህረ ወሊድ የባህሪ ለውጥ ፣ የቀዶ ጥገና ወይም የስቲች ቁስል ስቃይ፣ የምግብ ፍላጎት መጥፋት ወይም የመወፈር ስጋት መሠል ችግሮቿ መፍትሔ ብናበጅላት ካልሆነ ግንአያቷን እናቷንና አክስቶቿን እንድታዳምጥ ብንተዋት አይሻልም?
ነገርን ነገር ካነሳው በዛሬ ጊዜ ሩጫ አንዲት ልጇን ጡት የምታጠባ እናት በስራዋ ላይ ለማጥባት የምትፈልገውን አጭር ዕረፍት ስትጠይቅ ገና ለመከልከል መቼ ወልዳልኝ የሚል አለቃ: የማይተባበር(ይገርማል የማትተባር) ባልደረባ: በቤት ውስጥ የማያግዝ ባል ሁሉ = ስለ ትውልዱ IQ፣ ስለ ት/ት ጥራት፣ ፖለቲካና ዶላር ...
መልካም የጡት ማጥባት ሳምንት!

02/08/2024
"ጉሮሮውንም ሲያመው፤ ሲያስለውም አሞክሳሲሊን ስለሚሰጡት፤ አሁን ራሴ እየገዛሁ ነው የምሰጠው።" (አንዲት እናት ስለ ለአራት ዓመት ህፃን ልጃቸው) ፀረ-ባክቴሪያዎችን ከመድሀኒት ቤቶች በቀጥታ...
01/07/2022

"ጉሮሮውንም ሲያመው፤ ሲያስለውም አሞክሳሲሊን ስለሚሰጡት፤ አሁን ራሴ እየገዛሁ ነው የምሰጠው።" (አንዲት እናት ስለ ለአራት ዓመት ህፃን ልጃቸው)
ፀረ-ባክቴሪያዎችን ከመድሀኒት ቤቶች በቀጥታ ገዝቶ በተለይ ለህፃናት መስጠት ጎጂ ልምድ ነው።
ጤናዎን በተመለከተ በማንኛውም ጊዜ በነፃ የሚያማክሩት የቤተሰብዎ ክሊኒክ።
መዳን ክሊኒክ : ዕምነት የሚጥሉበት!!!
ባህርዳር፤ ዓባይ ማዶ :- አባ ይግዛው ዋርካ
ዳያስፖራ ንግድ ባንክ ፊት ለፊት

ALWAYS seek the advice of a qualified health care professional before taking antibiotics.

Antibiotics can be used as part of treatment for many infections, including:
- Pneumonia
- Urinary Tract Infections
- Gonorrhoea
- Syphilis
- Trachoma
- Tuberculosis

Remember: Antibiotics do not treat viral infections, like colds and flu.

Address

ዓባይ ማዶ ምድረ-ገነት አዲሱ አስፓልት
Bahir Dar

Telephone

+251984142737

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Medan Clinic / መዳን ክሊኒክ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Medan Clinic / መዳን ክሊኒክ:

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram