Yejubie Health Center

Yejubie Health Center Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Yejubie Health Center, Medical and health, Yejubie, Bahir Dar.

30/12/2022

እንኳን ደስ አላችሁ !!!
በምስራቅ ጎጃም ዞን የባሶ ሊበን ወረዳ በጤና መድህን ከክልል 1ኛ በመውጣቱ #፣አንድ ኮምፒውተር ከነ ፕሪንተሩ የፌደራል መንግስት # አንድ ኮምፒውተር ከነ ፕሪንተሩ የአማራ ክልል መንግስት በድምሩ 2 ኮምፒውተር እና 2ፕሪንተር እንዲሁም ለየጁቤ ጤና ጣቢያ # አንድ አልትራ ሳውንድ በተጨማሪም ዋንጫና ሰርተፍኬት በሽልማት የተበረከተ በመሆኑ የባሶ ሊበን ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ማስተዋል አንማው ለወረዳው አመራርና ህዝብ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል ። የባሶ ሊበን ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ማስተዋል አንማው ባስተላለፉት መልዕክት ይህ ውጤት የተገኘው አመራሩና ህዝቡ እንዲሁም ባለድርሻ አካላት በመቀናጀት ስለሆነ ወደፊትም ይህ መተባበርና መደጋገፍ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።

28/12/2022

በምስራቅ ጎጃም ዞን የጤና ትራስፎርሜሽን ያሳኩ 9 ወረዳዎች በክልል ደረጃ እውቅና ማግኘታቸውን የምስራቅ ጎጃም ዞን ጤና መምሪያ ገለፀ።
**************
ታህሳስ 19/2015 ዓ.ም (ምስራቅ ጎጃም ዞን ኮሙዩኒኬሽን):የአማራ ክልል ጤና ቢሮ " #አሳታፊ የጤና አገልግሎት ለወረዳ ትራንስፎርሜሽን ተፈፃሚነት" በሚል መሪ ሀሳብ የጤና መድህን አገልግሎት አሰጣጥ፣ የንቅናቄና የእውቅና መድረክ ታህሳስ 18/2015 ዓ.ም በባሕር ዳር ከተማ አካሂዷል።

በመድረኩ ላይ ከምስራቅ ጎጃም ዞን በወረዳ ትራንስፎርሜሽንና በጤና መድህን የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ወረዳዎች እውቅና መሰጠቱን የዞኑ ጤና መምሪያ ገልጿል።

የምስራቅ ጎጃም ዞን ጤና መምሪያ ኀላፊ አቶ መልካሙ ጌትነት እንደገለፁት በክልል አቀፍ ደረጃ በተደረገው የጤና ንቅናቄ መድረክ በጤና ትራንስፎርሜሽን አፈፃፀም ሁለት እጁ እነሴ ፣ሸበል በረንታ ፣ደብረ ኤልያስ፣ ማቻከል ፣ስናን፣ቢቡኝ፣እነማይ፣ሰዴ እና ጎንቻ ሲሶ እነሴ በድምሩ 9 ወረዳዎች የተሻለ አፈፃፀም በማስመዝገባቸው እውቅና ማግኘታቸውን ተናግረዋል።

የአማራ ክልል ጤና ቢሮ በማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ዘርፍ በሰጠው እውቅናና ምስጋና በጤና መድህን የላቀ አፈፃፀም ከምርጥ 10 ወረዳዎች መካከል ባሶሊበን እና ጎዛምን አንደኛ እና ሁለተኛ ሁነው ሲሸለሙ ባሶ ሊበን ወረዳ ተጨማሪ ልዩ ሽልማት የተበረከተለት ሲሆን ሁለት እጁ እነሴና ደብረ ኤልያስን ጨምር ከዞኑ 4 ወረዳዎች የምርጥ 10 እውቅና ማግኘት መቻላቸውን መምሪያ ኀላፊው አስረድተዋል።

ባሶ ሊበን ወረዳ በአገር አቀፍ ደረጃ ተሞክሮ የተወሰደበትን የጁቤ ጤና ጣቢያን የፈጠረ በሚል በመድረኩ ላይ ከፍተኛ አድናቆትና እውቅና ተሰጥቶታል ያሉት አቶ መልካሙ ጌትነት የጁቤ ጤና ጣቢያ ከአማራ ክልል ጤና ቢሮ እና ከኢትዮጵያ ጤና መድህን አገልግሎት እውቅናን ማግኘቱን ተናግረዋል።

መመምሪያ ኀላፊው የምስራቅ ጎጃም ዞን መምሪያውን ጨምሮ በወረዳዎች የተገኘው እውቅና እና የሃብት ስጦታ ከሌሎች አካባቢዎች ጋር ሲነፃፀር አበረታች መሆኑን ገልፀው የተገኘውን ውጤት ወደ ላቀ አፈፃፀም ለማሳደግ የበለጠ እንደሚሰራ አስረድተዋል።

አቶ መልካሙ ዞኑ በጤናው ዘርፍ የላቀ አፈፃፀም እንዲኖረው ርብርብ ላደረጉ የዞንና ፣የወረዳ የዘርፉ ባለሙያዎች ፣የስራ ኀላፊዎችን እንዲሁም ማህበረሰቡን አመስግነዋል።

በክልል ደረጃ እውቅናና ምስጋና ፕሮግራም ላይ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎች የክልል፣የዞንና የወረዳ የስራኃላፊዎችና የሚመለከታቸው አካላት የተሳተፉበት ነበር።

20/11/2022

👉 ስትሮክ (Stroke) ምንድን ነው?
👇👇👇
ስትሮክ እጅግ በጣም አሳሳቢ የሆነ በሽታ ሲሆን በአለም ላይ በየሁለት ሰከንዱ አንድ ሰው በስትሮክ ሕመም ይጠቃል።

ይህም የአካል ጉዳት እና ሞትን ከሚያስከትሉ በሽታዎች አንዱ ነው ። ስትሮክ ጭንቅላታችን ውስጥ ያሉ ሴሎች ኦክሲጅን እንዳያገኙ በማድረግ እና በሰውነታችን ውስጥ በቂ የደም ዝውውር እንዳይኖር በማድረግ የሚከሰት ህመም ነው።

ሁለት አይነት የስትሮክ አይነቶች አሉ።

1)Hemorrhagic ወይም የሚደማ:- በጭንቅላታችን ውስጥ ደም ሲፈስ ወይም አርተሬዎቻችን ተጎድተው ደም ወደ ውጪ በመፍሰሱ ምክንያት የሚከሰት አይነት ነው።

2)Ischemic ወይም የኦክሲጅን እጥረት:- የደም ዝውውር ሲገታ ወይም መተላለፍ ሳይችል ሲቀር እና በቂ ኦክሲጅን ወደ ሰውነታችን መዘዋወር በለመቻሉ ምክንያት የሚከሰት አይነት ነው።

👉 የበሽታው ምልክቶች
# ራስ ምታት
# የእጅ / የእግር መዛል/ መድከም/ ፓራላይሲስ
# የተወሰነ የሰውነት ክፍል ለመንቀሳቀስ ወይም ለመራመድ መቸገር
# ለመናገር የአፍ መተሳሰር ወይም ቃላት ለማውጣት መቸገር
# የፊት መጣመም

👉 የስትሮክ በሽታ በምን ምክንያት ሊከሰት ይችላል?

# ዋንኛው የደም ግፊት በሽታ ሲሆን የደም ግፊት ፤ የስኳር ፤ የልብ ፤የኮልስትሮል ህመም ያለባቸው ሰዎች መድሃኒታቸውን በአግባቡ ካለመውሰድ ወይም በማቋረጣቸው ምክንያት ለስትሮክ ይጋለጣሉ።

# አልኮል አዘውትሮ በመጠጣት
# ሲጋራ በማጨስ
# ሆርሞናል ኢንባላንስ ወይም በተለያዩ መድሃኒቶች ምክንያት የሆርሞን መዛባት መከሰት
# የእድሜ መግፋት

👉 የበሽታው መከላከያ መንገዶች

# ጤናማ የአመጋገብ ስርዓት መከተል እንደ ቅባት ጮማ የበዛባቸው ምግቦች አለመመገብ
# አልኮል አለመጠጣት
# ሲጋራ አለማጨስ
# አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ
# እንደ ደም ግፊት ፤ የስኳር ፤ የልብ ፤የኮልስትሮል ህመም ያለባቸው ሰዎች መድሃኒታቸውን በሕክምና ባለሙያዎች ትእዛዝ መሰረት በአግባቡ መውሰድ

# በአቅራቢያዎ ወደሚገኙ የጤና ተቋማት በመሄድ የምርመራ የጤና ክትትል ማድረግ

ለበለጠ መረጃ በነጻ የስልክ ጥሪ 952 ይደውሉ የጤና ምክርና መረጃ ያግኙ!!የመረጃ ምንጭ ጤና ሚንስተር

16/02/15ዓ.ምየየጁቤ ጤና ጣቢያ የ2015ዓ.ም አንደኛ ሩብ አመት የስራ አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ፡፡በስብሰባውም የባ/ሊ/ወ/ጤ/ጥ/ፅ/ቤት ሃላፊዎች፣የስራ አመራር ኮሚቴዎች ፣የቀበሌ አስተዳ...
26/10/2022

16/02/15ዓ.ም
የየጁቤ ጤና ጣቢያ የ2015ዓ.ም አንደኛ ሩብ አመት የስራ አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ፡፡በስብሰባውም የባ/ሊ/ወ/ጤ/ጥ/ፅ/ቤት ሃላፊዎች፣የስራ አመራር ኮሚቴዎች ፣የቀበሌ አስተዳዳራዎች፣የቀበሌ ስራ አስካጅዎች፣ጤና ኤክስቴንሽኖች እና የጤና ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን ጤና ጣቢያው አሁን ካለው አፈፃፀም ከፍ ለማድረግ 1.የሴቶች አደረጃጀት ማጠናከር
2.የእናቶች ጤና አገልግሎት ማሻሻል
3.ሞደል ቀበሌ መፍጠር
4.የማህበረሰብ ተሳትፎን ማጠናከር ላይ መስራት እንዳለብን በመግባባት እና የስራ ስምሪት በመስጠት እንድሁም ጤና ጣቢያውን በማስጐብኘት ተጠናቋል፡፡

30/12/14 ዓ.ምየምስ/ጐጃም ዞን ከፍተኛ አመራሮች የየጁቤ ጤና ጣቢያን ሲጐበኙ፡-
05/09/2022

30/12/14 ዓ.ም
የምስ/ጐጃም ዞን ከፍተኛ አመራሮች የየጁቤ ጤና ጣቢያን ሲጐበኙ፡-

29/12/14 ዓ.ምየጐንቻሲሶእነሴ ወረዳ ጤና ጥበቃ ፅ/ቤትየወረዳ አመራሮችንየጤና ጣቢያ ስራ አመራር ቦርዶችንየጤና ጣቢያ ሀላፊዎችን እና የሚመለከታቸው ጤና ባለሙያዎችን በመያዝ ከየጁቤ ጤና ...
04/09/2022

29/12/14 ዓ.ም
የጐንቻሲሶእነሴ ወረዳ ጤና ጥበቃ ፅ/ቤት
የወረዳ አመራሮችን
የጤና ጣቢያ ስራ አመራር ቦርዶችን
የጤና ጣቢያ ሀላፊዎችን እና የሚመለከታቸው ጤና ባለሙያዎችን በመያዝ ከየጁቤ ጤና ጣቢያ ተሞክሮ ሲወስዱ፡-

26/12/14 ዓ.ምጐዛመን ወረዳ ጤና ጥበቃ  ፅ/ቤት  ከየጁቤ ጤና ጣቢያ ተሞክሮ ሲወስድ፡-
03/09/2022

26/12/14 ዓ.ም
ጐዛመን ወረዳ ጤና ጥበቃ ፅ/ቤት ከየጁቤ ጤና ጣቢያ ተሞክሮ ሲወስድ፡-

Sede And Awabel Woreda Experience sharing ...
27/08/2022

Sede And Awabel Woreda Experience sharing ...

በቀን 09/12/14ዓ.ም እና 13/12/14ዓ.ም ሁለት እጅ እንብሴ፣ደባይ፣እናርጅ፣አነደድ እና ደብር ኤልያስ ወረዳዎች የየጁቤ ጤና ጣቢያን ተሞክሮ ሲወስዱ
19/08/2022

በቀን 09/12/14ዓ.ም እና 13/12/14ዓ.ም ሁለት እጅ እንብሴ፣ደባይ፣እናርጅ፣አነደድ እና ደብር ኤልያስ ወረዳዎች የየጁቤ ጤና ጣቢያን ተሞክሮ ሲወስዱ

25/07/2022

የቀን 7 ሰዓት አማርኛ ዜና… ሐምሌ 18/2014 ዓ.ም

24/07/2022

Address

Yejubie
Bahir Dar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yejubie Health Center posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram