FGAE NWAO Volunteers'

FGAE NWAO Volunteers' FGAE NWAO Volunteers group

ፈጣሪ ነብስህን በአፀደ ገነት ያኑርልን ወጣት አደራው ቢሰጥ በደረሰበት ድንገተኛ ህልፈት የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማህበር ሰሜን ምዕራብ አካባቢ ጽ/ቤት የአማካሪ ቦርድ አባላት፣ የቋሚ ኮሚቴ...
26/01/2023

ፈጣሪ ነብስህን በአፀደ ገነት ያኑርልን
ወጣት አደራው ቢሰጥ በደረሰበት ድንገተኛ ህልፈት የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማህበር ሰሜን ምዕራብ አካባቢ ጽ/ቤት የአማካሪ ቦርድ አባላት፣ የቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ በጎፈቃደኞች እና ሰራተኞች የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለፅን ለቤተሰቦቹና ለጓደኞቹ መጽናናትን እንመኛለን፡፡

22/03/2022
IYAFP alongside USAID Momentum is looking for a set of dynamic youth to participate in a virtual consultation aimed at c...
08/02/2021

IYAFP alongside USAID Momentum is looking for a set of dynamic youth to participate in a virtual consultation aimed at collecting information for a Meaningful Adolescent and Youth Engagement (MAYE) Strategic Planning Guide! Are you fluent in either English, French, Spanish or Arabic? We want to hear what you’ve got to say! ✨
Application closes February 14, 2021. Apply now:

Home About Us Global Consensus Statement on MAYE Join Us Knowledge & Resources Contact Us Meaningful Adolescent and youth Engagement CHECK OUT OUR LATEST OPPORTUNITIES BELOW PAID OPPORTUNITIES We’re looking for Virtual Consultation Participants! All Virtual Consultation participants must be under ...

01/01/2021

ኤች.አይ.ቪን በጋራ መመርመ ጥቅሙ
በጋራ መመርመር ማለት ምን ማለት ነው?
በጋራ መመርመር ማለት ባልና ሚስት፣ የፍቅር ጓደኞች ወይም ለመጋባት የወሰኑ አንድ ወንድና አንዲት ሴት አንድ ላይ በጋራ ኤች.አይ.ቪን ተመርምረው ውጤታቸውንም በጋራ ሲያውቁ ማለት ነው፡፡
በግል ከመመርመር በጋራ መመርመር ለምን ተመራጭ ሆነ?
በጋራ መመርመር በግል ከመመርመር የበለጠ ብዙ ጥቅሞች ስላለው በጣም ተመራጭ ነው፡፡
በጋራ መመርመር ብዙ ጥቅሞች ሲኖሩት ከብዙ በጥቂቱ፡
 ጥንዶች አንድ ላይ ሲመረመሩ ውጤቱ የሚነገረው በጋራ ነው
 ከአማካሪው ምክርን በጋራ ያገኛሉ
 ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ ቢገኝ ቶሎ ወደ ህክምናና እንክብካቤ አገልግሎት ለመግባት ያመቻል
 በህክምና ላይ ጥሩ መደጋገር ስለሚኖር ህክምናውንና እንክብካቤውን ውጤታማ ያደርጋል
 የተቀሩትን የቤተሰብ አባላትን ለማስመርመር አመቺ ሁሌታን ይፈጥራል
 ተገቢ የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎትን ለማግኘት አመቺ ሁኔታን ይፈጥራል
 የምርመራው ውጤት የተለያየ ከሆነ ደግሞ የወደፊት የግብረ-ስጋ ግንኙነት ሕይወታቸውን ለመወሰን ያስችላቸዋል
 ተመርማሪዎቹ የግብረ ስጋ ግንኙነት ያልፈፀሙና ያልተጋቡ ከሆነ የወደፊት የአብሮነት ሕይወታቸውን አቅጣጫ ለመወሰን ያስችላቸዋል፡፡
በባልና በሚስት መካከል ወይም የግብረ ስጋ ግንኙነት በሚፈፅሙ የፍቅር ጓደኞች መካከል የተለያየ የኤች.አይ.ቪ የምርመራ ውጤት ሊኖር ይችላል
አዎ ሊኖር ይችላል፡፡ በአጠቃላይ በጋራ ምርመራ የየሚገኘው ውጤት ከሶስት የውጤት ዓይነቶች አንዱ ሊሆን ይችላል፡፡ እነርሱም፡
1. ሁለቱም ከቫይረሱ ነፃ የሚሆኑበት
2. በሁለቱም ውስጥ የቫይረሱ መኖር
3. በአንዱ ውስጥ ቫይረሱ ኖሮ በሌላኛው ውስጥ የቫይረሱ አለመኖር ናቸው፡፡
በጋራ ለመመርመር አገልግሎቱን ከየት ነው የምናገኘው?
በጋራ ለመመርመር አገልገሎቱን ከሁሉም የቤተሰብ መምሪያ ክሊኒኮች፤ የመንግስት ጤና ጣቢያዎችና መንግስታዊ ያልሆኑ የጤና ተቋማትም ማግኘት ይቻላል፡፡
በጋራ ተመርምረንና ውጤታችንን በጋራ አውቀን ኤች.አይ.ቪን በጋራ እንከላከል!
የተዋልዶ ጤና ለቤተሰብዎ ብልፅግና!
ለሚኖራችሁ ማንኛውም በስነ-ተዋልዶ ጤና ዙሪያ በመልዕክት ማስቀመጫው ይላኩልን አልያም በነፃ ጥሪ ዘወትር በስራ ሰዓት ይደውሉልን፡፡ እንዲሁም ማዕከላችን በመምጣት የባለሙያ ምክርና እገዛ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማኅበር

Address

Bahir Dar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when FGAE NWAO Volunteers' posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram