Health Informatics in west gojjam zone assocition

Health Informatics in west gojjam zone assocition Health Informatics page

16/09/2021
From muhe
26/05/2021

From muhe

#ወሳኝ #ነገሮች #ለተመራቂ #ተማሪዎች
ሪሰርች ስትሰሩ ከዚህ በታች የጠቀስኳቸው ከከበዷችሁ በምርጥ አቀራረብ ቪዲዮ ይዥላችሁ ቀርቤያለሁ።
ግን ይህንን ፔጅ Like አድርገዋል? Like ቢያደርጉ ስለቴክኖሎጅ ይማራሉ ያውቃሉ!
✅ Automatic References
✅ Automatic List of tables
✅ Automatic List of figures
✅ Citation
በምርጥ አቀራረብ በYouTube ተዘጋጅቶ ለእይታ ዝግጁ ነው ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን መመልከትና መማር ትችላላችሁ!

https://youtu.be/VujbubSHkZs

ከዚህ በታች የዘረዘርኳቸው
✔️ Automatic Tables of Content.
✔️ Page Break እንዴት እንሰራለን? ለሚለው ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ይመልከቱ

https://youtu.be/aB-z5uKq75U
የYouTube ቻናሉን Subscribe በማድረግ ምርጥ ምርጥ ትምህርቶችን ይማሩ!
⏺ የYouTube channel Subscribe በማድረግ ጥሩ ጥሩ ትምህርታዊ ቪዲዮችን ይከታተሉ።
የ YouTube ቻናል ሊንክ 👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ
⏺ በቴሌግራም ቻናሌ ጥሩ ጥሩ ትምህርታ አዘል መረጃዎችን ያግኛሉ 👇👇👇👇👇 https://t.me/MuhammedComputerTechnology

19/05/2021

ትምህርታቸውን ላሻሻሉ የመንግስት ሠራተኞች/ ባለሙያዎች አመዳደብና የደመወዝ አከፋፈል በሚመለከት የተሻሻለ መመሪያ ቁጥር 5/2013
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
ግን ይህንን ፔጅ Like አድርገዋል? Like ቢያደርጉ ስለቴክኖሎጅ ይማራሉ ያውቃሉ!
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
✅መግቢያ
ትምህርት የአንድን አገር ልማት ለማፈጠን እጅግ ጠቃሚ በመሆኑ በአገር ደረጃም ሆነ በክልላችን ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራባቸው ከሚገኙ ዘርፎች ውስጥ በቀዳሚነት የሚጠቀስ ነው፡፡

ስለሆነም የትምህርት ተቋማትን በመጠቀም የፈጻሚውን አቅም ማጎልበት በሲቪል ሰርቪሱ የሚታየውን የመፈጸም አቅም ክፍተት መሙላት ስለሚያስችል የትምህርት ደረጃቸውን አሻሽለው የሚመለሱ የመንግስት ሠራተኞችን/ባለሙያዎችን በአግባቡ ምደባ ለመስጠትና ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያሥችል መመሪያ ተሻሽሎ ከሰኔ 2011 ጀምሮ ስራ ላይ እንዲውል የተደረገ ቢሆንም እንደገና ማሻሻል አስፈልጓል፡፡

👉ስለሆነም፡-
✅ በተለያዩ ጊዚያት የወጡ ሰርኩላሮችን የዚህ መመሪያ አካል በማድረግ ለተጠቃሚው ምቹ ሁኔታ ለመፍጠርና በአፈጻጸም የታዩ ግድፈቶችን ለማረም በማስፈለጉ፣
✅ ከነጥብ የስራ ምዘናና ደረጃ አወሳሰን ጥናት ጋር የተዛመደ የመመሪያ ማሻሻያ ማድረግ በማስፈለጉ ፡
✅በየደረጃው ትምህርታቸውን አጠናቀው ለሚመለሱ ባለሙያዎች የትምህርት ዝግጅታቸውን መሠረት ያደረገ ምደባ በወቅቱ መስጠት በማስፈለጉ፣
✅ በሃገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሃገር በመንግስት ድጋፍ ትምህርታቸውን አሻሽለው ለሚመለሱ ባለሙያዎች ተገቢ የስራ ምደባና አቅምን ያገናዘበ ማበረታቻ በመስጠት አቅማቸውን አሟጠው እንዲጠቀሙ ማስቻል በማስፈለጉ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በተሻሻለው የመንግስት ሠራተኞች አዋጅ 253/2010 አንቀጽ 96 ንዑሥ አንቀጽ 2 በተሰጠው መመሪያ የማውጣት ስልጣን መሰረት ይህን መመሪያ አውጥቷል፡፡

👉ክፍል አንድ
▶ጠቅላላ
1.1 አጭር ርዕስ
ይህ መመሪያ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ትምህርታቸውን ያሻሻሉ የመንግስት ሠራተኞች አመዳደብና የደመወዝ አከፋፈል መመሪያ ቁጥር 5/2013 ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

👉1.2 ትርጓሜ
የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ መመሪያ ውስጥ፣
1.2.1 "የመንግሥት መ/ቤት" ማለት በየትኛውም የአስተዳደር እርከን እራሱን ችሎ በአዋጅ ወይም በደንብ የተቋቋመ እና ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ከመንግስት በሚመደብለት በጀት የሚተዳደር የመንግስት መስሪያ ቤት ነው፡፡
1.2.2 "ኮሚሽን" ማለት የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ነው፡፡
1.2.3 “የመንግስት ሠራተኛ ” ማለት በመንግሥት መሥሪያ ቤት ውስጥ በቋሚነት/በጊዚያዊነት ተቀጥሮ የሚሠራ ሰው ነው ፡፡
1.2.4 “መደበኛ ፕሮግራም “ ማለት በመንግስት ድጋፍም ይሁን በግል ስፖንሰር አድራጊነት ከመደበኛ ስራቸው ውጭ ሆኖ ትምህርቱን ለመከታተል የመረጠው መርሀ-ግብር ነው፡፡
1.3 “በርቀት፤በማታ፤በክረምት ፕሮግራም”ማለት በመንግስትድጋፍምይሁንበግልስፖንሰር አድራጊነት መደበኛ ስራውን እያከናወነ ትምህርቱን ለመከታተል የመረጠው መርሀ-ግብር ነው፡፡
1.4 ማንኛውም በወንድ ፃታ የተገለፀው የሴት ፆታንም ያካትታል፡፡
1.5 የተፈፃሚነት ወሰን
ይህ መመሪያ ተፈፃሚነት የሚኖረው በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 253/2010 በሚተዳደሩ መ/ቤቶችና ሠራተኞች ላይ ብቻ ነው፡፡

👉ክፍል ሁለት
▶ትምህርታቸውን ያሻሻሉ ባለሙያዎች/ሰራተኞች አመዳደብና የደመወዝ አከፋፈል ሁኔታ

2.1. የአመዳደብ ሁኔታ
2.1.1 በመንግስት ድጋፍ በማንኛውም ኘሮግራም በየትኛውም ደረጃ ትምህርታቸውን አጠናቀው የሚመጡ ባለሙያዎች ምደባ የሚያገኙት ወደ ትምህርት ከመግባታቸው በፊት ይሰሩበት በነበረው ወይም ውል አስይዞ በላካቸው ወይም በስልጠናው ወቅት ለሰልጣኙ ደመወዙን ይከፍል በነበረው መ/ቤት ይሆናል፡፡
2.1.2 በነጥብ የስራ ምዘና ዘዴ ደረጃ ከተሰጠው በኋላ ወደ ትምህርት የሄደ ባለሙያ ትምህርቱን አጠናቆ ሲመለስ ይዞት የነበረው የስራ ደረጃ ተጠብቆለት ምደባ ይደረግለታል፡፡ሆኖም ግን ይዞት የነበረው የስራ ደረጃ ተሻሽሎ ከሆነ የተሻሻለውን የስራ ደረጃ ዝቅተኛ ተፈላጊ ችሎታውን ማሟላቱ ተረጋግጦ ከተሻሻለው የስራ ደረጃ ላይ ይመደባል፡፡

2.1.3 በመንግስት ድጋፍ በማንኛውም ኘሮግራም ሁለተኛ ዲግሪና በላይ ትምህርታቸውን ያሻሻሉ ባለሙያዎች በንኡስ አንቀጽ 2.2.1. የተፈቀደላቸውን ጥቅማጥቅም እንዲያገኙ በማድረግ በነበራቸው ደረጃ ላይ እንዲመደቡ ይደረጋል፡፡ ይህም ሆኖ ከትምህርት መልስ ይዘውት ከነበረው ደረጃ በላይ ከፍ ብለው በጊዚያዊነት የሚመደቡ ሠራተኞች ቢኖሩ ከፍ ብለው የተመደቡበትን የስራ ደረጃ የሚያገኙት ከሌሎች ሰራተኞች ጋር በደረጃ ዕድገት ተወዳድረው አሸናፊ ሲሆኑ ነው፡፡

2.1.4 ከላይ በንዑስ አንቀጽ 2.1.1 የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ በመንግስት ድጋፍ በማንኛውም ኘሮግራም በየትኛውም ደረጃ ትምህርታቸውን አጠናቀው የሚመጡ ባለሙያዎች ምደባ የሚያገኙት ወደ ትምህርት ከመግባታቸው በፊት ይዘውት ከነበረው ደረጃ አቻ በሆነ ደረጃ ላይ ዝቅተኛ ተፈላጊ ችሎታ ማሟላታቸውን በማረጋገጥ ይሆናል፡፡ ሆኖም ክፍት የሥራ መደብ ካልተገኘ እስከ ሁለት ደረጃ ከፍ ወይም እስከ ሁለት ደረጃ ዝቅ ብለው በጊዚያዊነት እንዲመደቡ ይደረጋል፡፡ ከፍ ብለው የሚመደቡት የሥራ ደረጃውን ወይም ጥቅሙን የሚያገኙት በደረጃ እድገት አግባብ ከሌሎች ሠራተኞች ጋር ተወዳድረው ሲያሸንፉ ብቻ ይሆናል፡፡ ዝቅ ብለው የተመደቡትም ሆነ ከፍ ብለው የተመደቡት በተሸሻለው የመንግስት ሰራተኞች ምልመላና መረጣ መመሪያ አንቀጽ 1.3.4 መሠረት ማንኛውም ስምሪት ከመከናወኑ በፊት በትይዩ እንዲመደቡ ይደረጋል፡፡

2.1.5 በንዑስ አንቀጽ 2.1.1 እና 2.1.2 የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ በመንግሥት ድጋፍ በማንኛውም ፕሮግራም ሁለተኛ ዲግሪና በላይ ትምህርታቸውን ያሻሻሉ ባለሙያዎች ለምደባ ሲመጡ በተመረቁበት የትምህርት ዘርፍ ወይም የትምህርት ዝግጅት ሊያስመድባቸው የሚያስችል ክፍት የሥራ መደብ ካልተገኘ በንኡስ አንቀጽ 2.2.1. የተፈቀደላቸውን ጥቅማጥቅም እንዲያገኙ በማድረግ ከአሻሻሉት የትምህርት ዘርፍ /ዝግጅት/ በፊት በነበራቸው የትምህርት ዝግጅት ሊመደቡ ይችላሉ፡፡

2.1.6. ከላይ በን/አንቀጽ 2.1.2 - 2.1.4 የተገለጸው ቢኖርም በመንግሥት ድጋፍ በማንኛውም ፕሮግራም ከ2ኛ ዲግሪ በታች ትምህርታቸውን ያሻሻሉ ባለሙያዎች ወደ ትምህርት ከመግባታቸው በፊት ይዘውት የነበረው የስራ ደረጃ መነሻ ደመወዝ ከአሻሻሉት ትምህርት ደረጃ መነሻ ደመወዝ ደረጃ በታች የሚሆንበት ሁኔታ ሲያጋጥም ያለ ስራ ልምድ የተሻሻለው ትምህርት ደረጃ መነሻ ደመወዝና ከዚያ በላይ ደመወዝ ሊያስከፍል በሚችል ደረጃ ያለው ስራ መደብ ላይ ይመደባሉ፡፡ ሆኖም ግን ሊመደቡ የሚችሉበት የስራ መደብ ከሌለ እየሰሩ ባሉበት የስራ ደረጃ ላይ የትምህርት ዝግጅት መነሻ ደመወዝ እንዲያገኙ በማድረግ በጊዚያዊነት ይመደባሉ፡፡

2.1.7. ከላይ በን/አንቀጽ 2.1.2 - 2.1.6 የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ ባለሙያው ከሄደበት መ/ቤት የሚመደብበት ክፍት የሥራ መደብ ከጠፋ ብቻ በየደረጃው ባለው የሲቪል ሰርቪስ መ/ቤት አማካኝነት ባለሙያው ይሰራበት የነበረው መ/ቤት ባለበት የአስተዳደር አርከን ባሉ ሌሎች ሴክተር መ/ቤቶች ባሉ ክፍት ስራ መደቦች ላይ እንደአስፈላጊነቱ በጀቱን እንደያዘ ወይም ሳይዝ እንዲመደቡ ይደረጋል፡፡
2.1.8. ከላይ በን/አንቀጽ 2.1.7 በተገለጸው መልኩ ምደባ መስጠት ካልተቻለ የሚመጥናቸው ክፍት የሥራ መደብ እስከሚገኝ ድረስ በተላኩበት የአስተዳደር እርከን ውስጥ በጊዜያዊነት በማንኛውም ስራመደብ ላይ ተመድበው እንዲሰሩ ይደረጋል፡፡ ይህም ሆኖ ጊዚያዊ የስራ መደብ ከጠፋ የወረዳና ከተማ አስተዳደር ሠራተኞችን በዞን በኩል ዞን ሴክተሮች ላይምሆነ በዞኑ ውስጥ ባሉ ወረዳዎች ወይም ከተማ አስተዳደሮች ላይ እንዲመደቡ ይደረጋል፡፡ የዞን ሴክተር መ/ቤት ሠራተኞች ምደባ ግን በዞን ሲቪል ሰርቪስ መ/ቤት አማካኝነት ይጠናቀቃል፡፡

2.1.9 ከላይ በን/አንቀጽ 2.1.8 የተገለጸው ቢኖርም ሠራተኛው የሚመደብበት ክፍት የስራ መደብ ባለመገኘቱ ከነበረበት የአስተዳደር እርከን ወደ ላይኛው አስተደር እርከን ተስቦ የሚመደብ ሠራተኛ ቢኖር ከነበረበት አስተዳደር እርከን ከፍተኛ የስራ ደረጃ በላይ ሊመደብ አይችልም፡፡
2.1.10. የካርየር ተጠቃሚ የሆነ ሠራተኛ በመንግስት ድጋፍ በማንኛውም ፕሮግራም ከሁለተኛ ዲግሪ በታች በሆነ የትምህርት ደረጃ ትምህርቱን አጠናቆ ሲመለስ ለትምህርት ከመሄዱ በፊት ያገኝ የነበረው ደመወዝ ካሻሻለው የትምህርት ዝግጅት መነሻ ደመወዝ በታች ከሆነ በካርየሩ መነሻ ደመወዝ የሥራ ደረጃ ላይ እንዲመደብ ይደረጋል፡፡ ሆኖም ግን ለትምህርት ከመሄዱ በፊት ያገኝ የነበረው ደመወዝ ካሻሻለው የትምህርት ዝግጅት መነሻ ደመወዝ በላይ ከሆነ በሚያገኙ ደመወዝ ትይዩ ባለው የካርየር ሥራ ደረጃ ላይ ከመመደብ በስተቀር የሚደረግለት ጭማሪ አይኖርም ፡፡
2.1.11. የካርየር ተጠቃሚ የሆነ ሠራተኛ በመንግስት ድጋፍ በማንኛውም ፕሮግራም ሁለተኛ ዲግሪና ከዚያ በላይ በሆነ የትምህርት ደረጃ ትምህርቱን አጠናቆ ሲመለስ የትምህርት ማስረጃውን ካያያዘበት ቀን ጀምሮ ለትምህርት ከመሄዱ በፊት ያገኝ በነበረው ደመወዝ ላይ የሦስት ዕርከን ጭማሪ ተደርጎለት በካርየሩ ሊያርፍ ወደ ሚችልበት የሥራ ደረጃ ላይ እንዲመደብ ይደረጋል፡፡

2.1.12. ከላይ በንኡስ አንቀጽ 2.1.11 የተገለጸው ቢኖርም አንድ ትምህርቱን ያሻሻለ ጤና ባለሙያ በመንግስት ድጋፍ ከስራ ገበታው በመለየት በመደበኛ ፕሮግራም የመጀመሪያ ዲግሪና ከዚያ በላይ በሆነ የትምህርት ደረጃ ትምህርቱን አጠናቆ ሲመለስ ሊመደብ የሚችለው የትምህርት ማስረጃው የጤና ባለሙያዎችን ሙያ በመመዘን የፓናል ደረጃ እንዲወስን ስልጣን በተሰጠው አካል የተወሰነ የፓናል ውሳኔ ሲያቀርብ ባቀረበው ደረጃ መሰረት የሚመደብ ይሆናል፡፡
2.1.13 ከላይ በንዑስ አንቀጽ 2.1.12 የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ ሠራተኛው ለ2ኛ ዲግሪና በላይ ትምህርት ከመሄዱ በፊት ያገኝ የነበረው ደመወዝ በፓናል ከተወሰነለት ደረጃ መነሻ ደመወዝ አኩል ወይም የበለጠ የሚሆነበት አጋጣሚ ሲኖር ለትምህርት ከመሄዱ በፊት ያገኝ በነበረው ደመወዝ ላይ በንኡስ አንቀጽ 2.2.1. የተፈቀደው ጥቅማጥቅም ተጨምሮለት በካርየር መመሪያው ለትምህርት ደረጃው ሲባል በተዘጋጀ ደመወዝ ስኬል አቻ መነሻ ደመወዝ ባለው ስራ ደረጃ ላይ ይመደባል፡፡ነገር ግን ለ2ኛ ዲግሪና በላይ ትምህርት ከመሄዱ በፊት ያገኝ የነበረው ደመወዝ በፓናል ከተወሰነለት ደረጃ መነሻ ደመወዝ ያነሰ ከሆነ ወደ ፓናል መነሻ ደመዎዝ እንዲመደብ ይደረጋል፡፡

2.1.14 በመንግስት ድጋፍ በመደበኛ ፕሮግራም ከስራ ገበታው በመለየት የመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርቱን ያሻሻሉ የጤና ባለሙያዎች ት/ት ከመሄዳቸው በፊት ያገኝ የነበረው ደመወዝ በፓናል ከተወሰነለት ደረጃ መነሻ ደመወዝ አኩል ወይም የበለጠ የሚሆነበት አጋጣሚ ሲኖር ለትምህርት ከመሄዱ በፊት ያገኝ የነበረው ደመወዝ እንደያዘ በተወሰነለት የፓናል ደረጃ ላይ ይመደባል፡፡ ነገር ግን ትምህርት ከመሄዱ በፊት ያገኝ የነበረው ደመወዝ በፓናል ከተወሰነለት ደረጃ መነሻ ደመወዝ ያነሰ ከሆነ ወደ ፓናል መነሻ ደመዎዝ እንዲመደብ ይደረጋል፡፡

2.1.15 ቀደም ሲል የካርየር ተጠቃሚ ያልነበረ ሰራተኛ በመንግስት ድጋፍ ከመደበኛ ስራው ተለይቶ የካርየር ስራ መደብ ላይ በሚያስመድብ የትምህርት ዝግጅት አይነት ሁለተኛ ዲግሪና ከዚያ በላይ በሆነ ደረጃ የትምህርት ደረጃውን አሻሽሎ ሲመለስ ለትምህርት ከመሄዱ በፊት ይከፈለው በነበረው ደመወዝ ላይ በንኡስ አንቀጽ 2.2.1. የተፈቀደውን ጥቅማጥቅም እንዲያገኝ ይደረጋል፡፡ ሆኖም ደመወዙ ለትምህርት ደረጃው ከሚፈቅደው መነሻ ደመወዝ የሚያንስ ከሆነ በካርየር ስራ መደብ ላይ ተመድቦ ለትምህርት ደረጃው የተወሰነውን መነሻ ደመወዝ እንዲከፈለው ይደረጋል፡፡

2.1.16 ከላይ በንኡስ አንቀጽ 2.1.10፤2.1.11፤ 2.1.14ና 2.1.15 የተገለጸው ቢኖርም ደመወዙ በካርየር መመሪያው ለትምህርት ደረጃው ከተወሰነው መነሻ ደመወዝ እኩል ወይም የሚበልጥ ከሆነ ሠራተኛው ደመወዙን እንደያዘ በካርየሩ መነሻ የስራ ደረጃ እንዲመደብ ተደርጐ የካርየር ቆይታ ጊዜው ከተመደበበት ጊዜ ጀምሮ ታስቦ የእድገት መሰላል ተጠቃሚ ይሆናል፡፡
2.1.17 ቋሚ የመንግሥት ሠራተኛ ሆነው ወደ ትምህርት በመግባት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ቆይተው በተለያዩ ምክንያቶች በቋሚነት ትምህርታቸውን አቋርጠው የተመለሱ ሠራተኞች ቀድሞ የነበራቸውን ደመወዝ እንደያዙ ወደ ሥራ እንዲመለሱ ይደረጋል፡፡

ሆኖም ትምህርታቸውን በጊዜያዊነት አቋርጠው የተመለሱ ሠራተኞች ይሠሩበት በነበረው መ/ቤት በጊዜያዊነት በተገኘው ክፍት የሥራ መደብ ተመድበው እንዲቆዩ ይደረጋል፡፡
2.1.18 ከላይ በተራ ቁጥር 2.1.17 በተገለጸው አግባብ ምደባ የሚሰጠቸው ባለሙያዎች ትምህርታቸውን ያቋረጡበትን ምክንያት የሚገልጽ ማስረጃ ከዩኒቨርስቲው ሪጅስትራር ጽ/ቤት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡

👉2.2 የደመወዝ አከፋፈል ሁኔታ፣
2.2.1 በመንግስት ድጋፍ ከስራ ገበታቸው በመለየት በመደበኛ ፕሮግራም፤ እንዲሁም በስራ ላይ ሆነው በየትኛውም ኘሮግራም/ በመደበኛ፣ በማታ፣ በክረምትና በርቀት/ የሁለተኛ ዲግሪያቸውንና ከዚያ በላይ ትምህርታቸውን አጠናቀው የሚመለሱ ባለሙያዎች ትምህርት ቤት ከመግባታቸው በፊት ወይም ትምህርታቸውን ከማጠናቀቃቸው በፊት ይዘውት ከነበረው ደረጃ እና ደመወዝ ላይ የሶስት እርከን ጭማሪ ይደረግላቸዋል፡፡ ክፍያውም የሚፈጸመው የትምህርት ማስረጃቸውን ካያያዙበት ቀን ጀምሮ ሲሆን ከውጭ አገር የተገኘ የትምህርት ማስረጃ ግን በሚመለከተው አካል ከተሰጠ አቻ ግምት ማስረጃ ጋር ሲቀርብ ብቻ ክፍያው የሚፈጸም ይሆናል፡፡

2.2.2 በግል ወጫቸው ሁለተኛ ዲግሪና ከዚያ በላይ ትምህርታቸውን የሚያጠናቅቁ ባለሙያዎች ከያዙት ደመወዝ ላይ የሶስት እርከን ጭማሪ ይደረግላቸዋል፡፡ ክፍያውም የሚፈጸመው የትምህርት ማስረጃቸውን ካያያዙበት ቀን ጀምሮ ነው፡፡ነገር ግን ክፍያውን ለመፈጸም ትምህርቱን ከማጠናቀቃቸው በፊት ከሚሰሩበት መ/ቤት አንድ ዓመትና በላይ ማገልገል ይጠበቅባቸዋል፡፡
2.2.3 በአንቀጽ 2.2.2 ላይ የተጠቀሰው ቢኖርም የካርየር ተጠቃሚ የሆኑ ባለሙያዎች በግል ወጫቸው ሁለተኛ ዲግሪና ከዚያ በላይ ትምህርታቸውን ሲያጠናቅቁ የሶስት እርከን ጭማሪ አይደረግላቸውም፡፡

2.2.4 በአንቀጽ 2.2.1፤ 2.2.2ና 2.2.3 ላይ የተጠቀሰው ቢኖርም የካርየር ተጠቃሚ ለሆኑ ባለሙያዎች ይህ ጥቅም የሚሰጠው በመንግስት ድጋፍ ከስራ ገበታቸው በመለየት በመደበኛ ፕሮግራም ትምህርታቸውን ለተከታተሉ ባለሙያዎች ብቻ ነው፡፡ ይህ ማለት በትምህርት ጊዜው የካርየር እድገት ተጠቃሚ የሆኑ ባለሙያዎች የሶስት አርከን ጭማሪ ተጠቃሚ አይሆኑም ወይም የሶስት እርከን ጭማሪ ጥቅም የሚሠጠው በትምህርት ጊዜው የካርየር እድገት ጥቅም ተቋርጦ የነበረ ከሆነ ብቻ ነው፡፡
2.2.5 በአንቀጽ 2.2.4 ላይ የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ የትምህርት ደረጃው ያለሥራ ልምድ ከሚያስከፍለው መነሻ ደመወዝ በታች ከሆነ የትምህርት ደረጃቸው ያለሥራ ልምድ የሚያስገኘውን መነሻ ደመወዝ እንዲከፈላቸው ይደረጋል፡፡

👉ክፍል ሦስት
✅ልዩ ልዩ ጉዳዮች
3.1 በመንግስት ስፖንሰር አድራጊነትም ሆነ በግል ወጫቸው ትምህርታቸውን አሻሽለው ምደባ የሚያገኙ ባለሙያዎች በስራ ላይ ያለው የምልመላና መረጣ መመሪያ የሚጋብዛቸው ከሆነ ተጨማሪ የመቆያ ጊዜ ሳያስፈልጋቸው ለከፍተኛ የስራ ደረጃዎች በደረጃ እድገት አግባብ ሊወዳደሩ ይችላሉ፡፡ በውድድር ወቅትም ወደ ትምህርት ከመሄዳቸው በፊት ባለው አንድ ዓመት ውስጥ የተሞላላቸው ሥራ አፈፃፀም ይያዝላቸዋል፡፡

3.2 በመንግስት ስፖንሰር አድራጊነት 2ኛ ዲግሪና ከዚያ በላይ የትምህርት ደረጃቸውን የሚያሻሽሉ ባለሙያዎች የሶስት እርከን ጭማሪ የሚያገኙት ትምህርታቸውን ጀምረው እስከ ሚያጠናቅቁ ድረስ ባስተማራቸው መ/ቤት ከቆዩ ብቻ ይሆናል፡፡

ሆኖም የነበሩበትን መ/ቤት በደረጃ ዕድገት፤ በዝውውርና በምደባ የለቀቁ ሰራተኞች/ባለሙያዎች የተመደቡበት ፤ያደጉበት ወይም የተዛወሩበት መ/ቤት በጀት ይዞ እንዲከፍል ይደረጋል፡፡ ሆኖም ግን ሰራተኛው ሲመደብ ፣ ሲዛወርና ደረጃ እድገት ሲያድግ የነበረበት መ/ቤት ለተቀባይ መ/ቤት በመንግስት ስፖንሰር አድራጊነት ትምህርቱን እየተከታተለ የነበረ ስለመሆኑ ማሳወቅ አለበት፡፡ ከላይ የተገለፀው ቢኖርም በራሱ ፈቃድ መልቀቂያ ጠይቆ የለቀቀን ባለሙያ/ሰራተኛ አይመለከተውም፡፡

3.3 በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 253/2010 አንቀጽ 96 ን/አንቀጽ 2 መሠረት ይህን መመሪያ የመለወጥ፣ የማሻሻል ወይም በሥራ ላይ በሚውልበት ጊዜ ማብራሪያ ወይም ትርጉም የመስጠት ኃላፊነት የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ነው፡፡
3.4 ሰኔ 2011 ዓ/ም ወጥቶ በሥራ ላይ የነበረው ትምህርታቸውን ያሻሻሉ ባለሙያዎች አመዳደብና ደመወዝ አከፋፈል አፈጻጸም መመሪያና ይህንን አስመልክቶ የተላለፉ ሰርኩላሮች በዚህ መመሪያ ተተክተዋል፡፡

3.5 ይህን መመሪያ በተዛባ መልኩ ወይም ያለአግባብ የሚያስፈጽም ማንኛውም አካል ወይም የስራ ኃላፊ አግባብ ባለው ህግ ተጠያቂ ይሆናል

3.6 በዚህ መመሪያ ላይ አፈፃፀም ላይ የሚኖር ቅሬታ በስራ ላይ ባለው የቅሬታ ዓቀራረብ ስነ-ሥርዓት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
3.7 ይህ መመሪያ ከህዳር /2013 ዓ/ም ጀምሮ የፀና ነው፡፡
©sewagegnew Fikru Atalay

31/05/2020

መፅሀፍ ቅዱሳዊ ስምች እና ትርጉማቸው…!!!

እስቲ ሁላችንም ሼር በማድረግ ለልጆቻቸው ስም ማውጣት ለተቸገሩ እህት እና ወንድምቻችን ግንዛቤን እንፍጠር። እኛም የምናውቀው ያልተጠቀሰ ስም ካወቃችሁ ኮሜንት አርጉንልን።

10/05/2020

@@እነሆ@@
ከሚያዝያ ጀምሮ
ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆነው የነጥብ ምዘና (Job
evaluation and grading-JEG)
ከደረጃ 1-22 የቀረበው የመነሻ ደመወዝ ስኬል ይህን ይመስላል። እናንተ ስንተኛው ደረጃ ላይ ናችሁ? ለማንኛውም ስራችሁንና ደረጃችሁን ታነፃፅሩት ዘንድ እነሆ ብያለሁ---!
ደረጃ 1= 1,100
ደረጃ 2= 1,338
ደረጃ 3= 1,624
ደረጃ 4= 1,958
ደረጃ 5= 2,344
ደረጃ 6= 2,799
ደረጃ 7= 3,333
ደረጃ 8= 3,934
ደረጃ 9= 4,609
ደረጃ 10= 5,358
ደረጃ 11= 6,193
ደረጃ 12= 7,071
ደረጃ 13= 8,017
ደረጃ 14= 9,056
ደረጃ 15= 10,160
ደረጃ 16= 11,305
ደረጃ 17= 12,579
ደረጃ 18= 13,926
ደረጃ 19= 15,265
ደረጃ 20= 16,979
ደረጃ 21= 18,071
ደረጃ 22= 20,408

09/05/2020

የአማራ ክልል ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ
በተስተካከለው ጄአጄ ከግንቦት ጀምሮ ደሞዝ እንደሚከፍል አስታውቋል።
ከሚያዝያ 30/2012 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኔ ያለውን ወር በጀት ስለተለቀቀለት የሚያዝያን ወር በመልሶ ክፍያ, ከግንቦት ጀምሮ ደግሞ መክፈል እንደሚጀምር የቢሮ ሃላፊው አስታውቀዋል ።
የኑሮ ውድነትን በተመለከተ ሲያብራሩም ጭማሪው ሐምሌ 01/2011 ዓ.ም ነው የተተገበረው ስለዚህ በዚያን ወቅት ተጨምሯል አሁን ላይ መጨመር ግን አይቻልም ብለዋል።

01/05/2020

ቃል በቃል የተወሰደ ስለ HI/HIT ጭማሪ የተባለ ነገር የለም።
የአብክመ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ የመንግስት
ሰራተኞች የJEG ክፍያን በተመለከተ ማሳሰቢያ መስጠቱን
የክልሉ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አስታወቀ።
**************************************
የመንግስት ሰራተኞች የJEG ክፍያ መዘግየቱን ተከትሎ
ከክልሉ ሰራተኞች በቢሮዉ የፌስ ቡክ ገጽ እና በተለያዩ
መንገዶች ተደጋጋሚ አስተያቶች እና ጥያቄዎች እየደረሱን
ሲል ገልጿል፡፡
የJEG ክፍያዉ ከታሰበዉ ጊዜ በላይ የዘገየ መሆኑንና
ሰራተኛዉ እያነሳ ያለዉ ጥያቄ ተገቢ መሆኑን ቢሮዉ
ያምንበታል፡፡
ክፍያዉ የዘገየዉ በቢሮዉ ምክንያት ሳይሆን የፌደራል
ገንዘብ ሚኒስቴር ለJEG የተጠየቀዉን በጀት ባለመልቀቁ
መሆኑን እያሳወቅን በጀቱና ገንዘቡ ለክልሉ ሲደርስ
ያለምንም መዘግየት ክፍያ የምንፈጽም መሆኑን እና
ቢሮዉም የፌደራል መንግስት የጉዳዩን አሳሳቢነት
ተገንዝቦ ገንዘቡን በፍጥነት እንዲልክልን በተደጋጋሚ
እየጠየቅን መሆኑን እንድትረዱልን በዚሁ አጋጣሚ
እንጠይቃለን ሲል በተቋሙ የፌስ ቡክ አድራሻ አሳወቋል፡፡
በአብክመ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽንም በኩል ተመሳሳይ
ጥያቄዎች አስተያየቶችን ስሰጡ የነበራቻሁ በዚሁ
አጋጣሚ የህንን ማሳሰቢያ ወስዳችሁ በትግስት
እንድትጠብቁ እናሳስባለን።
ምንጭ፦ ANRS Civil service commission ድረ
ገጽ

21/04/2020

how are you doing? how was ester?
now a day we talk about corona virus in the world but inside these we also discuss about JEG. all sectors get jeg written paper except health so please aske RHB before give written paper about jeg to us.

30/03/2020

ሰበር ዜና
ከዛሬ ጀምሮ ወደ አማራ ክልል የሚገባ የሕዝብ
ማመላለሻ ተሽከርካሪ እንደማይኖር የክልሉ
መንግሥት አስታወቀ።
ባሕር ዳር ፡ መጋቢት 20/2012 ዓ.ም (አብመድ)
ከአገሪቱ ከየትኛውም አቅጣጫ ወደ አማራ ክልል
የሚገቡ ማንናቸውም ዓይነት የሕዝብ ማጓጓዣ
ተሽከርካሪዎች ከዛሬ መጋቢት 20/2012 ዓ.ም
ከሌሊቱ 6፡00 ጀምሮ ወደ ክልሉ መግባት
የማይችሉ መሆኑን የአማራ ክልል መንግሥት የኮረና
ወረርሽኝ መካላከል ኮማንድ ፖስት አስታውቋል።
ከዩኒቪርስቲ ወደ ቤተሰቦቻቸው እየመጡ የሚገኙ
የአማራ ክልል ተወላጅ ተማሪዎች ግን በልዩ ሁኔታ
የሚገቡ መሆኑን ኮማንድ ፖስቱ ለአማራ ብዙኃን
መገናኛ ድርጅት ገልጿል። ይህ ውሳኔ ተግባራዊ
እንዲሆንም ለፀጥታ አስከባሪ ኃይል ተዕዛዝ
ተሰጥቷል።

Address

Bbb
Bahir Dar

Telephone

+251920763728

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Health Informatics in west gojjam zone assocition posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram