22/05/2025
“...
'ብራዲ' ግን ምንድን ናት ?
እኔ D እባላለሁ የሁለት ልጆች እናት ነኝ የልጆቼ አባትም የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት ሀኪም ነው። Intern እያለ ነበረ ፍቅር የጀመርነው ቶሎ ወደቁም ነገር እናሳድገው ብለን Gp ሆኖ በአመታችን ለመጋባት ወሰንን።እኔም በተመረቋት ትምህርት በትንሽዩ ደሞዝ ተቀጥሬ መስራት ጀመርኩ (ትንሽ አለመሆኗን እና ከሱ እኩል ይከፈለኝ እንደነበር ያወኩት ስራየን ከለቀኩኝ በኋላ ነበር😭😭)
አንድ በጣም መልከመልካም ፣ፀባዪ ንጉስ፣ሀኪም በስርዓተ ቤተክርስቲያን ላገባ እንደሆነ ቤተሰቦቼ የሰሙ ጊዜ....አቤት 😃😃😃ደስታ ፣ፈንጠዝያ። ሰርጉ እንደተጠበቀው በጥሎሽ እና በቁርጥ ያበደ አልነበረም፣ እኔም እሱም አላማችን ቶሎ ቤት መመስረት እንጅ ሰፈር ማብላት አልነበረም።(ውስጡን ለ...)
ኑሮ ጀመርን፣ ልጅ ተወለደ፣ ሀሳብ መጣ፣ኑሮ ጨመረ፣ ደሞ ሌላ እድል መጣ:- የትምህርት እድል (Residency)። ተመችቶን ከምንኖርባት የገጠር ከተማ ወደ አዲስአበባ ስደት፣ ከመንግስት ሰራተኝነት እኔ ስራ አጥ እሱ ደሞ ተማሪ ብቻ ህይወታችን በፈተና የተመላች ሆነች።
የአዲስአበባን ኑሮ ማሰብ አልፈልግም ለእግዚአብሔር ነግሬ መልስ አገኝበታለሁ ብዪ በእምባዪ ፅፌ አስቀምጬዋለሁ😭😭😭
ከተከራየናት ቤት ጀርባ ያለው ባለሱቅ ገና ስሄድ የዱቤ መመዝገቢያ ደብተሩን ያወጣ ነበር፣ብር ይዤ እንደማልሄድ ያውቃል ዋጋ ከፋይ ያድርግልኝ ብዪ እወስዳለሁ አሁንም ዱቤ አሁንም ብድር አሁንም የልጅ ወተት መግዣ ብድር።😭😭
ዶክተሩ ባለቤቴ ቤታችን ከሚማርበት በጣም ሩቅቅቅቅቅቅ ስለሆነ 11:00 ይነሳል ምሳ እቃውን እና 5ተኛ አመት ተማሪ እያለ አጎቱ የገዛለትን ላፕቶፕ ይዞ ይወጣል፣ ተረኛ ካልሆነ ማታ 1:30 ቤት የደርሳል አዳር ተረኛ ከሆነ ደግሞ እዛው ውሎ ከ36 ስዓታት በኋላ ይመለሳል።አቤት ድካም፣አቤት መጎሳቆል፣አቤት የእንቅልፍ እጦት፣አቤት ርሀብ😭😭
ቤት ይመጣል ስላችሁ በአካል ነው እንጅ መንፈሱ ሁሌም እዛው ሆስፒታል ነች፣ይደውላል፣ሜሴጅ ይልካል፣Voice ይልካል...ወዘተ
''ያቺ CS የሰራንላት.....ያቺኛዋ 'ብራዲ' ሆና....ጁኒየሩ ጋር ይደውላል
አስተማሪዎቹ ይደውላሉ
ህፃኑ እንዴት ሆነ
የየትኛዋ
የብራዲዋ😂
ሳላውቃት ይቺን ቃል ስወዳት😂
ሁሌ ይጠራታል
'None' ብላ ደግሞ የምትጀምር ሌላ ቃል አለች እሷም እኛ ቤት ቤተሰብ ነች😂
ብቻ አራት ሆነናል አኔ ፣ባለቤቴ፣ልጄ እና ታካሚዎቹ❤
እኔ በፊት ከቢሮ ቤቴ ሄጄ አንድም ስሰራው የዋልኩት ነገር ትዝ አይለኝም ነበር፣ እሱ ግን ቤት ይዟቸው ይመጣል ለካን የኔ ወረቀት እና ኮምፑዪተር የሱ ደሞ የሰው ህይወት ነው።
ሌሊት 5:30 ስልክ ይደወላል አነሳሁት ሴት ነች😏😏😏
ባሌ ሀኪም ባይሆን ምን ሊታሰብ እንደሚችል ታቁታላችሁ።
Intern ነች sorry
Doc
ዶ/ር የለም እንዴ
Hello
ኤጭ
ሰላም ነሽ እሱ ተኝቷል አስቸኳይ ነገር ከሆነ...ተናግሬ ሳልጨርስ ጆሮዪ ላይ ዘጋችው
ቀሰቀስኩት
መልሶ ደወለ
OR እየገባን ነው አሉት
ደም የፈሰሳትን እናት በድጋሚ ሊሰሩላት
ቁጭ ብለን እስከሚወጡ ጠበቅን
አይከፈለኝም አንጅ በጣም ብዙ ከተፃፉ ብዙ መፅሀፍ የሚወጣላቸው ገጠመኞች እና እንቅልፍ አልባ ሌሊቶችን አሳልፌያለሁ።
R4 እያለ አጎቱ ታመው መጡ፣ በአስተማሩት ዶክተሩ ልጃቸው ሊታከሙ😏😏😏
ኡኡ እቴ
በገንዘብ ማገዙን ተውትና ምናለበት ቤተሰብ ለማሳከም እንኳን ጊዜ ቢኖርህ ብሎ ተስፋ ቆርጦበት ተመለሰ
እናቴ ልትጠይቀን ዘመድም ልትሰናበት መጣች፣ቤታችንን ስታያት ደነገጠች፣ ወደ ውስጥ ስትገባ ደግሞ የበለጠ ተበሳጨች ሁሉ። አልጋና ፍራሽ ፣2 ኩርሲ፣ የምግብ መስሪያ እቃዎች በጣም በጥቂቱ ነበር ያለን። አዘነችልን፣ ምነው ተዘርፋችሁ ይሆን አለች😭 አይ እማ አወ ሌባው አልታወቀም እንጅ አወ ተዘርፈን ነው😭
መጨረስ አይቀርም 4ቱ አመት አለፈ፣አለቀ ተመስገን🙏🙏🙏አልኩኝ አልን አመሰገንን ስለታችንን አስገባን🙏
አዲስአበባንም ለቀቅን👏
እንደገና ሌላ አዲስ ቅጥር እና አዲስ ህይወት ተጀመረ። እዚህ ጋ ነው አለም ልክ አለመሆኗን የተረዳሁት፣ለተማሩ ሰዎች ቦታ እንደሌላት ያወኩት። ከበፊቱ በተመሳሳይ ደሞዝ ተቀጠረ፣ የሚሰራው ስራ ግን የስፔሻሊት ነው ገንዘቡ ግን ከ 4 አመት በፊት ሲከፈለው የነበረው ጋ ምንም ልዪነት የለውም።
ለምን???????
እሱም አኔም ተስፋ ቆረጥን
ቤተሰቦቻቸን እማ ቆዩ በኛ ተስፋ ከቆረጡ፣የጠላናቸው ሁሉ ከመሰላቸው ቆዪ። የኔን ባል ሳይሆን የታላቅ እህቴን እንጨት ነጋዴ ባሏን እያመሰገኑ እየመረቁ ይኖራሉ።
ተጨማሪ ስራ መስራት እንዳለብን መነጋገር ጀመርን፣ሆስፒታል ከሚያሳልፈው ጊዜ ላይ ቀንሶ ለኔና ለልጁ፣ለእምነቱ ፣ለራሱ፣ለቤተሰቡ ማዋል እንዳለበት ሽማግሌ አስቀምጬ አስመከርኩት።
ወደ ቀልቡ ተመለሰ እና ከነበረበት አዚም መንቃት ጀመረ እኔ ስራ እንድጀምር ገንዘብ ከቤተሰብ ተበደርን🙏 ትንሽየ የግል ስራ ጀመርኩ፣ እሱም የቤቱን ሀሳብ ማገዝ ጀመረ።
በሶስተኛው ወር አንድ ኩንታል ጤፍ ከራሴ ገንዘብ ላይ ስገዛ እና የልጄን የትምህርት ቤት ክፍያ ስከፍል የተሰማኝ ስሜት🙏🙏🙏
መማር ቤተሰብን መበተን ከሆነ ይቅር
መማር ልጅን ማስራብ ከሆነ ተውት
መማር እና ማወቅ ራስን መጉዳት ከሆነ ለምን ተብሎ ቢቀርስ
አሁንም ህዝብ አልነቃ ብሎ ነው እንጅ የጤና ባለሙያዎች ጥያቄ የኛ ነበር መሆን የነበረበት።
አልገባንም እንጅ የተማሩት የሰው ህይወት ማዳንን ነው፣ ወረቀት ላይ መግለጫ እንደመፃፍ ቀላል ነገር አይደለም ።
ሀኪሞች በስራቸው እና በትምህርት ምክንያት የበተኑት ቤተሰብ አሁን ላይ ወጥቶ ጥያቄው የኛ ነው ማለት ነበረበት።
መንግስት ቀልድ የሚመስል ቁማር በህዝቡ ላይ እየተጫወተ ይመስላል፣ አንዲት ነርስ ታካሚን የምትንከባከበውን ያክል ለልጇ ጊዜ ሰጥታ ለመንከባከብ አትችልም ሁኔታዎች አያስችሏትም።
ብራዲ
ታኪ
ነን ሪያሹሪንግ
ምን እንደሆኑ አሁን ገብተውኛል
አሁን አልገባሽ ያለኝ የዚህ System Non-reassuring Pattern ነው
ሁለተኛ ልጄ ወንድ ነው ስሙን 'ስር ነቀል' ብለውስ🤔
የጤና ባለሙያ በማግባቴ ከከፈልኩት ዋጋ ፣ካሳለፍኩት መከራ 0.1% አካፈልኳችሁ።
አይዟችሁ፣አይዞን🙏🙏
እህታችሁ D”