Eyasta Medical Center/እያስታ የህክምና ማዕከል

Eyasta Medical Center/እያስታ የህክምና ማዕከል The service we provide:

Diagnosis and follow up of chronic illnesses like hypertension,diabetes,heart diseases and other noncommunicable diseases.

Eyasta Specialty Clinic is a combined Internal Medicine and Gyne/Obs Clinic established by a group of Specialist doctors located in Kebele 14,Behind Bahirdar Cinema. Eyasta Specialty Clinic is a combined Internal Medicine and Gynecology/Obstetrics clinic established in February 2015 with the motto of delivering quality medical services to its customers with a team of Specialist from different disciplines.The Clinic is equipped with modern medical equipments
like chemistry machine,complete blood count machine,different serological tests,ECG machine and other basic laboratory tests.The Clinic has also imaging modalities like X-rays,ultrasound and others. Prompt diagnosis and treatment of infectious diseases like tuberculosis,HIV,pneumonia,
malaria,urinary tract infection and many more. Screening and vaccination of hepatitis and other vaccine preventable diseases

Antenatal care and follow up throughout pregnancy and postnatal period

Work up of infertility and family planning

Labor &delivery with obstetrician/gynecologist

Minor surgical procedures and implantation contraceptive devices

Pathological tests like FNAC,Cytology,,,,

Our pharmacy is well equipped with essential and affordable drugs

We have also many diagnostic tool on the pipeline

21/09/2025
በቀን 28/12/2017ዓ.ም በእያስታ የህክምና ማዕከል በአለው የሥራ አፈፃፀም ከፌደራል ፣ ከአበክመ ጤና ቢሮ ኃላፊዎች እና በአማራ ክልል ወሰጥ የሚገኙ  የሆስፒታል ሰራ አስኪያጅች በማዕከላ...
04/09/2025

በቀን 28/12/2017ዓ.ም በእያስታ የህክምና ማዕከል በአለው የሥራ አፈፃፀም ከፌደራል ፣ ከአበክመ ጤና ቢሮ ኃላፊዎች እና በአማራ ክልል ወሰጥ የሚገኙ የሆስፒታል ሰራ አስኪያጅች በማዕከላችን በመገኘት የተቋማችን ስራ አፈፃፀም እና የልምድ ልውውጥ አድርገናል መጥታችሁ ሰጓበኛችሁን እንዲሁም ስላበረታታችሁን እናመሰግናለን።

እያስታ የእርሰዎ ትክክለኛ የህክምና መዳረሻዎ!!

03/09/2025
ስለ አንጀት ካንሰር ምን ያህል ያውቃሉ?የመጋቢት 15 ቀን 2017 ዓ.ም ዕትምከዛሬ ዘጠኝ ዓመት በፊት ነው ጉዳዩ የተከሰተው:: አንዲት ዕድሜያቸው በሃምሳዎቹ መጨረሻ ላይ የሚገኙ እናት ነበሩ...
06/05/2025

ስለ አንጀት ካንሰር ምን ያህል ያውቃሉ?
የመጋቢት 15 ቀን 2017 ዓ.ም ዕትም
ከዛሬ ዘጠኝ ዓመት በፊት ነው ጉዳዩ የተከሰተው:: አንዲት ዕድሜያቸው በሃምሳዎቹ መጨረሻ ላይ የሚገኙ እናት ነበሩ:: በሕይዎት ዘመናቸው ከባድ ሕመም ታመው ወደ ሕክምና ተቋም ደርሰው አያውቁም ነበር:: ነገር ግን አልፎ አልፎ በሚያጋጥማቸው የሆድ ሕመም ወደ ክሊኒክ ጎራ ይሉ ነበር:: ታዲያ በወቅቱ ሀኪም አገኘሁት እሚላቸው በሽታ አሜባ እና ጃርዲያ ነበር:: ከዚህ የከፋ ሕመም አጋጥሟቸው አያውቅም::
ሆኖም በሕይዎት ከማለፋቸው አንድ ዓመት አካባቢ ሲቀራቸው በተደጋጋሚ የሆድ ሕመም እና ቶሎ ቶሎ የሚመጣ ደም የቀላቀለ ተቅማጥ ተከሰተባቸው:: ሕመሙ ፋታ የሚሰጥ አልነበረም:: እንደበፊቱ በአሜባ መድሃኒት የሚታገስም አልሆነ። በመሆኑም ሐኪሙ የኮሎኖስኮፒ ምርመራ አዘዘላቸው:: ኮሎኖስኮፒ ጫፉ ላይ ካሜራ ያለው ቀጭን ረዥም እና ተጣጣፊ ቱቦ ሲሆን በፊንጢጣ በኩል በመግባት አንጀትን የሚያሳይ መሳሪያ ነው:: በኮሎኖስኮፒው አማካኝነት ከአንጀት ዕባጩ ላይ ትንሽ ፈሳሽ በመውሰድ ምርመራ ከተደረገላቸው ከ15 ቀን በኋላም ውጤቱ ደረጃ አራት የደረሰ የትልቁ አንጀት ካንሠር ነበር የተባሉት:: በሽታው ከታወቀ ስድስት ወር ባልሞላ ጊዜም ሕይዎታቸውን ሊያጡ እንደቻሉ ዛሬ ልጃቸው በፀፀት የነበረውን ሁኔታ በዐይነ ህሊናዋ እያስታወሰች ነግራናለች::
ልጃቸው እንደምትለው ምናልባት የኮሎኖስኮፒ ምርመራው አስቀድሞ ቢታዘዝላቸው ኖሮ ካንሠሩ ቀድሞ ይታወቅና ሕክምና ተደርጎላቸው መዳን ይችሉ ነበር::
ይህ ታሪክ የብዙ ሰዎች ነው:: የሆድ ሕመምን ቀለል አድርጎ ማሰብ፣ የሕክምና ባለሙያውም ምልክቶችን አይቶ የኮሎኖስኮፒ ምርመራ በፍጥነት አለማድረጉ ካንሠሩ ወዲያው ላለመታከሙ ምክንያቶች ናቸው::
ስንቶቻችን ነን ስለ አንጀት ካንሠር ግንዛቤው ያለን? መልካም ግንዛቤው ካለዎት ለሌለው እንዲያደርሱ አደራ እያልን፤ ግንዛቤው ከሌለዎት ደግሞ ስለ አንጀት ካንሠር ሙያዊ ማብራሪያ ለማግኘት በእያስታ ሕክምና ማዕከል የውስጥ ደዌ፣ የጨጓራ፣ አንጀት እና የጉበት ሰብ ስፔሻሊስት ዶ/ር ክብረቴ ወልዴ ጋር ያደረግነውን ቆይታ በጽሞና ታነቡ ዘንድ ጋብዘንዎታል!
ካንሠር ማለት ምን ማለት ነው? የአንጀት ካንሠርስ? ለሚለው ጥያቄያችንም ይህንን መልስ ሰጥተውናል:: ካንሠር ሰውነታችን ማይቆጣጠረው ጤነኛ ያልሆኑ የሴሎች እድገት ማለት ነው:: ካንሠር በሁሉም የሰውነት ክፍሎች ላይ ሊከሰት ይችላል:: ካንሠር በጥቅሉ እንደ ሀገር እያደገ የመጣ ችግር ነው:: በፊት በበለጸጉ ሀገራት ላይ ነበር የሚከሰተው። አሁን ግን በታዳጊ ሀገራትም በብዛት መከሰት ጀምሯል ነው ያሉን::
የአንጀት ካንሠር ደግሞ በብዛት የትልቁ አንጀት ካንሠር ማለት እንደሆነ ነው፤ ባለሙያው ያብራሩት:: ምክንያቱም የአንጀት ካንሠር የሚነሳው ከትልቁ አንጀት እና ከፊንጢጣ አካባቢ ላይ ካለ ዕጢ ነው:: የአንጀት ካንሠር በዓለም አቀፍ ደረጃ በሦስተኛ ላይ ይገኛል:: በገዳይነቱ ደግሞ በሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ በሽታ እንደሆነ ነው የጠቆሙት::
ለአንጀት ካንሠር የሚያጋልጡ ሁኔታዎች የመጀመሪያዉ ዕድሜ እንደሆነ የሚያብራሩት ዶ/ር ክብረቴ ፤ እድሜያቸው ከ50 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎች ለካንሠሩ ተጋላጭ ናቸው:: ሌላው በቤተሰብ (አባት፣ እናት፣ እህት ወንድም) የአንጀት ካንሠር ያለበት ሰው የመያዝ አጋጣሚው ይጨምራል:: ክብደት መጨመር፣ አልኮል መጠጣት፣ ሲጋራ ማጨስ፣ አትክልት እና ፍራፍሬ አለማዘውተር፣ ስጋን አብዝቶ መመገብ ለበሽታው እንደሚያጋልጡ ነው የተናገሩት::
የአንጀት ካንሠር መጀመሪያ ላይ ትንሽ ዕጢ ነው ሚሆነው:: ዕጢው እያደገ ሲመጣ ነው ወደ ካንሠር የሚቀየረው:: ዕጢዋ በእንግሊዘኛ ፖሊፕ ትባላለች፤ ወደ ካንሠር ለመቀየር እድገቱ እስከ 10 ዓመት ሊቆይ ይችላል:: በየጊዜው ምርመራ የምናደርግ ከሆነ ግን እብጠቱ ወደ ካንሠር ከመቀየሩ በፊት ችግሩ ሊለይ እና ሊታከም እንደሚችል ነው የተናገሩት::
ዶ/ር ክብረቴ እንደሚሉት በኢትዮጵያ ካንሠር ይከሰትበታል ተብሎ ከሚጠበቀው ዕድሜ በታች እየተከሰተ ይገኛል::
እሳቸው እንደሚሉት ካንሠር የሚከሰተው ከቤተሰብ ጋር ተያይዞ የካንሠር ታሪክ ያለው ቤተሰብ ካልሆነ በቀር ብዙውን ጊዜ ዕድሜያቸው ሃምሳ ዓመት እና በላይ በሆኑ ሰዎች ነበር:: ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ቀድሞ መታየት ጀምሯል::
አብዛኛው ሰው ሆዱን ሲታመም ‘አሜባ ነው፣ የምግብ መበከል ነው …’ በሚል አመጋገቡን ለማስተካከል ይሞክራል እንጂ ወደ ሕክምና ተቋም እንደማይመጣ ነው ባለሙያው የተናገሩት:: “በየቀኑ የምናየው ነገር በመሆኑም ብዙ ታካሚ የሚመጣው ዘግይቶ ነው:: ካንሠሩ ከተሰራጨ በኋላ ነው ወደ እኛ ለሕክምና የሚመጡት ”ይላሉ::
የአንጀት ካንሠር ከአንድ እስከ አራት የሕመሙ ደረጃዎች እንዳሉት የተናገሩት ዶክተር ክብረቴ በደረጃ አንድ የካንሠር ሕመም ላይ የሚገኝ ታማሚ ካንሠሩ በመጠን ትንሽ እና ወደ ሌሎች የአካል ክፍል ያልተሰራጩበት ነው:: ደረጃ ሁለት ካንሠር ደግሞ በመጠን ትልቅ ሲሆን እሱም ልክ እንደ ደረጃ አንድ ሁሉ ካንሠሩ ወደ ሌሎች የአካል ከፍሎች ያልተሰራጨ ነው::
ደረጃ ሦስት ካንሰር የሚባለው ደግሞ ካንሠሩ በአካባቢው ወዳሉ ሌሎች የሰውነት ክፍሎች (ሊምፍ ኖድስ) ተሠራጭቶ ይገኛል:: ደረጃ አራት ካንሰር የሚባለው የመጨረሻው ደረጃ ሲሆን ካንሠሩ ወደ ሌሎች የሰውነት ክፍሎች በመሰራጨት ሁለተኛ ዕጢ ይፈጥራል። አንድ ሰው ደረጃ አራት የደረሰ የአንጀት ካንሠር ካለው የመዳን ዕድሉ የመነመነ እንደሆነ ነው የተናገሩት::
ዶ/ር ክብረቴ እንደሚሉት ከፍተኛ ድካም፣ ከዐይነምድር ላይ ደማቅ ቀይ ወይም ጠቆር ያለ ቀይ ደም፣ በተደጋጋሚ መፀዳጃ ቤት መጠቀም፣ ተቅማጥ ወይም ድርቀት ሲከሰት፣ መፀዳጃ ቤት ከተጠቀሙ በኋላ በደንብ ያልተጻዳዱ የሚመስል ስሜት መሰማት፣ ንፍጥ የቀላቀለ ዐይነ ምድር፣ ትንሽ ከተመገቡ በኋላ ሆድ የሞላ መምሰል፣ በታችኛው የሆድ ክፍል ላይ ሕመም ወይም እብጠት ሲኖር፣ የደም ማነስ፣ ስፖርት ሳይሰሩ ወይም ለክበደት መቀነስ የሚረዳ ነገር ሳያደርጉ የክብደት መቀነስ፣ እነዚህ ምልክቶች ለሦስት ሳምንታትና ከዚያ በላይ ለሆነ ጊዜ ካጋጠመዎት በፍጥነት በሐኪም መታየት ይኖርበዎታል:: ምክንያቱም እነዚህ ምልክቶች የአንጀት ካንሠር ሊሆኑ ይችላሉና::
የአንጀት ካንሠር ምልክቶች ከታዩ ፈጠን ብሎ ሐኪም ማማከር በሽታውን ለመቆጣጠር ወሳኝ ነው። ምርመራውም ቱቦ በመጠቀም ሁሉንም የአንጀት ክፍሎች በካሜራ በሚያሳይ መሣሪያ (ኮሎኖስኮፒ) በማድረግ ካንሠሩ መኖርና አለመኖሩን ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው።
በመጀመሪያው የአንጀት ካንሰር ደረጃ ላይ ምርመራ ያደረጉ ሰዎች በሽታውን በቶሎ በመለየት አስፈላጊው ሕክምናን በወቅቱ ማግኘት ስለሚችሉ የሚከሰተውን ጉዳት በከፍተኛ ደረጃ መቀነስ ይቻላል። የካንሠር በሽታ በብዛት የሚከሰተውና ገዳይ የሚሆነው ዕድሜያቸው በገፉ ሰዎች ላይ በመሆኑ ልክ እንደ ሌሎች የካንሠር በሽታዎች ሁሉ በአንጀት ካንሰር የተያዙ ከ15 እስከ 40 ባለው የዕድሜ ክልል የሚገኙ ሰዎች በሕይወት የመቆየታቸው ዕድል ሰፊ ነው።
ጤናማ የሕይወት ዘይቤን በመከተል፣ በቂ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ፣ በብዛት አሰር ያላቸውን ምግቦች በመመገብ እና ስብን በመቀነስ እንዲሁም በቀን ውስጥ ከስድስት እስከ ስምንት ብርጭቆ ውሃ በመጠጣት የአንጀት ካንሠርን ቀድሞ መከላከል እንደሚቻል ተናግረዋል:: እንዲሁም በየትኛውም የዕድሜ ክልል በበሽታው ለተያዘ ሰው ሕክምናው እንደሚሰጥ ሕክምናውም ቀዶ ሕክምና፣ ኬሞቴራፒ፣ ራዲዮቴራፒ (ጨረራ) ወይም ደግሞ እንደየግለሰቡ የካንሠር ሁኔታ ሌሎች ሕክምናዎች ሊሰጡ እንደሚችሉ ነው ያብራሩት:: የአንጀት ካንሠር ቀድሞ ተለይቶ ከታከመ ተመልሶ እንደማይከሰት ነው የተናገሩት::
በመጨረሻም ዶ/ር ክብረቴ እንደሚሉት ሕብረተሰቡ እላይ የተጠቀሱት ምልክቶች ሲያጋጥሙት በፍጥነት ወደ ሕክምና ተቋም መሄድ ይኖርበታል:: በባሕላዊ መንገድ አለመታከም፣ የኮሎኖስኮፒ ምርመራን አለመፍራት ሲሉ ምክራቸውን ለግሰዋል:: (ሳባ ሙሉጌታ)
በኲር የመጋቢት 15 ቀን 2017 ዓ.ም ዕትም
በአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዘወትር ሰኞ የምትታተመውን የበኲር ጋዜጣን ሙሉ ፒዲኤፍ
በhttp:// www.ameco.et/Bekur
በቴሌግራም - https://t.me/bekur123 ላይ ማግኘት ይችላሉ።

ትኩረት ያልተሰጠው የጉበት በሽታ የሚያዝያ 27 ቀን 2017 ዓ.ም ዕትምጉበት  በሰው ልጅ አካል ውስጥ በትልቅነቱ ከቆዳ ቀጥሎ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ ይሁንና በአሁኑ ጊዜ በርካታ ሰዎ...
06/05/2025

ትኩረት ያልተሰጠው የጉበት በሽታ
የሚያዝያ 27 ቀን 2017 ዓ.ም ዕትም

ጉበት በሰው ልጅ አካል ውስጥ በትልቅነቱ ከቆዳ ቀጥሎ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ ይሁንና በአሁኑ ጊዜ በርካታ ሰዎች በጉበት ህመም እየተሰቃዩ እና አለፍ ሲልም ለሞት እየተዳረጉ ነው፡፡
በጥበበ ጊዮን ሆስፒታል እና በእያስታ ልዩ የህክምና ማዕከል የውስጥ ደዌ እና የአንጀት የጨጓራ እና የጉበት ሰብ ስፔሻሊስት ዶ/ር ክብረቴ ወልዴ እንዳሉት ጉበት በርካታ ሥራዎችን ያከናውናል፡፡ ከተግባራቱ መካከልም በአፋችን የምንወስደው ማንኛውም ነገር ወደ አንጀት ከገባ በኋላ ለምግብነትም ሆነ ለመጣራት ወደ ጉበት ነው የሚሄደው፡፡ ማንኛውም በሰውነታችን ውስጥ የገቡ መርዛማ የሆኑ (መድሃኒቶች) ነገሮችንም ያስወግዳል፡፡ እንዲሁም ፕሮቲን እና የደም መርጋት እንዳይከሰት የተለያዩ ንጥረ ነገሮች ያመርታል፡፡

በየሶስት ወሩ በአዲስ የሚተካው ደም /ሲያረጅ/ የሚወገደው በጉበት ነው፡፡ ጉበት ሌሎች በርካታ ሥራዎችንም እንደሚያከናውን ነው ዶ/ር ክብረቴ የተናገሩት፡፡
ጉበት በተለምዶ “ገራገር” ይባላል፤ ይህን ስያሜ ሊያገኝ የቻለው ብዙ ጉዳት ቢደርስበትም መልሶ መለምለም (ሪጀኔሬት) ስለሚችል እንደሆነ ባለሙያው ተናግረዋል፡፡ ለአብነትም የጉበት ንቅለ ተከላ ሲደረግ ከጤነኛው ክፍል ጥቂት ተቆርጦ እንደሆነ ነው ያስረዱት፡፡ ይህ የሚደረገውም ከእንደገና ስለሚያድግ ወይም ስለሚለመልም ነው፡፡

እንደ ዶ/ር ክብረቴ ሙያዊ ማብራሪያ ጉበት ሲጎዳ ምልክት ሳያሳይ ለብዙ ጊዜ ሊቆይ ይችላል፡፡ በዋነኛነት ያሚያጠቃው ሂፓታይተስ የሚባለው የጉበት ቫይረስ ነው፡፡ ሂፓታይተስ የጉበት ሴል ቁስለት ማለት እንደሆነ የጠቆሙት የህክምና ባለሙያው አምስት አይነት የጉበት ቫይረሶች እንዳሉም ነግረውናል፡፡ ሄፓታይተስ ኤ፣ቢ፣ሲ፣ዲ፣እና ኢ ተብለው ይጠራሉ፡፡
አብዛኛውን ጊዜ ከፍተኛ ጉዳት ብሎም ወደ ጉበት ካንሠር የሚቀየሩት ሄፓታይተስ ቢ እና ሲ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡ ሂፓታይተስ ዲ እና ኢ ግን ያልተለመዱ እና አልፎ አልፎ የሚከሰቱ ናቸው፡፡
ጉበት በመድሃኒቶች ዕክል ሊፈጠርበት እንደሚችል የጠቆሙት ዶ/ር ክብረቴ በተለይም "ወፍ" በሚል የባህል መድሃኒት የሚወስዱ ሰዎች ጉበታቸው ሊጎዳ እንደሚችል ነው የተናገሩት፡፡

ከፍተኛ ጉዳት በማስከተል ለሞት የሚዳርጉት ሂፓታይተስ ቢ እና ሲ የጉበት ቫይረሶች ከሰው ወደ ሰው ይተላለፋሉ፡፡ መተላለፊያ መንገዶችም ስለታማ ቁሳቁሶችን በጋራ በመጠቀም፣ ልቅ በሆነ የግብረ ስጋ ግንኙነት፣ ከእናት ወደ ልጅ በወሊድ ጊዜ ናቸው፡፡ በንቅለ ተከላ ጊዜም ሳይመረመር የሚሰጥ ጉበት ቫይረሶቹን ሊያስተላልፉ ይችላሉ፡፡
ሄፓታይተስ ኤ ደግሞ ከንጽህና ጉድለት የሚመጣ ሲሆን በምንመገባቸው ምግቦች እና መጠጦች አማካኝነት ቫይረሱ ወደ ሰውነት ሊገባ ይችላል፡፡ እንደ ዶ/ር ክብረቴ ማብራሪያ ሄፓታይተስ ኤ ብዙውን ጊዜ በልጆች ላይ ሲከሰት ሄፓታይተስ ኢ ደግሞ በነፍሰጡሮች ላይ ይከሰታል፡፡

ሄፓታይተስ ሲ በጊዜ ህክምና ከተደረገ ሊድን ይችላል፡፡ ይሁንና ምልክቶቹን ቀለል አድርጎ በማየት በፍጥነት ወደ ህክምና ቦታ ስለማይመጡ ለከፍተኛ ጉዳት እንደሚዳርግ ገልጸዋል፡፡ ሄፓታይተስ ቢ ግን ፈጽሞ አይድንም፡፡ ይሁንና ከሁለት ዓመት በላይ መድሃኒቶችን ሳያቋርጡ በመውሰድ በደም ውስጥ የሚገኘውን የቫይረሱን ቁጥር (viral laod) መቀነስ እንደሚቻል ተናግረዋል፡፡

በእኛ ሀገር ሁኔታ የሄፓታይተስ ቢ ቫይረስ ከአንድ መቶ ሰዎች መካከል በ10 ሰዎች ውስጥ እንደሚገኝ የጠቆሙት ዶ/ር ክብረቴ ይህ አሃዝ ከፍተኛ በመሆኑ ጥንቃቄ እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል፡፡

ሁሉም አይነት የጉበት ቫይረሶች ትኩሳት፣ የድካም ስሜት ፣ማቅለሽለሽ፣ የምግብ ፍላጎት ማጣት፣ በቀኝ በኩል የሆድ ህመም፣ የሰገራ መጥቆር፣ የሆድ መነፋት፣ የሰውነት እብጠት ፣ የማሰብ አቅም መቀነስ፣ የእንቅልፍ ሰዓት መዛባት… ምልክቶችን ያሳያሉ፡፡ ከፍተኛ የጉዳት ደረጃ ላይ ሲደርሱ ዐይን ቢጫ መሆን፣ ደም ማስታወክ እና የሰውነት እብጠት ብሎም ካንሠር ያመጣሉ፡፡

ዶ/ር ክብረቴ እንዳሉት ሰዎች እነዚህ የህመም ምልክቶች ሲያጋጥሟቸው “ወፍ ዞረችኝ” በማለት ወደ ባህላዊ ህክምና ይሄዳሉ፡፡ የሚሰጣቸው ባህላዊ መድኃኒትም የባሰ ጉበታቸው ላይ ጉዳት ሊያደርስባቸው እንደሚችል ተናግረዋል፡፡ “ወፍ የሚባል በሽታ የለም፤ ሳይንሱ አላረጋገጠውም፤ ስለዚህ ምልክቶቹን ካያችሁ ወደ ሕክምና ተቋማት መምጣት አስፈላጊ ነው!” በማለትም ምክራቸውን ለግሰዋል፡፡

የጉበት ቫይረስ በሰውነት ውስጥ መኖር አለመኖሩን እና አይነቱን በደም ምርመራ ማወቅ እንደሚቻልም ባለሙያው አስታውቀዋል፡፡ ቫይረሱ በደም ውስጥ እንዳለ ከተረጋገጠ ጉበት ምን ያህል ተጎድቷል የሚለውን ለማወቅ ደግሞ የአልትራሳውንድ እና የሲቲስካን ምርመራዎች እንደሚታዘዙ ነው ባለሙያው ያብራሩት፡፡

ሄፓታይተስ ቢ የመከላከያ ክትባት ሲኖረው ሄፓታይተስ ሲን ለመከላከል የሚያስችል ክትባት ግን እስካሁን አልተገኘም፡፡ ሄፓታይተስ የተገኘበት ሰው የምግብ ፍላጎቱ ስለሚቀንስ እንደምንም ብሎ በደንብ መውሰድ አለበት፡፡ በኛ ሀገር ሁኔታ ታማሚዎች የሚመጡት ዘግይተው በመሆኑ ይህ ሁኔታ መቀየር አለበት፤ ለሌላ አካሉ ትኩረት የሚሰጠውን ያህል ለጉበቱም ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት በየጊዜው ምርመራ ማድረግ እንዳለበት መክረዋል፡፡
በተለይም ሄፓታይተስ ሲ ምልክት ሳይኖርው ለ20 እና ለ30 ዓመታት ሊቆይ ስለሚችል በጊዜ መመርመር ከከፍተኛ ስቃይ እና ሞት ይታደጋል ሲሉም አስገንዝበዋል፡፡

የጉበት ቫይረስን ለመከላከል ልቅ ከሆነ የግብረስጋ ግንኙነት መታቀብ፣ የአልኮል መጠጥን እና ሲጋራ ማጨስ ማቆም፣ በሀኪም ካልታገዘ በቀር ማንኛውንም አይነት መድኃኒት ከመውሰድ መቆጠብ እንደሚገባ ባለሙያው መክረዋል፡፡ የባህል መድኃኒቶችን ከመውሰድ መቆጠብ፣ እንደ ጠባሳ/ሲርሆሲስ/ እና የጉበት ጮማ መኖራቸውን ለማረጋገጥ በየጊዜው ክትትል ማድረግ፣ ከታማሚው ጋር በጋራ የሚኖሩ ሰዎች ካሉ ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ መኖሩን ለማረጋገጥ የደም ምርመራ ማድረግ እንዲሁም ክትባት መውሰድ እና ህክምና ጀምረው ከሆነ ደግሞ በሃኪም የታዘዙ መድሃኒቶችን በአግባቡ መውሰድ፣ በተጨማሪም ያለ ሀኪም ትእዛዝ መድሃኒቶችን አለመውሰድ እንደሚገባ ዶ/ር ክብረቴ ተናግረዋል፡፡

(ሳባ ሙሉጌታ)
በኲር የሚያዝያ 27 ቀን 2017 ዓ.ም ዕትም
በአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዘወትር ሰኞ የምትታተመውን የበኲር ጋዜጣን ሙሉ ፒዲኤፍ
በhttp:// www.ameco.et/Bekur
በቴሌግራም - https://t.me/bekur123 ላይ ማግኘት ይችላሉ።

06/05/2025

ትኩረት ያልተሰጠው የጉበት በሽታ
የሚያዝያ 27 ቀን 2017 ዓ.ም ዕትም

ጉበት በሰው ልጅ አካል ውስጥ በትልቅነቱ ከቆዳ ቀጥሎ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ ይሁንና በአሁኑ ጊዜ በርካታ ሰዎች በጉበት ህመም እየተሰቃዩ እና አለፍ ሲልም ለሞት እየተዳረጉ ነው፡፡
በጥበበ ጊዮን ሆስፒታል እና በእያስታ ልዩ የህክምና ማዕከል የውስጥ ደዌ እና የአንጀት የጨጓራ እና የጉበት ሰብ ስፔሻሊስት ዶ/ር ክብረቴ ወልዴ እንዳሉት ጉበት በርካታ ሥራዎችን ያከናውናል፡፡ ከተግባራቱ መካከልም በአፋችን የምንወስደው ማንኛውም ነገር ወደ አንጀት ከገባ በኋላ ለምግብነትም ሆነ ለመጣራት ወደ ጉበት ነው የሚሄደው፡፡ ማንኛውም በሰውነታችን ውስጥ የገቡ መርዛማ የሆኑ (መድሃኒቶች) ነገሮችንም ያስወግዳል፡፡ እንዲሁም ፕሮቲን እና የደም መርጋት እንዳይከሰት የተለያዩ ሆርሞኖችን ያመርታል፡፡

በየአራት ወሩ በአዲስ የሚተካው ደም /ሲያረጅ/ የሚወገደው በጉበት ነው፡፡ ጉበት ሌሎች ጥቃቅን ሥራዎችንም እንደሚያከናውን ነው ዶ/ር ክብረቴ የተናገሩት፡፡
ጉበት በተለምዶ “ገራገር” ይባላል፤ ይህን ስያሜ ሊያገኝ የቻለው ብዙ ጉዳት ቢደርስበትም መልሶ መለምለም (ሪጀኔሬት) ስለሚችል እንደሆነ ባለሙያው ተናግረዋል፡፡ ለአብነትም የጉበት ንቅለ ተከላ ሲደረግ ከጤነኛው ክፍል ጥቂት ተቆርጦ እንደሆነ ነው ያስረዱት፡፡ ይህ የሚደረገውም ከእንደገና ስለሚያድግ ወይም ስለሚለመልም ነው፡፡

እንደ ዶ/ር ክብረቴ ሙያዊ ማብራሪያ ጉበት ሲጎዳ ምልክት ሳያሳይ ለብዙ ጊዜ ሊቆይ ይችላል፡፡ በዋነኛነት ያሚያጠቃው ሂፓታይተስ የሚባለው የጉበት ቫይረስ ነው፡፡ ሂፓታይተስ የጉበት ሴል ቁስለት ማለት እንደሆነ የጠቆሙት የህክምና ባለሙያው አምስት አይነት የጉበት ቫይረሶች እንዳሉም ነግረውናል፡፡ ሄፓታይተስ ኤ፣ቢ፣ሲ፣ዲ፣እና ኢ ተብለው ይጠራሉ፡፡
አብዛኛውን ጊዜ ከፍተኛ ጉዳት ብሎም ወደ ጉበት ካንሠር የሚቀየሩት ሄፓታይተስ ቢ እና ሲ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡ ሂፓታይተስ ዲ እና ኢ ግን ያልተለመዱ እና አልፎ አልፎ የሚከሰቱ ናቸው፡፡
ጉበት በመድሃኒቶች ዕክል ሊፈጠርበት እንደሚችል የጠቆሙት ዶ/ር ክብረቴ በተለይም "ወፍ" በሚል የባህል መድሃኒት የሚወስዱ ሰዎች ጉበታቸው ሊጎዳ እንደሚችል ነው የተናገሩት፡፡

ከፍተኛ ጉዳት በማስከተል ለሞት የሚዳርጉት ሂፓታይተስ ቢ እና ሲ የጉበት ቫይረሶች ከሰው ወደ ሰው ይተላለፋሉ፡፡ መተላለፊያ መንገዶችም ስለታማ ቁሳቁሶችን በጋራ በመጠቀም፣ ልቅ በሆነ የግብረ ስጋ ግንኙነት፣ ከእናት ወደ ልጅ በወሊድ ጊዜ ናቸው፡፡ በንቅለ ተከላ ጊዜም ሳይመረመር የሚሰጥ ጉበት ቫይረሶቹን ሊያስተላልፉ ይችላሉ፡፡
ሄፓታይተስ ኤ ደግሞ ከንጽህና ጉድለት የሚመጣ ሲሆን በምንመገባቸው ምግቦች እና መጠጦች አማካኝነት ቫይረሱ ወደ ሰውነት ሊገባ ይችላል፡፡ እንደ ዶ/ር ክብረቴ ማብራሪያ ሄፓታይተስ ኤ ብዙውን ጊዜ በልጆች ላይ ሲከሰት ሄፓታይተስ ኢ ደግሞ በነፍሰጡሮች ላይ ይከሰታል፡፡

ሄፓታይተስ ሲ በጊዜ ህክምና ከተደረገ ሊድን ይችላል፡፡ ይሁንና ምልክቶቹን ቀለል አድርጎ በማየት በፍጥነት ወደ ህክምና ቦታ ስለማይመጡ ለከፍተኛ ጉዳት እንደሚዳርግ ገልጸዋል፡፡ ሄፓታይተስ ቢ ግን ፈጽሞ አይድንም፡፡ ይሁንና ከሁለት ዓመት በላይ መድሃኒቶችን ሳያቋርጡ በመውሰድ በደም ውስጥ የሚገኘውን የቫይረሱን ቁጥር (viral laod) መቀነስ እንደሚቻል ተናግረዋል፡፡

በእኛ ሀገር ሁኔታ የሄፓታይተስ ቢ ቫይረስ ከአንድ መቶ ሰዎች መካከል በ10 ሰዎች ውስጥ እንደሚገኝ የጠቆሙት ዶ/ር ክብረቴ ይህ አሃዝ ከፍተኛ በመሆኑ ጥንቃቄ እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል፡፡

ሁሉም አይነት የጉበት ቫይረሶች ትኩሳት፣ የድካም ስሜት ፣ማቅለሽለሽ፣ የምግብ ፍላጎት ማጣት፣ በቀኝ በኩል የሆድ ህመም፣ የሰገራ መጥቆር፣ የሆድ መነፋት፣ የሰውነት እብጠት ፣ የማሰብ አቅም መቀነስ፣ የእንቅልፍ ሰዓት መዛባት… ምልክቶችን ያሳያሉ፡፡ ከፍተኛ የጉዳት ደረጃ ላይ ሲደርሱ ዐይን ቢጫ መሆን፣ ደም ማስታወክ እና የሰውነት እብጠት ብሎም ካንሠር ያመጣሉ፡፡

ዶ/ር ክብረቴ እንዳሉት ሰዎች እነዚህ የህመም ምልክቶች ሲያጋጥሟቸው “ወፍ ዞረችኝ” በማለት ወደ ባህላዊ ህክምና ይሄዳሉ፡፡ የሚሰጣቸው ባህላዊ መድኃኒትም የባሰ ጉበታቸው ላይ ጉዳት ሊያደርስባቸው እንደሚችል ተናግረዋል፡፡ “ወፍ የሚባል በሽታ የለም፤ ሳይንሱ አላረጋገጠውም፤ ስለዚህ ምልክቶቹን ካያችሁ ወደ ሕክምና ተቋማት መምጣት አስፈላጊ ነው!” በማለትም ምክራቸውን ለግሰዋል፡፡

የጉበት ቫይረስ በሰውነት ውስጥ መኖር አለመኖሩን እና አይነቱን በደም ምርመራ ማወቅ እንደሚቻልም ባለሙያው አስታውቀዋል፡፡ ቫይረሱ በደም ውስጥ እንዳለ ከተረጋገጠ ጉበት ምን ያህል ተጎድቷል የሚለውን ለማወቅ ደግሞ የአልትራሳውንድ እና የሲቲስካን ምርመራዎች እንደሚታዘዙ ነው ባለሙያው ያብራሩት፡፡

ሄፓታይተስ ቢ የመከላከያ ክትባት ሲኖረው ሄፓታይተስ ሲን ለመከላከል የሚያስችል ክትባት ግን እስካሁን አልተገኘም፡፡ ሄፓታይተስ የተገኘበት ሰው የምግብ ፍላጎቱ ስለሚቀንስ እንደምንም ብሎ በደንብ መውሰድ አለበት፡፡ በኛ ሀገር ሁኔታ ታማሚዎች የሚመጡት ዘግይተው በመሆኑ ይህ ሁኔታ መቀየር አለበት፤ ለሌላ አካሉ ትኩረት የሚሰጠውን ያህል ለጉበቱም ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት በየጊዜው ምርመራ ማድረግ እንዳለበት መክረዋል፡፡
በተለይም ሄፓታይተስ ሲ ምልክት ሳይኖርው ለ20 እና ለ30 ዓመታት ሊቆይ ስለሚችል በጊዜ መመርመር ከከፍተኛ ስቃይ እና ሞት ይታደጋል ሲሉም አስገንዝበዋል፡፡

የጉበት ቫይረስን ለመከላከል ልቅ ከሆነ የግብረስጋ ግንኙነት መታቀብ፣ የአልኮል መጠጥን እና ሲጋራ ማጨስ ማቆም፣ በሀኪም ካልታገዘ በቀር ማንኛውንም አይነት መድኃኒት ከመውሰድ መቆጠብ እንደሚገባ ባለሙያው መክረዋል፡፡ የባህል መድኃኒቶችን ከመውሰድ መቆጠብ፣ እንደ ጠባሳ/ሲርሆሲስ/ እና የጉበት ጮማ መኖራቸውን ለማረጋገጥ በየጊዜው ክትትል ማድረግ፣ ከታማሚው ጋር በጋራ የሚኖሩ ሰዎች ካሉ ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ መኖሩን ለማረጋገጥ የደም ምርመራ ማድረግ እንዲሁም ክትባት መውሰድ እና ህክምና ጀምረው ከሆነ ደግሞ በሃኪም የታዘዙ መድሃኒቶችን በአግባቡ መውሰድ፣ በተጨማሪም ያለ ሀኪም ትእዛዝ መድሃኒቶችን አለመውሰድ እንደሚገባ ዶ/ር ክብረቴ ተናግረዋል፡፡

(ሳባ ሙሉጌታ)
በኲር የሚያዝያ 27 ቀን 2017 ዓ.ም ዕትም
በአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዘወትር ሰኞ የምትታተመውን የበኲር ጋዜጣን ሙሉ ፒዲኤፍ
በhttp:// www.ameco.et/Bekur
በቴሌግራም - https://t.me/bekur123 ላይ ማግኘት ይችላሉ።

21/04/2025

የሀሞት ጠጠር
የሚያዝያ 13 ቀን 2017 ዓ.ም ዕትም
የሀሞት ከረጢት ጠጠር በሀሞት ከረጢት ውስጥ ሊፈጠር የሚችል ጠጣር የሀሞት ክምችት ነው። የሀሞት ከረጢት ጠጠሮች መጠናቸው ከትንንሽ የአሸዋ ቅንጣቶች እስከ የ“ጎልፍ” ኳሶች ሊደርሱ ይችላሉ፡፡ ብዙ የሀሞት ከረጢት ጠጠር ያለባቸው ሰዎች ምንም ምልክት ባይኖራቸውም የሀሞት ጠጠር ወደ አንጀት የሚወስደውን ቱቦ በመዝጋት ድንገተኛና ከባድ የሆድ ሕመም ሊያስከትልባቸው እንደሚችል የጤና ጉዳዮችን በብዛት በመተንተን የሚታወቀው ዓለም ዓቀፉ ዊቢ ኤ ምዲ (www.WebMD.com) ድረ ገጽ አስነብቧል፡፡
ታዲያ እኛም በዚህ ሳምንት የጤና አምዳችን ስለ ሀሞት ጠጠር የበለጠ ግንዛቤ ይፈጥርልን ዘንድ በእያስታ የጤና መዕከል የአጠቃላይ ቀዶ ጥገና ስፔሻሊስት እና የጉበት፣ የቆሽትና የሀሞት ከረጢት ሳብ ስፔሻሊስት ከሆኑት ዶ/ር ዘበናይ ውቤ ጋር ቆይታ አድርገናል፡፡
ዶ/ር ዘበናይ እንዳሉት ሀሞት በጉበት ተመርቶ በሀሞት ከረጢት ተጠራቅሞ እና አስፈላጊ ሲሆን ወደ ትንሹ አንጀት የሚረጪ ፈሳሽ ነው፡፡
በዋናነት ቅባታማ ምግቦች /ጮማ/ በምንመገብበት ጊዜ የምግብ ሥርዓት ስብስቡን ያሳልጣል፡፡ ይህ ማለት ምግብ በምንመገብበት ጊዜ (በተለይ ቅባታማ ምግቦችን) ሀሞት ይረጫል፡፡ እንዲሁም አንዳንድ ቆሻሻዎችን ከሰውነት እንዲወገዱ እና አላስፈላጊ ባክቴሪያዎች ከአንጀት እንዲወገዱ ያደርጋል፡፡
የሀሞት ከረጢት ጠጠር የሚፈጠረው በሦስት መንገዶች እንደሆነ የተናገሩት ዶ/ር ዘበናይ አንደኛው በሀሞት ብክለት (ኢንፌክሽን) ሲሆን ሁለተኛው የሀሞት ከረጢት እንቅስቃሴ በሚቀንስበት እና ሦስተኛው ደግሞ የቀይ ደም ሕዋሳት በብዛት በሚመረቱበት ጊዜ ነው፡፡
የሀሞት ከረጢት ጠጠር እንዲፈጠር ከሚያደርጉ ሁኔታዎች መካከል ዕድሜ (ከ40 ዓመት በላይ በሆኑ ሰዎች) ፣ በእርግዝና ወቅት፣ የሆርሞን ሕክምና በሚያደርጉ ሰዎች፣ ከዚህ በፊት በቤተሰብ የሀሞት ከረጢት ጠጠር ያለባቸው ሰዎች፣ አንዳንድ መድኃኒቶች (ለአብነትም ኮሌስትሮል ያለባቸው ሰዎች የሚወስዱት መድኃኒት) ተጠቃሽ ናቸው፡፡
አትክልትና ፍራፍሬ አለማዘውተር፣ ቅባታማ መግቦችን ማዘውተር፣ በቂ ፈሳሽ አለመውሰድ፣ በቂ የሰውነት እንቅስቃሴ አለማድረግ፣ አልኮል በብዛት መውሰድ፣ ክብደት በፍጥነት መጨመር እና በፍጠነት መቀነስ ለሀሞት ጠጠር መከሰት ምቹ ሁኔታዎችን እንደሚፈጥሩም ዶ/ር ዘበናይ አብራርተዋል።
ባለሙያው እንደተናገሩት በአብዛኛው ሰዎች (80 በመቶ የሚሆኑት) የሀሞት ከረጢት ጠጠሩ ምንም ዓይነት የሕመም ምልክት ሳይፈጥርባቸው ለረዥም ጊዜ ሊቆዩ ይችላሉ፡፡ ወይም ፈፅሞ ሕመም ላይኖራቸው ይችላል። የሀሞት ከረጢት ጠጠር እንዳለባቸው የሚታወቀው በሌላ ሕመም ምክንያት አሊያም ለሕክምና ክትትል በሚታዘዝ የአልትራሳውንድ ምርመራ ነው፡፡
የሀሞት ከረጢት ጠጠር ያለባቸው ሰዎች ምናልባት ምልክት በሚኖራቸው ጊዜ በብዛት የሚስተዋሉት በቀኝ በኩል ከጎድን አጥንት ዝቅ ብሎ ውጋት፣ አልፎ አልፎ ከሕመሙ ጋር የተያያዘ መጠነኛ ትኩሳት፣ ማቅለሽለሽና ማስመለስ እንዲሁም የዓይን ቢጫ መሆን ናቸው። ብዙ ጊዜ ሕመሙ ምግብ ከተበላ ከ30 እና 40 ደቂቃ በኋላ የሚጀምር ሲሆን ሕመሙም ከአንድና ከሁለት ሰዓት በኋላ ተመልሶ የሚጠፋ ይሆናል ብለዋል፡፡
እንደ ዶ/ር ዘበናይ ማብራሪያ አንዳንድ ጊዜ የሀሞት ከረጢት ጠጠር ኖሮም ሌሎች ተያያዥ ሕመሞች (ለምሳሌ የጨጓራ ሕመም) ሊኖሩ ይችላሉ። በዚህ ጊዜ ሕመሙን መለየት ይገባል። ከላይ ከተገለጹት የሕመሙ ምልክቶች ባሻገር የተለዬ ነገር ከተሰማን በሕክምና መረጋገጥ አለበት ሲሉም ያሳስባሉ፡፡
የጨጓራ ሕመማቸው የሚመላለስ (በተደጋጋሚ የሚከሰት) እና መፍትሔ ከሌለው የሀሞት ጠጠር ሊሆን ስለሚችል ቢታዩት መልካም ነው ሲሉም ይመክራሉ።
የሀሞት ከረጢት ከጠጠሩ ጋር ተያይዞ ብክለት (ኢንፌክሽን) በሚኖርበት ጊዜ ልትፈነዳ ትችላለች፡፡ ይህ ሁኔታ በፍጥነት ካልታከመ ለሞት እንደሚዳርግ ነው የሕክምና ባለሙያው የሚናገሩት፡፡ ኢንፌክሽን ሲፈጠር በፊት ለአንድ ስዓት እና ለሁለት ስዓት ያህል ይቆይ የነበረው ሕመም እስከ ሁለት ቀናት ሊቆይ እንደሚችልም ጠቁመዋል። ከዚህ በሻገር ከፍተኛ ሙቀት (ትኩሳት)፣ የምግብ ፍላጎት መቀነስና ማቅለሽለሽ ይኖረዋል፡፡ እንዲሁም ሕመሙ በፊት ከነበረው በጣም ጠንካራ ይሆናል፡፡ በዚህ ጊዜ በፍጥነት ወደ ሕክምና ተቋም ከተደረሰ የሀሞት ከረጢት ሳትፈነዳ ማከም እንደሚቻል ተናግረዋል፡፡
በዋናነት የሀሞት ከረጢት ጠጠር ሕክምና ጠጠሩን ከነሀሞት ከረጢቱ በቀዶ ጥገና ሕክምና ማስወገድ ሲሆን ይኸውም ሆድን በመክፈት አሊያም በሆድ ግድግዳ ላይ ትንንሽ ቀዳዳዎች በማበጀት በካሜራ ዕይታ እየታገዘ ሊሠራ ይችላል። ይህም ሕክምና ላፓራስኮፒ እንደሚባል ነው ዶ/ር ዘላለም የገለጹልን፡፡
ላፓራስኮፒ ያልተወሳሰበ የሀሞት ከረጢት ጠጠር በሚኖርበት ጊዜ ተመራጪ ሲሆን የሚፈጠረው ክፍተት ከአንድ ሴንቲ ሜትር አይበልጥም፡፡ በላፓራስኮፒ የሚደረግ ቀዶ ጥገና ታካሚዎች ቶሎ እንዲያገግሙ ስለሚያደርግና አነስተኛ ማስታገሻዎችን እንዲወስዱ ስለሚያስችል ተመራጭ ነው፡፡ ሁለተኛው ሕክምና ከአራት እስከ አምስት ሴንቲ ሜትር ሰውነትን በመክፈት የሚከናወን ቀዶ ጥገና ነው፡፡ ይህም የሚከናወነው የላፓራስኮፒ መንገድ ውስብስብ ከሆነ ነው። እንዲሁም ኢንፌክሽን ሲኖር ተመራጩ ቀዶ ጥገና ነው፡፡
የሀሞት ከረጢት አለመኖር ብዙም የሚያመጣው ችግር የለም፡፡ ሆኖም የሀሞት ከረጢቷ ከተወገደች በኋላ ቅባታማ ምግብ እና እስክንጠግብ ስንመገብ የሕመም ስሜት ሊኖር እንደሚችል ነው የሕክምና ባለሙያው የጠቆሙት፡፡ በተለይ የሀሞት ከረጢቷ ከተወገደች በኋላ ባሉት ከሦስት እስከ ስድስት ወራት በአንድ ጊዜ እስክንጠግብ እና እንዲሁም ቅባታማ ምግቦችንም መመገብ አይመከርም ይላሉ፡፡
ባለሙያው አክለውም አንዳንድ የአኗኗር ዘይቤ ለውጦችን በማድረግ የሀሞት ጠጠርን እንዳይከሰት ማድረግ እንደሚቻል ያብራራሉ። ለአብነትም አትክልትና የጥራጥሬ እህሎችን፣ ብዙ ፋይበር እና አነስተኛ ቅባት ያላቸውን ምግቦች (ለውዝ፣ ስንዴ፣ አጃ፣ የወይራ ዘይት እና አሳ) አዘውትሮ መመገብ ይመከራል። ይህም ፋይበር ከመጠን በላይ ኮሌስትሮል ከሰውነት ውስጥ ለማስወገድ ይረዳል።
ከዚህ በተጨማሪም መደበኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን በቀን ቢያንስ ለ30 ደቂቃዎች ማከናወን ተመራጭ መሆኑን የጤና ባለሙያው ይመክራሉ። “ታሞ ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ” ነውና ብሂሉ ይተግብሩት መልዕክታችን ነው።
(ሳባ ሙሉጌታ)
በኲር የሚያዝያ 13 ቀን 2017 ዓ.ም ዕትም
በአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዘወትር ሰኞ የምትታተመውን የበኲር ጋዜጣን ሙሉ ፒዲኤፍ
በhttp:// www.ameco.et/Bekur
በቴሌግራም - https://t.me/bekur123 ላይ ማግኘት ይችላሉ።

ስለ አንጀት ካንሰር ምን ያህል ያውቃሉ⁉ከዛሬ ዘጠኝ ዓመት በፊት ነው ጉዳዩ የተከሰተው:: አንዲት ዕድሜያቸው በሃምሳዎቹ መጨረሻ ላይ የሚገኙ እናት ነበሩ:: በሕይዎት ዘመናቸው ከባድ ሕመም ታ...
01/04/2025

ስለ አንጀት ካንሰር ምን ያህል ያውቃሉ⁉

ከዛሬ ዘጠኝ ዓመት በፊት ነው ጉዳዩ የተከሰተው:: አንዲት ዕድሜያቸው በሃምሳዎቹ መጨረሻ ላይ የሚገኙ እናት ነበሩ::
በሕይዎት ዘመናቸው ከባድ ሕመም ታመው ወደ ሕክምና ተቋም ደርሰው አያውቁም ነበር::
ነገር ግን አልፎ አልፎ በሚያጋጥማቸው የሆድ ሕመም ወደ ክሊኒክ ጎራ ይሉ ነበር:: ታዲያ በወቅቱ ሀኪም አገኘሁት እሚላቸው በሽታ አሜባ እና ጃርዲያ ነበር:: ከዚህ የከፋ ሕመም አጋጥሟቸው አያውቅም::
ሆኖም በሕይዎት ከማለፋቸው አንድ ዓመት አካባቢ ሲቀራቸው በተደጋጋሚ የሆድ ሕመም እና ቶሎ ቶሎ የሚመጣ ደም የቀላቀለ ተቅማጥ ተከሰተባቸው:: ሕመሙ ፋታ የሚሰጥ አልነበረም:: እንደበፊቱ በአሜባ መድሃኒት የሚታገስም አልሆነ። በመሆኑም ሐኪሙ የኮሎኖስኮፒ ምርመራ አዘዘላቸው::

ኮሎኖስኮፒ ጫፉ ላይ ካሜራ ያለው ቀጭን ረዥም እና ተጣጣፊ ቱቦ ሲሆን በፊንጢጣ በኩል በመግባት አንጀትን የሚያሳይ መሳሪያ ነው:: በኮሎኖስኮፒው አማካኝነት ከአንጀት ዕባጩ ላይ ትንሽ ፈሳሽ በመውሰድ ምርመራ ከተደረገላቸው ከ15 ቀን በኋላም ውጤቱ ደረጃ አራት የደረሰ የትልቁ አንጀት ካንሠር ነበር የተባሉት:: በሽታው ከታወቀ ስድስት ወር ባልሞላ ጊዜም ሕይዎታቸውን ሊያጡ እንደቻሉ ዛሬ ልጃቸው በፀፀት የነበረውን ሁኔታ በዐይነ ህሊናዋ እያስታወሰች ነግራናለች::

ልጃቸው እንደምትለው ምናልባት የኮሎኖስኮፒ ምርመራው አስቀድሞ ቢታዘዝላቸው ኖሮ ካንሠሩ ቀድሞ ይታወቅና ሕክምና ተደርጎላቸው መዳን ይችሉ ነበር::
ይህ ታሪክ የብዙ ሰዎች ነው:: የሆድ ሕመምን ቀለል አድርጎ ማሰብ፣ የሕክምና ባለሙያውም ምልክቶችን አይቶ የኮሎኖስኮፒ ምርመራ በፍጥነት አለማድረጉ ካንሠሩ ወዲያው ላለመታከሙ ምክንያቶች ናቸው::

ስንቶቻችን ነን ስለ አንጀት ካንሠር ግንዛቤው ያለን? መልካም ግንዛቤው ካለዎት ለሌለው እንዲያደርሱ አደራ እያልን፤ ግንዛቤው ከሌለዎት ደግሞ ስለ አንጀት ካንሠር ሙያዊ ማብራሪያ ለማግኘት በእያስታ ሕክምና ማዕከል የውስጥ ደዌ፣ የጨጓራ፣ አንጀት እና የጉበት ሰብ ስፔሻሊስት ዶ/ር ክብረቴ ወልዴ ጋር ያደረግነውን ቆይታ በጽሞና ታነቡ ዘንድ ጋብዘንዎታል‼

ካንሠር ማለት ምን ማለት ነው? የአንጀት ካንሠርስ? ለሚለው ጥያቄያችንም ይህንን መልስ ሰጥተውናል:: ካንሠር ሰውነታችን ማይቆጣጠረው ጤነኛ ያልሆኑ የሴሎች እድገት ማለት ነው:: ካንሠር በሁሉም የሰውነት ክፍሎች ላይ ሊከሰት ይችላል:: ካንሠር በጥቅሉ እንደ ሀገር እያደገ የመጣ ችግር ነው:: በፊት በበለጸጉ ሀገራት ላይ ነበር የሚከሰተው። አሁን ግን በታዳጊ ሀገራትም በብዛት መከሰት ጀምሯል ነው ያሉን::

የአንጀት ካንሠር ደግሞ በብዛት የትልቁ አንጀት ካንሠር ማለት እንደሆነ ነው፤ ባለሙያው ያብራሩት:: ምክንያቱም የአንጀት ካንሠር የሚነሳው ከትልቁ አንጀት እና ከፊንጢጣ አካባቢ ላይ ካለ ዕጢ ነው:: የአንጀት ካንሠር በዓለም አቀፍ ደረጃ በሦስተኛ ላይ ይገኛል:: በገዳይነቱ ደግሞ በሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ በሽታ እንደሆነ ነው የጠቆሙት::

ለአንጀት ካንሠር የሚያጋልጡ ሁኔታዎች የመጀመሪያዉ ዕድሜ እንደሆነ የሚያብራሩት ዶ/ር ክብረቴ ፤ እድሜያቸው ከ50 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎች ለካንሠሩ ተጋላጭ ናቸው:: ሌላው በቤተሰብ (አባት፣ እናት፣ እህት ወንድም) የአንጀት ካንሠር ያለበት ሰው የመያዝ አጋጣሚው ይጨምራል:: ክብደት መጨመር፣ አልኮል መጠጣት፣ ሲጋራ ማጨስ፣ አትክልት እና ፍራፍሬ አለማዘውተር፣ ስጋን አብዝቶ መመገብ ለበሽታው እንደሚያጋልጡ ነው የተናገሩት::

የአንጀት ካንሠር መጀመሪያ ላይ ትንሽ ዕጢ ነው ሚሆነው:: ዕጢው እያደገ ሲመጣ ነው ወደ ካንሠር የሚቀየረው:: ዕጢዋ በእንግሊዘኛ ፖሊፕ ትባላለች፤ ወደ ካንሠር ለመቀየር እድገቱ እስከ 10 ዓመት ሊቆይ ይችላል:: በየጊዜው ምርመራ የምናደርግ ከሆነ ግን እብጠቱ ወደ ካንሠር ከመቀየሩ በፊት ችግሩ ሊለይ እና ሊታከም እንደሚችል ነው የተናገሩት::

ዶ/ር ክብረቴ እንደሚሉት በኢትዮጵያ ካንሠር ይከሰትበታል ተብሎ ከሚጠበቀው ዕድሜ በታች እየተከሰተ ይገኛል::

እሳቸው እንደሚሉት ካንሠር የሚከሰተው ከቤተሰብ ጋር ተያይዞ የካንሠር ታሪክ ያለው ቤተሰብ ካልሆነ በቀር ብዙውን ጊዜ ዕድሜያቸው ሃምሳ ዓመት እና በላይ በሆኑ ሰዎች ነበር:: ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ቀድሞ መታየት ጀምሯል::

አብዛኛው ሰው ሆዱን ሲታመም ‘አሜባ ነው፣ የምግብ መበከል ነው …’ በሚል አመጋገቡን ለማስተካከል ይሞክራል እንጂ ወደ ሕክምና ተቋም እንደማይመጣ ነው ባለሙያው የተናገሩት:: “በየቀኑ የምናየው ነገር በመሆኑም ብዙ ታካሚ የሚመጣው ዘግይቶ ነው:: ካንሠሩ ከተሰራጨ በኋላ ነው ወደ እኛ ለሕክምና የሚመጡት ”ይላሉ::

የአንጀት ካንሠር ከአንድ እስከ አራት የሕመሙ ደረጃዎች እንዳሉት የተናገሩት ዶክተር ክብረቴ በደረጃ አንድ የካንሠር ሕመም ላይ የሚገኝ ታማሚ ካንሠሩ በመጠን ትንሽ እና ወደ ሌሎች የአካል ክፍል ያልተሰራጩበት ነው:: ደረጃ ሁለት ካንሠር ደግሞ በመጠን ትልቅ ሲሆን እሱም ልክ እንደ ደረጃ አንድ ሁሉ ካንሠሩ ወደ ሌሎች የአካል ከፍሎች ያልተሰራጨ ነው::

ደረጃ ሦስት ካንሰር የሚባለው ደግሞ ካንሠሩ በአካባቢው ወዳሉ ሌሎች የሰውነት ክፍሎች (ሊምፍ ኖድስ) ተሠራጭቶ ይገኛል:: ደረጃ አራት ካንሰር የሚባለው የመጨረሻው ደረጃ ሲሆን ካንሠሩ ወደ ሌሎች የሰውነት ክፍሎች በመሰራጨት ሁለተኛ ዕጢ ይፈጥራል። አንድ ሰው ደረጃ አራት የደረሰ የአንጀት ካንሠር ካለው የመዳን ዕድሉ የመነመነ እንደሆነ ነው የተናገሩት::

ዶ/ር ክብረቴ እንደሚሉት ከፍተኛ ድካም፣ ከዐይነምድር ላይ ደማቅ ቀይ ወይም ጠቆር ያለ ቀይ ደም፣ በተደጋጋሚ መፀዳጃ ቤት መጠቀም፣ ተቅማጥ ወይም ድርቀት ሲከሰት፣ መፀዳጃ ቤት ከተጠቀሙ በኋላ በደንብ ያልተጻዳዱ የሚመስል ስሜት መሰማት፣ ንፍጥ የቀላቀለ ዐይነ ምድር፣ ትንሽ ከተመገቡ በኋላ ሆድ የሞላ መምሰል፣ በታችኛው የሆድ ክፍል ላይ ሕመም ወይም እብጠት ሲኖር፣ የደም ማነስ፣ ስፖርት ሳይሰሩ ወይም ለክበደት መቀነስ የሚረዳ ነገር ሳያደርጉ የክብደት መቀነስ፣ እነዚህ ምልክቶች ለሦስት ሳምንታትና ከዚያ በላይ ለሆነ ጊዜ ካጋጠመዎት በፍጥነት በሐኪም መታየት ይኖርበዎታል:: ምክንያቱም እነዚህ ምልክቶች የአንጀት ካንሠር ሊሆኑ ይችላሉና::

የአንጀት ካንሠር ምልክቶች ከታዩ ፈጠን ብሎ ሐኪም ማማከር በሽታውን ለመቆጣጠር ወሳኝ ነው። ምርመራውም ቱቦ በመጠቀም ሁሉንም የአንጀት ክፍሎች በካሜራ በሚያሳይ መሣሪያ (ኮሎኖስኮፒ) በማድረግ ካንሠሩ መኖርና አለመኖሩን ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው።

በመጀመሪያው የአንጀት ካንሰር ደረጃ ላይ ምርመራ ያደረጉ ሰዎች በሽታውን በቶሎ በመለየት አስፈላጊው ሕክምናን በወቅቱ ማግኘት ስለሚችሉ የሚከሰተውን ጉዳት በከፍተኛ ደረጃ መቀነስ ይቻላል። የካንሠር በሽታ በብዛት የሚከሰተውና ገዳይ የሚሆነው ዕድሜያቸው በገፉ ሰዎች ላይ በመሆኑ ልክ እንደ ሌሎች የካንሠር በሽታዎች ሁሉ በአንጀት ካንሰር የተያዙ ከ15 እስከ 40 ባለው የዕድሜ ክልል የሚገኙ ሰዎች በሕይወት የመቆየታቸው ዕድል ሰፊ ነው።

ጤናማ የሕይወት ዘይቤን በመከተል፣ በቂ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ፣ በብዛት አሰር ያላቸውን ምግቦች በመመገብ እና ስብን በመቀነስ እንዲሁም በቀን ውስጥ ከስድስት እስከ ስምንት ብርጭቆ ውሃ በመጠጣት የአንጀት ካንሠርን ቀድሞ መከላከል እንደሚቻል ተናግረዋል::

እንዲሁም በየትኛውም የዕድሜ ክልል በበሽታው ለተያዘ ሰው ሕክምናው እንደሚሰጥ ሕክምናውም ቀዶ ሕክምና፣ ኬሞቴራፒ፣ ራዲዮቴራፒ (ጨረራ) ወይም ደግሞ እንደየግለሰቡ የካንሠር ሁኔታ ሌሎች ሕክምናዎች ሊሰጡ እንደሚችሉ ነው ያብራሩት:: የአንጀት ካንሠር ቀድሞ ተለይቶ ከታከመ ተመልሶ እንደማይከሰት ነው የተናገሩት::

በመጨረሻም ዶ/ር ክብረቴ እንደሚሉት ሕብረተሰቡ እላይ የተጠቀሱት ምልክቶች ሲያጋጥሙት በፍጥነት ወደ ሕክምና ተቋም መሄድ ይኖርበታል:: በባሕላዊ መንገድ አለመታከም፣ የኮሎኖስኮፒ ምርመራን አለመፍራት ሲሉ ምክራቸውን ለግሰዋል::

ምንጭ ፦በኲር የመጋቢት 15 ቀን 2017 ዓ.ም ዕትም

28/03/2025
A brief explanation about colon cancer.
27/02/2025

A brief explanation about colon cancer.

Watch, follow, and discover more trending content.

Address

NOC
Bahir Dar

Opening Hours

Monday 00:00 - 23:59
Tuesday 00:00 - 23:59
Wednesday 00:00 - 23:59
Thursday 00:00 - 23:59
Friday 00:00 - 23:59
Saturday 00:00 - 23:59
Sunday 00:00 - 23:59

Telephone

+251582264260

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Eyasta Medical Center/እያስታ የህክምና ማዕከል posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Eyasta Medical Center/እያስታ የህክምና ማዕከል:

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram