MediLab

MediLab Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from MediLab, Medical and health, .

ጥብቅ ማሳሰቢያ ይህ የጤና ባለሞያዎች ንቅናቄ  የፖለቲከኞች  አይደለም የለፍቶ አዳሪ ዜጎች ነው::ስለዚህም በአንዳንድ ፖለቲከኞች እየተደረገ የሚሰተዋለውን ድምፅን የመጥለፍ እና ከእናንተ በላ...
08/05/2025

ጥብቅ ማሳሰቢያ

ይህ የጤና ባለሞያዎች ንቅናቄ የፖለቲከኞች አይደለም የለፍቶ አዳሪ ዜጎች ነው::

ስለዚህም በአንዳንድ ፖለቲከኞች እየተደረገ የሚሰተዋለውን ድምፅን የመጥለፍ እና ከእናንተ በላይ እኔ አውቅላቹሀለሁ አካሄድ ንቅናቄያችንን ፈፅሞ የማይወክልና አጥብቀን የምንቃወመው ነው::

ውድ ጤና ባለሙያዎች ከንቅናቄው መሪዎች ስር ከሚገኙ ማህበራዊ ሚዲያዎች ከሚተላለፉ መመሪያዎች እና መረጃዎች በስተቀር በተናጠል ለአክቲቪስቶችም ሆነ ለሌሎች አካላት መረጃ ከመስጠት እና ከመቀበል እንዲሁም ከማሰራጨት እንድትቆጠቡ በጥብቅ እናሳስባለን!

ማሳሰቢያ (Alert) ⚠️እስካሁን በነበሩት ቀናቶች ሁሉም የጤና ባለሞያ የንቅናቄው ባለቤት በመሆን እጅግ ብስለትና ጨዋነት በተሞላበት አካሔድ እንሆ የንቅናቄው አምስተኛ ቀን ላይ እንገኛለን።...
08/05/2025

ማሳሰቢያ (Alert) ⚠️

እስካሁን በነበሩት ቀናቶች ሁሉም የጤና ባለሞያ የንቅናቄው ባለቤት በመሆን እጅግ ብስለትና ጨዋነት በተሞላበት አካሔድ እንሆ የንቅናቄው አምስተኛ ቀን ላይ እንገኛለን።

የባለሞያው ችግር ገብቷቸው ከጎናችን በመሆን ድምፅ የሆኑ አያሌ (ብዙ) ከዘርፉ ውጭ ያሉ ኢትዮጵያዊያን ላደረጉት አብሮነት የከበረ ምስጋናችን በባለሞያው እና በንቅናቄው ስም እናቀርባለን።

ነገር ግን መንግስት ሊረዳው የሚገባው ነገር አንዳችም ትዕዛዝም ሆነ የመፍትሔ አቅጣጫ ከፓለቲከኞችም ሆነ አክቲቪስቶች ንቅነቄው የማይጠይቅ እና የማይቀበል መሆኑን ማረጋገጥ እንፈልጋለን።

የጤና ባለሞያው ከዚህ ሰዓት ጀምሮ ማንኛውንም ሀሳብ,መልዕክት እና ጥያቄወቹን ለንቅናቄው መሪወች ብቻ በመላክ ጥንቃቄ በተሞላበት መቀጠል እንዳለብን እናሳስባለን።

ንቅናቄው በራሱ መረጃዎችን ማድረስ የሚችበት የማህበሩ ሚዲያ ፕላትፎርም ያለው በመሆኑ በግላቹ ለግለሰቦች የምትልኩትን መልዕክት ንቅናቄው እውቅና የማይሰጠው መሆኑን ማሳሰብ እንፈልጋለን።

ይህ ሳይሆን ቀርቶ መንግስት ንቅናቄያችንን ፓለቲካዊ ይዘት ሰጥቶ ለማሸማቀቅ ሙከራ ሊያደርግ ይችላል።ነገር ግን የፈለገውን ስያሜ ቢሰጥ መሪውም ባለቤቱም የጤና ባለሞያው ስለሆነ ስራ ከማቆም ወደሗላ ሚመልሰን አካል እንደማይኖር ልናረጋግጥላቸሁ እንወዳለን።

ዛሬም ጤና ሚንስትርም ሆነ የሚመለከተው የመንግስት አካል የጠየቅናቸውን ጥያቄወች መፍትሔ መስጠት ላይ ጥኩረት ሰጥቶ እንዲሰራ ደጋግመን ማሳሰብ እንፈልጋለን!!

በመጨረሻ ማረጋገጥ የምንፈልገው ነገር ቢኖር 👇👇

📌ንቅናቄው የትኛውንም የፓለቲካ አመለካከት አይዎክልም!

📌ንቅናቄው የትኛውንም የፓለቲካ ፓርቲ አይወክልም !

📌ንቅናቄው ብሔር, ዘር, ቀለም, የለውም!

📌ንቅናቄ ለየትኛውም የፓለቲካ ፓርቲ ደብዳቤ ፅፎ ጥያቄ አላቀረበም !

📌ንቅናቄው ባለቤትነቱ የጤና ባለሞያው ብቻ ነው!

📌 ንቅናቄው የመሰረታዊ ፍላጎት ጥያቄ ነው!

📌በማሸማቀቅ, በማሰር, ስም በማጥፋት የማህበረሰብን ጤና መጠበቅ አይቻልም!

''አጀንዳችን ንቅናቄያችን''!

5 ቀናት ይቀሩናል!!

Now or Never!!

የኢትዮጵያ ጤና ባለሞያዎች ንቅናቄ (©️EHPM Board )

30/08/2017 ዓ.ም

08/05/2025

የጤና ባለሙያዎችን የሚያንገላቱ የፀጥታ አካላት ቢያሥቡበት መልካም ነው :: የጠየቁት የዳቦ ጥያቄ ነዉ!
ይሄ ጊዜ ያልፍና ነገ እንተዛዘባለን: ዛሬ ያንገላቱትን ባለሙያ ነገ ያገኙታል: ያኔ በማን እጅ ሊታከሙ ይሆን???? ቤተሰባቸዉን ሚስቶቻቸዉንና ልጆቻቸዉን ከአገር ዉጭ ሊያሳክሙ ነዉ ምክንያቱም ዛሬ የተንገላታና የታሰረ ባለሙያ ነገ እንዴትና በምን ሞራል ይሠራል
ቢታሠብበት ይሻላል !!!

07/05/2025

" የጤና ባለሙያ በመሆናችን ብቻ አንገታችንን እንድንደፋና ከሰዎች በታች የሆነ ኑሮ እንድንገፋ ተገደናል "

" በወቅታዊ የጤና ባለሙያዎች ጉዳይ ላይ ከኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማህበር  የተሰጠ  መግለጫ "   ጤና ባለሙያዎች እያነሷቸዉ ያሉ  ጥያቄዎች ተገቢ በመሆናቸዉ መንግስት አስቸኳይ መፍትሔ ሊ...
07/05/2025

" በወቅታዊ የጤና ባለሙያዎች ጉዳይ ላይ ከኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማህበር የተሰጠ መግለጫ "


ጤና ባለሙያዎች እያነሷቸዉ ያሉ ጥያቄዎች ተገቢ በመሆናቸዉ መንግስት አስቸኳይ መፍትሔ ሊሰጥ ይገባል።
የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማህበር በተለያዬ ጊዜ ጤና ባለሙያዎች የሚያነሷቸዉን ጥያቄዎች ህጋዊ አግባብን ተከትሎ ለሚመለከታቸዉ የመንግስት አካላት ማለትም ጤና ሚኒስቴርን ጨምሮ ለሃገሪቱ ከፍተኛ የመንግስት መስርያ ቤቶች ማቅረቡ ይታወቃል። ነገር ግን ጤና ባለሙያዎች የሚያነሷቸዉ ጥያቄዎች በወቅቱ እና በተገቢ ሁኔታ ባለመመለሳቸዉ ጤና ባለሙያዎች አሁንም በተለያዩ መንገዶች እየጠየቁ ይገኛሉ።
ማህበሩ ጤና ባለሙያዎች መብታቸዉን ለማስከበር የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ይደግፋል እዉቅናም ይሰጣል ነገር ግን ሃገርን እና ማህበረሰብን በማይጎዳ መልኩ መሆን አለበት ብሎ ያምናል።
መንግስት ጤና ባለሙያዎች የሚያነሷቸዉን ጥያቄዎች ችላ ከማለት ወጥቶ ጉደዩ በሃገር ላይ ችግር ከማስከተሉ በፊት ለሚነሱ ጥያቄዎች ተገቢዉን ቦታ እና ምላሽ እንዲሰጥ ማህበሩ በአፅኖት ይጠይቃል።

አጭር ምክር ለጤና ሚኒስትር የቀድሞ ባልደረቦቼ!(From former Deputy Director for Reproductive Health in FMOH)የጤና ባለሞያ እሮሮ (demotivated hea...
06/05/2025

አጭር ምክር ለጤና ሚኒስትር የቀድሞ ባልደረቦቼ!
(From former Deputy Director for Reproductive Health in FMOH)

የጤና ባለሞያ እሮሮ (demotivated health professionals) ባለበት ሀገር የጤና ግቦችን አሳካለሁ ብሎ ማሰብ ውሀ ቅዳ ውሀ መልስ አይነት ጨዋታ ነው።

ስለዚህ በዘመናት ውስጥ እየተጠራቀመ ሞልቶ ሊፈነዳ የደረሰውን የጤና ባለሞያዎች ጥያቄ በተለምዶው መንገድ ፖለቲካዊ በማድረግና በማስፈራራት እንዲሁም ማፈን የባሰ መዘዝ ይዞ ከጓሮ እንደሚመጣ ማወቅ ያስፈልጋል። አሁን ላይ አዕምሮው ማገናዘብ የሚችል ሰው ሁሉ እንደሚያስተውለው ጥያቄው ከቅንጦት አልፎ የህልውና ሆኗል። ምንም እንኳን አንዳንድ የፖለቲካ የደም ቁማርተኞች የጤና ባለሞያውን የመኖር ጥያቄ ጠልፈው ለፖለቲካቸው ንግድ ሊጠቀሙበት ሲሯሯጡ ቢታይም፣ መንግስት ግን እውነታውን አስተውሎ ቀድሞ መገኘት አለበት ብዬ አምናለሁ። እንደሚታወቀው በከረሙ በደሎች የሚነሳ የባለሞያ እና የህዝብ እሮሮ ለፖለቲካ ንግድ ይመቻል። መንግስት ግን ቀድሞ ለጥያቄዎቹና ለእሮሮው በቂ ትኩረት ከሰጠ፣ ነገሩ ለፖለቲካ ንግድነት ሳይውል መፍታት ይችላል ብዬ አምናለሁ። ብሩህ የህዝብ አስተዳዳሪ ወይም ደግሞ ተወዳጅ መንግስት ፖለታካውን በበላይ መምራት ያለበት መንገድም ይሄ ነው ብዬ አምናለሁ። ነገሩን ግን ለማፈን መሞከር ውስጥ ውስጡን ሞቶ እድሜውን ለማስረዘም የሚታገል መንግስት መገለጫ ነው። በመሆኑም ጤና ሚንስትርም ሆነ መንግስት እሮሮውን ሀገር በምትችለው መጠን ለመፍታት ያላቸውን ቁርጠኝነት ማሳየት ይኖርባችኋል። ከዚህ በፊትም በተለያየ መድረክ ሀሳቤን እንደገለፅኩት መንግስት ይሄን ችግር ለመፍታት ቁርጠኝነቱና እምነቱ ካለው ከባለሞያው ጋር መግባባት ይችላል።

ማንኛውም ችግር በሚፈታበት ሂደት ችግሩን "time bounded" በሆነ በአጭር ጊዜ፣ በመካከለኛ ጊዜ እንዲሁም በረጅም ጊዜ የችግር አፈታት እቅዶችን አስቀምጦ ወደተግባር መግባት ያስፈልጋል።

እንደሚታወቀው የኛንም ሀገር ጨምሮ የብዙ ታዳጊ ሀገራት የመንግስት ችግር የገንዘብ እጥረትና ለባለሞያው የሚገባውን ለመክፈል የኢኮኖሚው ውስንነት ነው። የእኛ ሀገር የጤና ፖሊሲ ደግሞ ደሀ ተኮር ስለሆነ የጤናው ዘርፍ በቂ የሆነ ገቢ (revenue) አያስገባም ወይንም ደግሞ ጀነሬት አያደርግም። ይልቁንም አብዛኞቹ የጤና ኘሮግራሞቻችን እራሱ ከውጪ መንግስታት ከሚመጡ ቸሮታ ላይ የተመሰረቱ ናቸው። ቸሮታው ሲቆም ህክምናዎቹን መስጠት እስከማይቻል ሊቆሙ የሚችሉ ማለት ነው።

ትልቁ የቤት ስራ ታዲያ ሀገር እንደዚህ አይነት ገቢ ሊያስገባ አይደለም በኪሳራ በሚደጎም ደሀ ተኮር የጤና ፖሊሲ ውስጥ እንዴት የጤና ባለሞያውን ጥያቄ ትመልስ የሚለው ነው።

ለዚህም ነው በግልፅ ሊመዘን በሚችል የአጭር ጊዜ፣ መካከለኛ እና እረጅም ጊዜ ሰሌዳ እቅድ አውጥቶ ባፋጣኝ ወደስራ መግባት ሚያስፈልገው። እኔ በጥራዝ ነጠቅነት ጥቆማ ለመስጠት ይህንን ልበል!

በአጭር ጊዜ እቅድ Focus on motivational benefits

1. Free medical care የመንግስት ጤና ተቋም የሚሰራ ማንኛውም የጤና ባለሞያ ከነ ቀዳማይ ቤተሰቦቹ ሲታመም ሁሉም የመንግስት ተቋም ውስጥ በነፃና በቅድሚያ ህክምና የሚያገኝበትን ወጥ መታወቂያ ማዘጋጀትና መስጠት

2. Tax exceptions የጤና ባለሞያዎችን ለማበረታታት መንግስት ተጨማሪ መክፈል ባይችል እንኳን በግብር ምላሽ መልክ ከደሞዝ የሚቆረጠውን መተው

3. Housing and transportation benefits ማንኛውም በመንግስት ተቋም የሚያገለግል የጤና ባለሞያ የሚካተትበት መንግስት እንደኮንዶሚኒየም ደጉሞ የሚሰራው የቤቶች ልማት መጀመርና በአነስተኛ ክፍያ ጤና ባለሞያዎች ሁሉም የሚያገኙበትን ስርዓት መዘርጋት (As part of SDG goal attainment, health professional motivation should be considered and SDG budget utilization justification could be submitted/negotiated by higher bodies)። ሌላው አማራጭ ደግሞ የጤና ባለሞያውን እንደመሀበር እያቧደኑ ቤት ሊሰራበት የሚችል መሬት መስጠት። (መሬት መንግስት ያለው አንድ ትልቅ ሀብት ነው። መንግስት ደሀ ነኝ መክፈል አልችልም ሲል በተለዎጭ (in kind) ግን ሀብታም እንደሆነ ቢያውቅ።)

በመካከለኛ ጊዜ እቅድ

1. Tax exemption to buy cars and other motor vehicles. የጤና ባለሞያዎች መኪናም ሆነ ሌላ ተሽከርካሪ ያለግብር እንዲያስገቡ መፍቀድ

2. ወታደር፣ መምህርና የጤና ባለሞያ የ10% የህዝብ አገልጋይ ቅናሽ (public service discount) በማንኛውም ሸቀጦች፣ ምግ ቤቶች እንዲሁም ግብይቶች ላይ እንዲያገኙ የሚያስገድግ ሀገራዊ ህግ ማውጣት

በረጅም ጊዜ እቅድ

1. Health sector revenue generation and health professionals motivation በረጅም ጊዜ እቅድ መካከለኛና ከፍተኛ ገቢ ያላቸው ሰዎች ሁሉም በገቢያቸው መጠን ለጤናው ዘርፍ የሚገባ ግብር እንዲከፍሉ ተደርጎ ተመጣጣኝ ክፍያ ለጤና ባለሞያዎች

2. Health sector burden tax and sin tax የጤና ዘርፋን በሂደት ጫና ውስጥ የሚከቱ ሸቀጦች ላይ የተለየ የጤና ግብር በመጣል ገቢው ለጤናው ሴክተር እንዲውል ማድረግ። ለምሳሌ አልኮሆል፣ ሲጃራ፣ ጫት፣ ኬሚካሎች፣ የታሸጉ ምግቦች፣ አርቴፊሻል ማጣፈጫ ያላቸውን ምግቦችና የመሳሰሉትን

ከላይ በጥራዝ ነጠቅ የጠቆምኳቸውን አይነት የለውጥ ውሳኔዎች በቁርጠኝነት ወስኖ ከባለሞያው ጋር እጅ እና ጓንት ሆኖ ከታቀደ ለውጥ ይመጣል ብዬ አስባለሁ። የጤና ባለሞያዎቻችንም ችግር ጠቃሽ ብቻ ሳይሆኑ የመፍትሄውም ሀሳብ አመንጪና አካል እንዲሆኑ ወጣት የባለሞያዎች ንቅናቄ መሪዎችን አቅርቦ በሀገር ባለቤትነት ስሜት አብረው እንዲሰሩ ማድረግ ያስፈልጋል።

ክብር እና ፍቅር ለኢትዮጵያ ህብረተሰብ አገልጋዮች እንዲሁም የጤና ባለሞያዎች እላለሁ

ዶ/ር አብርሃም ታሪኩ
May 6, 2025

04/05/2025

ጤና ባለሙያ የሆናችሁ እስኪ 🙌

17/04/2025

26 🫵
ሕይወት ስናድን ኖረናል! አሁን ግን የራሳችንንም ሕይወት ማዳን ይኖርብናል! ሰዓቱ እያለቀ ነው! 26 ቀናት ብቻ ቀርተዋል !ዝምታው አሁን ያብቃ!

We save lives! Now it's time to save ours too! The Clock is Ticking! 26 Days to Hold the System Accountable. The Silence Should End Now!

lubbuu baraaraa jiraanne! Amma garuu lubbuu ofii keenyaas baraaruu qabna!
Sa'aatiin lakkaawaa jira! Guyyoota 26 qofatu hafe! Amma booda hin callisnu!

ህይወት እናድሓና ፀኒሕና ኢና! ሕጂ ንዓርስና ነድሕነሉ ግዜ እዩ!
እቲ ሰዓት ይውዳእ ኣሎ! 26 መዓልቲ ጥራሕ ቀርየን! ሱቕታ ሕዚ ይኾናኖ!

shemppuwa ashiidi gam'ida,ha'i nu shemppuwa ashanaw bessees





Hamster እና የጤና ባለሙያየሰሞኑ የጤና ባለሙያዎች ጥያቄ ሲነሳ አንዳንድ የማህበረሱ ክፍል መደናገጥ ይታይባቸዋል። የዉሸትም የመሰላቸው አለ። ፡ጤና ባለሙያ የሀገሪቱ ከፍተኛ ተከፋይ፣  በ...
15/04/2025

Hamster እና የጤና ባለሙያ

የሰሞኑ የጤና ባለሙያዎች ጥያቄ ሲነሳ አንዳንድ የማህበረሱ ክፍል መደናገጥ ይታይባቸዋል። የዉሸትም የመሰላቸው አለ። ፡ጤና ባለሙያ የሀገሪቱ ከፍተኛ ተከፋይ፣ በውብ ቤት የሚኖር፣ መኪና ያለው እና ኑሮ ደልቶኣቸው የፈለጉትን እያደረጉ የሚኖሩ ነበር የሚመስላቸው። እውነታው ግን በተቃራኒ ነው። ከስራ ጫና አንፃር ዝቅተኛ ተከፋይ: የWHO የክፈያ እርከን እንኳ ያልደረሱ። በኢትዮጵያ የደሃ መስፈርት ከድህነት በታች ላይ ተመዳቢ አይደለም ቤት፣ መኪና በቀን 2 ጊዜ መብላት የማይችል፡ የቤት ኪራይ መክፈል የከበደው ፡ በእዳ ምክንያት አንገቱን ደፍቶ የሚኖር እና ቤተሰቦቹን እንኳ ለማይየት ያልታደለ ነው።

ሰሞኑን ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚዘዋወሩ የጤና ባለሞያ ጥያቄዎች መኖር ከበደን እንጂ ስራ አንሰራም አይደለም። እየራበን ነው እንጂ የቢራ መጠጫ አነሰን አይደለም። የቤት ኪራይ መክፈል አልቻልንም እንጂ ቤተመንግሥት ገንቡልን አይደለም።

24/7 ሳይሰለች ደከመኝ ሳይል የሚሰራ ሰራተኛ ራበኝ ሲል፣ መኖር ከበደኝ ሲል ፡ መታከም ከብዶት ሀኪሙ በገንዘብ እጥረት ሲሞት እንዴት ዝም ይባላል። እንዴት ፖለቲካ ይሆናል።

ቤተሰብ መመስረት ዘበት ነው። ተቸግረው ያሰተማሩትን ወላጆች ፡ አሳዳጊዎች፡ ጓደኞችን ማገዝ ማስደሰት ብርቅ ነው። መዝናናት፣ ከሚወዱት ጋር ጊዜ ማሳለፍ አይታሰብም። ይህ የጤና ባለሙያ ህይወት ነው።
ለስፔሻሊት 12K ለዶክተር 10K ሌሎች ከ9K በታች ይከፈላቸዋል። በቅርባችን ኬንያ የበግ ጠባቂዎች ደሞዝ ይበልጠናል።

ሀምሰተር ከJunior Nurse እስከ senior nurse
ከ GP እስከ specialist Dr. ሁሉም የጤና ባለሙያ ሀምሰተር ሲሰሩ ነበር። ይህ ምን ያክል የጤና ዘርፍ ሰራተኞች ህይወት እንደከበዳቸው ያሳያል። ምን ያክል ችግር ውስጥ እንዳሉ ይመሰክራል።

ጤናማ ያልሆነ ሀኪም ሊያክም አይችልም። እየተራበ Focus ሊያደርግ አይችልም። እዳ እያለበት ሊረጋጋ አይችልም።

የጤና ባለሙያተኞች ጥያቄያቸው የኔም ያንችም የሁሉም ዜጋ ጥያቄ መሆን አለበት።
ነገ ላይ ልጅህ ሚስትህ/ ባለሽ እናትና አባታችህ በነሱ እጅ ይታከማሉ። ይህ ጥያቄ ችላ ተብሎ ሊሆን ይችላል። ነብሰ ጡር ሚሰትህን ፣ ICU ተኝቶ የሚታከም ልጅህ ፣ ድንገተኛ የሚመጣ አባትህ ፣ ክትትል የምታደረገዋ እናትህ ህክመና ሲያጡ አትውቀሳቸው። ወደው ሳይሆን የጠፉት ምግብ ፈለጋ ሄደው ነው። አንትን ማገልገል ሳይፈልጉ ቀርተው ሳይሆን እዳቸውን ለመክፈል ስራ ፈልገው ሄደው ነው። ማህበረሰቡን ማከም ተሰላችተው ሳይሆን የታኪሲ አተው ነው የቀሩት። ተረዳቸው።

ለጤና ባለሙያተኞች ድምፅ እንሁናቸው።

ህይወት ስናድን ኖረናል አሁን የራሳችንን እናድን።

ዘላለም (አንስቴቲስት)

ሕይወት ስናድን ኖረናል! አሁን ግን የራሳችንንም ሕይወት ማዳን ይኖርብናል! ሰዓቱ እያለቀ ነው! 28 ቀናት ብቻ ቀርተዋል !ዝምታው አሁን ያብቃ!

We save lives! Now it's time to save ours too! The Clock is Ticking! 28 Days to Hold the System Accountable. The Silence Should End Now!

lubbuu baraaraa jiraanne! Amma garuu lubbuu ofii keenyaas baraaruu qabna!
Sa'aatiin lakkaawaa jira! Guyyoota 28 qofatu hafe! Amma booda hin callisnu!

ህይወት እናድሓና ፀኒሕና ኢና! ሕጂ ንዓርስና ነድሕነሉ ግዜ እዩ!
እቲ ሰዓት ይውዳእ ኣሎ! 28 መዓልቲ ጥራሕ ቀርየን! ሱቕታ ሕዚ ይኾናኖ!

shemppuwa ashiidi gam'ida,ha'i nu shemppuwa ashanaw bessees





ተመስገን ዳኜ እባላለሁ። ነርስ ነኝ ከ3 ዓመት ተኩል በላይ ሰርቻለሁ 3 ዓመት በሙሉ ያለምንም የትርፍ ሰዓት ክፍያ በነፃ በደመወዝ ብቻ ከታክስ በኋላ 4770 ብር እየተከፈለኝ ሰርቻለሁ። በአ...
09/04/2025

ተመስገን ዳኜ እባላለሁ። ነርስ ነኝ ከ3 ዓመት ተኩል በላይ ሰርቻለሁ 3 ዓመት በሙሉ ያለምንም የትርፍ ሰዓት ክፍያ በነፃ በደመወዝ ብቻ ከታክስ በኋላ 4770 ብር እየተከፈለኝ ሰርቻለሁ። በአጋጣሚ ወደ ቤተሰብ ከ2 ዓመት በኋላ ነው የምሄደው።

በዚህ አመት መስከረም ላይ ቤተሰብ ጠይቄ ስመለስ ድንገተኛ አደጋ ገጠመኝ :- በመኪና ጉዞ ለይ የታጠቁ ሀይሎች ጥይት ተኩሰው እኔ ተመታሁ። በፈጣሪ ቸርነት ብዙ ደም ቢፈሰኝም የተመታሁበት ቦታ አስፈሪ ቢሆንም እንደምንም ከ1 ሰዓት ጭንቅ ጉዞ በኋላ ሆስፒታል ደረስኩ።

ሆስፒታልም ወደ ሳንባዬ ብዙ አየርና ደም ገብቶ ስለነበር በቱቦ እንድወጣ ተደረገ። የግራ እጅ ደም ስሮችና ነርቮች ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው ተነገረኝ። ለዚህም ለኦፕሬሽን እንድዘጋጅ ተነገረኝ። በመሀል የምሰራበት ሆስፒታል የስራ ባልደረቦቼና ጓደኞቼ ጉዳዩን ሰምተው የማሳከሚያ ገንዘብ በማዋጣት ላኩልኝ። ቤተሰቦቼ ግን ጉዳዩን አያውቁም ነበር ምክንያቱም ሩቅ ነበሩ በዛ ላይ በድንጋጤ ሌላ ችግር የሚፈጠር መስሎ ስለተሰማኝም እንድሰሙ አልፈለኩም።

ለሚሰራልኝ የፕላስቲክ ሰርጀሪ እቃ ተገዝቶ እየተዘጋጀሁ ሳለሁ ጊዜው እረፍዷል ቢሰራ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል የሚል ውሳኔ ተወሰነ። ከዚያም ከ3 ቀን በኋላ የደም ስሮቼ ወደ ስራቸው የመመለስ ሁኔታ አሳዩ። እኔም ሰራተኞች አዋጥተው በላኩልኝ ገንዘብ በሆስፒታሉ ህክምናዬን ስከታተል ቆይቼ ከነ ነርቭ ጉዳቴ ወጣሁ። ግን ሞትን አመለጥኩት። የጤና ባለሞያዎች የጤና መድህን አለመኖሩና የሚከፈለው ገንዘብ ምን ድረስ ሊጠቅም እንደሚችል እኔ ማሳያ ነኝ...

ክብር ጤናቸውን አጥተው የሌሎችን ጤና ለሚመልሱ ባለሞያዎች!!!
ተመስገን ዳኘ

እኔ ምን አደረኩኝ እስካሁን ??1 እኔ ምን አደረኩ እስካሁን ??🔘እኔ profile ቀይሪያለሁ🔘እኔ social media ላይ campaign እያደረኩ ነው🔘እኔ ትግሉን ላለመጎተት ቃለ ገብቻለሁ...
07/04/2025

እኔ ምን አደረኩኝ እስካሁን ??

1 እኔ ምን አደረኩ እስካሁን ??
🔘እኔ profile ቀይሪያለሁ
🔘እኔ social media ላይ campaign እያደረኩ ነው
🔘እኔ ትግሉን ላለመጎተት ቃለ ገብቻለሁ
🔘እኔ አላስፈላጊ ንትሪክ ውስጥ ባለመግባት ትግሉን አግዛለሁ
🔘እኔ ንቁ ተሳትፎ አደርጋለሁ !
🔘እኔ ለእራሴ መብት እታገላለሁ !
🔘እኔ ምንም የሚቀየር ነገር የለም ብየ ሳይሆን መብቴን እንደማስከብር በእራሴ እተማመናለሁ !
🔘እኔ ሌሎች ዋጋ ከፍለው ለውጥ እንዲያመጡ አልጠብቅም

አንተስ ምን አደረክ ??
አንተስ ምን አደረክ ??

2 ትፈራለህ ??
🔘መብቴን ለመጠየቅ መቼም አልፈራም
🔘ብትታሰርስ ፦ አሁን የምኖረው ኑሮ እኮ ከአሉት በታች ከሞቱት በላይ እኮ ነው !
🔘ለቤተሰብህ አታሰብም
ሚታገሉት ቤተሰብ ስለሌላቸው ነው እንዴ ?

3 ሌላው ዝዎ ብሎ እያየ ለምን አንተ ትጋፈጣላህ ?
🔘ሠው ህይወቱን ሰጥቶ ሌላውን ነፃ ለማውጣት ጫካ ይገባ የለ እንዴ እኔ ለእራሴ መብት እንዴት መታገል ያቅተኛል !

4 ፖለቲከኛ አመፅ አነሳህ ብሎ ቢያንገላታህሰ ?
🔘እስካሁን ከተንገላታሁት እና ዝቅ ካለው ክብሬ የባሰ ምን ይመጣል

5 ፖለቲከኛ እና ካድሬ ለመከፋፈል ቢሞክር እና ጥያቄህ እንደባለፈው የሽንገላ መልስ ቢሆንስ ?
🔘ጥያቄየ እስኪመለስ አጀንዳየን አልቀይርም በትንሽ ድል ግቤን ሳልመታ ወደኋላ አልልም !

6 እሺ እንደሌሎቹ አማራጭ ምትምክረው ነገር ስለሌህ ወይስ ወደ ውጭ ለመውጣት ስለማትሞክር ነው የምትታገለው?
🔘የሚገባኝን ስለማውቅ ፣ እኔ ብሄድስ የእኔን ቤተሰብ ማን ሊያክምልኝ ፣ ዋጋ ለሚከፈሉት እና የሚገባቸውን የጠየቁ ጓደኞቸ ብሶት እና ስቅይ ስለምረዳ እና ስለ ሚገባቸውም !!

7 ለምን ተፍ ተፍ ብለህ Or አሸቃብጠህ የራስህ ቦታ አታመቻችም ??
🔘የሚታገሉት ፋራ ሁነው ወይም ማሽቃበጥ ስለ ማይችሉ ሳይሆን ህሊና ስላላቸው እና ሚገባቸውን ስለሚያውቁ፣ ለሙያው እና ለራሳቸው ክብር ስላላቸው እንዲሁም ስለ ወገናቸው እና ቀጣይ ትውልድ ስለሚያሳስባቸው አብሪያቸው እታገላለሁ !

8 እስከ መቼ ነው የምትታገለው የሚመለከተው አካል ጀሮ ባይሰጥህስ ??
🔘እንዲህ አይነት ስር ነቀል ለውጥ በአንድ ጀምበር እንደማይመጣ ስለማወቅ ሙሉ ጥያቄየ እስኪ መለስ ድረስ አጀንዳየን አልቀይርም !

9 ትሠላቻለህ ፣ ምን ላይ ደረሱ ትላለህ ፣ ማይረቡ ሰዎች እስካሁን ድረስ ምን ጠብ ያለ ነገር አላመጡም እያልክ ግሩፑን ተጠያቂ ታደርጋለህ ?
🔘የእኔ አለመታገል እና የእኔ ደካማነት እንደሆነ አምኜ እራሴን ወቅሽ ሁሌም ባርያ ለመሆን እዘጋጃለሁ !

10 አሁንም egoህ ያስቸግርሃል
🔘Egoማ ክብሬን አሳጣኝ ፣ በጋራ ሆኜ ሚገባኝን እንዳልጠይቅ መሳቂያ እና መሳለቂያ አደረገኝ ምናልባት መብቴን ካስመለስኩ ስለ ego እናወራለን

11 ለምንድን ነው እስካሁን ጥያቄያቸው መፍትሄ ያላገኘው ብለህ ታስባለህ?
🔘Egoየ ጠላቴ ነበር ፣ የእኔ ጥቅም አይነካም ብየ አስቤ ነበር ፧ ፊት ለፊት ሳልጋፈጥ smart ለመሆን እየሞከርኩኝ ሌሎች የእኔን መብት እንዲያስከብሩልኝ ስጠበቅ ነበር !!

12 በመጨረሻም ለጓደኞችህ ምን ትጠይቃቸውለህ ?

🔘አንተ ምን እያረክ ነው እስካሁን ?
🔘አሁንም እነ እገሌን እየጠበቅ ነው ?
🔘አሁንም መናቅ እና ባሪያ መሆን አልሠለቸህም ?
🔘አሁንም ምን ላይ ደረሱ አይነት ፌዝ ውስጥ ነህ
🔘ከዚህ በላይ ምን እስክትሆን ነው ምትጠብቀው?
🔘ምን እንዳታጣ ነው አሁንም ምትፈራው ወደኋላ ምትለው ምታፌዘው ??

ለፍቶ አዳሪው:ሙያ አበዳሪው: ገንዘብ ተበዳሪው የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያ================ሁሉም እንደሚረዳው የሰው ልጂ በምድር ላይ ከተፈጠረ በኋላ የማይደራደርበት የመጨረሻው ቀይ መስመ...
07/04/2025

ለፍቶ አዳሪው:ሙያ አበዳሪው: ገንዘብ ተበዳሪው የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያ
================
ሁሉም እንደሚረዳው የሰው ልጂ በምድር ላይ ከተፈጠረ በኋላ የማይደራደርበት የመጨረሻው ቀይ መስመር በሂወት የመኖር ጉዳይ ነው! ውድ ሂወቱን ለመንጠቅ ፈታኝ ነገር ሲገጥመው ወይ ወደ ፈጣሪው ይማጸናል አልያም ወደ ህክምና ቦታ ይሄዳል። ህክምና ደግሞ ከፈጣሪ ቀጥሎ የሰውን ልጂ ውድ ሂወት እንድትቀጥል እና ከህመሟ እንድትፈወስ ማድረግ የሚችለውን ሁሉ አድርጎ ወደ ቀጣይ የሂወት ምእራፍ ማሸጋገር እና አድስ ተስፋ ማለምለም ነው።

ይህ ሲባል በህክምና አለም ውስጥ አንዱ ሙያ ከአንዱ የማይበልጥ / የማያንስ ሆኖ የተሰራ እና በሰንሰለት የተሳሰረ በጋራ ሂወትን የመታደግ ጉዳይ ነው[Professional team work].

ሁሉም እንደሚረዳው ህክምና በትምህርቱ ብዙ ደክሞና የተሻለ ውጤት ያስመዘገበ ተማሪ የሚቀላቀልበት ተቋም ሲሆን ከገባ በኋላም መጠነ ሰፊ ድካምን አስተናግዶ ብዙ ግዚያትን አባክኖ የሚወጣበት ዘርፍ ነው::

ታዲያ ይሄን ሁሉ ውጣ ውረድ አሳልፎ ከተመረቀ እና ወደስራ ከገባ በኋላ እንደማንኛውም የሰው ልጂ ፍጡር ሂወት መስርቶ ለመኖር ይፈልጋል: ነገር ግን እንዳለመታደል ሆኖ ሃገራችን ኢትዮጵያ ከአፍሪካም ሆነ ከአለም ሃገራት ለጤና ባለሙያዎች ዝቅተኛ ደመወዝ ከፋይ ሃገር ነች! አሁን ላይ ደግሞ ይባስ ብሎ ለህክምና ተቋማት ዝቅተኛ ግብአት አቅራቢ ሃገርም ሆናለች!

ይህ የሆነው ግን የኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች አስፈላጊውን የህክምና ቁሳቁስ ቢቀርብላቸው: በሙያቸው የተመሰከረላቸውና ሙያ ማበደር የሚችሉ ባለሙያዎች ያሏት አገር ነበረች: ዳሩ ግን እኛ ሃገር በሚሰራው አስነዋሪ ቢሮክራሲ ብዙዎች ሃገር ጥለው ተሰደዋለ: ሂወታቸውን ተነጥቀዋል: የፓለቲካ መቆመሪያ ሆነዋል አልያም ስራ እየለቀቁ ይገኛሉ::

እና የጤና ባለሙያው እስከመቸ ድረስ የጽድቅ ስራ ብቻ እየሰራ ይኖራል? እስከመቼስ ''የጤና ባለሙያ ደመወዙ ታማሚን በማዳን እርካታ ማግኘት ነው'' ይባላል?? እርካታ ብቻውን እንጀራ/ዳቦ ይሆናል?? እንደሌላው ሰው ትዳር መመስረት አያምረውም? ልጂ ወልዶ ማሳደግና ማስተማር አያምረውም? ቢታመም መታከም የለበትም? ......

የሰው ልጂ በሂወቱ ብዙ ፍላጎት ቢኖረውም ካለው አቅም አንጻር ብዙዎችን ገድቦ ይኖራል: አሁን ግን ጥያቄው ''እርቦናል'' የሚል መፈክር ላይ ደርሷል! ከዚህ በላይ ህመም ምን አለ??

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when MediLab posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

  • Want your practice to be the top-listed Clinic?

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram