29/10/2025
❤
በክልላችን የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዮት መረጃ መሰረት ባለ [ ⭐⭐⭐⭐] ከሆኑት በክልሉ ካሉ ከሁሉም የግልና የመንግሥት የሕክምና ተቋማት መካከል ከሁለት የመንግሥት ሆስፒታሎች በመቀጠል ቀጣዩን ደረጃ ይዞ አጠናቋል። በዚህም ተቋማችን ለሦስት አካላት ተጨማሪ ምስጋናውን ያቀርባል።
1ኛ/ ኃላፊ ፣ ቅኑና ታታሪው ባለሙያ ምስጋናችን ይድረስህ።
2ኛ/ የአብክመ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለእኛ ብቻ ሳይሆን የሕክምና ተቋማት በሙሉ በተለይ እጅግ አስፈላጊ በሆነው አገልግሎት ላይ አተኩራችሁ ፣ የማሕበረሰቡን ተጠቃሚነት ማዕከል አድርጋችሁ ለምትደክሙት ድካም ተቋማችን ከፍ ያለ ምስጋና ያቀርብላችኋል።
3ኛ/ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ፣ ብዙ እጥረቶችንና ውጣውረዶችን በመቋቋም ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ማሳያ የሆነውን ደረጃ በዚህ ልክ ያሳካችሁ በወረዳ ያላችሁ የመንግሥት ሆስፒታሎች ለእናንተ ክብር ይገባችኋል ፤ በምታገለግሉት ወገናችን ስም እናመሰግናቸዋለን።
/ #ባሕርዳር።