17/09/2021
ምች የሚባል በሽታ ግን ምንድነው ?
( ምች በፀሐይ ይመጣል ወይስ አይመጣም?)
🔘 ምች የሚባለው በሽታ በእንግሊዘኛው herpes labialis የሚባለው ሲሆን ዋናው የበሽታው ምልክት ደሞ ሄድ መጣ የሚሉ ትናንሽ ዉሃ የቋጠሩ በከንፈር ዙሪያ የሚወጡ ቁስሎች ናቸዉ።
የምች መንስኤው ምንድነው?
የበሽታው ዋናው መንስኤው herpes simplex የሚባለው ቫይረስ ሲሆን በመሳሳም ወይም በ ሌሎች አካላዊ ግንኙነቶች አማካኝንት ከአንድ ሰዉ ወደ ሌላዉ ሰዉ በቀላሉ የሚተላለፍ ነው ::
ምልክቶቹ
- የመጠቅጠቅና የማሳከክ ስሜት
- ዉሃ የቋጠሩ ቁስሎች
- ትኩሳት
-የራስ ምታት
- የጡንቻ ላይ ህመም
-የአንገት ላይ ንፍፊትቶች እብጠት
-ለምች የሚያጋልጡ ነገሮች ምንድናቸው?
1. ለፀሃይ ብርሃን መጋለጥ
ፀሐይ ብርሃን ለብቻው ምች አያመጣም።
ነገር ግን ምች የሚያመጣው ቫይረስ (herpes simplex 1) ቀድሞ ይዞን እራሱ ነርቭ ህዋሶች ዉስጥ ይደብቃል ።
የፀሐይ ብርሃን ዉስጥ ባለው ultraviolet የሚባለው ጨረር ደሞ ሊነሳሳው (re activate ሊያረገው) እና ከተደበቀበት የነርቭ ስር ዉስጥ በ መውጣት ድጋሚ ወደ ቆዳ አካባቢ በመሄድ ሄድ መለስ የሚል ቁስል ሊያመጣ ይችላልይችላል
2. ቅባት ያለዉ ምግብ መመገብ
3. ጭንቀት
4. ኤች አይ ቪ ኤድስ
5. የካንሰር ህክምና
6. የወር አበባ ዑደት ጊዜ የሆርሞን መለዋወጥ
የጤና ባለሙያ ማማከር ያለብን መቼ ነው ?
- የበሽታ መከላከል ብቃት መቀነስ/የተዳከመ ከሆነ
- ቁስሉ በሁለት ሳምንት ጊዜ ዉስጥ ካልዳነ
- የህመሙ ምልክቶች ከፍተኛ ከሆኑ
- ህመሙ በተደጋጋሚ ከተከሰተ
-በአይን የመቆጥቆጥ ስሜት ሲሰማ
ሕክምናውስ ምንድን ነው?
-ጸረ- ቫይረስ መድሃኒት እና የህመም ማስታገሻ መድሐኒት መዉሰድ
- በቫይታሚንሲ የበለጸጉ እንደ ሎሚ፣ብርቱካን እና ፓፓያ ያሉ ምግቦችን
-በቀዝቃዛ ዉሃ በተነከረ ጨረቅ ወይም በበረዶ ቁራጭ በቀን ዉስጥ ለተወሰኑ ጊዜያት ከ5-10 ደቂቃ በቦታዉ ላይ መያዝ
- የአእምሮ ዉጥረትን/ ጭንቀትን መቅነስ
- ዳማከሴ (Ocimum Lamiifolium) የተባለዉ ተክል ቅጠል በማሸት ቁስሉ ላይ ማድረግ/መቀባት
( በነገራችን ላይ ዳማከሴ በተወሰነ ደረጃ ቢሆንም ቫይረስን የመቆጣጠር እና የማጥፋት ባህሪ እንዳለው ብዙ ጥናቶች ጠቁመዋል ።)
-ዉሃ የቋጠረ ቁስል ባለበት ወቅት የቆዳ ለቆዳ ንክኪ እንዳይኖር መከላከል፤
- ቫይረሱ በከፍተኛ ሁኔታ የሚዛመተዉ በሚያዥበት/ዉሃ በሚቋጥርበት ጊዜ ስለሆነ ሌላዉን የሰዉነት ክፍልዎን እንዳይነኩ መጠንቀቅ :- በተለይ አይንንና የብልት አካብቢ ለቫይረሱ በጣም ተጋላጭ ስለሆኑ ላለመንካት መጠንቀቅ፤
- የመገልገያ ዕቃዎችን በጋራ ያለመጠቀም፡- እንደ ፎጣ፣ መመገቢያ ዕቃዎችንና የመሳሰሉትን
-የእጅን ንፅህና መጠበቅ፡- ሌላ ሰዉ ከመንካት በፊት እጅዎን በደንብ ይታጠቡ ።