Andro Dental Clinic

Andro Dental Clinic A dental clinic giving service at Bonga town by a senior dental surgeon and other specialists

እንኳን ለ2017 ዓ.ም አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ  🌼🌼🌼 አመቱ የሰላም፣ የጤና፣ የመተሳሰብ ፣ ሰርተን የምንለወጥበት ነግደን የምናተርፍበት ❤️❤️ የፈገግታ ዘመን እንዲሆን እንመኛለን ...
10/09/2024

እንኳን ለ2017 ዓ.ም አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ 🌼🌼🌼 አመቱ የሰላም፣ የጤና፣ የመተሳሰብ ፣ ሰርተን የምንለወጥበት ነግደን የምናተርፍበት ❤️❤️ የፈገግታ ዘመን እንዲሆን እንመኛለን 🥰🥰 መልካም በዓል 🏵️🏵️

በአዳዲስ ማሽኖችና ብቁ ባለሞያዎች የተደራጀው አንድሮ የጥርስ ክሊኒክ በአገልግሎት ጥራትና ቅልጥፍና ''ኑ ፈገግ ብለው ይመለሱ'' ይላል::  ዶ/ር ቸርነት እና ሌሎች ባለሞያዎችን ያካተተው ክ...
17/07/2024

በአዳዲስ ማሽኖችና ብቁ ባለሞያዎች የተደራጀው አንድሮ የጥርስ ክሊኒክ በአገልግሎት ጥራትና ቅልጥፍና ''ኑ ፈገግ ብለው ይመለሱ'' ይላል:: ዶ/ር ቸርነት እና ሌሎች ባለሞያዎችን ያካተተው ክሊኒካችን ዘመኑ የደረሰበትን መሳሪያ በመጠቀም ሙሉ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።
1. የተቦረቦረ ጥርስ መሙላት
2. ጥርስ ማጠብ
3. የጥርስ ነርቭ ህክምና
4. ታክሞ ማይድን ጥርስ መንቀል
5. ምቹና ውብ የሰው ሰራሽ ጥርሶችን መትከል
6. የብሬስ ህክምና
7.በአደጋ ጊዜ የተነቃነቀ ጥርስ ማጥበቅና ማከም
8. የአፍ ውስጥ ቀዶ ህክምና
9. የህፃናት ጥርስ አበቃቀል ክትትልና ህክምና ከተጨማሪ የማማከር አገልግሎት ጋር እየሰጠ ይገኛል።
አድራሻችን :- ቦንጋ ከተማ ገቢዎች ፅ/ቤት ወረድ ብሎ ሆስፒታል መግቢያ ሳይደርስ ቡስጣ ምንጭ አጠገብ ያገኙታል።
https://t.me/androdentalclinic

ጥርስ ከተነቀለ በኋላ የሚፈጠር ህመም | Alveolar Ostitisጥርስ በተለያዩ ምክንያቶች ሊነቀል ይችላል ከተነቀላ በኋላ ግን የከፋ ህመም በብዙ ምክንያት ሊከሰት ይችላል ይህም የሚፈጠረው...
08/05/2024

ጥርስ ከተነቀለ በኋላ የሚፈጠር ህመም | Alveolar Ostitis

ጥርስ በተለያዩ ምክንያቶች ሊነቀል ይችላል ከተነቀላ በኋላ ግን የከፋ ህመም በብዙ ምክንያት ሊከሰት ይችላል ይህም የሚፈጠረው ሐኪምዎ እንዲተገብሩ ያዘዝዎትን ትዛዝ ሳያከብሩ ሲቀሩ፣ ሴቶች በወር አበባ መምጫ ሰዓት ጥርስ የሚነቀሉ ከሆነ፣ የወሊድ መቆጣጠርያ መድኃኒት እየወሰዱ የሚነቀሉ አሆነ፣ ጥርስ ከተነቀለ በኋለ በአንድ ሳምንት ውስጥ ትምባሆ የሚያጨሱ ከሆነ የተባለው ህመም ሊከሰት ይችላል።

የህመሙ ዓይነት የሚጠዘጥዝ ህመም ሲሆን የተነቀለበት ቦታ ቁስሉ ወደ ግራጫ መልክ የመቀየር፣ የአፍ ጠረን የማምጣት እና ብሎም እብጠትም ጭምር ሊኖረው ይችላል።

ነገር ግን ጥርስ ከተነቀለ በኋላ ሊተገበሩ የሚገቡ የጥንቃቄ ዓይነቶች አሉ እነሱም

1. ጥርስ ከተነቀለበት ደቂቃ አንስቶ ቢያን ለ 30 ደቂቃ ያህል ሐኪምዎ ያስነከሰዎትን ጥጥ በተነቀለበት ቦታ ነክሰው ማቆየት

2. ጥርስ ከተነቀለበት ደቂቃ አንስቶ ለተከታታይ 24 ሰዓታት ትኩስ ነገር መብላትም ሆነ መጠጣት አይመከርም መመገብ ካለብዎ በረድ ወይም ለብ ያለ ነገር መሆን አለበት

3. ጥርስ ከተነቀለበት ደቂቃ አንስቶ ለተከታታይ 24 ሰዓታት ደምም ይሁን ምራቅ መዋጥ እንጂ መትፋት በፍፁም የተከለከለ ነው

4. ጥርስ ከተነቀለበት ደቂቃ አንስቶ ለተከታታይ 24 ሰዓታት የትኛውም ዓይነት ፈሳሽ ነገር ሲጠጡ መምጠጫ(Straw) መጠቀም አይመከርም

5. ቁስሉ እስኪድን ድረስ ጥርስ የተነቀለበትን ቦታ በእጅ፣ በምላስ እና በተለያዩ ቁሳቁሶች መነካካት አይመከርም

6. ምግብ ከበሉ በኋላ የበሉት ምግብ በቁስሉ በመከማቸት ለኢንፌክሽን የማጋለጥ ዕድሉ የሰፋ ስለሆነ እንደተመገቡ ጨው በውኃ በመቀላቀል ለብ አድርገው ተጉሞጥምጦ መትፋት

7. ቁስሉ እንዲድን አጋዥ ይሆናሉ ተብሎ በሐኪም የታዘዙ መድኃኒቶች ካሉ በትዕዛዙ መሰረት መውሰድ

8. ጥርስ ከተነቀለበት ደቂቃ አንስቶ ቢያንስ ለተከታታይ 10 ቀናት ትምባሆ ማጨስ አይመከርም።

9. ከላይ የተጠቀሱትን ትዕዛዛት ሁሉ ተግብረው ነገር ግን ህመም እየበረታ ከሔደ እና እብጠት ካመጣ ፈጥነዉ ሐኪምዎትን ያማክሩ።

እነዚህን ትዕዛዛት ከተገበሩ ሊመጣ የሚችለውን ህመም መከላከል ይችላሉ።

የሙያዬን ድጋፍ እና የማማከር አገልግሎት ካስፈለገዎ በ +251913308628 ወይም የ ቴሌግራም ማስፈንጠሪያዬን https://t.me/androdentalclinic ተጠቅመው ያለዎትን ጥያቄ ማድረስ ይችላሉ።

መልዕክቱ ጠቃሚ ሆኖ ካገኙት ለወዳጅ ዘመድዎ ያጋሩት።

በዶ/ር ቸርነት አለማየሁ ፡ senior Dental Surgeon

እንኳን አደረሰን 💚💛❤️  እንኳን ለከተራ እና ለብርሃነ ጥምቀቱ በሠላም አደረሰዎ!በዓሉ የደስታ፣ የፍቅርና የአብሮነት እንዲሆንልዎ ከልብ እንመኛለን!መልካም በዓል!
19/01/2024

እንኳን አደረሰን 💚💛❤️

እንኳን ለከተራ እና ለብርሃነ ጥምቀቱ በሠላም አደረሰዎ!
በዓሉ የደስታ፣ የፍቅርና የአብሮነት እንዲሆንልዎ ከልብ እንመኛለን!
መልካም በዓል!

27/09/2023

Address

Bonga

Telephone

+251913308628

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Andro Dental Clinic posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share