30/03/2025
ሾተላይ (Rh-isoimmunization) ምንድነዉ?
❣️ሾተላይ የሚባለው በሽታ ሊከሰት የሚችለዉ በዕርግዝና ወቅት የባልና የሚሰት የደም አይነት ተለያይቶ ባል Rh positive ሲሆን ሚሰት Rh negative ስትሆንና የተፀነሰዉም ልጅ Rh positive ሲሆን ነዉ፡፡
❣️ከእርግዝና ዉጪ ሲሆን ሚሰት Rh negative ሆና Rh positive ደም ወደ እናቲቱ ደም ከገባ ወይም ከወሰደች ነው።
❣️ከሁለተኛ ጀምሮ የሚወለዱ ህፃናትን የሚያጠቃ በሽታ ሲሆን ይህም በእናትና በፅንሱ መሀከል የደም አይነት አለመጣጣም(Rh incompatability) ምክንያት የሚከሰት ነው ማለት ነዉ።
❣️ስለዚህ ሾተላይ እንዲከሰት መሟላት ያለባቸዉ ነገሮች
❣️ሚስት Rh negative መሆን ይኖርባታል እና ፅንሱ Rh positive መሆን ይኖርበታል
ባል Rh negative ከሆነ ሾተላይ አይከሰትም
ሾተላይ ለምን ይከሰታል?
የሰው ልጅ ከወላጆቹ ዘረመል ተነስቶ ከ4 የደም አይነቶች ውስጥ አንዱን ሊይዝ ይችላል። እነኝህም
❣️A------B------AB---ወይም----O ናቸዉ
በሰውነት ውስጥ የሚገኙ ቀይ የደም ህዋሶች(RBCs) የላይኛው ሽፋናቸው ላይ Rh የተባለ ፕሮቲን (protein) ካላቸው ሴቲቱ Rh positive ናት ማለት ሲሆን እነኚህ ፕሮቲኖች ከሌሉ ደግሞ Rh negative ናት ማለት ነው።
❣️አንድ እናት Rh negative ሆና ከRh positive ባል አርግዛ Rh positive ፅንስ ስትጸንስ ሰዉነቷ የማያቀዉን Rh ለተባለ ፕሮቲን (protein) እየተጋለጠች ነዉ ማለት ነዉ፡፡
❣️በዚ ሰዓት የሴቲቱ ሰዉነት የማያቀዉን በዓድ ነገር ለመመከት እነሱን የሚያጠፋ ንጥረ ነገሮች (Antibodies) ማምረት ይጀምራል፡፡
➡️ስለዚህ አንዲት ሴት ሾተላይ የሚባለው ችግር ሊከሰትባት የሚችለው እሷ Rh negative ሆና በተለያዩ አጋጣሚዎች Rh positive የሆነ ደም ወደ ሰውነቷ ሲገባ ሰውነቷ እነኚህን Rh positive የደም አይነቶች የሚያጠፉ ንጥረ ነገሮች (Antibodies) ሲያመነጭ (ሲያመርት) ነው። እነኚህም እስከ እድሜልክ በሰውነቷ ይቆያሉ።
እነኚህ የተመረቱት ተከላካይ ንጥረ ነገሮች(Antibodies) የመጀመሪያው ልጅ ላይ ምንም ተፅዓኖ ሳይኖራቸው ልጁ በሰላም ሊወለድ ይችላል ነገር ግን የሁለተኛው ፅንስ የደም አይነቱ Rh positive ከሆነ ወደ ፅንሱ በማለፍ የፅንሱን Rh positive የቀይ የደም ህዋሶች ያጠቃሉ ማለት ነው፤ ይህም ፅንሱን ለተለያየ አደጋዎች ሊያጋልጠው ይችላል።
ይህም ችግር ፅንሱ ላይ የተለያዩ ጉዳቶችን ሊያመጣ ይችላል፡-
➡️የፅንሱ የደም ማነስ
➡️በፅንሱ የተለያዩ የአካል ክፍሎች ውሀ መቋጠር
➡️በተደጋጋሚ የፅንስ መውረድ
➡️ፅንሱ በማህፀን ውስጥ እንዳለ ጊዜው ሳይደርስ ህይወቱ ማለፍ
➡️ህፃኑ ከተወለደ በውሃላ ቆዳው ቢጫ መሆን እና የጨረር ህክምና ማስፈለግ
➡️በከፍተኛ ደም ማነስ ምክንያት ደም ለመውሰድ መጋለጥ
ሾተላይ እንዴት ይታከማል?
❣️ከመታከም በላይ ግን መከላከል ትልቅ ዋጋ አለዉ!!!
Rh negative የሆነች እናት ባለቤቷ Rh positive ከሆነና ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩት ነገሮች ከገጠሟት
❣️ውርጃ ካጋጠማት
❣️ከእንግዴ ልጅ ላይ የሚነሳ እጢ (Gestation trophoblastic disease) ካጋጠማት
❣️በእርግዝና ወቅት አደጋ ከደረሰባት፤
❣️ከማህፀን ውጭ እርግዝና ካጋጠማት
❣️በክትትል ወቅት ከእንግዴ ልጅ ወይም ከእሽርት ዉሃ በመሳሪያ ናሙና ከተወሰደ
➡️Anti D ኢሚውኖግሎቡሊን (immunoglobulin) መዉሰድ አለባት፡፡
❣️Anti D የተባለ ኢሚውኖግሎቡሊን (immunoglobulin) መድሀኒት በመውሰድ ሾተላይን መከላከል ይቻላል!!!
በእርግዝና ጊዜ Anti D የተባለውን መድሃኒትን በ 7 ወር(28 ሳምንት) ላይ እና ህፃኑ ከተወለደ ቦሃላ የደም አይነቱ ተሰርቶ Rh positive ከሆነ ቢቻል እስከ 72 ሰዓት ውስጥ በመስጠት የሾተላይ በሽታን መከላከል ይቻላል።
➡️ከወለደች ቦሃላ የልጁን የደም አይነት ማሰራት የሚያስፈልገዉ ምናልባት የልጁ የደም አይነት Rh negative ሊሆን ስለሚችል ነዉ፡፡ ❣️በዚ ጊዜ እናትየዉ Anti D ኢሚውኖግሎቡሊን (immunoglobulin) አያስፈልጋትም ማለት ነዉ፡፡
➡️Rh negative የሆነች እናት(ባል Rh positive) የእርግዝና ክትትሏ ከሌሎች እናቶች ለየት ያለ እና የሚሰጣትም ቀጠሮ በዛ ያለ ይሆናል።
ይህም በልጇ ላይ ሊከሰቱ የሚችሉትን የሰውነት ውሀ መቋጠር(መጠራቀም) እና የፅንሱ ደም ማነስ ካለ ቀድሞ በማወቅ ህክምናውን በቶሎ ዘመኑ በደረሰበት ቴክኖሎጂ እዛው ማህፀን ውስጥ እንዳለ ደም በመለገስ እና ወቶ ለመኖር ብቁ በሆነበት ጊዜ ቀድሞ እንዲወለድ በማድረግ ተጨማሪ የሆኑ የህክምና እርዳታዎች እንዲደረግለት ማድረግ ይቻላል።
በክትትል ወቅት ንጥረ ነገሮች (Antibodies) ስለመፈጠራቸዉ የሚለይ ምርመራ(indirect coomp’s test) መሰራት አለበት፡፡
❣️መች መሰራት አለበት:- First trimester እና የእርግዝናዉ ጊዜ ከተገባደደ ቦሃላ፡፡
❤️ይህንነና የመሳሰሉት አገልግሎቶች ለማግኘት እና ቀጣይ አቅጣጫዎች ለማስያዝ እናት መካከለኛ ክሊኒክን ይጎብኙ።