28/09/2025
ጡት ማጥባት ///Breast feeding
:::::::::::::::::::::::::::
አንድ ህፃን አንደተወለደ በ አንድ ስሃት ውስጥ ጡት መጥባት አለበት ይላል የ አለም ጤና ድርጅት(WHO). በ 24 ሰሀት ወስጥ መፀዳዳት አለበት ይለናል፡፡ ነገር ገን ይህ በተለያያ አገጣሚ ላይሆን የሚችልበት አጋጣሚ ይኖራል፡፡
>>>>
ብዙ ጊዜ ግን ወላጆች የሚገጥማቼው ነገር ህፃኑ ካካ ሳይል ብዙ ቀን ይቆያል፡ ይሉናል፡ ፡በዚህም የተነሳ ጭንቀት ውስጥ የሚገቡበት ነገር ይሰተዋላል፡፡ምክንያቱ ግን በዋናነት የጡት ማጥባት ችግር ነው፡ እዴት ቢሉ ብዙዎች እናቶች በቀን ስንት ጌዜ እና በምን ሁኔታ ማጥባት እንደለባቼው አይረዱም:ሁሉንም በተለምዶና ወደ በባህል ማያያዝ ይስተዋላል፡፡
ስለዚህ ጡት ስታጠቡ እነዚህን ተከተሉ:-
# # # # # # # # # # # # # # # # # # #
#1 ጡትን በየተራ ማጥባት
#2 ህፃኑ መጀመሪያ አንድን ጡት ሲጠባው የሚያገኜው በብዛት ውሃ መሆኑን ማወቅ፡ተፈጥሮ ለህፃኑ ውሃ እንዳይጠማው መጀመሪያ ውሃ እዬሰጠች መሆኑን መረዳት፡ከዛ በመቀጠል ጠቃሚ ንጥረ ነገር ማለትም የበለጠ ፕሮቲን ዬያዘው ጡት ይወጣል ማለት ነው፡ ስለዚህ ጡቴ አኩርሷል ስንል የ ያዘው መጀመሪያ ከለይ ውሃ የሚበዛበትና እየቆዬ ከስር ፕሮቲኑ ይወጣል ማለት ነው፡፡
ለዚህም ነው አንዱን ጡት ሳይጨርስ ሌላኛውን ጡት መስጠት የለብንም ፡ የምንለው፡፡ምክንያቱም ከጡቱ የመጀመሪያ ከላይ ያለውን ለህፃኑ ከሰጠነው ህፃኑ በውሃ ብቻ ይሞላውና ሽንትብቻ ይሼናል ማለት ነው፡፡ሁልጊዜ ይህ ከተደጋገመ ህፃኑ ካካ አይልም ማለት ነው ምክንያቱም ውሃ እንጅ ፕሮቲን እያገኜ ስላልሆነ፡፡
#3 በትንሹ ማንቀሳቀስ ወይም ማፍታታት እግርን እጥፍ ዘርጋ ማድረግ በጀርባ አስተኝቶ፡፡
#4 ጥዋት ከጠቡ በኋላ ለ 15 ደቂቃ ፀሀይ ማሞቅ
#5 ከ 3 ወር በኋላ በጥንቃቄ በሆድ ማስተኛት
በቀን ከ 8 እስከ 12 ጊዜ ማጥባት እንዳለብዎ ይወቁ፡፡
ለበለጠ በ 0903662166 ወይም
በ0953232165
ቢደውል በ አካልም መጥተን አልያም በስልክ እናማክረወታለን፡፡