ምቾት የቤት ለቤት ህክምና አገልግሎት Michot Home Based Health Care Service

  • Home
  • Ethiopia
  • Debra Markos
  • ምቾት የቤት ለቤት ህክምና አገልግሎት Michot Home Based Health Care Service

ምቾት የቤት ለቤት ህክምና አገልግሎት Michot Home Based Health Care Service Michot Home Based health care servie at Debre Markos

16/04/2025
04/09/2024

ስለ ሪህ (GOUT)

#ሪህ በሽታ ( ) ምንድነው?

👉 ሪህ በመገጣጠሚያዎቻችን ላይ ከሚከሰቱና ከፍተኛ ህመም ሊያመጡ ከሚችሉ በሽታዎች በዋነኝነት የሚጠቀስ ሲሆን መንስኤውም የዩሪክ አሲድ (uric acid) ቅንጣጢቶች በአንጓዎቻችን ውስጥ ከመጠን በላይ መከማቸት ነው። ዩሪክ አሲድ ከተለያዩ ምግብና መጠጦቻችን የሚፈጠር ተረፈ ምርት ሲሆን ሰውነታችን በሽንት በኩል በአግባቡ ሊያስወግደው ካልቻለ በደማችን ውስጥ በመጠራቀም ለሪህ ህመም ሊያጋልጥ ይችላል። ከሪህ በተጨማሪም ክምችቱ የኩላሊት ጠጠሮችን ሊፈጥር ይችላል።

🩺 ምልክቶቹ ምንድን ናቸው?

👉 በድንገት ሌሊት ላይ የሚከሰት ከባድ የመገጣጠሚያ ህመም ዋናው ምልክት ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ ከእግር አውራ ጣት ይጀምራል፡፡ ይሁን እንጂ ቁርጭምጭምት ፣ ጉልበት እና ሌሎች መገጣጠሚያዎች ላይም ይከሰታል፡፡ 👉 ከህመሙ በተጨማሪ የመገጣጠሚያ መቅላት እና ማበጥ ሊከሰት ይችላል፡፡ ሪህ ካልታከመ የዩሪክ አሲድ ቅንጣጢቶች አንድ ላይ በመሰባሰብ እባጮችን (Tophi) ይፈጥራሉ፡፡
👉 እባጮች አብዛኛውን ጊዜ መገጣጠሚያዎች፣ ክርን እና ጆሮ ላይ የሚፈጠሩ ሲሆን በሽታው የከፋ መሆኑን ያመለክታሉ ፡፡
👉 እኒህ እባጮች መገጣጠሚያ ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ሲሆን በጀርም ሊበከሉ እና ኢንፌከሽን ሊፈጥሩም ይችላሉ ፡፡

🩺 አጋላጭ መንስኤዎች፡

👉 ውፍረት ፣ የስኳር በሽታ ፣ የኩላሊት በሽታ ፣ የደም ግፊት ፣ የሰውነት ቅባት (ኮሌስቴሮል) መጨመር ፣ የእድሜ መግፋት፣ ማረጥ ፣ በቤተሰብ የሪህ በሽታ መኖር ፣
👉 ለተለያዩ ህመሞች የሚታዘዙ መድሃኒቶች (ለምሳሌ ዳዩሬቲክስ/Diuretics)፣
👉 የዩሪክ አሲድ መጠንን የሚጨምሩ ምግቦች እና መጠጦች (ለምሳሌ ቀይ ስጋ ፣ ጉበት ፣ አንዳንድ የዓሳ ዝርያዎች ፣ አልኮል እና ጣፋጭ/ስኳራማ የለስላሳ መጠጦች) ወዘተ

🩺 ለሪህ ህመም የሚያስፈልጉ ምርመራዎች

👉 ከደም ናሙና በመውሰድ የዩሪክ አሲድ መጠንን መለካት

👉 የተጠቃውን መገጣጠሚያ በራጅ ወይም ሶኖግራፊ መመርመር

👉 ከመገጣጠሚያ (አንጒ) መሀከል የሚገኝን ፈሳሽ ናሙና በመውሰድ በላቦራቶሪ መመርመር ሊያስፈልግ ይችላል።

🩺 የሪህ ሕክምና

💊 የህክምናው አላማ ብግነትን (inflammation) በማስቆም ምልክቶችን ማስታገስ፣ ደግመው እንዳይከሰቱ ማድረግና የመገጣጠሚያን ጉዳትን መቀነስ ነው።
የህመም ምልክቶችን የሚያስታግሱ መድሃኒቶች፡- ኮልቺሲን ፣ NSAID (ለምሳሌ ኢንዶሜታሲን ፣ ዳይክሎፈናክ ፣ አይቡፕሮፌን) እና ስቴሮይድ (ለምሳሌ ፕሪዲንሶሎን)።
💊 እነዚህም መድሀኒቶች በኪኒን ወይም በመርፌ ሊሰጡ ይችላሉ።

*የመገጣጠሚያ ጉዳትን ለመከላከል እና በደማችን ውስጥ የሚገኘውን የዩሪክ አሲድ መጠን ለመቀነስ ከሚያግዙ መድሀኒቶች፡- አሎፕሪኖል (Allopurinol) ዋናው ነው፡፡

🩺 ከመድኃኒቶች ውጭ ያሉ ሕክምናዎች፤

👉 ክብደትን መቀነስ፡- ከመጠን በላይ ውፍረት ከሪህ ጋር ይዛመዳል ስለዚህ ክብደትን መቀነስ ሪህን ለማስታገስ እና ለአጠቃላይ ጤንነት ጥሩ ውጤት አለው ፡፡

👉 ጤናማ አመጋገብ፡- የሪህ ምልክቶችን ለማስወገድ እና ክብደት ለመቀነስ ይረዳል ፡፡

👉 “አጋላጭ መንስኤዎች” ከሚለው ስር የተጠቀሱትን ምግቦች እና መጠጦችን ማስወገድ

👉 ፍራፍሬዎችን ፣ አትክልቶችን እና ጥራጥሬዎችን አዘውትረው መመገብ፡፡

👉 በቂ ውሃ መጠጣት፡፡

👉 በሚያምዎ ቦታ ላይ በረዶ ማድረግ፡፡

🕛 የሕክምናው ለውጥ በደም ውስጥ ያለውን የዩሪክ አሲድ መጠን በመለካት ይገመገማል፡፡
👉 ዓላማው የደምዎ ዩሪክ አሲድን መጠን ከ 6 mg/dl በታች እንዲቀንስ

01/09/2024

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Abishe Gerba, Endaweke Tilahun

Address

Debra Markos

Telephone

+251929576709

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ምቾት የቤት ለቤት ህክምና አገልግሎት Michot Home Based Health Care Service posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share