Debre Markos city administration health office

Debre Markos city administration health office በዚህ ገፅ ዓለም አቀፋዊ፣ አገራዊ፣ ክልላዊ፣ የከተማውንና የአካባቢውን ወቅታዊ የጤና ጉዳይ መረጃዎችን እናጋራለን።

30/07/2025
25/07/2025

Self-care isn’t selfish. It’s science.

25/07/2025

ማስታወቂያ
_________

የብቃት ምዘና ፈተና ለምትወስዱ ጤና ባለሙያዎች በሙሉ
ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ Medicine, Nursing, Public Health, Anesthesia, Pharmacy, Medical Laboratory Science, Midwifery, Dental Medicine, Medical Radiology Technology, Environmental Health, Psychiatric Nursing, Pediatric & Child Health Nursing, Emergency & Critical Care Nursing, Surgical Nursing, Physiotherapy, Optometry እና Human Nutrition ሙያዎች በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቃችሁ የመውጫ ፈተና ያለፋችሁ እንዲሁም በድጋሜ የብቃት ምዘና ፈተናን ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ ለምትገኙ ጤና ባለሙያዎች፣ ምዝገባው ከሀምሌ 15 - 24/2017 ዓ.ም የሚከናወን መሆኑን እያሳወቅን
http://hple.moh.gov.et/hple/ ላይ በመግባት እንድትመዘገቡና ሲስተሙ የሚሰጣችሁን የፈተና መለያ ቁጥር (Registration No) የያዘ ስሊፕ print አድርጋችሁ እንድትይዙ እናሳስባለን፡፡

በተጨማሪም ተመዛኞች አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ የሚረዱና ጠቃሚ መረጃዎችን የያዙ Information Booklets እንዲሁም የመለማመጃ ጥያቄዎችን የያዙ የ Practice Test Booklets በቴሌግራም ቻናላችን ላይ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ማሳሰቢያ፦
- እያንዳንዱ የፈተና ጣቢያ በየሙያ መስኩ ማስተናገድ በሚችለው ከፍተኛ የተመዛኝ ቁጥር ልክ ገደብ ስለተቀመጠለት ተመዛኞች ምዝገባውን ቀድማችሁ በማጠናቀቅ ተጠቃሚ መሆን የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን ከፍተኛው የተመዛኝ ቁጥር በደረሰበት የፈተና ጣቢያ ላይ ተጨማሪ ምዝገባ ማከናወን የማይቻል መሆኑን እናሳስባለን።

- ማንኛውም ተመዛኝ ወደ ፈተና ጣቢያ ሲመጣ ሲስተሙ የሚሰጠውን የፈተና መለያ ቁጥር (Registration No) የያዘ ወረቀት /ስሊፕ/ print አድርጎ ካልያዘ ፈተናውን መውሰድ የማይችል መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን፡፡

- ከላይ ከተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውጪ ምንም ዓይነት የምዝገባ ጥያቄ የማናስተናግድ መሆኑን አውቃችሁ በተጠቀሱት ቀናት እንድትመዘገቡና እያሳሰብን ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115186275/0115186276 መደወል የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

Website: moh.gov.et
Facebook: Ministry of Health,Ethiopia
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/
Tiktok: tiktok.com/
Telegram: t.me/M0H_EThiopia

25/07/2025
https://www.facebook.com/100064757674313/posts/1175172854651293/?mibextid=rS40aB7S9Ucbxw6v
22/07/2025

https://www.facebook.com/100064757674313/posts/1175172854651293/?mibextid=rS40aB7S9Ucbxw6v

Note:- በዚህ ምስል ላይ "የኢትዮጵያ ሴት ጠበቆች ማህበር" ተብሎ የተጠቀሰው በስህተት ሲሆን 7711 "የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር" የነጻ የህግ ማማከሪያ አገልግሎት መሆኑን እያሳወቅን ለተፈጠረው ስህተት ይቅርታ እንጠይቃለን!

#ትንኮሳ #ጥቃት

ደም መለገስ ህይወት ማዳን ነው!
18/07/2025

ደም መለገስ ህይወት ማዳን ነው!

18/07/2025

#የጥንቃቄ #መልክት

የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን

በቲክ ቶክ በምስሉ የሚታየው ግለሰብ የኢትዮጵያ ምግብ መድኃኒት ባለስልጣን ፍቃድ ያገኘ በማስመሰል እውቅና አግኝቻለሁ ብሎ በሀሰት የተቋሙን ሎጎና ስም በመጠቀም ምንነቱ የማይታወቅ ምርት እያስተዋወቀ መሆኑ በማህበራዊ ሚዲያ ባደረግነው ዳሰሳ ደርሰንበታል።

ግለሰቡ ምንም አይነት ፈቃድም ሆነ የማስመዝገብ ሂደት ውስጥ የሌለና ሀሰተኛ መሆኑን እያስታወቅን። በኢትዮጵያ ውስጥ ማንኛውም የመድኃኒት ወይም የጤና ግብዓት ምርት ገበያ ላይ ከመዋሉ በፊት ተመዝግቦ ጥብቅ ቁጥጥር የሚደረገበት መሆኑና ለህብረተሰብ ከመቅረቡና ከቀረበ በኃላ ደህንነቱ፣ ጥራቱ እና ውጤታማነቱ የማረጋገጥ ስራ ይሰራል።

ባለሰልጣን መስሪያ ቤቱ እያንዳንዱ ዜጋ ጥንቃቄ እንዲያደርግ እና ማንኛውንም ከጤና ጋር የተገናኘ ምርት ከመጠቀሙ በፊት ትክክለኛነት እንዲያረጋግጥ እያስታወቀ።በሀኪም በታዘዘለት መሰረት ከህጋዊ ተቋማት ብቻ የጤና ግብዓቶች እንዲጠቀም ያሳውቃል፡፡ካልተረጋገጡ ምንጮች በተለይም ምርቶችን ያለ ምንም ፍቃድ በሚያስተዋውቁ ሰዎች በፍፁም አይተማመኑ በተጨማሪም እንዳይታለሉ ያሳስባል።በሀሰተኛ ማስታወቂያ ህብረተሰቡን ለማጭበርበር እየሰራ የሚገኘውን ይህን ግለሰብ ላይ የማጣራት ስራ በመስራት ተገቢውን ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ እገልጻለን፡፡

ማንኛው የጤና ግብዓቶች ሐሰተኛ ማስታወቂዎች በማሰራጨት ጥራትና ደህንነታቸው እና ፈዋሽነታቸው ያልተረጋገገጡ እንደሁም በባለሰልጣን መስሪ ቤቱ ያልተመዘገቡና ህገወጥ የጤና ግብዓቶች ሲሸጥ ካስተዋሉ ወይም ምርቱ ያልተመዘገበ እንደሆነ ከተጠራጠሩ እባክዎን ወዲያውኑ ለባለስልጣኑ በነጻ ስልክ መስመር 8482፣አቅሪያባዎ ለሚገኙ ፍትህ አካልት ወይም ለክልል የጤና ተቆጣጣሪ አካላት ያሳውቁ።

17/07/2025

4⃣ principles that help volunteering thrive:

📌 Freedom to volunteer
📌 Gender equality in volunteering
📌 Safety and security for all volunteers
📌 Voice and recognition of volunteer groups

17/07/2025
11/07/2025

የማይበገር ጠንካራ የጤና ሥርዓት ለመገንባት ከሚሰሩ ስራዎች አንዱ የማህበረሰቡን ጤና መጠበቅ ነው፤

አቶ አብዱልከሪም መንግሥቱ
የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ


#አብክመጤናቢሮ

Address

Ethiopia, Amhara Region
Debra Markos

Telephone

+251587711940

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Debre Markos city administration health office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Debre Markos city administration health office:

Share