29/01/2020
ለክቡራን ደንበኞቻችን
በፈለገ ሕይወት ሆስፒታል የፊትና የአፍ ውስጥ ቀዶ ህክምና ክፍል የከንፈርና የላንቃ መሰንጠቅ ህክምና በቋሚነት መስራት የጀመርን መሆኑን በታላቅ ደስታ እንገልጻለን። ስለሆነም እድሜያቸው ለከንፈር መሰንጠቅ ከ6 ወር ለላንቃ መሰንጠቅ ደግሞ ከ9 ወር ጀምሮ የሆናቸውን ህጻናት መጥታችሁ በማስመርመር አገልግሎቱን ማግኘት የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን።