Gizachew Medium Clinic

Gizachew Medium Clinic Providing quality health care to the people of Moja.

05/08/2021
02/07/2021
28/06/2021
28/06/2021
18/11/2020

*ጉበት ከሰባ ምን ረባ* ሲባል ሰምተው ያውቃሉ?

Liver (Hepatic Steatosis)

ለዛሬ ስለ #ጉበት #መስባት (በጉበት ላይ ስለሚከማች ስብ) ጠቃሚ መረጃ እናጋራችሗለን።
• ለመሆኑ የጉበት መስባት ምን ማለት ነው? ከፍተኛ የሆነ የስብ ክምችት በጉበት ላይ ሲኖር የጉበት መስባት(Fatty Liver) ይባላል። ትንሽ መጠን ያለው የስብ ክምችት እንደ ችግር አይቆጠርም።
• እንደሚታወቀው ጉበት ከሰውነታችን አካል ክፍሎች በትልቅነቱ 2ኛ ደረጃ ሲሆን በምግብና መጠጥ አማካኝነት ወደ ሰውነታችን የገቡ ነገሮችን በማጣራትና በመፈተሽ ሰውነትን ሊጎዱ የሚችሉ ነገሮችን በማስወገድና የጉዳት መጠናቸውን በመቀነስ ሰውነት ላይ ሊደርስ የሚችልን ከባድ ችግር ያስቀራል።
• ባጭሩ ጉበታችን ለሰውነታችን ዋና #የጉሙሩክ ጣቢያና ባትሪም ነው። ሞባይልም ሆነ ኮምፒውተር ያለባትሪ ዋጋ እንደሌለው ሰውነትም ያለጉበት ባትሪ ሎው ብሎ ህይዎትን ያቆማል።
• መጠኑ የጨመረ የስብ መጠን ለጉበት መጠቃትና መመረዝ ያጋልጣል። ይህም ጉበት ላይ ጠባሳ እንድፈጠር ያደርጋል። ይህ ደግሞ ጉበት ስራውን በአግባቡ እንዳያከናውን ያደርገዋል።
• የጉበት ስብ እንድፈጠር መጠኑ የጨመረ የአልኮል መጠን ትልቁን ድርሻ ይይዛል።
#በጉበት ውስጥ ስብ ሲከማች ሊታዩ የሚችሉ ምልክቶች
• ብዙ ጊዜ ቶሎ አያሳይም። እየቆየ ግን በቀኝ የላይኛው የሆድ ክፍል ላይ ህመምና መጥፎ ስሜት
• የጉበት ጠባሳ መፈጠር
#የጉበት ጠባሳ ካለ የሚታዩ ምልክቶች
1. የምግብ ፍላጎት መቀነስ
2. የክብደት መቀነስና ድካም ስሜት
3. አቅም ማነስ
4. በአፍንጫ ደም መፍሰስ
5. የቆዳ ማሳከክ
6. ቆዳና አይን ቢጫ መሆን
7. የሆድ ህመም
8. የሆድ ማበጥ
9. የእግር ማበጥ
10. በወንዶች ላይ ጡት ማበጥ
11. ግራ መጋባት
#የጉበት ጠባሳ በጣም ከባድ ችግር ነው። ለህይዎትም አስጌ ስለሆነ የጤና ባለሙያ ክትትልና እንክብካቤ በእጅጉ አስፈላጊ ነው።
#በጉበት ላይ ለምን ስብ ይጠራቀማል?
• ሰውነት ስብን መጠቀም አለመቻል።
• ብዙ ጣፋጭ ተጠቃሚ መሆን
• መጠኑ ከፍ ያለ አልኮል መጠጣት
#ችግሩን የሚያባብሱ ነገሮች
• ውፍረት
• ከፍተኛ ደም ግፊት
• ስኳር በሽታ
• ብዙ ስብ በሰውነት ውስጥ መከማቸት
• የጉበት ቫይረስ ሲ
• መድሀኒቶች(methotrexate, tamoxifen, amiodorone and valproic)
• ለመርዛማ ነገሮች መጋለጥ
• እርግዝናና ሌሎችም ናቸው።
#መመርመሪያ መንገዶች
• የተለያዩ ጥያቄዎች በመጠየቅ
• የተለያዩ ምልክቶችን በማየት
• አካላዊ ምርመራ በማድረግ
• የደም ናሙና በመውሰድ
• የተለያዩ የማያ መሳሪያዎች በመጠቀም
• ከጉበት ናሙና በመውሰድ
#ህክምናው
• የሚታዘዝ መድሀኒት ባይኖርም አልኮልን ባለመጠጣት፡ ክብደትን በመቀነስና የባለሙያ ምክርንና ክትትልን በማክበር መቀነስና ከችግሩ መላቀቅ ይቻላል።
#ለተጨማሪ መረጃ እኛጋ ቤተሰብ ይሁኑ። መልእክቱን ያጋሩ ፣ ጤናችሁ ይብዛ!

Address

1000
Debre Birhan

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gizachew Medium Clinic posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Gizachew Medium Clinic:

Share

Category