19/07/2023
በምስራቅ ጎጃም ዞን በትምህርት ዘርፉ ባለፉት ሁለትና ሶስት አመታት በተሰራ ውጤታማ ስራ አበረታች ውጤቶች ተመዝግቧል፡፡
ባለፉት ሁለት አመታት በ1 ቢሊዬን 100 ሚሊዬን 259 ሽ 845 ብር በሚሆን ወጭ አዳዲስ ትምህርት ቤቶች፣ መማሪያ ክፍሎች፣ ቤተ መጻህፍት፣ ቤተ ሙከራዎች ተገንብተዋል፡፡
መምሪያው የዚህ አመት የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ከፍተኛ ውጤት እንዲያስመዘግቡ አልሞ እየሰራ ነው፡፡
ሀገር በትውልድ፤ ትውልድ ደግሞ በትምህርት ይገነባል። ስለሆነም ለአንድ ሃገር እድገት ትምህርት የማይተካ ሚና አለው፡፡ ምክንያቱም ያለ ትምህርት የእድገት ማማ ላይ የወጣ ሃገር የለምና፡፡
የሃገራችን ትምህርት በበርካታ ምክንያቶች የቁልቅለት ጉዞ በመሄድ ላይ እንደ ነበር መናገር ለቀባሪ ማርዳት ነው፡፡
በመሆኑም የምስራቅ ጎጃም ዞን አስተዳደር የዞኑ ትምህርት እየሄደበታ ካለው እጅግ አደገኛ የቁልቁለት ጉዞ በመግታት ወደ ነበረበት ከፍታ ለመመለስና ችግሮቹ እንዲፈቱና ትምህርት ቤቶች ያሉባቸው መሰረታዊ ችግሮች እንዲፈቱ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ነው፡፡
ላለፉት አመታት በትምህርት ዘርፉ የተፈጠረውን መቀዛቀዝ በማነቃቃት ወደ ስራ ለማስገባት በርካታ የምክክር መድረኮችን ከአጋርና ባለድርሻ አካላት እንዲሁም ከሙያው ባለቤቶች ጋር በመፍጠር ችግሮችን የመለየትና በሚስተካከሉበት መንገድ መግባባት ተደርሷል፡፡ በዚህም በርካታ ውጤት ተመዝግበዋል፡፡
© በተፈጠረውን የንቅናቄ መድረክ ተከትሎ የትምህርት ቤቶች ደረጃ እንዲሻሻል ተደርጓል፡፡ ለአብነት፡-
~ በበጀት ዓመቱ 45 የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤቶች ደረጃ አንድ የነበሩ ሲሆን በተሰራዉ ስራ 29 ት/ቤቶች የደረጃ ሽግግር ማድረግ ችሏል፤
~ 36 ት/ቤቶች ወደ ደረጃ 3 እንዲሸጋገሩ አድርገናል፡፡
~ የት/ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል የነበረዉ የስራ ትጋት እጅግ አበረታች ነበር፤
~ 7 የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ወደ ደረጃ 3 እንዲገቡ አድርገናል፤
© የተናበበና የተቋሙን ችግር በራሱ አቅም ሊፈታ የሚችል ተቋም እየተገነባ ነው፤
© እያንዳንዱን ት/ቤትና ወረዳ ብሎም ዞኑን የመልካም ተሞክሮዎች መፍለቂያ ማዕከል እየሆነ ነው፤
© የትምህርት ውስጣዊ ብቃት ችግሮችን መፍታት ተችሏል፡፡
© በዘርፉ የተሰማሩ አካላት መነቃቃት ተፈጥሯል፡፡
© በዞኑ ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ በአንድ ጀምበር ተማሪን የመመዝገብ ስራ በመፈጸም ግንባር ቀድም ዞን ሆኗል፡፡
© የተማሪዎች የነፍስ ወከፍ ገቢ 100 ፕርሰንት መመደብ ተችሏል፡፡
ትምህርት ቤቶች ውብና ማራኪ እንዲሆኑ ለማድረግና በተማሪ መማሪያ ክፍል ጥምርታ ማለትም የመማሪያ ክፍል እጥረት ምክንያት የነበረውን ችግር ለመቅረፍ በዚህ ሁለት አመት መሰረታዊ ለውጦች ተመዝግበዋል፡፡
በምስራቅ ጎጃም ዞን በ78 ትምህርት ቤቶች 78 ብሎክ 335 የመማሪያ ክፍሎች በ181 ሚሊዬን 498ሽ 481ብር በ2013 ዓ.ም ግንባታቸው ተጀምሮ በ2014 ዓ.ም ተጠናቀው ለአገልግሎት ውለዋል፡፡ የእነዚህ መማሪያ ክፍሎች መገንባት ከ16570 አዲስ ተማሪዎች የመማር እድል እንዲያገኙ ማድረግ ተችሏል፡፡ በተጨማሪም በ10 ሚሊዬን 155ሽ 000 ብር ቤተመጽሐፍት፤ ቤተሙከራ እና መጸዳጃ ቤት በመገንባት ለአገልግሎት ማዋል ተችሏል፡፡
በተመሳሳይ በ2014 በጀት አመት በዞኑ ያለውን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ችግር ለመቅረፍ 4 ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች በመገንባትና እንዲጠናቀቁ በማድረግ በዚህ አመት በአዲስ ስራ እንዲጀምሩ ማድረግ ተችሏል፡፡
በ2015 የትምህርት ዘመን መምሪያው ባካሄደው የንቅናቄ መድረክ በተደራጀና በከፍተኛ የህዝብ ንቅናቄ የትምህርት ቤቶችን ገጽታ ለመቀየር በእጅጉ ውጤታማ ስራ ተሰርቷል፡፡ ለአብነት ዞኑ በአንድ ትምህርት ቤት አንድ ብሎክ በሚል መሪ ቃል አቅዶ ለመስራት ባደረገው ጥረት በ2015 የትምህርት ዘመን በ441 ሚሊዬን 238ሽ 124 ብር 45 ሳንቲም በሆነ ወጭ በ140 ት/ቤት 208 ብሎክ እና 620 መማሪያ ክፍሎች ተገንብተዋል፡፡
መምሪያው የህብረተሰቡን እምቅ አቅም በመጠቀም በትምህርት ዘርፍ ያለውን ችግር ለመቅረፍ እቅድ አቅዶ ውጤታማ ስራ እየሰራ ነው፡፡ በ2015 በጀት አመት የትምህርት ዘመን በህብረተሰቡ ተሳትፎ በጥሬ ገንዘብ፣ በቁሳቁስ፣ በጉልበት በድምር 545 ሚሊዮን 319ሽ 743 ብር በመሰብሰብ የእቅዱን 189.7 %በማሳካት የትምህርት ቤቶችን ገጽታ በመቀየርና ቸግሮቹን በመፍታት የህብረተሰቡ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት ጥረት ተደርጓል፡፡
በትምህርት ዘርፍ ላይ የሚሰራው ስራ ውጤቱን በአጭር ጊዜ ለማየት ከባድ ቢሆንም የ8ኛና የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የተሸለ ውጤት እንዲያመጡ ለማስቻል በርካታ ስራዎች ተሰርተዋል፡፡ ለአብነት
- ተማሪዎችን በትርፍ ጊዚያቸው እስከ ምሽቱ ድረስ ለሚያግዙ መምህራን ከ3.47 ሚሊዬን ብር በላይ ተመድቦ አገልግሎት ላይ ውሏል፡፡
- ቤተ መጻፍቶቹ ሳምንቱን ሙሉ እስከ ምሽቱ አራት ሰዓት ክፍት እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡
- ሞዴል ፈተና በዞንና በክልል ወጥቶ እንዲፈተኑ ተደርጓል፡፡
በመጭው ሃምሌ 19 /2015 የዞኑ 60 ትምህርት ቤቶች 24,518 የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ያስፈትናል፡፡
የምስራቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ ለተፈታኝ ተማሪዎች መልካም እድል ይመኛል፡፡
East Gojjam Communication