South Wollo Zone Co-operative Office

South Wollo Zone Co-operative Office Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from South Wollo Zone Co-operative Office, Dessi.

02/01/2018
በደቡብ ወሎ ዞን ወረኢሉ ወረዳ የውባዬ ኃላፊነቱ የተወሰነ ህብረት ስራ ማህበራት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ዩኒዬን ጠቅላላ ጉባኤና የቢሮ ምረቃ አደረገ ፡፡ የውባዬ ኃላፊነቱ የተወሰነ ህብረት ስ...
18/12/2017

በደቡብ ወሎ ዞን ወረኢሉ ወረዳ የውባዬ ኃላፊነቱ የተወሰነ ህብረት ስራ ማህበራት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ዩኒዬን ጠቅላላ ጉባኤና የቢሮ ምረቃ አደረገ ፡፡
የውባዬ ኃላፊነቱ የተወሰነ ህብረት ስራ ማህበራት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ዩኒዬን የካቲት 3/2001 ዓ.ም በደቡብ ወሎ ዞን ወረኢሉ ወረዳ 01 ቀበሌ ሦስት ወረዳዎችን (ወረኢሉ፣ ለገሂዳ፣ ጃማ)፣36 ቀበሌዎችን እና 29 ህብረት ሥራ አባላትን (በአይነት 14 ሁለገብ፣ 11 ገንዘብ ቁጠባ፣ 4 ሸማች) 38,604 የአባል አባል ብዛት፣ 7 አመራሮች፣ 3 ቁጥጥር ኮሚቴ፣ 3 ቅጥር ሰራተኞች፣ 498,000 ብር የካፒታል መጠን በመያዝ የስራ ቦታ ቢሮ በትውስት ከወረኢሉ ወረዳ ወጣቶችና ሴቶች ማህበር ያለ ኪራይ በመዋስ ስራውን ሲሰራ ቆይቷል፡፡
ዩኒዬኑ በአሁኑ ገዜ እስከ ሰኔ 30/2009 ዓ.ም 3 ወረዳዎችን እና 64 ቀበሌዎችን (58 የገጠር፣ 6 የከተማ) በማቀፍ 76 አባል ህብረት ሥራ ማህበራት፣ 7 አይነት ህብረት ሥራ ማህበራት፣49,874 የአባል አባሎችን በማፍራት፣ 304 የጠቅላላ ጉባኤ ተወካዮች፣ 7 ስራ አመራር፣ 3 ቁጥጥር ኮሚቴ፣ 3 ቋሚ ንብረት ገማች ኮሚቴ እና 6 ቅጥር ሰራተኞች በመያዝ በአሁኑ ሰአት ስራውን እየሰራ ይገኛል፡፡ ዩኒዬኑ 3,512,600 ብር ከእጣ ከእጣ ሽያጭ የተሰበሰበ ሲሆን ቁጠባቸውም 3123688.30 ብር መደበኛ ቁጠባ፣ 20,108,320.01 ብር መደበኛ ያልሆነ ቁጠባ፣ 4,135,000 ብር የጊዜ ገደብ ቁጠባ፣ 8,216,000 ብር ከቤቶች ህብረት ስራ የተሰበሰበ ቁጠባ፣ 35,583,008.31 ብር ጠቅላላ ቁጠባ መሰብሰብ ችሏል፡፡
ዩኒዬኑ ለ76 ህብረት ስራ ማህበራት እና 65,597 የአባል አባላት የቁጠባና የብድር አገልግሎት ይሰጣል፡፡ አባል ህብረት ሥራ ማህበራት ከተመሰረተበት እስከ አሁን ከ35 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰብ ችሏል፡፡ ለአባል ህብረት ሥራ ማህበራት ከ93 ሚሊዬን ብር በላይ የብድር አገልግሎት በመስጠት ተጠቃሚ ማድረግ ችሏል፡፡ ከብድር እና የቁጠባ አገልግሎት በተጨማሪም የአነስተኛ መድን ዋስትና ሽፋን ይሰጣል፣ አባላት ውጤታማ የሂሳብ አያያዝ ስርአት እንዲያከናውኑ እገዛ ያደርጋል፡፡ ልዩ ልዩ ተቀማጭ ሂሳቦችን በማሰባሰብ ያስተዳድራል፡፡ ለአካባቢው ህብረተሰብ ወጣትና ህፃናትን የቁጠባ አገልግሎት አስፈላጊነትን በማስተማር የቁጠባ ባህል እንዲዳብር ያደርጋል፡፡ የተለያዩ የምክርና የመረጃ አያያዝን ቴክኒካዊ እገዛ ለአባል ማህበራት ይሰጣል፣ ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር ከልደት ዩኒዬን፣ ከመካነ ሠላም ዩኒዬን፣ ከጎል፣ ከአባይ ባንክ እና ከልማት ባንክ ጋር ትስስር በመፍጠር ከ70 ሚሊዬን ብር በላይ ብድር ማግኘት ተችሏል፡፡
ዩኒዬኑ ከክልል ህብረት ሥራ ኢንዱስተሪና ከተማ ልማት፣ ከደቡብ ወሎ ዞን ህብረት ሥራ ማህበራት ማስፋፊያ ተጠሪ ጽ/ቤት ጋር በመነጋገር ለወረኢሉ ወረዳ መሪ ማዘጋጃ ቤት ጋር ውይይት በማድረግ ህብረት ሥራ ማህበራት የመስሪያና የመሸጫ ቦታ ያለምንም ክፍያ በነፃ እንደሚያገኙ በመወያየት እና በጠቅላላ ጉባኤ ፊት ቀርቦ ሃሳብ እንዲሰጥ በማድረግ በወረኢሉ ወረዳ ከተማ 01 ቀበሌ ከመነሐሪያ ዝቅ ብሎ 756 ካሬ ሜትር ቦታ በመረከብ እና በአጥር በመከለል ሀሳቡን ለጠቅላላ ጉባኤው ቀርቦ 36,213 ብር ከወረኢሉ ወረዳ 19 ህብረት ሥራ ማህበራት፣ 65,035 ብር ከጃማ ወረዳ 16 ህብረት ሥራ ማህበራት፣ 26,910 ብር ከለገሂዳ ወረዳ 6 ህብረት ሥራ ማህበራት፣ በጠቅላላው 128,158 ብር በማሰባሰብ እና ከዩኒዬኑ 2,621,124.74 ብር በመጨመር ጠቅላላ 2,749,282.74 ብር ወጪ በማድረግ ግራውንድ ፕላስ አንድ ህንፃ የተሰራ ሲሆን ህንፃውም ስምንት ክፍል ቢሮ፣ ሁለት አነስተኛና መካከለኛ የመሰብሰቢያ አዳራሽ አለው፡፡ ቢሮው በህዳር 10/2010 ዓ.ም በተካሂደው ጠቅላላ ጉባኤ በማስመረቅ የተለያዩ የቁጠባና የብድር ስራዎችን አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡
ዩኒዬኑ በቀጣይም የቁጠባን አስፈላጊነት በሰፊው ማስተማር፣ ተሽከርካሪ በመግዛት ሁሉንም ህብረት ስራ ማህበራት ተደራሽ ማድረግ፣ ከተለያዩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር በጋራ መስራት እና በሁለት ወረዳዎች ቅርንጫፍ ከፍቶ ተደራሽ በማድረግ ሰፊ ስራ ለመስራት እቅድ አቅዷል፡፡

በደቡብ ወሎ ዞን አርጎባ  ወረዳ ህብረት ስራ ማህበራት ማስፋፊያ ጽ/ቤት የ2009ዓ.ም እቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2010 ዓ.ም እቅድ ኦረንቴሽን የንቅናቄ መድረክ ችግሮችን ለመፍታት የሚያ...
08/12/2017

በደቡብ ወሎ ዞን አርጎባ ወረዳ ህብረት ስራ ማህበራት ማስፋፊያ ጽ/ቤት የ2009ዓ.ም እቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2010 ዓ.ም እቅድ ኦረንቴሽን የንቅናቄ መድረክ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል የጋራ መግባባት ላይ ተደርሶ ተጠናቀቀ፡፡

በአማራ ክልል የደቡብ ወሎ ዞን ህብረት ሥራ ማህበር ማስፋፊያ ተጠሪ ጽ/ቤት በሦስት ዩኒዬኖች (እሪኩም፣ ታቦር፣ የወል)  የግብይት ትስስር መድረክ ከ29/02/2010 እስከ 30/02/2010 ...
07/12/2017

በአማራ ክልል የደቡብ ወሎ ዞን ህብረት ሥራ ማህበር ማስፋፊያ ተጠሪ ጽ/ቤት በሦስት ዩኒዬኖች (እሪኩም፣ ታቦር፣ የወል) የግብይት ትስስር መድረክ ከ29/02/2010 እስከ 30/02/2010 ዓ.ም የግብይት ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል የጋራ መግባባት ላይ ተደርሶ ተጠናቀቀ፡፡
የዞኑ ህብረት ስራ ማህበራት ማስፋፊያ ጽ/ቤት ኃላፊ ተወካይ አቶ አለማየሁ ታደሰ የ2009 ዓ.ም የግብይት ትስስር ስራ አፈፃፀምን አስመልክቶ እንደተናገሩት በ2009 ዓ.ም መሠረታዊ ማህበራት ትልቅ ስራ እየሰሩ በመሆኑ ውጤታማ መሆን ችለናል ብለዋል፡፡ ሰብል በማቅረብ በኩልም ያደረግነው አስተዋጽኦ ውጤታማ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በ2010 ዓ.ም ሰርተን ውጤት ማስመዝገብ እንችላለን ሲሉም አክለው አቶ አለማየሁ ታደሰ ተናግረዋል፡፡

በአማራ ክልል የደቡብ ወሎ ዞን ህብረት ሥራ ማህበር ማስፋፊያ ተጠሪ ጽ/ቤት የ2009 ዓ.ም የሥራ አፈፃፀም ግምገማ እና የ2010 እቅድ ትውውቅ መድረክ ከ27/02/2010 እስከ 28/02/20...
07/12/2017

በአማራ ክልል የደቡብ ወሎ ዞን ህብረት ሥራ ማህበር ማስፋፊያ ተጠሪ ጽ/ቤት የ2009 ዓ.ም የሥራ አፈፃፀም ግምገማ እና የ2010 እቅድ ትውውቅ መድረክ ከ27/02/2010 እስከ 28/02/2010 ዓ.ም ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል የጋራ መግባባት ላይ ተደርሶ ተጠናቀቀ፡፡
በስብሰባው እለት የሁሉም ወረዳ ኃላፊዎች እና የስራ ሂደት አስተባባሪዎች ከዩኒዬን የሁሉም ዩኒዬን ስራአስኪያጆች እና ሌሎችም አጋር አካላት የተገኙ ሲሆን የስብሰባውን መክፈቻ ንግግር የደቡብ ወሎ ዞን ኃላፊ ተወካይ አቶ አለማየሁ ታደሰ የመክፈቻ ንግግር በማድረግ ተጀምሯል፡፡
የዞኑ ህብረት ስራ ማህበራት ማስፋፊያ ጽ/ቤት ኃላፊ ተወካይ አቶ አለማየሁ ታደሰ የ2009 ዓ.ም የስራ ዘመን አፈፃፀምን አስመልክቶ እንደተናገሩት የ2009 ዓ.ም አፈፃፀምን በጥንካሬና በእጥረት ለይተን በማዬት ለወደፊቱ በጥንካሬ ያየናቸውን አጠናክረን በመቀጠል የታዩብንን እጥረቶችንም ለመፍታት ትግል ይጠይቃል ሲሉ ተናግረዋል፤ በ2010 በጀት አመትም ሁሉም ወረዳ፣ ዩኒዬኖችና መሠረታዊ ማህበራት ውጤታማ ሥራ ሰርተን በተግባር ማሳየት አለብን ሲሉ አቶ አለማየሁ ታደሰ ትኩረት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡
ከደቡብ ወሎ ዞን ንግድና ኢንዱስትሪ አቶ አብደላ ያሲን የስኳርና ዘይት አቅርቦት ለማህበረሰቡ ከማዳረስ አንፃር የሚመደበው መጠን አነስተኛ በመሆኑ በተቻለ መጠን የማዳረስ ስራ እንሰራለን ብለዋል፡፡ንግድና ኢንዱስተሪ ብቻውን የሚሰራው ነገር የለምና ሁሉም ወረዳ ህብረት ስራ ማህበራት እና ዩኒዬን በግብረ ሃይል መስራት አለብን ሲሉ አቶ አብደላ ያሲን አከለው ተናግረዋል
የመቅደላ ወረዳ ህብረት ሰራ ኃላፊ የሆኑት አቶ ሙሀመድ አፈፃፀማቸውን በዝርዝር አቅርበዋል፤ ይህንን አስመልክተው የልማት ሰራዊት ግንባታችን ውስንነት ቢሆንም የተሻለ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡የመልካም አስተዳደር ስራዎችን በየደረጃው እየለየን በቁርጠኝነት እየሰራን እንገኛለን ብለዋል፡፡ የ2009 ዓ.ም እቅድን በታቀደው ልክ አልሰራንም በ2010 ዓ.ም ውጤታማ ስራ እንሰራለን ሲሉም አቶ ሙሀመድ አክለው ተናግረዋል፡፡
በመጨረሻም የ2009 ዓ.ም የተሻለ አፈፃፀም ያላቸውን ወረዳዎችና ዩኒዬኖች የእውቅና የምስክር ወረቀት በመስጠት ተጠናቋል፡፡

07/12/2017

ክፍል ሁለት PART TWO
ስለመብቱ አፈጻጸም Implementation of the Right
1. የእኩል መስተንግዶ መርህ 1. Principle of Equal Treatment
1. በክልሉ ውስጥ የገጠሩና የከተማው ነባራዊ ሁኔታዎች የተለያዩ ከመሆናቸው የተነሳ የመኖሪያ ቤትም ሆነ የዚሁ መስሪያ ቦታ አሰጣጥ ስርዓቱ የሚለያይ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በሁሉም አካባቢዎች ተመድበው በሚያገለግሉ መምህራን መካከል የዚህን ደንብ ድንጋጌዎች አተገባበር አስመልክቶ ብሄር--ብሄረ-ሰብን፣ ሀይማኖትን፣ ማህበራዊ አመጣጥንና የመሳሰሉትን ጉዳዮች መሰረት ያደረገ አንዳች አይነት ልዩነት አይደረግም፡፡ ሁሉም ያለአድልዎ የመስተናገድና በእድሉ እኩል የመጠቀም መብት ይኖራቸዋል፡፡ 1. Due to the fact that the natural conditions of rural and urban areas are quite different throughout the Regional State, without prejudice to the prevailing disparity in the delivery system of dwelling house and land for the construction of same, no discrimination shall be made amongst teachers duly assigned to serve in all localities on the basis of nation-nationality, religion, social origin and the like matters with regard to the implementation of the provisions of this regulation. All shall be treated without discrimination and have the right to equally enjoy with the opportunity thereof;
2. በክልሉ መንግስት አማካኝነት የተሰራ መኖሪያ ቤት ያለ እንደሆነ መምህራን ይህንኑ እንዳግባብነቱ ከኪራይ ነጻ በሆነ መንገድ ወይም በተመጣጣኝ ኪራይ የማግኘት ወይም አገልግሎታቸው 2 ዓመትና ከዚያ በላይ በሆነ ጊዜ ለመኖሪያ ቤት መስሪያ የሚሆን ባዶ ቦታ የማግኘት መብት አላቸው፡፡ የመኖሪያ ቤትም ሆነ የባዶ ቦታ አሰጣጥ ስርዓቱ በተቻለ መጠን የተጠቃሚዎቹን ፍላጎት ያማከለ ይሆናል፡፡ 2. Teachers shall, where there exist dwelling houses constructed by the regional government, have the right to obtain same in a manner that is free from rent or with a reasonable amount of rent, as deemed appropriate, or a vacant plot of land for the purpose of constructing dwelling house where their services have been two years and above. The delivery system of the dwelling house or vacant plot of land shall conform with the interest of individual beneficiaries, as much as possible.

3. በዚህ አንቀፅ ንኡስ አንቀፅ (2) ስር የተደነገገው ቢኖርም መምህራኑ የደንቡ ተጠቃሚ ሊሆኑ የሚችሉት ከመኖሪያ መንደር፣ ከኮንዶሚኔም፣ መንግስት ከሚሰጠው የኪራይ ቤት ወይም በምሪት ቦታ ከተሰሩ ቤቶች መካከል አንደኛውን ብቻ በመምረጥ ይሆናል፡፡ 3. Notwithstanding the provision of Sub-Art. (2) of this Article hereof, teachers shall be able to become beneficiaries of the regulation only by preferring one from amongst the residential village, condominium, rental house to be provided for by the government or those houses constructed on the land permitted for the purpose.
2. ስለመምህራን ነጻ የመኖሪያ ቤትና ቦታ አሰጣጥ፡- 2. Delivery of Free Dwelling House and Land for Teachers
1. በንዑስ ማዘጋጃ-ቤቶች፣ በታዳጊ ከተሞችና በገጠር ቀበሌዎች ውስጥ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የሚያስተምሩ መምህራን፡- 1. Teachers who happen to teach at those schools found in sub-municipalities, emerging towns and rural Kebeles:
ሀ. ጉዳዩ በሚመለከተው ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ወይም በዙሪያ አካባቢው በክልሉ መንግስት በጀት ወይም በአካባቢው ህብረተሰብ የቁሳቁስና የጉልበት ተሳትፎ በተሰሩ የመምህራን መኖሪያ መንደሮች ውስጥ በነጻ እንዲኖሩ ይደረጋል፤ A. shall be made to reside in the teachers’ residential villages duly constructed by the Regional Government budget or through the material and labor participation of the local community in the premises of the school concerned or the surrounding area;
ለ. እነዚሁ የመምህራን መኖሪያ መንደሮች በዋነኛነት በትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ የመማር ማስተማሩን ስራ በማያውክ ርቀት ላይ ይገነባሉ፤ B. these teachers’ residential villages shall be constructed mainly in the premises of the school in a distance where they do not disturb the teaching-learning activity;
ሐ. በተባለው ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ወይም በዙሪያ አካባቢው በቂ መሬት ያልተገኘ እንደሆነ አግባብ ያለው የቀበሌ አስተዳደር ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተመካክሮ በሚያመቻቸው አቅራቢያ ቦታ ላይ ይገነባሉ፡፡ C. Where adequate plot of land is not available in the premises of the said school or the surrounding area, the teachers’ residential houses shall be constructed nearby in a place to be set aside by the pertinent Kebele Administration in consultation with the organs concerned thereto.
2. በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀፅ (1) ስር የሰፈረው አጠቃላይ ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ አገልግሎታቸው 2ዓመትና ከዚያ በላይ የሆነ መምህራን በሚሰሩበት ትምህርት ቤት15 ኪሎ ሜትር ራዲየስ ውስጥ ከሚገኙት ከተሞች በመረጡት በአንደኛው በራሳቸው ወጪ የግል መኖሪያ ቤት መስራት እንደሚፈልጉ ገልፀው ያመለከቱ እንደሆነ የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት ለነባርና አዳዲስ የህብረት ስራ ማህበራት ጥር 12 ቀን 2009 ዓ.ም አሻሽሎ ባወጣው የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ አቅርቦትና የግንባታ አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 28/2009ዓ.ም ውስጥ የተመለከተውን የማህበራት ቦታ ስፋት ልክ ሳያልፍ የጠየቁት የቤት መስሪያ ቦታ ሊሰጣቸው ይችላል፡፡ ይኸው በኮሚቴ እየተጣራ በንዑስ ማዘጋጃ-ቤት ከተሞች ሲሆን በሊዝ መነሻ ዋጋ፣ በታዳጊ ከተሞች ሲሆን ደግሞ በአመታዊ ኪራይ ተመን ይሰጣቸዋል፡፡ 2. Without prejudice to the general provision laid down under Sub-Art. (1) of this Article hereof, where teachers whose service has been two years and above notify that they preferentially desire to construct private dwelling houses on their own expense in one of the cities found within the radius of 15 kilometers from the school in which they work, they may be provided with the plot of land they have requested for the construction of house not exceeding the limit of the cooperative land size indicated under the Revised Dwelling Houses Construction Land Supply and Building Determination Directive No. 28/2017 which the Council of the Regional Government has issued on January 20 2017 for the benefit of the old and new cooperative societies. Such shall be scrutinized via a committee and be provided to them through an initial lease price, where the land is located in sub-municipalities, and through annual rental rate in the case of emerging towns.
3. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (2) ስር የሰፈረው ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ በ15 ኪሎ ሜትር ራዲየስ ውስጥ ተፈላጊውን የከተማ ቦታ ማግኘት ያልቻሉ መምህራን ቢኖሩ በአቅራቢያቸው በሚገኙ የቀበሌ ማእከላት ውስጥ የጠየቁት የቤት መስሪያ ቦታ ሊሰጣቸው ይችላል፡፡ 3. Without prejudice to the provision laid down under Sub-Art. (2) of this Article hereof, should there exist teachers who have been unable to obtain the required urban land within the radius of 15 kilometers, they may be provided with the plot of land they have requested at the Kebele center located in their surroundings.
4. መምህራን በሚሰሩበት ወረዳ ውስጥ ካሉት ከተሞች መካከል ራሳቸው በመረጡት ከተማ ውስጥ የመኖሪያ ቤት ለመስራት የፈለጉ እንደሆነ መመሪያ ቁጥር 28/2009 ዓ.ም በሚፈቅደው መሰረት እንደማንኛውም ዜጋ 14ና ከዚያ በላይ እየሆኑ በማህበር ተደራጅተውና ከቤት መስሪያ ዋጋው 20 ከመቶ የሚሆነውን ገንዘብ መቆጠባቸውን አረጋግጠው ቦታውን ሊያገኙ ይችላሉ፡፡ 4. Where teachers desire to construct a dwelling house in the town they have preferred among the cities existing in the Woreda wherein they work, they may, having been organized in cooperatives of 14 in number and ascertained that they have managed to save the money to the amount of 20% of the total price for the construction of the house, obtain such land in accordance with the Directive No. 28/2017.
5. የዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ (4) ድንጋጌ ቢኖርም ቀደም ሲል በማህበር ተደራጅተው የቤት መስሪያ ቦታ የተረከቡ መምህራን በዚሁ በተረከቡት ቦታ ላይ የአካባቢው አስተዳደር ያወጣውን ደረጃ የጠበቁ መኖሪያ ቤቶችን በራሳቸው ወጪ ሊገነቡ ይችላሉ፡ 5. Notwithstanding the provision of Sub-Art. (4) of this Article hereof, teachers who already had been organized in cooperatives and received land for the construction of houses may build same having maintained the standard set by the local administration on their expense at such land they have acquired thereof.
6. በከተማው ለመኖሪያ ቤት መስሪያ ከሚዘጋጀው ቦታ ውሥጥ ከ20-30 ከመቶ የሚሆነው ለመምህራን ቅድሚያ ተሰጥቶ ይመደባል፡፡ 6. 20 through 30% of the land to be prepared for the construction of dwelling houses in the city shall be allotted for teachers, having been given priority thereof.
7. በዚህ ደንብ ድንጋጌዎች መሰረት መምህራንን ተጠቃሚ ለማድረግ ሲባል የካሳ ክፍያ አስፈላጊ ሆኖ በሚገኝበት ጊዜ የክልሉ መንግስት ለተፈናቃዮቹ በህግ አግባብ ተገቢውን ካሳ በቅድሚያ በመክፈል ወይም ትክ ቦታ በመስጠት የቤት መስሪያ ስፍራውን ከሶስተኛ ወገን ነጻ ያደርጋል፡፡ 7. Where payment of compensation is a necessity to benefit teachers in accordance with the provisions of this regulation, the regional government shall make the land for housing construction free from third party by, in advance, disbursing the appropriate compensation in line with the law to the displaced persons or providing substitute plots of land for them.
3. በአነስተኛ ከተማ አስተዳደሮች ስር በተቋቋሙ ትምህርት ቤቶች ስለሚያስተምሩ መምህራን፡- 3. Teachers Teaching in Schools Established under Smaller City Administrations
1. የራሳቸው አስተዳደር ባላቸው አነስተኛ ከተሞች ውስጥ የሚያስተምሩ መምህራን በትምህርት ቤቶቻቸው አካባቢ በክልሉ መንግስት በጀትና በህዝብ ተሳትፎ ደረጃ በደረጃ በሚሰሩ የመኖሪያ መንደሮች በነፃ እንዲኖሩ ይደረጋል፡፡ 1. Teachers who happen to teach in smaller cities having their own administrations shall be made to reside freely in the residential villages to be constructed, step by step, in the surrounding area of their schools by the regional government’s budget and the participation of the public.
2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) ስር የሰፈረው ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ በመስኩ ያበረከቱት አገልግሎት 2 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆነ መምህራን በራሳቸው ወጪ የግል መኖሪያ ቤት መስራት የፈለጉ እንደሆነ መመሪያ ቁጥር 28/2009 ዓ.ም በሚፈቅደው መሰረት ቁጥራቸው 14ና ከዚያ በላይ እየሆኑ በማህበር ተደራጅተው ቦታ ከጠየቁና ከቤቱ መስሪያ ጠቅላላ ዋጋ ውስጥ 20 ከመቶ የሚሆነውን ስለመቆጠባቸው ካረጋገጡ ቦታው በሊዝ መነሻ ዋጋ ይሰጣቸዋል፡፡ 2. Without prejudice to the provision laid down under Sub-Art. (1) of this Article hereof, where those teachers, whose service contributed in the field has lasted two years and above, so desire to construct private dwelling houses on their own expense and thereby request for land by having organized themselves in cooperatives numbering 14 and above as well as ascertained that they have managed to save 20% of the total price of the housing construction as permitted by the Directive No. 28/2017, such land shall be provided for them at the initial lease price.
3. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (2) ስር የተመለከተው ቢኖርም ጥያቄ አቅራቢ መምህራኑ ቁጥራቸው ከ14 በታች በሆነ ጊዜ በተናጠልም ቢሆን በሊዝ መነሻ ዋጋ የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ የማግኘት መብታቸው ይጠበቅላቸዋል፡፡ 3. Notwithstanding the provision laid down under Sub-Art. (2) of this Article hereof, where the number of those teachers submitting the request is below 14, their right to obtain land for the construction of dwelling houses at the initial lease price shall be respected even on an individual status.

4. ከዚህ በላይ በአንቀፅ 6 ንኡስ አንቀፆች (5)፣ (6)ና (7) ስር በንኡስ ማዘጋጃ-ቤቶች፣ ታዳጊ ከተሞችና የገጠር ቀበሌዎች ውሥጥ በተቋቋሙ ትምህርት ቤቶች የሚያስተምሩ መምህራንን በተመለከተ የሰፈሩት ድንጋጌዎች በአነስተኛ የከተማ አስተዳደሮች ውስጥ ለሚያስተምሩ አቻዎቻቸውም በተመሳሳይ ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡ 4. The provisions laid down under Sub-Arts. (5), (6) and (7) of Art. 6 herein above with regard to the teachers teaching in schools set up under sub-municipalities, emerging towns and rural Kebeles shall Mutatis mutandis apply to their counterparts teaching in smaller city administrations.
4. በመካከለኛ የከተማ አስተዳደሮች ውስጥ ባሉ ትምህርት ቤቶች ስለሚያስተምሩ መምህራን፡- 4. Teachers Teaching at Schools Located in the Medium City Administrations
1. በመካከለኛ የከተማ አስተዳደሮች ውስጥ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የሚያስተምሩ መምህራን በትምህርት ቤቶቻቸው አካባቢ በክልሉ መንግስት በጀትና በህዝብ ትብብር ደረጃ በደረጃ በሚገነቡ የመምህራን መኖሪያ መንደሮች ውስጥ ያሉ ቤቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ተከራይተው እንዲኖሩ ይደረጋል፡፡ 1. Teachers teaching at schools found in the Medium City Administrations shall be made to reside in those houses existing in the teachers’ residential villages to be constructed, step by step, by the regional government’s budget in collaboration with the public in the surrounding area of their schools, having accessed them with a reasonable amount of rent.
2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) ስር የሰፈረው ድንጋጌ ቢኖርም በመስኩ ያበረከቱት አገልግሎት 2 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆነ መምህራን በራሳቸው ወጪ የግል መኖሪያ ቤት መስራትን የመረጡ እንደሆነ መመሪያ ቁጥር 28/2009ዓ.ም በሚፈቅደው መሰረት ቁጥራቸው 14ና ከዚያ በላይ እየሆኑ በማህበር ተደራጅተውና ከቤቱ መስሪያ ጠቅላላ ዋጋ ውስጥ 20 ከመቶ የሚሆነውን ስለመቆጠባቸው አረጋግጠው የጠየቁት ቦታ በከተማው የሊዝ መነሻ ዋጋ ሊሰጣቸው ይችላል፡፡ 2. Notwithstanding the provision laid down under Sub-Art. (1) of this Article hereof, where those teachers, whose service contributed in the field has lasted two years and above, prefer to construct private dwelling houses on their own expense and thereby request land by having organized themselves in cooperatives numbering 14 and above in accordance with the Directive No. 28/2017 as well as ascertained that they have managed to save 20% of the total price of the housing construction, such land which they have requested shall be provided to them at the city’s initial lease price.
3. ከዚህ በላይ የሰፈረው ንዑስ አንቀጽ (2) ቢኖርም የጥያቄ አቅራቢዎቹ ቁጥር ከ14 በታች በሆነ ጊዜ መምህራኑ በተናጠልም ቢሆን የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ በሊዝ መነሻ ዋጋ ሊሰጣቸው ይችላል፡፡ 3. Notwithstanding the provision of Sub-Art. (2) laid down herein above, where the number of teachers submitting the request is below 14, they may be provided with the land for the construction of dwelling houses against the city’s initial lease price, even on an individual basis.
4. ይህ የማይቻልበት ሁኔታ በተፈጠረ ጊዜ የከተማ አስተዳደሩ ለከተማው ነዋሪዎች ከሚገነባቸውና ለክልሉ መንግስት ሰራተኞች ከሚሰጣቸው አፓርተማዎች ወይም የጋራ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ 20 ከመቶ በሚሆነው ድርሻ እኩል የሚጠቀሙ መሆናቸው ሳይቀር መምህራን 10 ከመቶ ተጨማሪ እድል ተሰጥቷቸው እርስ በርሳቸው ለብቻ ይወዳደራሉ፡፡ 4. Where such an impossible condition has been encountered, teachers shall, without regard to the fact that they equally benefit from the 20% share out of the apartments or condominiums to be constructed by the city administration for the urban dwellers and allocated for the regional civil servants, solely compete amongst themselves, having been given ten percent additional opportunity.
5. ከዚህ በላይ በአንቀፅ 6 ንኡስ አንቀፆች (5)፣ (6)ና (7) ስር በንኡስ ማዘጋጃ-ቤቶች፣ ታዳጊ ከተሞችና የገጠር ቀበሌዎች ውሥጥ በተቋቋሙ ትምህርት ቤቶች የሚያስተምሩ መምህራንን በተመለከተ የሰፈሩት ድንጋጌዎች በመካከለኛ የከተማ አስተዳደሮች ውስጥ ለሚያስተምሩ አቻዎቻቸውም በተመሳሳይ ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡ 5. The provisions laid down under Sub-Arts. (5), (6) and (7) of Art. 6 herein above with regard to those teachers teaching at schools set up under sub-municipalities, emerging towns and rural Kebeles shall mutatis mutandis apply to their counter-parts teaching in the medium city administrations.
5. በሜትሮፖሊታን ከተሞች ስለሚያስተምሩ መምህራን፡- 5. Teachers Teaching in the Metropolitan Cities
1. በሜትሮፖሊታን ከተሞች በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚያስተምሩ መምህራን የክልሉን መንግስት አቅም ባገናዘበ ሁኔታ የጋራ መኖሪያ መንደር ደረጃ በደረጃ ከተገነባ በኋላ ቤቱ በተመጣጣኝ ኪራይ እንዲሰጣቸው ይደረጋል፡፡ 1. Following the construction, step by step, of condominiums by taking the capacity of the regional government into consideration, the houses therein shall be provided for teachers who happen to teach at the schools found in the metropolitan cities with a reasonable amount of rent.
2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) ስር የሰፈረው ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ በመስኩ ያበረከቱት አገልግሎት 2 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆነ መምህራን በራሳቸው ወጪ የግል መኖሪያ ቤት መስራት የፈለጉ እንደሆነ መመሪያ ቁጥር 28/2009 ዓ.ም በሚፈቅደው መሰረት ቁጥራቸው 14ና ከዚያ በላይ እየሆኑ በማህበር ተደራጅተው ከጠየቁና ከቤቱ መስሪያ ጠቅላላ ዋጋ ውስጥ 10 ከመቶ የሚሆነውን ስለመቆጠባቸው ካረጋገጡ ቦታው በከተማው ሊዝ መነሻ ዋጋ ይሰጣቸዋል፡፡ 2. Without prejudice to the provision laid down under Sub-Art. (1) of this Article hereof, where those teachers, whose service contributed in the field has lasted two years and above, so desire to construct private dwelling houses on their own expense and thereby request for land by having organized themselves in cooperatives numbering 14 and above in accordance with the Directive No. 28/2017 as well as ascertain that they have managed to save 10% of the total price of the housing construction, such land shall be provided to them against the city’s initial lease price.
1. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (2) ስር የተመለከተው ቢኖርም ጥያቄ አቅራቢ መምህራኑ ቁጥራቸው ከ14 በታች በሆነ ጊዜ በተናጠልም ቢሆን በከተማው ሊዝ መነሻ ዋጋ የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ የማግኘት መብታቸው ይጠበቅላቸዋል፡፡ 1. Notwithstanding the provision indicated under Sub-Art. (2) of this Article hereof, where the number of teachers submitting the request is below 14, their right to obtain land for the constructionn of dwelling houses against the city’s initial lease price shall be respected, even on an individual status.
2. በሜትሮፖሊታን ከተማ አስተዳደሮች ስር በሚጠቃለሉ የገጠር አካባቢዎች በተቋቋሙ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚያስተምሩ መምህራን ጥያቄ አግባብ ያላቸውን የዚህን ደንብ አንቀጽ 6 ድንጋጌዎች መሰረት በማድረግ ለማስተማር በተመደቡባቸው የገጠር ቀበሌ ማዕከላት በኩል ይስተናገዳል፡፡ 2. The request of those teachers serving at the schools set up in the rural areas embraced in the metropolitan city administrations shall be addressed on the part of the rural Kebele centers, wherein they have been assigned to teach, in accordance with the pertinent provisions of Art. 6 of this Regulation hereof.

1. ከዚህ በላይ በአንቀፅ 6 ንኡስ አንቀፆች (5)፣ (6)ና (7) ስር በንኡስ ማዘጋጃ-ቤቶች፣ ታዳጊ ከተሞችና የገጠር ቀበሌዎች ውሥጥ በተቋቋሙ ትምህርት ቤቶች የሚያስተምሩ መምህራንን በተመለከተ የሰፈሩት ድንጋጌዎች አግባብነታቸው እየታየ በሜትሮፖሊታን ከተሞች ውስጥ ለሚያስተምሩ ኣቻዎቻቸውም በተመሳሳይ ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡ 1. The provisions laid down under Sub-Arts. (5), (6) and (7) of Art. 6 herein above shall, with regard to the teachers serving at the schools set up under sub-municipalities, emerging towns and rural Kebeles, shall, mutatis mutandis, apply to their counterparts teaching in metropolitan city administrations, having due regard to their appropriateness.

በደቡብ ወሎ ዞን ለጋምቦ ወረዳ ህብረት ስራ ማህበራት ማስፋፊያ ጽ/ቤት የ2009ዓ.ም እቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2010ዓ.ም እቅድ ኦረንቴሽን የንቅናቄ መድረክ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስች...
07/12/2017

በደቡብ ወሎ ዞን ለጋምቦ ወረዳ ህብረት ስራ ማህበራት ማስፋፊያ ጽ/ቤት የ2009ዓ.ም እቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2010ዓ.ም እቅድ ኦረንቴሽን የንቅናቄ መድረክ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል የጋራ መግባባት ላይ ተደርሶ ተጠናቀቀ፡፡
የወረዳው ህብረት ስራ ማህበራት ማስፋፊያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሀይሌ ገብረ መስቀል የ2009ዓ.ም እቅድ አፈጸጸምን አስመልክተው እንደተናገሩት ከሰራዊት ግንባታ ጀምሮ እስከ ፊዚካል ስራ ድረስ በተለያዩ ተግባራት ዙሪያ ውስንነቶች አሉ ብለዋል፡፡ ህብረት ስራ ማህበራት የኪራይ ሰብሳቢዎች መነሃሪያ በመሆናቸው ክፍተት በታየባቸው ህብረት ስራ ማህበራት ላይ ትኩረት አድርገን እንሰራለን ያሉት ኃላፊው በ2010 በጀት አመት ብድር ማስመለስና ግብይትን በማጠናከር በኩል ሰፊ ስራ ለመስራት አቅደናል ሲሉ አብራርተዋል፡፡ የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትንም በቁርጠኝነት እንታገላለን ሲሉ አቶ ሀይሌ አክለው ገልጸዋል፡፡
የለጋምቦ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አህመድ ጋሎ በበኩላቸው ህብረት ስራ ማህበራትን ህዝባዊ ተቋማት ናቸው ብሎ በአግባቡ በመስራት በኩል ክፍተት አለ ብለዋል፡፡ በተቋማቱ የጉድለትና የኪሳራ ችግር የሚፈጠረው የቅጥር ሰራተኞችና ኮሚቴዎች ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ባለመወጣታቸው ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡ በወረዳው ተሰራጭቶ የቆዬ ከ10 ሚሊዬን በላይ የብድር ብር ለማስመለስና ጠንካራ ትስስር የተፈጠረበት የግብይት ስርአት ለማከናወን ወረዳው እንቅስቃሴ መጀመሩን አቶ አህመድ አብራርተዋል፡፡
ከተሳታፊዎች መካከል ካሳ ተካውና አሊ መንገሻ እንደተናገሩት ህብረት ስራ ማህበራት የተጠናከረ ድጋፍና ክትትል የማይደረግላቸው ከሆነ ለምዝበራና ለግለሰቦች መበልጸጊያ ሊሆኑ ስለሚችሉ ወረዳው ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራበት ይገባል፡፡ ችግር አለባቸው በሚባሉ ሰራተኞችም ላይ ተገቢ የሆነ ህጋዊ እርምጃ መወሰድ አለበት ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

በኩታበር ወረዳ የ2009 ዓ.ም  ዕቅድ  አፈጻጸም  ግምገማና የ2010 ዕቅድ ትውውቅ ከ12-14/03/2010 በወረዳ ደረጃ ተከናውኗል፡ በውይይቱ ይሳተፋሉ ተብለው የተገመቱ ወንድ 284  ሴት...
07/12/2017

በኩታበር ወረዳ የ2009 ዓ.ም ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2010 ዕቅድ ትውውቅ ከ12-14/03/2010 በወረዳ ደረጃ ተከናውኗል፡ በውይይቱ ይሳተፋሉ ተብለው የተገመቱ ወንድ 284 ሴት 25 ድምር 309 የተገኙ ወንድ 243 ሴት 13 ድምር 256 ናቸው፡ የወረዳው የ ህ/ስ/ማህበራት ማስፋፊያ ፅ/ቤት በ2009 ዓ.ም የልማት ሰራዊት የፊዚካል ስራዎች አፈፃፀምን በዝርዝር ካቀረበ በኋላ ውይይት ተካሂዷል፤
ውይይቱ ያተኮረው በዕጥረቶቸ ላይ ነው፤ ዋናዋናዎቹም፡
1. አዋጆቸ ደንቦች እና መመሪዎች በህ/ስራ ማህበራት ጽ/ቤት አለመገ ገኘ ቢኖሩም በስራ ላይ አለመዋል፣
2. ቅጥር ሰራተኛ በተለይ በወረዳው በስራ አስኪያጂ የሚታገዝ ህ/ስራ ማህበራት አለመኖር፣
3. ጠቅላላ ጉባዔ ወቅቱን ጠበቆ አለመካሂድ፣
4. የትርፍ ክፍፍል የተቆራረጠ መሆን፣
5. የገባያ ትስስር የለለ መሆን /እሪኩም ተፈላጊ ሸቀጣ ሸቀጥ አለማቅረብ፣
6. ቁጥጥር ኮሚቴ ተግባሩን እየተወጣ አለመሆኑ፣
7. የተበላሸ ምርጥ ዘር በሁለገቦች ተከማችቶ እያለ አለመወገዱ፣
8. የቦታ ጥያቄ ፈጣን ምላሸ አለማግኘት ሌሎቸም ነጥቦች በተሰብሳቢዎች ቀርበው በስፋት ውይይት ተደርጎባቸዋል፤
የተደረሰባቸው የመፍትሄ ሀሳቦች
1. የህብረት ስራ ማህበራት የሌሏቸው አዋጆች ደንቦች እና መመሪያዎች ተለይተው ህ/ስራ ማህበራት ወረቀትና ቀለም በጋራ እንድችሉ የወረዳው ጽ/ቤት አባዝቶ ድርሻቸውን እንድሰጣቸው፤
2. ስራ አስኪያጅን በተመለከተ 8ቱ ሁለገቦች እንድቀጥሩ፤
3. ትርፍ ክፍፍል በተለይ በሁለገቦች እያቆመ ስለሆነ የተሳትፎ ምዝገባ እንድካሄድ የተሳትፎ ምዝገባ ያደረጉትንሂ ሳባቸው እንደተመረመረ ማከፋፈል ፤
4. ከእሪኩም ጋር የገባያ ትስስር ለማድረግ መሠ/ህ/ስ/ማህበራት በቅድሚያ ዕቅዳቸውን ለእሪኩም እንዳሳውቁ፤
5. የተበላሸ ምርጥ ዘር በአወጋገድ መመሪያው መሰረት ለኮሚቴው በማቅረብ እንዳስወግዱ፤
6. የቦታ ጥያቄውን በተለይ የሸማቾችን በተመለከተ ከክልል በተሰጠው ትዛዝ መሰረት እንዲያስፈጽሙ ማቅረብ እና መከታተልና ለሌሎችም ጥያቄዎች የመፍትሄ ሀሳብ ቀርቦ ከስምምነት ላይ ተደርሷል፤

Address

Dessi

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when South Wollo Zone Co-operative Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram